Posts of Natty's Perspectives
ካልጠፋ ርዕስ Rudolf Bultmannን እና Paul Tillichን አስተምር ተብለህ ሲሰጥህ፣ ቁጭ ብለህ "ሳልናዘዝ የዘነጋሁት ኃጥያት ምን ይሆን ብለህ" መቁጠር ትጀምራለህ። ንባቡን ተትህ እንዲህ እንዲያ እያልክ በሃሳብ ተውጠህ ሳለህ middnight አልፏል። የዚህኔ ያንተን ኃጢአት መቁጠር ትተውና የBultmannና የTillichን ትቆጥራለህ፤ "መንግስተ ሰማይ ገብተው ይሆን" ብለህ ራስህን እየጠየክ መልሰህ ደግም "አይ!አይሆንም" ብለህ ለራስህ ጥያቄ ምላሽ እየሰጠህ በለሊት ከራስህ ትነጋገራለህ። ሰዓቱም መሮጡን አያቆምም፤አንተም በነሱ መማረርህን አታቆምም። ታዲያ በምሃል "ሊነጋ አቅላልቷልና" የሚለው ጥቅስ ትዝ ሲልህ ደግሞ መልስ ትልና መዘጋጀትህን ተቀጥላለህ። ሙት ወቃሽ የሆንኩበት ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት ወገን😁
Open in Telegram"Those who behold the Lord in his glory, they penitently cry, 'Woe is me.' And they boldly say, 'Here am I, send me.' And friends, this personal looking to Christ, yourself, it matters to those whom you pastor. Because the reality is it is not just your words that your people hear. It is out of the overflow of your heart, whatever's in your heart that you will speak. And you will give away more than you mean to. And even if people can't put their finger on it, you are going to carry with you the aroma of what you truly glory in. You can try to hide it, but what you love will over time show itself. And you will carry this atmosphere about with you. And your people will learn from you what to glory in." Michael Reeve @Romans148
Open in Telegramርዕስ:- ለጌታው ታማኝ ባራያ መሪ ጥቅስ:- ማቴ 25፥14-30 አስተዋፆኦ 1. አውድ 2. የምሳሌው ትንተና 3. የምንማራቸው 3 ነገሮች:- 3.1. የጌታን ደግነት ማወቅ 3.2. የጌታን ጌትነት ማወቅ 3.3. የጌታን ዓላማ ማወቅ 4. መደምደሚያ @Romans148
Open in TelegramI have been following Wes Huff's case over the past couple of days. I don't want to comment on that. But whenever weaknesses or sinful practices of God's servants come to light, I remember Luke 13:1-5. I take it as a call to repentance. Instead of focusing on analyzing and commenting on other people's failures, I think we should see them as a call to repentance—to examine our lives and attune them to God's word. ሉቃ 13፡1-5 1 በዚያን ጊዜም ሰዎች መጥተው ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች አወሩለት። 2 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። እነዚህ የገሊላ ሰዎች ይህ ስለ ደረሰባቸው ከገሊላ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ኃጢአተኞች የሆኑ ይመስሉአችኋልን? 3 እላችኋለሁ፥ አይደለም፤ ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ። 4 ወይስ በሰሌሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ አሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን? አይደለም፥ እላችኋለሁ፤ 5 ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ። @Romans148
