.. ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ❝ አንድ ባሪያ አላህ ዘንድ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ነው፡፡ ሱጁድ ላይ ዱዓ አብዙ፡፡ 🖊ሙስሊምዘግቦታል። አልሃምዱሊላህ ሰጅዳህ ላይ ያለው ሰላም ግን..🤍.
Open in TelegramPosts of 𝐑𝐢𝐨 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜✌️
قَالُوا كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ ۖ إِنَّهُ هُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ እንደዚህ ጌታሽ ብሏል፡፡ «እነሆ እርሱ ጥበበኛና ዐዋቂ ነውና» አሏት፡፡ ሱረቱል ዛሪያት ቁጥር 30
Open in Telegramታክሲ ውስጥ ነኝ ጠዋት ነው ከጎኗ ነኝ ድንገት የሆነ ነገር ክፍት አለ ስዞር እያዛጋች ነው ......በነፃነት ነው እስከ መጨረሻ የከፈተችው እጇን አፏ ላይ ጭና ማዛጋት አልፈለገችም .... በርግጥ እንዳከፋፈቷ ምኗንም ብትጭንበት የምትሸፍነው አይመስለኝም ገልመጥ አድርጊያት ዞርኩ .... አራት ደቂቃ አልሆነኝም ደግማ አዛጋች ይሄኛው ድምፅ አለው.... ልትበላኝ ነው እንዴ የሚያስብል ማዛጋት ነው "ቡና ነው ? ቁርስ ነው ? እንቅልፍ ነው ወይ?" አልኳት ? ዝም አለችኝ እጇን አፏ ላይ ለማድረግ የደከማት ልጅ ምን ብላ ከኔ ጋ ወግ ትገጥማለች እያልኩ በልቤ ሌላ ወሬ ልወረውር ወደሷ ስዞር እሷ ወደ እኔ ዞራ ስታዛጋ ተገጣጠምን .... ግማሽ ፊቴ አፏ ውስጥ የገባ አይነት ስሜት ነው የተሰማኝ ጭንቅላቴን ወደኋላ ስቤ ረዳት ረዳት ወራጅ ወራጅ ወራጅ ...አልኩ ይሄው ቀኑን ሙሉ ላንቃዋ፣ ጉሮሮዋ፣ መንጋጋዋና እንጥሏ አይኔ ላይ ነው የዋለው😁
Open in Telegram. ጥያቄ፡-ወንዶች ሂጃብ ያላትን ኒቃብ እና ጅልባብ ያደረገች ሴት ስታደንቁ ሸህዋችሁ እዛች ሴት ላይ ስለሚበረታ ነው? እንዴት እንዴት የተሸፈነችን ሴት ማሻአላህ ማለት በምን ሂሳብ ከመቼ ጀምሮ sexually መታየት ተጀመረ? ከሆነ እኛ ሴቶች ተሰባስበን ያሀዩ ያቀዩሙ እንላችኋለን። ወንዶቻችንን ለኛ ለቀቅ አርጉልን። እንዲ ስለሆነ ነው እንድያ ስለሆኑ ነው አይመለከታችሁም!!! ሌላኛው እኛ ኒቃብ በመልበሳችን ፣ፀጉራችን በመሸፈኑ፣ ባለመራቆታችን አትዘኑልን ወደነው ፈቅደነው መርጠነው ነው። አዛኝ ቅቤ አንጓች አትሁኑ።