Posts of የሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኀነት ሰንበት ት/ት ቤት መንፈሳዊ ቴሌግራም ገጽ
ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ በሰንበት ትምህርት ቤታችን የሚደረገውን የአመራር ምርጫ አስመልክቶ በተደጋጋሚ ካርድ እንዲወሰድ ሲነገር የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በስልክም የማሳወቅ ስራ የተሰራና እስከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ድረስ የወሰዱትን አባላትን እያመሰገንን በማሳሰቢያው መሠረት በቀን 13/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ምርጫው የሚከናወን መሆኑን አውቃችሁ የተመዘገባችሁ እና ካርድ የወሰዳችሁ በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ የምርጫ ካርዳችሁን ይዛችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን። መራሔድኅነት ሰንበት ትምህርት ቤት
Open in Telegramየሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ጉብርኤል ገዳም መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት በአዋቂዎች ዘርፍ የእሁድ ተከታታይ ትምህርት መርሐግብር መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት ሲያስተምራቸው የቆየውን በተለያየ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ኦርቶዶክሳውያን ጎልማሶች እና ወጣቶችን አስመረቀ። ሕዳር 2019 ዓ.ም ✝ሀ/ደ/ቅ/ገ/ገ መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት የፌስቡክ ገፅ:https://www.facebook.com/profile.php?id=100069444095761 የቴሌግራም አድራሻ: https://t.me/SaintGebrielSundaySchool የዩቲዩብ ገፅ:የማኅበራዊ https://youtube.com/@MerahiMedia19?feature=shared
Open in Telegram+++ ድንግል ያንቺ ልቅሶ በእጅጉ ይበቃኛል፡ ሁለተኛ እንዳላለቅስ በታምርሽ አድኚኝ ፥ አንች ሁልጊዜም የአዳምና የልጆቹ መድኃኒት ነሽና ኃጥአንን በቸርነቱ እስከአዳነ ድረስ ንጉሥ ልጅሽ ራቁቱን እንደተሰቀለ አስቢ + ማህሌተ ጽጌ ዘጥቅምት ፳፯
Open in Telegramሀ/ደ/ም/ቅ/ገ /ገ መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት በእሁድ መደበኛ መርሐግብር በአዋቂዎች ዘርፍ ተከታታይ ትምህርት ሲማሩ የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም ያስመርቃል። ቦታ :- መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት ሰዓት:- 9:00 ✝ሀ/ደ/ም/ቅ/ገ/ገ መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት
Open in Telegramየሰንበት ትምህርት ቤታችንን 58ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ ጉባኤ ጉባኤው ቅዳሜ ጥቅምት 21 እና እሁድ ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም በአውደ ምሕረት የሚካሄድ ይሆናል። ማሳሰቢያ በሰንበት ትምህርት ቤታችን የሚደረገውን የአመራር ምርጫ አስመልክቶ በተደጋጋሚ ካርድ እንዲወሰድ ሲነገር የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን እስከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ድረስ የወሰዱትን አባላትን እያመሰገንን በጉባኤው ምክንያት ምርጫው የተራዘመና በቀን 13/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ምርጫው የሚከናወን መሆኑን አውቃችሁ የተመዘገባችሁ እና ካርድ የወሰዳችሁ አባላት በቀኑ በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ የምርጫ ካርዳችሁን ይዛችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን። ✝ሀ/ደ/ም/ቅ/ገ /ገ መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት
Open in Telegramእንኳን ለአባታችን አቡነ አረጋዊ (የተሰወሩበት) ቅዱሳኑ ገብረ ክርስቶስ መራዊና ቅዱስ ሙሴ መራዊ ዓመታዊ በዓለ እረፍት በሰላም አደረሳችሁ ''ለተአምርኪሰ አንዘ ይነግር ረድኤቶ ቦ ዘፈለሰ ኃዲጎ ብእሲቶ ወቦ ገዳም ዘወፈረ መነኖ መንግሥቶ ''ማህሌተ ጽጌ ዘጥቅምት ፲፬ "ድንግል ሆይ የተዓምርሽን እርዳታ እያስተማረ ሚስቱን ትቶ የተሰደደ አለ ፤ መንግስቱንም ንቁ ወደ በረሃ ወደ ገዳም የመነነ አለ " አባ ጽጌ ድንግል ገድለ አቡነ አሪጋዊንና ገድለ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስን ከእመቤታችን ምስጋና አስተባብሮ የተናገረበት ይህ ድንቅ ምዕራፍ እጹብ ነው። የእመቤታችን ፍቅር ያገበረው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ እንደ ቅዱስ ሙሴ መራዊ የአማረ ቤቱን የተዋበች ሚስቱን ከጫጉላ ቤት ትቶ መነነ በግድ ንጉሳዊያን ቤተሰቡ ቢድሩት ሀሳቡ ከምናኔ ነውና ...አቡነ አረጋዊም በ፲፬ ዓመቱ ንግስቲቱ እናቱን ቅድስት እድና አስከትሎ ንግስናውን ትቶ ከአባ ጳኩሚስ ገዳም መመነኑን ያስረዳል እመቤታችን ጥንቱን ከፈጣሪ ልጇ ጋር መንና ምናኔን በስደቷ አስተምራለችና። የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን።
Open in Telegram✝ለሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ በቅርቡ የመራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት ሥራ አመራር ጉባኤ ምርጫ የሚካሄድ በመሆኑ ይህንን አስመልክቶ ከስር በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት የምርጫ ካርድ እንድትወስዱ ስንል እናሳውቃለን። 👉ካርድ ለመውሰድ የሚያስፈልጉ/ ማሟላት/ የሚገቡን ግዴታዎች ምንድናቸው…? 1) የሰንበት ትምህርት ቤቱ መደበኛ አባል መሆን ይገባል። 2) በሰንበት ትምህርት ቤቱ ባሉ የአገልግሎት ክፍላት በቋሚነት ወይንም በመደበኛነት እየተሳተፈ (እያገለገለ) ያለ/ ያለች ሊሆን ይገባል ። 3) ዕድሜ 18 ዓመት እና ከዛ በላይ መሆን ይኖርበታል። እነዚህን እና የመሳሰሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ አባላት የሰንበት ትምህርት ቤታችን ግንኙነት ክፍል በመገኘት የምርጫ ካርድ እንድትወስዱ እናሳስባለን። ✝ሀ/ደ/ም/ቅ/ገ/ገ መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት
Open in Telegram