Open in Telegramይህን ማስተዋል መልካም ነው። ጽድቅ "በእምነት ብቻ" ማለት "ጽድቅ በእምነት ብቻ" የሚለውን አስተምህሮ በማመን መጽደቅ ማለት አይደለም። የመጀመሪያው በክርስቶስ ሥራ ላይ ባለ መታመን/መደገፍ/ መዳን ሲሆን፤ የኋለኛው አስተምህሮውን በመታመን መዳን ነው፤ ይህ ደግሞ ኦሪታዊነት (legalism) ነው። @Romans148
Open in Telegramየዊኬንዱ የመጨረሻው ፓስት ከላይ ለተጠቀምኳቸው technical terms ማብራሪያ ለማከል ያህል፦ Analogical: አንድ ቋንቋ ለእኛና ለእግዚአብሔር ሲውል ምንነቱን በተገደበ ደረጃ እናውቃለን፣ ነገር ግን ምን ያህል ነው ምስስሉ የሚለውንና ለእግዚአብሔር ሲውል እንዴት እንደሚተገበር ሙሉ በሙሉ ልንገነዘብ አንችልም። ለምሳሌ፣ "ደግ" የሚለውን ቃል እንውሰድ። ደግ የሚለውን ቃል ስንጠቀም መልካም ማድረግን፣ ርህራሄንና የመሳሰሉትን ሃሳቦች ያዘለ ነው። ለምሳሌ፣ ቃሉን ለሰው ስንጠቀም ሰውን አለመግደልን ሊጨምር ይችላል። ነገር ግን እግዚአብሔር እየገደለም ደግ ነው። ይኸውም፣ ቃሉ ለእግዚአብሔር ሲውል "መልካም" እና የመሳሰሉትን ቢያዝልም ነገር ግን ሙሉ በሙሉ እኛ በምናስበው መልክና ፍጹም ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ለእግዚአብሔር ተግባራዊ ሊሆን አይችልም እንደ የanalogical እይታ። ምክንያቱም እግዚአብሔርን አውቀን አንጨርስም፤ እኛ ባሰመርንለትም እንዲወሰን አንጠብቅም። Hidden-revealed God distinction: ይህ ሉተር የእግዚአብሔርን አይታወቄነትና መገለጥ ለማሳየት የሚጠቀመው ነው። ስለ እግዚአብሔር ያልተገለጡልን የማናብረራቸው ነገሮች አሉ። ስለዚህ ሉተር የተሰወረወን የእግዚአብሔርን ባህሪ ለመጨበጥ የሚሞክሩትን ሰዎች theologians of glory ብሎ ይጠራቸዋል። ሉተር እኛ ስለ እግዚአብሔር መናገር የምንችለውና ማውራት ያለብን እሱ ራሱን በልጁ የገለጠልንን ብቻ ነው። ነገረ መለኮትን እንዲህ ባለ መንገድ የሚያጠኑትን the theologians of the cross ብሎ ይጠራቸዋል። Accommodation: ካልቪን ይህን ቋንቋ የሚጠቀመው እግዚአብሔር ለእኛ እንዴት ራሱን እኛ ልንረዳው በምንችለው መንገድ አድርጎ እንዳቀረበልን ለመግለጽ ነው። ለምሳሌ፣ እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ለመግለጥ ስለወደደ በሰው ቋንቋ በተጻፈ መጽሐፍ ራሱን አቀረበልን፣ የሰው አገላለጾችን ተጠቀመ። ይህ ማለት ልክ አዋቂ ለህጻን ልጅ ሊገባው በሚችል መልኩ መጥኖና አቅልሎ አንድን ነገር ሊያስረዳ ሲሞክር እንደማለት ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ራሱን እኛ እንድንረዳ አድርጎ ካቀረበበት መንገድ በእጅጉኑ ይልቃል። ልብ በሉ Aquinas፣ Luther እና Calvin ሶስቱም እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ እንደ ገለጠ ቢያምኑም፣ እሱ እኛ ልንረዳው ከምንችለው እጅ የላቀ፣ በሰው መደብ የማይወሰን መሆኑን በአትኩሮት ይናገራሉ። የዘመናውያኑ አቀራረብ ግን univocal የምንለው ነው። ይኸውም፣ ከላይ እንደ ገለጽኩት አንድን ቃል ለእኛና ለእግዚአብሔር ስንጠቀም ፈጽሞ የዓይነት ልዩነት የለውም የደረጃ ብቻ እንጂ የሚል ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር እኛ "ጥበብ"፣ "መልካምነት"፣ ወዘተ፣ ብለን በገለጥነው ወሰን ውስጥ መግጠም (fit ማድረግ) አለበት። ስለዚህ ዘመናውያኑ የማያውቁት የእግዚአብሔር ባህሪ ገጽታ እንዳለ ለመቀበል አይፈልጉም። ሁሉም ነገር ለእነሱ መብራራት አለበት (after all they are the "enlightened" ones)። እግዚአብሔርን እንደምንም አብራርተውት ሰው ባስቀመጠው ወሰን ውስጥ ሊያስቀምጡት ይገባል። በዚህም፣ ጸሐፊው እንደሚገልጸው የላቀውን(transcendent የሆነውን) እግዚአብሔር domesticate (እነሱ manage ሊያደርጉት የሚመች ቤተኛ) አደረጉት። በዚህም ምክንያት፣ በዘመናዊው ነገረ መለኮት transcendent የሚለው ነገረ መለኮታዊ ቋንቋ የእግዚአብሔርን ልህቀት ሳይሆን ርቀት የሚገልጥ ተደርጎ ተወሰደ። የእግዚአብሔር ሌላነት ደበዘዘ፤ እነሱ የሳሉት እግዚአብሔር በሰዎቸ ቋንቋ፣ አመክንዮና እውቀት ተገደበ። እንግዲህ ከዚህ ነው ቀስ በቀስ ልዕለ-ተፈጥሯዊ የሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተዘገቡ ተዓምራቶች እየተካዱ የመጡት። በእርግጥ ሁሉም ዘመናውያን አልካዱም። ነገር ግን እነሱን ያልካዱቱ orthodox የነገረ መለኮት ምሁራን እንኳን ሲሞግቱ "እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነው" ብለው ሳይሆን እነዛን እግዚአብሔርን በሰው ገደብ የሚወስኑ መደቦችንና አስተሳሰቦችን አምነው ተቀብለው ግን በዛ መደብ ውስጥ እንዴት ለእግዚአብሔር ተዓምራት ማድረግ አግባብ እንደሆነ፣ መደቡን እንደማይጥስ ለማሳየት በሞከር ነው። በመሆኑም፣ እንደነዛ ሊበራሎቹ ተዓምራትን ባይክዱም እግዚአብሔርን በሰው መደብ ገጥመው ከማኮሰስ ግን አላመለጡም። በመጨረሻም፣ አፓሎጂስት ለመሆን ለምታስቡ፣ በዘርፉ ለምትተጉ እንደ ዘመናውያኑ እግዚአብሔርን ቤተኛ እንዳታደርጉት ተጠንቁ፤ በማስተዋል ሁሉን አድርጉ። በተጨማሪም፣ አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ነገሮችን እንዳሉ ለማመንና ለመቀበል ሞክሮ እንጂ ለእናንተና ለሰው አእምሮ በሚመች መልኩ ለማቅረብ በማብራራት አታሳንሱት። ከሁሉ በላይ እግዚአብሔር ራሱን ወደ ገለጠበት ወደ መስቀል ዙሩ እንጂ እግዚአብሔር የሰወረውን ለመፈልፈል አትታትሩ። "God is God; You are not!" ~ Okamoto~ መልካም የጌታ ቀን! @Romans148
Open in Telegramየእኔ አስተማሪ ሁሌ እንደሚለው "God is God; You are not." እኛ ሀገር በወጣቱ ዘንድ የሚደረጉ የነገረ-መለኮት ውይይቶች በአመዛኙ በሞደርን የአስተሳሰብ ዘይቤ የተቃኙ ይመስላሉ። እንደው ይህችን መጽሐፍ ብታነቧት ታተርፋላችሁ። እግዚአብሔርን በሰው መደብ ከመመዘን ድፍረትና በራሳችሁ ውስን አእምሮ "እግዚአብሔርን" ሰፍታችሁ ወደ ጣኦትነት እንዳትቀይሩ ይረዳችኋል። የመጽሐፉ አንኳር ሀሳብ በቅድመ-ዘመናዊነት (premodern) የነበረው የAquinas, Luther, ና Calvin ስለ እግዚአብሔር የሚናገሩበት መንገድ በሞደረን የነገረ መለኮት ምሁራን ወደጎን እንደተተወና እስከዛሬ የዛ ገፈት ቀማሽ ሆነናል የሚል ነው። እነዚህ ቅድመ ዘመናውያን የእግዚአብሔርን ሌላነት(otherness)፣ ከእኛ መደብና አእምሮ የሚልቅ መሆኑን በሚገባ የተገነዘቡ ናቸው። ስለዚህም ስለ እግዚአብሔር ሲያወሩ ከእኛ አቻ አድርገው አይደለም ( ስለ እግዚአብሔር ሲናገሩ፥ Aquinas- analogical language፣ Luther hidden-revealed God distinction፣ ካልቪን ደግሞ accomodation ይጠቀማሉ።) Modern theologian ግን univocal language ይጠቀማሉ። ይኸውም፣ እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ያለው የመደብ/ዓይነት ልዩነት ሳይሆን የ ደረጃ(degree) ልዩነት ይሆናል። ለምሳሌ፣ እግዚአብሔር ጠቢብ ነው ስንል የግድ እኛ "ጥበብ" ብለን ባስቀመጥነው ገደብ ውስጥ መሆን አለበት ልዩነቱ እሱ "የበለጠ ጠቢብ" መሆኑ ብቻ ነው እንደ ዘመናውያኑ ከሆነ። ስለዚህ ለነሱ እግዚአብሔር ሰዎች በቀደዱለት የሚፈስ፣ ሰዎች በመደቡለት የሚወሰን፣ ከሰው በደረጃ ብቻ የሚበልጥ አካል ነው። ጸሐፊው ይህ ዓይነቱ አካሄ ከእነ ሉተር ያፈነገጠና እግዚአብሔርን የሚያኮስስ ነው ይላል። @Romans148
