Account

Posts of የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹

newest first

#6018Link preview
Views1,100+170%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6016Photo
Views1,530+276%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6014Link preview
Views1,410+246%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6013Link preview

ስለዚህ ከቶ ዝም አልልም፤ በመንፈሴ ጭንቀት እናገራለሁ፤ በነፍሴም ምሬት አጕረመርማለሁ። ኢዮብ 7፥11 አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን ስለምናመነታባቸው ነገሮች በግልጽ ከርሱ ጋራ ለመነጋገር በጣም ደካማ፣ የራቀ ወይም ለመናገር የማይፈልግ እንደ ሆነ አድርገን እናስባለን። ሌሎች ደግሞ መቼም በእግዚአብሔር ላይ ጥርጣሬ፣ ንዴት ወይም ሐዘን ያለባቸው ሰዎች ሆነው መቅረብ አይፈልጉም። ኢዮብ ግን ስሜቱን ለመግለጽ ዐይናፋር አልነበረም። በእግዚአብሔር ላይ ያለውን ንዴት፣ ሕመምና ሐዘን አልካደም ነበር። እግዚአብሔርን ከሚያከብርና ደስ በሚያሰኘውም መልኩ ከኖረ ሕይወት በመነጨ፣ እውነቱን ተናገረ (ኢዮብ 1፥1)። ምንም ብንደክም፣ ግራ ብንጋባም ወይም ምንም ዐይነት ወጀብ ውስጥ ብንሆን፣ እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ያለንን ግንኙነት እንድንጠብቅ እንደሚፈልግ ኢዮብ ትልቅ ማስታወሻችን ነው። በትግሎቻችሁ ውስጥ ምንም ዐይነት ስፍራ ላይ ብትሆኑ፣ ለእግዚአብሔር ግልጽ ሁኑ። ስለ ስሜቶቻችሁ ግልጽ ሆናችሁ እርሱን አውሩት። አሁን ስላላችሁበት የሕይወት ምዕራፍ ግልጽ ሆናችሁ፣ ለሚሰማችሁ ሕመምና ሐዘን ዕውቅና ስጡ። እውነተኛ ሕመማችሁን፣ የጠለቀውን ጭንቀታችሁንና ትልቁን ፍርሀታችሁን እንዲያውቅና እንዲያገለግላችሁ ፍቀዱለት። የመዝሙር መጽሐፍ ለእግዚአብሔር ብዙ የጥያቄና የግራ መጋባት ጩኸቶችን ያስቀምጣል። ኢዮብ ስለ መከራውና ስለ ሕይወት ኢፍትሓዊነት በግልጽ ተናግሯል። ስለዚህ እናንተም፣ ለእግዚአብሔር ግልጽ መሆን ትችላላችሁ። ለልባችሁ እውነት ያልሆኑ ያማሩና የተስተካከሉ ቃላትን አለመጠቀም ትችላላችሁ። መንፈስ ቅዱስ ቃላቶቻችሁን ሊያነጻና የማይነገሩ የልቦቻችሁን ስሜቶች ሊገልጽ ስለ እናንተ ይማልዳል (ሮሜ 8፥26-27)። ዝም አትበሉ፣ የመንፈሳችሁን ጭንቀትና የነፍሳችሁን ምሬት ለሚያዳምጣችሁና ለስሜታችሁ ለሚጠነቀቅላችሁ ለአባታችሁ ንገሩት። https://kedusbible.com

Open in Telegram
Views1,330+227%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6012Link preview
Views1,080+165%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6011Video

Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

No text

Open in Telegram
Views1,040+156%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6010Link preview

