Posts of የኔ' ማስታወሻ ..🧚
በእውነት የሚያፈቅር ወንድ አንቺን ላለማጣት ሲል ራሱን ለመለወጥ፣ መጥፎ ልማዶቹን ለመተውና የተሻለ ሰው ለመሆን በሙሉ ልቡ ይታገላል። ነገር ግን «እኔ ባህሪዬ ይሄ ነው፤ ካልተመቸሽ መሄድ ትችያለሽ» የሚልሽ ከሆነ፣ ለአንቺ ምንም ዓይነት መስዋዕትነት የመክፈል ፍላጎት እንደሌለው በግልጽ እየነገረሽ ነው።ለአንቺ ሲል የማይለወጥን ሰው ደግሞ በግድ ለማስተካከል መሞከር አይቻልም፤ ምክንያቱም ለፍቅሩ ዋጋ የማይሰጥ ሰው ላንቺም ዋጋ አይሰጥሽምና! ርዕስ፦ እንደ ሴት ሁኚ እንደ ወንድ አስቢ ደራሲ፦ ስቲቭ ሃርቬይ @poethaymi
Open in Telegramለማንም ብዬ የምቀይረው ማንነት የለኝም። የተወለድኩት ራሴን ሆኜ ነው። እርቃኔን። ከልብስም ሆነ ከሀሳብም ንፁህ ሆኜ ተወልጃለሁ። የምኖረውም በራሴ ዓለም ነው።ዛሬ ተመልክቶኝ ነገ ለሚረሳው ገፅታዬ ምንም የምቀባባው ማሳመሪያ አልፈልግም።እንዲሁ እንዳለሁ ከተቀበሉኝ እሰይ።ካልሆነ ግን ገደል ይግቡ! ርዕስ፦ጥሪ ወደ ሞት ደራሲ፦አህመድ ሁስ(ሻድ) @poethaymi
Open in Telegramአብዛኛው ሰው ከኮሌጅ ወይም ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀ በኋላ፣ ትንሽዬ ሥራ ሲያገኝ «በቃ ሥራ አገኘሁ!» ብሎ እፎይ ይላል። ለምን እንደዚያ እንደሚያስብ ብትጠይቁት፣ ከተመረቀ በኋላ ሥራ ማግኘት እንኳን የማይቻል መስሎ ስለሚታየው ነው። ሥራ ማግኘቱ ብቻ እንደ ትልቅ እፎይታ ይቆጠራል። ከሕይወት የሚጠብቀውን ነገር ገና ከጅምሩ ዝቅ ስላደረገው፣ በዚያች ባገኛት ትንሽ ደሞዝ ውስጥ ታስሮ ይቀራል። ሰው ለራሱ የሚሰጠው ግምት ሲያንስ፣ የሚያገኘውም ውጤት ያንኑ ያህል ይሆናል... ርዕስ: በትልቁ ማሰብ ✍️ደራሲ: ዴቪድ ሸዋርትዝ @poethaymi
Open in Telegramአንድ ሰው ያለምንም ምክንያት ድንገት ከመጠን በላይ ሲያሞግስህ ተጠንቀቅ! ልክ አዳኝ ወጥመድ ከማጥመዱ በፊት ማባበያ እንደሚያስቀምጥ፤ ከመጠን ያለፈ የሰው ውዳሴም ከጀርባው የተደበቀ ፍላጎት ወይም ቅናት አለው። በአጭሩ የሰው ልጅ ስሜት ቋሚ መሰረት የሌለው ተለዋዋጭ ማዕበል መሆንን ተረድተህ ሁሌም ራስህን ጠንቃቃ አድርግ! የሰው ልጅ የተፈጥሮ ሕጎች ✍️ ሮበርት ግሪን @poethaymi
Open in Telegram ያለፈውን ወይም የወደፊቱን ህይወቴን አልኖርም ። አሁን ብቻ ነው የሚያስደስተኝ ። ☺️☺️ ምንጊዜም በአሁን ላይ ማተኮር ከቻልክ ደስተኛ ሰው ትሆናለህ😉 @poethaymi
