ምህረቱን የለመዳችሁት ሰሞን ሀጢያተ አቅም ያገኛል እግዚብሔር ይምረናል በሚል ድፍረት ውስጥ የድፍረት ሀጢያት ቀላል ይሆናል። የትላንቱን ምህረት ለዛሬ ሀጢያት አቅም አታድጉ። Telegram
Open in TelegramPosts of S H E K A Y I N A H
መጽሐፈ ምሳሌ 10:19-21 •••••••••• ¹⁹ ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤ አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው። ²⁰ የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም። ²¹ የጻድቃን ከንፈሮች ብዙዎችን ያንጻሉ፤ ተላሎች ግን ከማመዛዘን ጕድለት ይሞታሉ። Telegram
Open in Telegramሁሉም ሀሳብ እውቀት ይሆናል ሁሉም እውቀት ፍቃድ እና ሰሜት ይሆናል ሁሉም ስሜት እና ፍቃድ ድርጊት እና ባህሪ ይሆናል ድርጊት እና ባህሪ ማንነት ይሆናል። ለሀስባቹ ተጠንቀቁ Telegram
Open in Telegramኦሪት ዘፍጥረት 19:15-16 (NASV) •••••••••• ¹⁵ ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥን፣ “ከከተማዪቱ ጋር አብራችሁ እንዳትጠፉ፣ ሚስትህንና ሁለቱን ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ” ብለው አቻኰሉት። ¹⁶ ሎጥ ሲያመነታም፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ስለ ራራላቸው ሰዎቹ የእርሱን፣ የሚስቱንና የሁለት ሴቶች ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዪቱ በደኅና አወጧቸው። በምታመነቱበት እና በምታነክሱበት የእግዚአብሔር ሀሳብ እግዚአብሔር ይራራላቹ መትረፍ ያለው በእግዚአብሔር ፍቃድ ውስጥ ነው Telegram
Open in Telegramበዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ላይ የምናገኘው ታሪክ ተራ ፍሬ የመብላት ታሪክ አይደለም። የውድቀቱ ዋና መሠረት “ራስን በራስ የማስተዳደር” (Autonomy) ፍላጎት ነው። እባቡ ሔዋንን ሲያታልል “እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ” አላት። ይህ ማለት መልካምና ክፉን የመወሰን ስልጣን ከእግዚአብሔር ነጥቆ ለራስ ማድረግ ማለት ነው እሱ እራሱን የፈጠፈጠው ይሄ ነበር። ሰው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሲያምፅ ሕይወትን ከምንጩ ተቆረጠ ውጤቱም ሞት ሆነ። የአብስራ ብዙአለም, ኬሪክስ, 5. Telegram
Open in Telegramመድረክ መኖሪያችን ሲሆን መኖሪያችን መድረክ ይሆናል የፈሪሳዊያን በሸታ ይህ ነው የመድረክ ስራ ከሚመስል ህይወት እግዚአብሔር ይጠብቀን Let it sink Telegram
Open in Telegramየኛ ህይወት በብዙ አማልክት አጀብ የሚስተካከል አልነበርም እግዚአብሔር ብቻውን መራን ከእርሱም ጋር ሌላ አማልክት አልነበረም ብቻውን ሆኖ በቂ የሆን አምላክ አለን እግዚአብሄር ብቻውን የበቃው ህዝብ ነን Telegram
Open in Telegramረጅም እድሚያችሁን በሙሉ የገነባችሁት ግንብ እግዚአብሔር ገንቡልኝ ያላላችሁ ይሆናል ግንባታ መሀል ሚጠየቅ አምላክ አለ ስራችሁን እንደ ኖህ መርከብ ያድርግላቹ አሜን አንተ የሌለህበት ቦታ ለምኔ ሀገር ለምኔ ከፍታ ለምኔ ክርስቶፎፖኒያ / Telegram
Open in Telegramሸክም ከባድም ሆነ ቀላል ምድራዊ ከሆን ከባድ ነው #ህግ ሸክም ቀሊል ሚሆነው ከእግዚአብሔር ሲሆን ነው አንድ አንድ የምታዩት መጉበጥ ከተሸከማቹት ሸክም የመነጨ ነው ትከሻቹን የሚያሳርፍ የእግዚአብሔር ሸክም ይብዛላቹ:: #ፀጋ የማቴዎስ ወንጌል 11:29-30 (AMH) •••••••••• ²⁹ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ³⁰ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። Telegram
Open in Telegram