Open in Telegramበዚህ ቻናል ያላችሁ አንዳንዶቻችሁ እንዴት አንባቢ ልሁን ብላችሁ ጠይቃችሁኝ ታቃላችሁ። ይኸው ሸልፌክስ መልካም ሀሳብ ይዞ መጥቷል። ጊዜአችሁ የሚፈቅድ ከሆነ ተቀላቀሉ plz. ሰላም ወዳጆች ያው በቴሌግራም ላይ እንደምታውቁኝ እኔ የሆነ አሪፍ ነገር ጀምሬ እንደማልጨርስ ነው በperseverance እያመንሁ persevere ማላደርግ አይነት ☺️ ለነገሩ እናንተ እንደ ሃበሻ በሞቅታ ትጀምሩና ትንሽ እንደቆየ መስነፍ ስትጀምሩ እኔም በዛው ቸል እላለሁ እንጂ እኔ በራሴ ሰንፌ አይደለም የጀመርሁትን ማልጨርሰው አላቆምም😁 አሪፍ የቴሌግራም የአንባቢያን ቪሌጅ ልከፍትላችሁ አሰብሁና ከናንተ ጋር ልመካከር ብዬ አሳቡን ወዲህ አመጣሁት.... የዚህ ማህበር አባል መሆን የሚችለው... 1 በወር 5 ነገረ መለኮታዊ መጸሃፍ ማንበብ የሚችልና ያነበበውን ላይቭ ገብቶ የሚወያይ፣ የሚከራከር፣ የመጸሃፉን ጠቅላላ አሳቡን ተረድቶ ሪፍሌክሽን መስጠት የምችል፤ 2 የዚህን ወር አምስቱ መጸሃፍት ሪኮመንድ የሚያደርጉት መስራቹና ባለ ራእይ ናቸው፤ ከቀጣዩ ወር ጀምሮ ግን ማንም መደበኛ የሆነና የተመዘገበ የማህበሩ አባል ሪኮመንድ ማድረግ ይችላል፤ 3 በወር 5 ጠለቅ ያሉ መጸሃፍት ለማንበብ ጊዜ የሌለው፣ ቢያነብ ራሱ ላይቭ የማይገባና ላይቭ እንኳን ቢገባና አሳብ ባይሰጥ ቻናሉን በጭራሽ እንዳይገባ፣ ቢገባ ራሱ ይቦለካል፤ 4 ሁሉንም ማለትም ካቶሊኩን፣ ኦርቶዶክሱን ወንጌላዊያንን ሁሉ ለማካተት ሲባል የመጸሃፍቱ አይነት እጅግ መልካቸው የተለያዩ ናቸው። የጥንታዊያን አባቶች መጸሃፍ የለ፣ የዘመናዊ ምሁራን የለ፣ የሪፎርመሮች ስራ ሁሉ ይካተቱበታል። ስለዚህ ቢያዝድ ያለበት ሰፈሩ እንዳይደርስ፤ 5 በሳምንቱ እሁድ ማታ ከ3: 00 ጀምሮ በእስኬጁላችን መሰረት የሳምንቱ ንባባችን ላይ የምንወያይበት፣ የምንሟገትበትና ሪፍሌክሽን የምንሰጥበት ይሆናል፤ 6 ሰው ከ13 ባያንስና ቢበዛ 18 ሰው ባያልፍ ይመረጣል፤ 7 በቻናሉ ቶክሲክ መሆን አይቻልም የቴሌግራማዊያን ኢመደበኛ ምሁራዊ ውይይቶችና መስተጋብሮች ብቻ ናቸው የሚፈቀዱት፤ 8 ለብ ለብ አንባቢያን፣ ለሌሎች ትራዲሽን ጥላቻ ያለባችሁ፣ የተነበበውን ማብራራት ላይ ዝግ የምትሉና ቲክቶከሮች ባትኖሩ ይመረጣል ስፍራችሁ እዚህ አይደለምና፤ 9 በሶስተኛው ወር ማለትም 15 መጸሃፍ ካነበብን በኋላ በአካል በመገናኘት አብረን ቆንጆ ምግብ እምንበላና ትኩስ ነገር እምንጠጣ የምንችል መሆን አለብን። 10 በዚህ ወር የሚነበቡ 5ቱ መጸሃፍት፤ 1 On the Christian Life – John Calvin 2 For the Life of the World (Schmemann, Alexander) 3 What is the Point of Being a Christian - Timothy Radcliffe 4 Gregory of Nyssa On the Human Image of God _ JOHN BEHR 5 Into the Heart of Romans (N. T. Wright).... 11 እስከ እሁድ ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉና እሁድ ላይቭ ገብተን ባርከን ማህበራችንን እናስጀምራለን። እስከ እሁድ ራሳችሁን አዘጋጁ ቀድማችሁ ማንበብ ከጀመራችሁም ጸዴ ነው መደበኛው የንባብ ቀን ግን ሰኞ ይጀምራል። 12 ይህ ማህበር ከተሳካ አቤት 😁ብዙ ነገሮችን በመመካከር የምናስሄድ ይሆናል። mምናልባት በወር ውስት 5 መጸሃፍ ማንበብ ይከብዳል ከተባለ ተመካክረን ወደ 3ትም ማውረድ እንችላለን ዋናው ምክክሩ ነው። መልካምም ይሆናል። ቻናሉ ይህ ነው @schola_theologica