አሁን ግን ቀድሞ ጠፍሮ አስሮን ለነበረው ሞተን፣ ከሕግ ነጻ ወጥተናል፤ ይህም አሮጌ በሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን፣ አዲስ በሆነው በመንፈስ መንገድ እንድናገለግል ነው። ሮሜ 7፥6 ጽድቅን ለማግኘት ሕግን ከመጠበቅ ነጻ ወጥተናል! ይህ ማለት ሕግ አልባ ነን ማለት ነውን? በፍጹም! ከሕግ ነጻ ያወጣን ጸጋ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስም በውስጣችን ዐብሮን እንዲኖር አድርጓል። መንፈሱ በራሳችን ፈጽሞ ልናደርግ የማንችለውን ማድረግ እንድንችል ኀይል ሊሰጠን ይችላል (ኤፌሶን 3፥14-21)። መንፈሱ በድካማችን ወቅት በልበ ሙሉነትና በመታመን መጸለይ እንድንችል ያግዘናል (ሮሜ 8፥26-27)። በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ፣ በእግዚአብሔር ጸጋና በክርስቶስ መንፈስ የተያያዙ ኀላፊነት የሚወስዱ ጓደኞች ያሉበት ኅብረት ውስጥ ገብተናል። የመንፈስ ፍሬዎች የሆኑት ማለትም ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ ገርነት፣ ራስን መግዛት (ገላትያ 5፡22-23) እናዳብር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳን እርስ በርስ መበረታታት እንችላለን። ኢየሱስን ስንፈልግና በሕይወታችን ስንገልጠው፣ እርሱን ይበልጥ እንመስላለን (2 ቆሮንቶስ 3፥17-18)። ቅድስናና ፍቅር በሚያስፈልግበት ዓለም ውስጥ በቅድስና እንድንኖር ይህን "አዲስ መንገድ" ስለ ሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን! https://kedusbible.com

Open in Telegram
Views1,030+153%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6009Link preview

መንገዳችሁንና ሥራችሁን በርግጥ ብታሳምሩ፣ በመካከላችሁ ቅንነት ቢኖር፣ መጻተኛውንና ድኻ አደጉን፣ መበለቲቱንም ባትጨቍኑ፣ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም ባታፈስሱ፣ የሚጐዷችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣ ለአባቶቻችሁ ለዘላለም ርስት አድርጌ በሰጠኋቸው ምድር፣ በዚህ ስፍራ አኖራችኋለሁ። ኤርምያስ 7፥5-7 የባሕርያችን ትክክለኛ መለኪያ ምንድን ነው? "ቤተ ክርስቲያን" ወይም እንደ እኛ ባሉ ሰዎች ፊት የምናሳየው ባሕርይ አይደለም። ባሕርያችንን ወይም እውነተኛ መንፈሳዊነታችን የሚፈትነው በሰማይ ካለው አባታችን ጋራ ያለን ግንኙነትና እርሱ የጠፉትን፣ የተረሱትን፣ የተዋረዱትንና የተሰበሩትን በማዳኑ ሥራ ላይ ያለውን መተባበር ነው። በዚህ ቊጥር ላይ ደግሞ፣ "መጻተኛውንና ድኻ አደጉን፣ መበለቲቱንም" በማለት ይገልጻል። ለራሳችን ብቻ ስንኖርና "የሌላቸውን" ሰዎች ደግሞ ፍቅር፣ ፍትሕና ምሕረት መስጠት ብናቆም የምንኖርበት ባህልና ማኅበረ ሰብ ይፈርሳል። ምክንያቱም ለተረሱና ብቸኛ ለሆኑ የሚሆነውን የእግዚአብሔር ልብ አይኖረንም። በተጨማሪም፣ "የሌላቸው" ሰዎች ውስጥ ቅንአትና ቂም ያድራል፤ "ያላቸው" ደግሞ የበላይነት ስለሚሰማቸው ማኅበረ ሰቡ እንደ ማኅበረ ሰብ መቀጠል አይችልም! የባሕርያችን እውነተኛ መለኪያ፣ በዙሪያችን ያሉ የተቸገሩትን ሰዎች የምንወድበትን መንገድ ነው። https://kedusbible.com

Open in Telegram
Views967+138%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6008Link preview
Views985+142%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6007Link preview
Views918+126%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6006Link preview
Views927+128%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6005Link preview
Views1,020+151%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6004Link preview
Views932+129%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6003Link preview
Views956+135%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—