Open in Telegramበሰዎች ዘንድ መወደድ ጥሩ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን መከበርና መፈራት የበለጠ ዋስትና ይሰጥሃል። ሰዎች የሚወዱትን ሰው እንደ ሁኔታው በቀላሉ ሊከዱት ወይም ሊረሱት ይችላሉ፤ የሚያከብሩትንና የሚያስፈራቸውን ሰው ግን ለመካድ ሁለት ጊዜ ያስባሉ። ስለዚህ በደግነትህና በየዋህነትህ ብቻ ሰዎች እንዲጫወቱብህ አትፍቀድ፤ የራሳቸው ወሰን እንዳላቸው አሳያቸው። 📕ርዕስ፦ልዑሉ ✍️ደራሲ፦ ኒኮሎ ማኪያቬሊ @poethaymi
Open in Telegram👉 “አንድ ሰው በእውነት እየተለወጠ መሆኑን ማወቅ ከፈለግክ… እነዚህን 3 ምልክቶች ተመልከት!” 1. #ለሁሉም_ነገር_ሰበብ_መፈለግ_ያቆማል። “እሱ ነው ያደረገው”፣ “እድሉ አልነበረኝም” ከማለት ይልቅ፣ “እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ?” ብሎ መጠየቅ ይጀምራል። 2. #ሁሉንም_ሰው_ማስደሰት_ያቆማል። በፊት ሰዎች ምን ይላሉ ብሎ ይጨነቅ ነበር። አሁን ግን የሚያውቀውን ትክክል ለማድረግ ይሞክራል። ምክንያቱም ሁሉንም ሰው ማስደሰት የማይቻል ሥራ መሆኑን ተረድቷል። 3. #ውጤት_ላይ_ያተኩራል_ማሳየት_ላይ_አይደለም። በፊት “እኔ እየሠራሁ ነው” ይል ነበር። አሁን ግን ብዙ አይናገርም ሥራው ይናገራል። @poethaymi
Open in Telegramአንቺ እስክታነሽው ባ'ራቱም አቅጣጫ ራሱን የሚጥል:- ደመራ ነው ልቤ በናፍቆትሽ ችቦ ነድዶ የሚቃጠል። ✍️ Solomon_sahle @poethaymi
Open in Telegram. ኢትዮጵያ የመንግስት ወሬ ነሽ፣ ያለብሽ ሺ ብድር መቅረፍ የማትችይ፣ የህዝብ አንድ ችግር ፈሪ ሲውልብሽ፣ ማያድርብሽ ደፋር የሌቦች ጉያ ነው፣ የድንበርሽም ዳር . ወደ ፊት ወደ ፊት፣ ምን ቢሉሽ ናት ከፊት ለኔ ካልደረሰ፣ ሚደርስልሽ ትንቢት ይኖራል ያሉትን፣ ካላየሁት ኑሬ ካለፈብኝ ኋላ፣ ቢያልፍልሽ ሀገሬ እንዳትቀየሚኝ፣ እቀየምሻለሁ ትንሳኤ ሲኖርሽ፣ ትንሳኤ እንዲኖረኝ፣ ሁሌ እናፍቃለሁ። 💚💛❤️ @poethaymi
Open in Telegramሰዎች ስለ እኔ ምን ይላሉ ? የሚል ሃሳብ ማቆም አለብህ፤ ሁሉም ነገር መሆን ያለበት አንተ ስለ ራስህ በምታስበው ነገር ላይ ነው።😊 @Poethaymi