Open in Telegramኮብላዩን ልቤን.. አቤቱ የሚባክን ልብ አለኝ። አንተን ትቶ መሮጥ የሚሻ፣ የማያዋጣው ጋር የሚጠጋ፣ ያማያዘልቀው ላይ የሚንጠለጠል ክፉ ልብ አለኝ። እባክህ ውሰደውና አንተ ባለህበት አድርገው። ሌላ እንዳይሻ በመንፈስህ አትመው። እንዳይንቀለቀል፣ እንዳይባክን፣ ሌላ እንዳያይ በውበትህ ግርማ አሳውረው። እባክህን አንተን ትቶ እንዳይሮጥ በፍቅር ገመድ እሰረው። ከእስርህ ሊያመልጥ እንኳን ቢቃጣው እንዳይሸሽ ፈቃዱን ንፈገው። ያዘው አባቴ። ካንተ ውጪ ሁሉ ጥፋት፣ ሁሉ ልፋት፣ ሁሉ ክርፋት ነው። ስለዝህ አቤቱ፣ አንተ ትችልበታለህና ከልጅህ ጋር ግመደው። አሜን!! O to grace how great a debtor daily I’m constrained to be! Let that grace now, like a fetter, bind my wandering heart to thee. Prone to wander, Lord, I feel it, prone to leave the God I love; here’s my heart; O take and seal it; seal it for thy courts above😭. @Romans148
Open in Telegramአንዳንዴ እንደ ዮናስ በእኛ አለመታዘዝ ሌሎችም ጭምር ዋጋ ይከፍላሉ (ዮና 1፡4-5)። ታዲያ የዚህን ጊዜ እንደ ዮናስ ከተኛንበት ነቅተን "ልጣል የሚገባኝ ኃጢአተኛ እኔ ነኝ" ብለን በእግዚአብሔር ፊት በትህትና መደፋት ማስተዋል ነው። አባታችን ደግሞ ስለ ልጁ ስለክርስቶስ ሲል ለትሁታን ጸጋን የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው (ያዕ 4:6):፡ ዛሬ የጌታ ቀን፣ በእግዚአብሔር ፊት በትህትና ቀርበን በምህረቱ የምንታደስበትና ቸርነቱን ከቅዱሳን ጋር የምናወድስበት ቀን ይሁንልን። "ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ። በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።" - ያዕ 4፡9-10 - መልካም የጌታ ቀን! @Romans148
Open in Telegramእስቲ ለweekend እቺን ጽሑፍ ጣጥሟት። "ከውኃና ከመንፈስ":-ዮሐ 3፡5 ለምን ስለ ጥምቀት ናገራል ብዬ አናምናለሁ? 1. ስነ ጽሑፋዊ አውድ፡ 1.1. ልብ ብላቹ ካጤናችሁ ከዚህ ከጌታ ንግግር ተከትሎ የሚመጣው ሃሳብ የውሃ ጥምቀት ነው (3፡22-4፡3)። እንዲሁም ምራፍ አንድ ላይ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ጥምቀት እናነባለን። በነዚህ ክፍሎች ላይ ውሃ ከጥምቀት ጋር ነው የተያያዘው። 1.1. ከውሃና ከመንፈስ ስለ መወለድ የተነገረው ኒቆዲሞስ በኢየሩሳሌም ያለ ፈሪሳዊ የአይሁድ አለቃ ነበር (3፡1፤ 2፡13)። ይህ ማለት ምራፍ አንድ ላይ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጽምቁ ዮሐንስን ማን እንደሆነና ለምን እንደሚያጠምቅ እንዲጠይቁት ሰዎችን ከላኩት መካከል ነው ማለት ነው (1፡19፣24-25)። ይህ ከሆነ ታዲያ ኒቆዲሞስ ዮሐንስ እርሱ በውሃ እንደሚያጠምቅ ኢየሱስ ግን በመንፈስ እንደሚያጠምቅ የተናገረውን ምስክርነት ጠንቅቆ ያውቃል ማለት ነው (1፡26-8፤ 1፡31-33)። ስለዚህም 3፡5 “ወሃና መንፈስ” የሚለውን ከዚህ ውጪ በሌላ መንገድ ሊረዳ ይችላል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። 2. መጽሐፍ ቀዱሳዊ አውድ 2.1. መጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ ጥምቀትና መንፈስ ቅዱስ በቅርበት ተቆራኝተው ይገኛሉ - ሐዋ 2፡38፤ ማቴ 3፡11፤ ማር 1፡8፤ 1 ቆሮ 12፡13። 2.2. በዮሐንስ 3፡5 ላይ የተጠቀሰው የዳግም ልደትና የመታደስ ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ ከጥምቀት ጋር ተያይዟል - ሮሜ 6፡3-4፣ ሐዋ 22፡16፤ 1 ጴጥ 3፡21፤ ኤፌ 5፡25-26፤ ቆላ 2፡12:: 2.3. ምንም እንኳን የመጀመሪያው ሰሚ (ኒቆዲሞስ) በዮሐ 3፡5 ላይ ውሃ የሚለውን ሲሰማ የመጥምቁ ዮሐንስን ጥምቀት ሊያስብ እንደሚችል ባይካድም፤ ነገር ግን ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈላቸው በ1ኛ ክፍለ ዘመን