ልዩ አስተዋፅኦ ይኑርህ ! አዞ በዉሃ ዉስጥ ከሚኖሩ ተሳቢ እንስሳት ዉስጥ አንዱ ሲሆን በተፈጥሮ ግዙፍ እና ጉልበተኛ ነዉ። ስጋ-በል (Carnivore) ሲሆን ሌሎች እንስሳትን እያደነ ይመገባል። ከተመገበ በኋላ በጥርሱ ዉስጥ ተሰግስጎ የሚቀርን የስጋ ቅሪት ግን ለራሱ ማፅዳት አይችልም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከአንድ የወፍ ዝርያ (Egyptian Plover ) ጋር ተስማምቶ እንደሚኖር ይነገራል። ከተመገበ በኋላ ወደ የብስ በመዉጣት አፉን ከፍቶ ጥርሱን አግጥጦ ወፏን ይጠብቃል። እርሷም መጥታ በጥርሶቹ መካከል የተሰገሰገዉን ትርፍ ስጋ እየለቀመች ትመገባለች። በተፈጥሮ አዞ ስጋ — በል ቢሆንም በፍቃዱ አፉ ዉስጥ የገባችዋን ወፍ ግን አያጠቃም። ትንሿ ወፍ በቂ ምግብ ታገኛለች — አዞዉም ጥርሱ በሚገባ ይፀዳል። ለአዞዉ በጥርሶቹ መሀል ቀርቶ ያስቸገረዉ ትርፍ ስጋ ለወፏ አጥጋቢ ምግብ ይሆናታል። የተሳካ ወዳጅነት ለመመስረት ከሌለኛው ጋር ተመሳሳይ ሀብት፣ ስልጣን፣ ጉልበት ወዘተ ግድ አይደለም። ለእሱ ጠቃሚ መሆን የሚቻልበትን ነገር ማወቅ ብቻ በቂ ነው። አንዳንዴ ሌላው ለራሱ ማድረግ የማይችለውን ነገር አንተ በተሻለ ሁኔታ ማድረግ ትችላለህ። ጠንካራ ግንኙነት አንዱ ሰጪ ሌላው ደግሞ ተቀባይ ብቻ በሚሆንበት ሁኔታ ሳይሆን ሁለቱም በሚጠቀሙበት ሁኔታ ላይ ይገነባልና በወዳጅነት ዉስጥ የምታበረክተዉ ልዩ አስተዋፅኦ ይኑርህ ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in TelegramPosts of Rise Daily
አትዉቀስ — ከቻልክ አግዝ ! በችግር መጠመድ ማለት መሸነፍ አይደለም። ደካማ መሆን ማለት ያለ አጋዥ እና ረዳት መቅረት ማለት አይደለም። ደጋግሞ መሞከርና አለመሳካትም ስኬት እስከ መጨረሻዉ የማይቻል መሆኑን አመላካች አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ያለህበትን ሁኔታ ተቋቁመህ እና አሸንፈህ ለመዉጣት የሚያስፈልግህ፦ ✅ ትክክለኛ ድጋፍ ✅ ትክክለኛ ግንኙነት ✅ ትክክለኛ አቅጣጫ እና ✅ በትዕግሥት ደጋግሞ መሞከር ነዉ። አንድ ሰው እራሱን ከችግር ማውጣት ስላልቻለ ብቻ ተስፋ አትቁረጥበት። አንዳንድ ጊዜ የሚያስፈልገው ወደ ጉድጓድ ስለወደቀ ብቻ መውቀስ ሳይሆን ሰዉየዉ ከችግሩ ለመዉጣት ፍቃደኛ እስከሆነ ድረስ ከዚያ ጉድጓድ እንዲወጣ ለማገዝ የሚችል እጅ ካለህ መዘርጋት እና ማገዝ ነው ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramሳይሻል አይቀርም ! ና ሲባል ከሄደ ሂድ ሲባል ከመጣ፣ ግራ ሲሉት ቀኙን ቀኝ ሲሉት ግራ ቀይሮ ካወጣ፣ ከፊት ሲባል ኋላ ከኋላ ሲሉት ፊት ከተደናበረ፣ ይባስ ብሎ ደግሞ ልክ እንደቅዱሳን ራሱን ከቆጠረ፣ ከማን ጋር ሊስማማ እንደት ብሎ ሊኖር? ህዝብ ተቀይሮ የሱ ቢጤ አረዳድ ካልሰፈነ በቀር ! አይሆንም! አይሆንም! ተፈጥሮ አይሻርም ፣ ህዝብ አይቀየርም እዉነታ አይጣልም፣ የተቀየረዉ ሰዉ ራሱን ቢቀይር ሳይሻል አይቀርም ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramተረጋጋ — Stay Calm ! ግርግርና ወከባ ስላጋጠመህ ብቻ አትደናገጥ — ተረጋጋ። የችግሩን ዋና ምንጭ፣ አቀናባሪ እና አስተባባሪ ለይ። ለእያንዳንዱ ትንኮሳ እና ተንኳሽ ምላሽ ለመስጠት አትሞክር። በደመነፍስ ከመፈራገጥ ይልቅ አፀፋ ለመስጠት ተገቢውን ጊዜ ጠብቅ። አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የተመጠነ ወሳኝ እርምጃ ውሰድ። በወከባ እና ግርግር ሊጎዱህ የሚሞክሩ አካላት ግዝፈት እና ብዛት የእነሱን ማንነት እንጂ የአንተን አቅም እንዲወስኑ አትፍቀድ። መረጋጋትህ ብቻ ያስደነግጣቸዋልና ስሜትህን ተቆጣጠር — ተረጋጋ ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramባለቤት ያቀለለዉን አሞሌ ባለእዳ አይቀበለዉም ! የራስህን ዋጋ ካላወቅህ ሌሎች እንዲያውቁት አትጠብቅ። የራስህን ሁለንተናዊ ማንነት፣ ንብረትና እሴት ደጋግመህ የምታቀልል ከሆነ፣ ሌሎች እንዲያከብሩትና እንዲቀበሉት የሚያደርጋቸዉ ምክንያት አይኖርም። ያለህን አታጣጥል። የራስህ የሆነን ነገር መጀመሪያ አንተ ተገቢ ዋጋ እና ቦታ ካልሰጠህ ሌሎች እንደ ተራ ነገር እና ዉዳቂ ቢቆጥሩት አይግረምህ። ቅድሚያ ራስህን እና የራስህን ነገር አክብር ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramሞክር — ትደርሳለህ ! ግልፅ የሆነ አላማ እስካለህ ድረስ ከመሞከር አትቦዝን። መሰናክል ቢያጋጥምህ እና ብትወድቅ እንኳን ተስፋ አትቁረጥ— በተለዬ መንገድ እንደገና ሞክር። ወደ አላማህ በምታደርገዉ ጉዞ ወደኋላህ አልያም የቅርብ እይታ ብቻ አይኑርህ። አርቀህ ተመልከት ። እይታህን ከመዳረሻህ ላይ አድርገህ ተጓዝ — በአሏህ ፍቃድ ትደርሳለህ ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramምንም — Nothing — لا شيء ! ሰዉ የጎዳ መስሎት ድንገት ከተነሳ ደርሶ ከበረረ፣ ቢሄድ ምን ያጎድላል እንዳለ እያሰበ ወትሮስ ያልነበረ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in TelegramAwolia College — Where I am a GC student this year ! Learning is beyond recieving Degrees. It is a process of Building Minds, Character and Impact. Education develops five important dimensions of a human being: ✅ Knowledge: What do you know? ✅ Thinking: How do you understand? ✅ Character: What values guide you? ✅ Competence: What can you accomplish? ✅ Contribution: What difference do you make in society? Learn to think. Learn to question. Learn to create. Learn to lead. Learn to serve. Be a generation that does not merely seek certificates, but develops the capacity