Account

Posts of Prince Faysul

newest first

#10229Text

(قَالَ كَذَلِكَ قَالَ رَبُّكَ هُوَ عَلَيَّ هَيِّنٌ وَقَدْ خَلَقْتُكَ مِن قَبْلُ وَلَمْ تَكُ شَيْئًا) ﴿مريم: 9﴾ (ጅብሪል) አለ፦ «(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ጌታህ፦ "ከዚህ በፊት ምንም ያልነበርክን የፈጠርኩህ ስሆን፣ ይህ በእኔ ላይ ቀላል ነው" ብሏል።» "እርሱ በእኔ ላይ ቀላል ነው" ነብዩላህ ዘከርያ (ዐ.ሰ) በዕድሜያቸው አመሻሽ ላይ አርጅተው፣ አጥንታቸው ደክሞ፣ ሚስታቸውም መካን ሆና ሳለ የልጅ ናፍቆት ጠናባቸው። አላህንም በዱዓ መጎትጎት አበዙ። አላህም ልጅ እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው። በዚህን ጊዜ በመገረም፦ «ጌታዬ ሆይ! በዚህ ሁኔታዬ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» ሲሉ ጠየቁ። አላህም በጅብሪል በኩል መለሰላቸው፦ «እርሱ በእኔ ላይ ቀላል ነው።» አዎ፣ ለአላህ ቀላል ነው። ያ እንደ ተራራ የከበደህ፣ ሌሊት እንቅልፍ የነሳህ ጉዳይ አንተንም ጉዳይህንም ለያዘው ለአላህ ቀላል ነው። ያ ለሰው መፍትሔ አልባ የሚመስልህ ጉዳይ ለአላህ ቀላል ነው። ልብህን አረጋጋ! አላህ በወሰነልህ ነገር (በቀደርህ) ውስጥ ምንም ስህተት የለም። በሕይወትህ የምታየው ሁሉ መልካም ነው፤ ምክንያቱም የጻፈው ፍጹም ዕውቀት ያለው፣ ሁሉን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ ፍትሐዊ፣ ከፍ ያለና የተከበረ አላህ ነው። የሁሉንም ነገር ምስጢር ያውቃል፤ በምክንያቶች ሁሉ ላይ የበላይ ነው፤ እጅግ አዛኝና ወደ ባሪያው ቅርብ ነው። ችሎታው በዚህች ዓለም ላይ ያለ ብቸኛው የማይናወጥ መሠረት ነው። ልብህን አረጋጋ፤ እርሱ አላህ ነው! እኛ በጥበቡ እርግጠኛ የሆንን አማኞች ነን። የተዘጉ መጨረሻዎችን፣ የተቆረጡ መንገዶችን ወይም የጠፋ አቅጣጫን አናውቅም። የልባችን ኮምፓስ ሁልጊዜ ወደ ሰማይ ያመለክታል፤ እዚያ ፈጽሞ የማይሳሳት እውነተኛ አቅጣጫ አለ። ያ አላህ! ያ አላህ! ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ተስፋ አንቆርጥም፤ አናዝንምም። ጌታችን «እርሱ በእኔ ላይ ቀላል ነው» ብሎ እያለ፣ ለምን ተስፋ እንቆርጣለን? ሰላም ለልብህ ይሁን። [በሰለዋት የደመቀ በመልካም ስራ የታጀበ ጁምዓ ይሁንልህ ወዳጄ💖]

Open in Telegram
Views481−80%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
16 h383
33 h481
  1. After 24 hours383
  2. Total to date481
#10226Text
Views1,250−48%vs avg
Forwards—
Reactions29
Comments—
#10220Text
Views4,030+68%vs avg
Forwards—
Reactions50
Comments—
#10216Text
Views4,330+80%vs avg
Forwards—
Reactions41
Comments—
#10213Text
Views3,860+61%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—
#10211Text
Views2,930+22%vs avg
Forwards—
Reactions41
Comments—
#10206Photo

Forwarded from "ኡማ ቲቪ " Tv

ዛሬ ደስ ያለኝን ነገር ላካፍላቹህ ከልጅነት ጀምሮ እስከ መርከዝና ትምህርት ቤት በቅርበት የማቀው አንድ ወንድም ነበር ። ልጁ ጋር ብዙ ነገራቶችን አብረን አሳልፈናል አሁን ላይ በሀገረ አሜሪካ ነው ያለው አላህ መረጠውና በቅርብ ታዲያ በወላጁ ስም ለአባቱ ሰደቀተል ጃሪያ ይሆንለት ዘንድ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በአርጡማ ፍርሲ ወረዳ በጭረቲ ከተማ በአቡበከር መስጅድ ላይ ትልቅ የከርሰ ምድር የውሀ ቁፍሮ ፕሮጀክት አካሂዶ በዛሬው እለት ተመረቀ ። ብዙ ጊዜ ደግ ልጆች ወላጆቻቸው በሞት ሲያጡ በነሱ ስም ሰደቀተል ጃሪያ ላይ ይሳተፍሉ ። ይህ ወንድማችን ግን አባቱ የሚሰግድበት መስጅድ ላይ እንዲሁም በህይወት እያሉ ማመስገን ነው የሚገባው ብሎ በአባቱ ስም ትልቅ ወቅፍ ሰደቀተል ጃሪያ ሰራላቸው ። ይህ ልጅ ምነኛ የታደለ ምነኛ የተባረከ ነው ። አላህ ይቀበለው አላህ መሰሎቹን ያብዛልን እንዲሁም አላህ ኢማን ያለው ሀብት ወፍቆን ለወላጆቻችን ትላልቅ ሰደቀተል ጃሪያ እየሰራን የምናስደስት ያርገን ።

Open in Telegram
Views2,900+21%vs avg
Forwards—
Reactions29
Comments—