መጨረሻ የኖሩት አማኞት፣ ከጳውሎስ መልክታት እና ከታሪክ እንደምንረዳው፣ ስር የሰደደ የክርስቲያን ጥምቀት ልምምድና አስተምህሮ በዳበረት ጊዜ ሆነው መልዕክቱን የሚያነቡና የሚሰሙ ናቸው። በመሆኑም፣ ክፍሉን ሲያነቡ/ሲሰሙ ያለጥርጥር የክርስቲያን ጥምቀት ጋር አቆራኝተው እንደሚሆን ጥያቄ የለውም። ይህን ሃሳብ የሚደግፈው ሌላው ፍንጭ ወንጌላዊ ዮሐንስ እንደሌሎቹ ወንጌል ጸሐፍት (ያው ሉቃስ ለሁለተኛው ቅጹ/ለሐዋርያት ስራ/ አቆይቶት ነው በወንጌሉ ላይ ያልዘገበው) ጌታ የጥምቀትን ስርዓት ሲደነግግ አለመጻፉ ነው። ይኸውም፣ በሌሎቹ ወንጌላውያን የተዘገበው የጥምቀት ስርዓት በዮሐንስ ወንጌል ላይ በግልጽ ሲዘገብ የማናየው በዚህ ክፍል ውስጥ ላይ ታሳቢ (assume) በመደረጉ እንድሆነ ልናይ እንችላለን። 3. ሌላው፣ ለክፍሉ አማራጭ ትርጓሜ ሆነው የሚቀርቡት ደካማ ናቸው። 3.1. የመጀመሪያው "ውሃ" የሚለውን ምሳሌያዊ አድርጎ መውሰድ ነው። ምሳሌያዊ ቋንቋ አድርጎ መተርጎም ከላይ በተጠቀሱትም ሆነ በሌሎቹ ምክንያቶች ደካማ ሆኖ እናገኘዋለን። 3.1.1. በዮሐ 3፡1-15 ባለው ጌታ ምሳሌያዊ ቋንቋን ሲጠቀም ችንጭ ይሰጣል። ለምሳሌ፣ በቁጥር 8 ላይ "ንፋስ"ን በምሳሌያዊ መንገድ ሲጠቀም “ከመንፈስ የሚወለድም እንዲሁ (οὕτως) ነው” በማለት ምሳሌያዊነቱን ግልጽ ያረጋል። እንዲሁም፣ በቁጥር 15 ላይም ሙሴ የሰቀለውን እባብ ከጌታ ስቅለት ጋር ሲያነጻጽር ምሳሌያዊ መሆኑን ሲያሳይ “እንዲሁ (οὕτως)…የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባል” ይላል። 3.1.2. በዮሐ 3፡5 ላይ ግን እንዲህ ምሳሌያዊ አድርገን እንድናንድብ የሚያደርግ ፍንጭ የለም። ታዲያ የዚህኔ ለምን ምሳሌያዊ ማድረግ ወደድን ብለን ራሳችንን መጠየቅ ጥሩ ነው። ማስረጃችን ምንድነው እንደዛ ለመተርጎም? እኛ ለመቀበል ስለከበደን ነው ወይስ በእርግጥም ክፍሉ ስለሚል ነው ምሳሌያዊ አድርገን መተርጎማችን? ምሳሌያዊ ካደረግነውስ ልምን ውሃውን ብቻ እናደርጋለን? “መንፈስ” የሚለውንስ ምሳሌያዊ እንዳናደርግ ምን ይከለክለናል (የተያያዙ በመሆናቸው)? 3.2. ሌላኛው፣ አንዳንድ አሁን ላይ ያሉ የዮሐንስ ወንጌል ልሂቃን (የእኔን መምህር ጨምሮ) የሚያቀርቡት አማራጭ ትርጓሜ፣ “እና” ተብሎ የተተረጎመውን የግሪክ ቃል (ካይ/ καί) “ማለትም” ብሎ መውሰድን ነው። ይህ በግሪክ ሰዋሰው epexegetical καί በመባል ይጠራል። ይህ ማለት "እና/kaί" የሚለው ቃል አያያዥ ሳይሆን ቀድሞ ለመጣው ቃል ተጨማሪ ማብራሪያ የሚሰጥ ነው ማለት ነው። ስለዚህ በዚ ፍቺ መሠረት “ከውሃ እና ከመንፈስ” ማለት “ከውሃ ይኸውም ከመንፈስ” ማለት ነው። ባጭሩ፣ ውሃ ማለት መንፈስ ማለት ነው። ይህ ትርጓሜ “ወሃ” ምሳሌያዊ ነው ከሚለው ሚዛን ይደፋል (በተለይ ደግሞ ዮሐ 4 እና 7ን ከግምት ስናስገባ)። በሚከተሉት ምክኒያቶች፣ ይህም ደካማ ትርጓሜ ሆኖ እናገኘዋለን። 3.2.1 አንደኛ፣ እና/καί የሚለው ቃል ትርጓሜ በዋነኛነት “እና” ማለት ነው። አገልግሎቱም አያያዥነት ነው። ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን በአንዲስ ኪዳን ውስጥ epexegetical καί መኖሩን ሁሉ ይጠራጠራሉ። ካለም በጣም ጥቂት ቦታዎች ብቻ ነው። ስለዚህ ከቃሉ ዋና ትርጉም ውጪ ሌላ ትርጓሜ ለ“እና/καί” ለመስጠት በጣም ልዩ የሆነ አሳማኝ ምክንያት ያስፈልጋል። 3.2.2. ሁለተኛ፣ ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት የክፍሉ የቅርብ ስነ ጽሑፋዊ አውድ ላይ ውሃ ተያይዞ የምናገኘው ከጥምቀት ጋር ነው። 3.2.3. በመጨረሻም፣ በወንጌላዊው ዮሐንስ ትረካ ሂደት መሠረት በምዕራፍ 3 ላይ ኒቆዲሞስ “ውሃ” የሚለውን ቃል የሚያውቀው ከጥምቀት ጋር በተያያዘ ብቻ ነው ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት። 4. በመጨረሻም፣ አብዛኛዎቹ የጥንት የቤተክርስቲያን አባቶች ዮሐ 3፡5ን ጥምቀትን እንደሚያመለክት አድርገው ነው ሲተረጉሙ የምናየው። አሳማኝ ምክርንያት ሳይኖር ከጥንት አባቶች የትርጓሜ መንገድ ማፈንገጥ ተገቢ አይደለም። @Romans148