Open in Telegramፀሎት ማድረግ የምችል አይመስለኝም። ሁልጊዜ ለፀሎት ስቆምም ሆነ ስንበረከክ የምለው ይጠፋብኛል። ምስጋና ሳበዛ የጎደለኝ ትዝ ይለኛል።ጥያቄ ሳበዛ የተደረገልኝ በአይነ ሕሊናየ ይመጣና ውለታ ቢስ የሆንኩ ይመስለኛል።ወዲያው ደግሞ ግሳንግስ ሐጥያቴ ትዝ ይለኝ እና የማመስገንም የመጠየቅም ሀሳቤ ይጠፋ እና ሀፋረቴ ይመጣል። ለማመጣጠን ስሞክር ደግሞ ፀሎቱን ትቼ ስራ የያዝኩ ይመስለኛል። በቃል ያጠናሁትን የተለመደ ፀሎት ባደርግ ይሻላል ብየ ስጀምር ራሴን መጨረሻው ላይ አገኘዋለሁ።በንባብም ቢሆን ያው ነው። አንዳንዴ ለራሴ ሠው እንዴት ከፈጣሪው ጋር መነጋገር ያቅተዋል??? ከስንቱ የሰው አይነት ጋር እየተግባባሁ እንዴት ከአምላኬ ጋር መግባባት ያቅተኛል??? እያልኩ በራሴ አዝናለሁ!!! ርዕስ:- ሚተራሊዮን ደራሲ:- ዶክተር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ @poethaymi
Open in Telegram( ሞክሼ ... ) ======== ያ ሁሉ እግዚኦ ያ ሁሉ ቢስሚላ ያ ሁሉ ጾም ጸሎት ያ ሁሉ ምህላ ... የት ነው የሚሄደው ስሚኝ እስቲ ሀገሬ ሞክሼ አለሽ ወይ ሌላ ?? Kiyorna @poethaymi @poethaymi
Open in Telegramአንድ ጠበቃ የውሃ ጉድጓዱን ለአንድ መምህር ሸጠለት። ከሁለት ቀን በኋላ ጠበቃው ወደ መምህሩ መጥቶ፦ "ጌታዬ! ውላችን እንደሚገልፀው የውሃ ጉድጓዱን ሸጥኩልህ እንጂ በውስጡ ያለውን ውሃ አልሸጥኩልህም! ውሃውን መጠቀም ከፈለግክ ተጨማሪ መክፈል አለብህ!" አለው። መምህሩም ፈገግ አለና እንዲህ ሲል መለሰለት፦ "አዎ፣ እኔም ወደ አንተ ልመጣ ነበር። ልልህ የነበረውም ውሃህን ከእኔ ጉድጓድ ውስጥ እንድታወጣልኝ ነው፣ አለበለዚያ ከነገ ጀምሮ በግድጓዴ ውስጥ ለሚኖረው ውሃህ ኪራይ መክፈል ይኖርብሃል" አለው። ጠበቃው ይህን ሲሰማ ደንግጦ፦ "ኦ! እኔ እኮ እየቀለድኩ ነበር!" አለዉ። መምህሩም እየሳቀ "እንደ አንተ ያሉ ሰዎች ጠበቃ የሚሆኑት እኮ ከእኛ ዘንድ ተምረው ነው!" አለው ይባላል። ©ተዋናይ @poethaymi
Open in Telegramከቀጠርሽኝ ቦታ ከቀጠሮው ሰዓት ቀድሜ መጥቼ ቆሜ ብጠብቅም አጥተሽኝ እንደሄድሽ አልጠራጠርም .... ✍️ Abreham aschalew @poethaymi
Open in Telegramእስኪ ንገሪኝ የኔ ቀረርቶ ፥ የኔማ ዛቻ መቁረጥ አያውቅም ፥ መገዝገዝ ብቻ፡፡ የኔም ስንብት ፥ የመለየቴ ጫፍ ቢቆይ እስከ ምሽት ፥ ቢርቅ እስከ ደጃፍ! "ቻው" ስልሽ ሰምቶ ከጭፍሮቹ ጋር ፥ መንገዴን ዘግቶ ናፍቆትሽ በሌት ፥ ይጠብቀኛል ፥ "አይኗስ?" ፥ ይለኛል "ሳቋስ?" ፥ ይለኛል "ጥርሷስ?" ፥ ይለኛል የማልችለውን ይጠይቀኛል፡፡ እስኪ ንገሪኝ … ስንቴ 'ቻው' ብልሽ ፥ ይቆርጥልኛል? ✍Habtamu Hadera @poethaymi
Open in Telegram