ምታዝኑልን ገላችን ለወንድ ስላልተገለጠ ነው? በየሩጫው መቀመጫጭችንን አይቶ ካልተኛሁበት ስላላለን? ወይስ እሙ አስገቢኝ የሚል የመንደር ወጠጤ ድምፅ ስላልደረሰን? እኛ እንደሙስሊም ሴት ደግሞ ሂጃብ እንደጠበቀን እንደሚጠብቀን እናምናለን ሂጀብ ከመጥጠበቅ ጋር ያገናኘዋልም! እኛ ደስተኛ ነን !!!ምን አልኩ? እኛ ደስተኛ ነን!! ለራሳችን ራሳችን እናውቃለን ማንም መጥቶ ስለሂጃባችን ሊያስተምረን ሊያስጠነቅቀን ስለወንዶች ኒያ ሊነግረን አይችልም። ባሌ ብቻ ልብሴን ሊያወልቅ ከጥቁሩ ስር የተደበቀውን ገላ ሊያይ የተገባ ነው። እንደሰፌድ ቆሎ ማንም እንዲዘግነኝ እያየኝ የሌሊት ደስታውን እንዲያሟላ አልፈቅድም! ማንም መጥቶ የተሸፈነች ካልተሸፈነች አትሻልም የማለትም መብት የለውም። ስለልቧ ጌታዋ ጋር ትተሳሰብ እኔ ማውቀው ስሜቷን ጨፍልቃ መታየትን ንቃ ስትር ያለች ሴት በላጭ እንደሆነች ነው….. ዋናው ልብ ነው እያላችሁ መርዝ አስተሳሰባችሁን አትርጩ.. Attention seeker አትሁኑ ምትሉ ድብን አርጌ ደግሞ ሙሉ አቴንሽኔን ምሰጠው ሂጃብን ለሚያደንቅ ለሚወድ ለሚያከብር ነው… አቴንሽን እንዲሰጠኝ ምፈልገውም የ እስልምና ህግ የሚገዛው እንጂ ለፈጣሪው ያልወደቀማ አንድ አልፎ አንድ አለ። እኛ እንደሙስሊም ሴት ደግሞ ሂጃብ እንደጠበቀን እንደሚጠብቀን እናምናለን ያገናኘዋልም። ሂጃብ ምርጫ አይደለም ከአላህ የመጣ ትዕዛዝ እንጂ!!! እናውቅላችኋለን የሚል አያስፈልገንም እኛው እናውቃለን Lastly ሙስሊም ሆናችሁ ፌሚኒስት ነን የሚሉ ስር ያዙኝ ልቀቁኝ የምትሉ ሴቶች መጀመርያ ቅሩ አሊፍ ትቁም ትተኛ ሳታውቁ ሰሀበቶችን ጥቀሱ ብትባሉ ከሰይደት አዒሻ እና ሰይደት ፋጢማ ውጪ ማታውቁ ምን ስለሌላ ideology ያስፈተፍታችኋል? አርፈሽ ቁጭ ብለሽ ቅሪና ሌላው ላይ ትደርሻለሽ። የተበደልሽ የመሰለሽ የነሱ ሀሳብ ልክ የመሰለሽ ስለ እስልምና ምታውቂው ነገር ስለሌለሽ ነው አደብ ያዙ አልያም እኔ እያላችሁ አውሩ። ሲቀጥል ተማሩ is እና with ሲሉ ትልቅ ነገር እየመሰላችሁ አትደናበሩ። ተማሩ የራሳችሁ አቋም ይኑራችሁ ማንም እየመጣ ጭቃ ሚደፋባችሁ አትሁኑ። ለኔ እና መሰሎቼ እስልምናችን በቂ ነው ጠብቆናል ይጠብናልም!!! @rio_islamic ©Anu Ni
Open in Telegramፈተናዎች በተደራረቡባችሁ ሰዓት ከአላህ በታች አይዞህ ባይ አያሳጣችሁ ስሜታችሁን ሚረዳ ህመማችሁ ሚሰማው ሰው ይስጣችሁ ዱንያ ያለ አይዞህ ባይ ትከብዳለች
Open in Telegramإذا ماتَ الحياءُ بقلبِ أُنثى، فتبّاً ثم تبّاً للجمالِ! وإنْ عاشَ الفتى للعِرْضِ ذِئبٌ، فَعارٌ أن يُعدّ من الرجالِ!
