Account

Posts of ĐɆⱤɆ Info Hub

newest first

#6111Text
Views113−59%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#6108Text
Views123−56%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#6106Text
Views269−4%vs avg
Forwards—
Reactions119
Comments—
#6098Text
Views4,520×16vs avg
Forwards—
Reactions111
Comments—
#6077Text
Views876+214%vs avg
Forwards—
Reactions264
Comments—
#6076Photo

📜 "የማይሞተው ሞተ... የማይታመመው ስለ እኛ ቆሰለ!" 🕊️🩸 ዓለም ዛሬም ድረስ በምክንያት ብትክደውም፤ የማይሞተው ጌታ ስለ እኛ መሞቱ የድክመት ሳይሆን የፍቅር ጥልቀት ነው! እርሱ ሰማይና ምድርን የፈጠረ አምላክ ሲሆን፣ ስለ እኛ ፍቅር ግን የሰው ልጅን ስጋ ለብሶ በመካከላችን ተገኘ። 📖 "እርሱ ግን ስለ እኛ ኃጢአት ቆሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የሰላማችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።" (ኢሳይያስ 53:5) ✨ ጌታችን ሆይ... 📍 አንተ ሳትበድል ተገረፍክ ⛓️💔 📍 ሳታጠፋ ተሰቀልክ 🩸☦️ 📍 የማይሞተው አንተ ስለ እኛ ስትል የሞትን ጽዋ ተጎነጨህ 🍷 ዓለም "አልሞተም" ብላ ብትከራከርም፣ እኛ ግን በፈሰሰው ደሙ ታጥበናል፤ በመስቀሉ ላይ በከፈለው ዋጋ ነጻ ወጥተናል። ነገር ግን ሞት ሊይዘው አልቻለም! ዛሬ መቃብሩ ባዶ ሆኗል! 🦁 "ክርስቶስ ተንስኣ እሙታን - በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!" ☀️✨ አሰሮ ለሰይጣን፤ አጋዕዞ ለአዳም! ሰላም... እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሓ ወሰላም! 🕊️🎉 ይህ የትንሳኤ ብርሃን፦ 🌿 የቆሰለውን ልባችሁን የሚጠገንበት 🌿 የጨለመውን ተስፋችን የሚያበራበት 🌿 የታሰረውን ማንነታችሁን የሚፈታበት 🌿 ቤታችሁን በበረከትና በጤና ይሙላበት "ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሳትህ የት አለ?" (1ኛ ቆሮንቶስ 15:55) ⛓️💥 እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! ዛሬ የተሰቀለው ሳይሆን "የተነሳው" ጌታ በልባችን ይንገስ! መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልን ! 🌼🐣🌼🙌🌼 Dere empire 🔥

Open in Telegram
Views1,320+373%vs avg
Forwards—
Reactions606
Comments—
#6075Photo

የፍቅር ጥግ - ዕለተ ዓርብ (ስቅለት) "እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የሰላማችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።" (ኢሳይያስ 53:5) እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ዛሬ በዕለተ ዓርብ፣ ዓለም ታላቅ ድንቅን አየች። የማይሞተው አምላክ ስለ ሟቹ የሰው ልጅ ሲል ሞትን ቀመሰ። ሞት በሕይወት ምንጭ ላይ ስልጣን ባይኖረውም፣ እርሱ ግን እኛን ከዘላለም ሞት ቀንበር ያወጣን ዘንድ በፈቃዱ በመስቀል ላይ ተሰቀለ። ይህ ዕለት ፍቅር በከፍታ ላይ የታየበት ቀን ነው። 📍 የማይራበው ስለ እኛ ተራበ፤ 📍 የማይጠማው ስለ እኛ ተጠማ፤ 📍 የማይታመመው ስለ እኛ ቆሰለ፤ 📍 ሞት የማያሸንፈው ጌታ፣ ሞትን በሞቱ ይገድል ዘንድ በመቃብር አደረ። ጌታችን በመስቀል ላይ ሆኖ "ተፈጸመ" ሲል፣ የሰው ልጅ የባርነት ዘመን አብቅቶ የነፃነት አዋጅ መታወጁን አበሰረ። ያ ስለ እኛ የፈሰሰው ቅዱስ ደሙ፣ ከበደል ሁሉ አጥቦ አዲስ ሕይወትን ሰጠን። በዚህ የተቀደሰ ዕለት፣ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የገለጠውን ያንን ወደር የሌለው ፍቅር እያሰላሰልን፣ እኛም እርስ በርስ በመዋደድና ይቅር በመባባል እንድናሳልፈው እንመኛለን። መልካም የሰላምና የበረከት የስቅለት በዓል ይሁንልን! ☦️✨ 𝙳𝙴𝚁𝙴 𝚎𝚖𝚙𝚒𝚛𝚎🫶

Open in Telegram
Views423+52%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—