Open in TelegramAs usual, Naol offers a thought-provoking perspective on the Amhara-Oromo relationship in an attempt to renew ETC. Let's chew on it and have some dialogue. አላችሁ?! My “theory” is this. In the early 20th century, Ethiopia had a real chance for Amhara and Oromo Christians to renew the Orthodox Church together, and perhaps contribute to nation building together as well. Abune Mateos, the Egyptian metropolitan (bishop of Shoa from 1881, head of the Church from 1889) destroyed everything. Here are the most important supporting points forr my claim: 1. Aleqa Taye of Begemder (the man whose photo you see above), Aleqa Tegenye and Qes Badima of Gojjam, and the Oromo translator Onesimos Nesib wanted to renew the Orthodox Church from within, not plant a foreign one. Remember these people were Amhara and Oromos. Gustav Arén counts them among those who sought “open-minded dialogue” with the Orthodox Church (Arén 1978, 442). With Menelik’s written permission, Taye preached in Orthodox churches, and “the clergy and the people rejoice[d] together” (Arén 1999, 23–26). 2. Amhara and Oromo worked side by side in Wollega. Clergy from Gojjam taught and preached in Boji alongside Onesimos’s Oromo evangelists. When Taye (Amhara) was imprisoned in Addis Ababa in 1911 and most of his friends kept away, Onesimos (Oromo) went to visit him (Arén 1999, 44). 3. Abune Mateos broke it up. Look what he did: • In 1906 he had Onesimos excommunicated and condemned. Menelik refused to confirm the verdict (Arén 1978, 425–29). Apparently, according to Arén, Menelik wasn't even the enemy. It was Mateos, the Egyptian! • In 1911 his Mateos' clergy put the Boji evangelists on trial for using books “in Oromo and Amarinya instead of Ge’ez” (Arén 1978, 433). Mateos wanted them mutilated, even executed, and they were exiled (Arén 1999, 127). • He had Heruy Walda Sellase jailed for revising the Amharic New Testament, and wanted Taye “shackled for life” (Arén 1999, 46, 126). Note this: this Egyptian dude opposed the Bible in Amharic as well as in Oromo. His problem wasn’t one ethnic group. It was ordinary people reading the Bible in their own language together. And I hold to a theory that he actually didn't like the union between the Oromo and Amhara evangelists. 4. Here is the sad part. What followed was that when they were pushed out of the Orthodox Church, the evangelical movement in Wollega grew separately, eventually becoming the Mekane Yesus Church. Boji, the community Mateos’s party prosecuted, was the birthplace of Baro Tumsa, who organised the 1973 meeting that founded the OLF. His brother, Gudina Tumsa, led the Mekane Yesus Church. Tell me this is a coincidence! Of course there are other many layers to the Oromo-Amhara political differences and conflicts over the last century but Mateos destroyed what could have been a historical unity or Oromos and Amharas under the Church. It’s sad to think what the Amhara–Oromo relationship might have looked like if that early partnership had been allowed to grow. Guys, don't die before reading Gustav Arén, Evangelical Pioneers in Ethiopia (1978) and Envoys of the Gospel in Ethiopia (1999). @Born_Crucified
Open in TelegramΕὐλογητὸς ὁ θεὸς καὶ πατὴρ⸌ τοῦ κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። Blessed is (be) the God and Father of our Lord Jesus Christ ኤፌ 1፡3 @Romans148
Open in Telegramማህበራዊ ሚድያ? ከታች የምትመለከቱት ቪዴኦ በጥናት ላይ የተደገፈ፣ content creators ላይ የሚደርሰውን የማንነት ቀውስ የሚዘግብ ነው። የምመለከቷቸው pictures ደግሞ ማሕበራዊ ሚድያያ በታዳጊ ወጣቶች የአእምሮ ጤና ላይ የሚያስከትለውን መዘዞች ከሚያሳይ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ የተቀነጨቡ ናቸው። በምስሉ ላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና መዘዞች ለመጠቆም ያህል፦ ድባቴ፣ ጭንቀት፣ የእንቅልፍ እጦት፣ የማንነት ቀውስ፣ ልክ በአደንዛዥ እጾችን በመጠቀም እንደሚሆነው አይነት የአምሮ ቅርጽ ለውጥ፣ ራስን መጉዳትና ሌሎችም። እንዲሁም፣ ከትንኮሳ ጋር ተያይዞ አንዳንዶቹ መዘዞች ሴት እህቶቻችን ላይ በብዛት ይታያሉ። በተጨማሪም፣ ጥናቱ ማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀማቸውን ከወትረው በመመቀነስ በቀን ወደ 30 ደቂቃ ዝቅ ያደረጉ ወጣቶች ላይ የታየወን የአእምሮ ጤንነት ለውጥም ይዘግባል። ባጭሩ፣ ማበራዊ ሚድያ መንፈሰዊ፣ ማህበራዊ፣ አካላዊና የአእምሮ ጤንነታችሁን ሊያላሽ የሚችል ኃይል አለው። ስለዚህ እባካችሁ በማስተዋል ተጠቀሙ። እስቴ ዛሬ አንድ ብላችሁ ማህበራዊ ሚድያ በቀን ለመጠቀም ያለባችሁን ሰዓት አስቡ። ብትችሉ ስልካችሁን በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በቀር እስከ ምሳ ሰዓት ሳትነኩ ለመዋል ሞክሩ። ይህ እንዲሁ ለጅማሬ ያክል ይሆናችኋል። https://youtu.be/vl3Kkjbvryk?is=_99c3byMMfcHQlJr @Romans148
Open in Telegram