Open in Telegramأَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يُزْجِي سَحَابًا ثُمَّ يُؤَلِّفُ بَيْنَهُ ثُمَّ يَجْعَلُهُ رُكَامًا فَتَرَى الْوَدْقَ يَخْرُجُ مِنْ خِلَالِهِ وَيُنَزِّلُ مِنَ السَّمَاءِ مِن جِبَالٍ فِيهَا مِن بَرَدٍ فَيُصِيبُ بِهِ مَن يَشَاءُ وَيَصْرِفُهُ عَن مَّن يَشَاءُ ۖ يَكَادُ سَنَا بَرْقِهِ يَذْهَبُ بِالْأَبْصَارِ አላህ ደመናን የሚነዳ መኾኑን አላየህምን ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፡፡ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፡፡ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ኾኖ ታየዋለህ፡፡ ከሰማይም (ከደመና) በውስጧ ካሉት ጋራዎች በረዶን ያወርዳል፡፡ በእርሱም የሚሻውን ሰው (በጉዳት) ይነካል፡፡ ከሚሻውም ሰው ላይ ይመልሰዋል፡፡ የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል፡፡ ሱረቱል ኑር ቁጥር 43
Open in Telegramእረ ውይይይይይይ ሴቶች ግን አስሬ በስልክ 😗😗😗 የሚሉትን ወንድ ነው ሲያገቡ የማየው ወላሂ ከአንድም ስንት ሴት እና እኔ ነኝ እንደናንተ 😙😙😙 ብዬው ማገባው??😭 ምንም እኮ በስልክ አይመስልም እኔ ጩጬዋን የእህቴን ልጅ እራሱ እንደዚህ አልላትም እየተሳሰብን እንጂ ወገን አንጨመላለቅ😏
Open in Telegramአንድ ጊንጥ ወንዝ ለመሻገር ፈልጎ መዋኘት ስለማይችል አንዲት እንቁራሪት ጋር ቀርቦ «ጀርባሽ ላይ አዝለሽ ወንዙን አሻግሪኝ» ሲል ይለምናታል። እንቁራሪቷም በፍርሃት «በፍጹም አላዝልህም፤ አንተ ጊንጥ ነህ፣ ወንዙ መሃል ስንደርስ ነድፈህ ትገለኛለህ» አለችው። ጊንጡም ምክንያታዊ መስሎ «እኔ ካንቺ ጋር እየዋኘሁ እንዴት እነድፍሻለሁ? አንቺ ከሞትሽ እኔም አብሬሽ እሰጥማለሁ፤ ስለዚህ ራሴን ልገድል አልፈልግም» ሲል አሳመናት። እንቁራሪቷም በንግግሩ አምና ጀርባዋ ላይ አዘለችው። ወንዙ መሃል ሲደርሱ ግን ጊንጡ መርዛማ ጅራቱን ሰብቆ በብርቱ ነደፋት። እንቁራሪቷ እየሰጠመች በመጨረሻው እስትንፋሷ «ለምን እንዲህ አደረግክ? ሁለታችንም እኮ ልንሞት ነው!» አለችው። ጊንጡም እየሰመጠ «ምንም ማድረግ አልችልም፤ ተፈጥሮዬ ስለሆነ ነው» ሲል መለሰላት። የሰው ልጅ የተፈጥሮ ባህሪ በምክንያት አይቀየርም፤ አጥፊ ሰዎችን ፀባያቸውን ይለውጣሉ ብሎ ማመን ከጥፋት አያድንም።
Open in Telegram. me:- email account ላክልኝ/ላኪልኝ them:- hack ልታረገኝ ነው 😵💫 ወላሂ በጣም ነው ምታናዱኝ እና ምታስቁኝ 😁 ማለት ነበር 👊
Open in Telegramውዱ ናፍቆቹን ያንገበገበው ❤️ ለሱ ነው ቀልባችን የሚንገበገበው❤️🩹 ጀማሉ በሆዴ አዲስ ያበበው 🤍 ሀድራሁን ዛታችን መቼ ጠገበው 💔 ሂርዜ መድሃኒቴ ማረፍያ ማረፈያ ነው ላይኔ💚 اللهم صل وسلم على نبينا محمد 🤲✨
Open in Telegramإِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ ሱረቱል አሕዛብ ቁጥር 56
Open in Telegram