to transform individuals, institutions, and society. እየተማርክ፣ እያጠናህ፣ እየጠየቅክ እየሰራህ፣ እያገለገልክም ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramተስፋ ካልቆረጥክ አትበላም ! መነከስ ማለት መሸነፍ አይደለም! በሕይወት ውስጥ ልንጎዳ፣ ልናዝን፣ ልንነከስ እንችላለን፤ ይህ ግን ተስፋ በመቁረጥ ጉዟችንን የምናቆምበት ምክንያት መሆን የለበትም። ወደፊት መራመድ እስከቻልን ድረስ ተስፋ አንቁረጥ — ወደፊት እንጂ ወደኋላ አንመልከት ! በፍርሃት ተዉጠህ በጭንቀት ውስጥ እየዋለልክ ከማመንታት ይልቅ ተጨባጭ እርምጃ ውሰድ — ወደፊት ! ሕይወት ከጥቃት ሁሉ ላትጠብቅህ ትችላለች። ከሁሉም ቁስል ልታድንህም አትችልም። ነገር ግን የተጎዳህበት ሁኔታ የመጨረሻ ዕጣ ፈንታህ እንዲሆን አትፍቀድ። የዛሬ ቁስልህ የነገ ሞትህ አይደለም፤ መነከስም መሸነፍ አይደለም ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramሀናን እና ኢምራን ! ሀናን አብዱረሂም እና ኢምራን አብዱረሂም የተባሉ የዘጠኝ ዓመት መንትያ ልጆች ናቸው። ምሽት 2፡30 ሰዓት አካባቢ በአንድ ሱቅ በር ላይ ቆመዋል። ከኋላቸው የነበረ አንድ ሰው፣ “ልጆች፣ ለምን ወደ ቤታችሁ ሄዳችሁ አታጠኑም? በዚህ ሰዓት የቤት ሥራችሁን መሥራት ነበረባችሁ” እያለ ሲመክራቸዉ ሰማሁ። ልጆቹ ከዝምታ የዘለለ ምላሽ አልነበራቸዉም። ምክሩ በራሱ ትክክል ነው። ግን ቀድሜ ልጆቹን አዉቃቸዉ ነበርና መካሪዉ ስለ ልጆቹ ተጨባጭ ሁኔታ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገመትኩ። እነዚህ ልጆች የሚመለሱበት፣ የሚዉሉበት፣ የሚያድሩበት፣ የሚኖሩበት የሆነ ቋሚ መኖሪያ የላቸውም። እናታቸው በህይወት የለችም፤ ከወራት በፊት ሞታለች። አባታቸው የተማረ እና ስራ የነበረዉ ሲሆን የባለቤቱን ሕይወት ለማዳን እና በህፃንነታቸዉ ይታመሙ የነበሩ እነዚህን መንትዮች ለማሳከም የሚችለውን ሁሉ አድርጓል። ለዚህም ሲል ስራዉን ለቋል፤ ገንዘቡን ሁሉ ጨፍጭፏል። ያለዉን ሁሉ ከሰጠ እና ዋጋ ከከፈለ በኋላ የባለቤቱን ህይወት መታደግ ባይቻለዉም ልጆቹ ድነዉለታል። ልጆቹ ጤናቸዉ ቢመለስም ግን ሀብት ንብረት እና ስራዉን ሁሉ መስዋዕት ስላደረገ ዛሬ ራሱን ለማስተዳደር እንኳ ተቸግሯል — ሞራሉ እጅግ ተጎድቷል — ተሰብሯል። ከእርሱና ከልጆቹ ጋር አሮጊት እናቱን ጭምር ይዞ ጎዳና ላይ ለመዉደቅ ተገዷል። አብዱረሂም አሁን ኖርማል አይመስልም። አያት — ልጅ — የልጅ ልጅ ሆነዉ ጎዳና ላይ ! ሀናን እና ኢምራን የጎዳናን ህይወት ጀምረዉታል — የፈጣን አእምሮ ባለቤቶች ቢሆኑም አይማሩም። በዚህ እድሜያቸዉ ከባድ ፈተና ገጥሟቸዋል። ከሱቁ በር ላይ የተገኙት ለራሳቸዉ፣ ለአባታቸዉም ሆነ ለአያታቸዉ የሚሆን ጉርስ ፍለጋ ነበር። ማስታወሻ:- ቤተሰቡን መርዳት የምትፈልጉ ሁሉ በዉስጥ @IbnuAbiih አናግሩኝ። በአካል ለምትፈልጉ ሱረያ መስጂድ በር ላይ ታገኟቸዋላችሁ 🙏። ከመፍረድህ በፊት ሁኔታውን አጣራ። ከዉጪ በምታያቸው ነጥቦች ላይ ብቻ ተመስርተህ ሰዎችን አትመዝን። የምታየው ችግር የመከራ ውጤት እንጂ የመጥፎ ባህሪ ማስረጃ ላይሆን ይችላል ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in TelegramForwarded from Rise Daily
ከመስመርህ አትዉጣ፤ ሀላፊነትህን ተወጣ ! በአጭር ርቀት ሩጫ ማንኛዉም ተወዳዳሪ ከራሱ መስመር መዉጣት አይችልም። ቢፈጥንም ቢዘገይም የራሱን መስመር ይዞ መሮጥ ግደታዉ ነዉ። ምክንያቱም የፍጥነት ሩጫ ስለሆነ መጠላለፍ ይፈጠርና ራሱንም ሆነ ሌለኛዉን አትሌት ይጎዳል። ስለሆነም አንድ ተወዳዳሪ ወደ ሌላ አትሌት መስመር ከገባ ከዉድድሩ ይሰረዛል። የዚህች አለም ህይወትም እንደዚሁ ነች። በምድር ላይ የምንቆየዉ ለአጭር ጊዜ ነዉ፤ ሩጫችን ግን በፍጥነት የተሞላ ነዉ። ታዲያ በዚህ ቆይታችን ሳንጠላለፍ ሰላማዊ የሆነ ጊዜ እናሳልፍ ዘንድ መስመራችንን መልቀቅ የለብንም። ወላጅ፣ ልጅ፣ መንግስት፣ ህዝብ፣ ባል፣ ሚስት፣ አስተማሪ፣ ተማሪ፣ የቢሮ ሀላፊ፣ የቢሮ ተራ ሰራተኛ ወዘተ ሁሉም መስመሩን በሚገባ ለይቶ መጓዝ አለበት። ሀላፊነትህን በአግባቡ ለይ፤ የሚጠበቅብህን ተወጣ። ከዚያ አልፈህ ከመስመርህ ወጥተህ በሌሎች መስመር የምትቦርቅ ከሆነ ተጠላልፈህ ትወድቃለህ፤ ሌላም ትጥላለህ ወዳጄ ! Stay disciplined, bear your responsibility and follow your track ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramአሏህ አለኝ ብለህ መንገድ ላይ አትተኛ፣ ይረግጥሀልና ያሏህ መንገደኛ ! በከንቱ መንፈሳዊ አትሁን። በአሏህ ላይ ከመመካትህ በፊት በምትችለዉ ልክ ተገቢ ሰበብ አድርስ ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in TelegramBe free of attachment ! Appreciate what you have without taking it for granted. Value what matters without making it your identity. Love deeply without becoming a prisoner of attachment. Enjoy life's blessings without becoming dependent on them. Remain free—so that losing something you had does not mean losing yourself. Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramቁረጥ — አስወግድ ! የተሻለ ቁመና ላለዉ ህንፃ ቤዝመንት ለመገንባት በዚያ ቦታ የሚገኘውን አፈር ማስወገድ ግድ ነዉ። አፈሩ የሚወገደዉ መጥፎ ስለሆነ ሳይሆን በተዘጋጀዉ የግንባታ ቦታ ላይ ስለማያስፈልግ ነዉ። በቀደመዉ ጊዜ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ቢሆንም ለታሰበዉ አዲስ ፕሮጀክት ግን አያስፈልግም — ይወገዳል ! የተሻለ ሕይወት ለመገንባት በእሳቤያችን ልክ ከቀድሞ ማንነታችን ቆርጠን መጣል ያለብንን ማንነት ሁሉ በልበ ሙሉነት መቀነስ እና ማስወገድ ያስፈልጋል። አንዳንድ ልማዶች እና የቀድሞ አስተሳሰቦች እንዲሁም አሁን ላይ የማይጠቅሙን አካሄዶች ምናልባት በአንድ ወቅት አገልግለዉን ይሆናል፤ ነገር ግን ወደምንፈልገው ደረጃ እንዳንደርስ እንቅፋት ሲሆኑ ልንቆርጣቸዉ ይገባል። አላስፈላጊውን ለማስወገድ ፈቃደኛ ካልሆንክ ለአዲሱ ነገር ቦታ መፍጠር አትችልምና ለእቅድህ እንቅፋት የሚሆንህን ማንነት ሁሉ ቀድመህ ቁረጥ — አስወግድ ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramሙክት — Buck ! ጉልበቱን፣ ጽናቱን እና አቅሙን ለራሱ ብቻ አያውልም፤ የመንጋውን ደህንነትና ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሳይሰስት ይሰራል፤ ያለዉን ሁሉ ለመንጋዉ ጥቅም ይለግሳል። እውነተኛ ጥንካሬ የሚለካው ለራሳችን በምናገኘው ነገር ሳይሆን፣ ጥንካሬያችንን ለሌሎች ጥቅም በምናውለው መጠን ልክ ነው። ጠንካራ ማለት ሌሎችን የሚገዛና የሚያስፈራ ሳይሆን፣ አቅሙን ለመርዳት፣ ለመጠበቅ፣ ለመደገፍ እና ሌሎችን ለማንሳት የሚጠቀም ሰው ነው። ጥንካሬ መብትና መልካም አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ኃላፊነት ነው። መሪነት ከሌሎች በላይ መቆም ሳይሆን ሌሎችን ማንሳት ነው። ጥንካሬ መጠቀሚያ ሳይሆን መጥቀሚያ ሲሆን እዉነተኛ ይሆናል። ኃላፊነትን ለመሸከም ጠንካራ፣ ችግርን ለመጋፈጥ ደፋር፣ ጥንካሬህንም ለሌሎች ጥቅም ለማዋል ቅን ሁን — ልክ እንደ ሙክት ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramበነደፉልህ ስትራቴጂ ዉስጥ አትፈራገጥ — ይበሉሀል! ሁላችንም የሚሆነንን ስልት ተግብረን ዉጤታማ ለመሆን እንሻለን። ያለንን ጥንካሬ ተጠቅመን ለማሸነፍ እንሞክራለን። አንዳንድ ጊዜ ግን የአንድኛችን ስኬት በሌሎች ዉድቀት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል። ለራሳቸዉ አግኝተዉ ከመደሰት ይልቅ የሌሎችን ዉድቀት እንደ ትልቅ ስኬታቸዉ የሚቆጥሩ "ምቀኞችም" ይኖራሉ። የትኛዉንም አካል ከነሱ በመጣ ስልት ለማሸነፍ አትሞክር። ቢሳካልህም ብዙ ሊያደክምህ ይችላል። ሁኔታውን መቀየር ከሁኔታው ጋር ከመታገል ይሻላል። የራስህን ስልት እና ጥበብ ተጠቀም — በእነሱ ስልት ዉስጥ አትድከም። ተገዳዳሪህን መቆጣጠር ባትችልም የትግሉን መድረክ ተቆጣጠር — የሚበጅህን ስልት ተግብር። ስልት መቀየር ጥበብ እንጂ ሽንፈት አይደለም ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegramእዉነተኛ አሸናፊ — True Champion ! እውነተኛ ስኬት ከሌሎች በላይ መቆም ብቻ አይደለም፤ ሌሎችም ከፍ እንዲሉ መርዳት እንጂ ! ከተፎካካሪዎችህ በልጠህ ዉድድሩን ልታሸንፍ ትችላለህ፤ ነገር ግን እውነተኛ አሸናፊ የምትሆነው የተፎካከሩህን ሰዎች ስታከብር ነው። ሌሎችን ወደ ላይ ማንሳት ያለህን ከፍታ አይቀንስም፤ እንዲያዉም ክብርህን ይጨምራል። እውነተኛ ጠንካራ ሰዎች ራሳቸውን ከፍታ እንዲሰማቸው የሌሎች ዝቅ ብሎ መቆም አያስፈልጋቸውም። እዉነተኛ አሸናፊ ሁን — በስኬትህ ጊዜ ከኋላህ ያሉትን ሁሉ አክብር ወዳጄ ! Join and Share @SeidEndre @SeidEndre
Open in Telegram