Account

Posts of ነገረ ወንጌላውያን

newest first

#1827Text

የስም ማጥፋት ነገር እንደ ስም መጥፋት ክስ ስሙ የጠፋ የሚገኝ አይመስለኝም። ክሱ ገንዘብ ያላቸውና ጡንቸኞች የሚገለገሉበት ሆኗል። ከሰሞኑ “ወንጌላውያን ነን” የሚሉ ሰዎች የተቃወሞቸውንና የተቿቸውን ሰዎች በስም ማጥፋት መክሰስን ደጋግመውታል። ለሦሥተኛ ትዳር የሚያኮበኩቡ፣ በመድረክ በጌታ ስም የሚያላግጡት፣ እኩይ ተቋም መፍጠራቸው ሳያንስ በሙስና የተዘፈቁት ሁሉ ስማቸው እንደጠፋ ማሰባቸው ይደንቃል። የሰው አይን በአደባባይ የሚነርቱ፣ አስገድዶ ደፋሪዎች፣ ሰው የሚያግቱና የሚያስደበድቡ ስማቸው መጥፋቱን ማሰባቸው ይገርማል። እውነታው መሆን የነበረበት ከየትኛው መልካም ስም ነው አዲስ ስም የተለጠፈባችሁ የሚል ነበር። ለመሆኑ የትኛው መልካም ስም ነው የጠፋው? ይሄ ሃሰተኛ ነብያት ክርስትና ያነሳው ስም ይሆን? ወይንስ የብልጸግና ወንጌልና የእምነት ቃል ትምህርትን ወንጌላዊ ያደረገው ፀረ ክርስቲያናዊ ስም? ለስራ ቅጥር ገንዘብ ያስከፈለ ስም ጠፍቶ ይሆን? አልያስ ተቋማዊ ምዝበራን አቋም ያደረገው ስም ጠፍቷል? በእምነት ስም ሰዎችን scam ለማስደረግ ተቋማዊ መደላድል የፈጠረው ስም ይሆን የጠፋው? የትኛው መልካም ስም ነው የጠፋው? ቦታ ለከፈላቸው ሁሉ እንዲሰጣቸው ያሳልጣሉ የሚለው ስም ይሆን የጠፋው? ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የቄሣር ድምጽ ይሰማሉ የሚለው ስም ጠፍቶ ይሆን? አንድ ሰው ለሌላ ሰው ወይም ተቋም ሊረጋገጥ የማይችል ሃሰተኛና ከእውነታ የራቀ ስም ሲሰጥ ስም ጠፋ ይባላል ሲሉ ሕግ አዋቂዎችን ማድመጤን አስታውሳለሁ። እነዚህ ያለስማችን ስም ተቸረን የሚሉት ሁሉም ሰዎችና ተቋማት ቀረብ ብሎ ለተመለከተ በስማቸውና ግብራቸው ተጠሩ እንጂ ያለ ስም ስም አልተቸራቸው። እንደውም በአግባቡ በስማቸው የጠራቸው ስለመኖሩ ያጠራጥራል። ጥቂት ሰዎች በስማችሁ ስለጠሯችሁ እንጂ ስማችሁ እንዲሆን የፈለጋችሁት ሳይሆን በግብራችሁ የገለጣችሁት ነው። ቴዲ ያደረገው በስም መጥራት ነው። መጠራት በምትሹት ሳይሆን ስራችሁ በሚገልጠው ስም። በጎ ስም እንዳላችሁ ብታምኑ ኖሮ ምግባራችሁ በተለየ ነበር። ባለቤቱ እንዳለችው “ታሳሪዎቹ ከሳሾቹ” ናችሁ። እግዚአብሔር ይፍታችሁ። አማኑኤል አሰግድ

Open in Telegram
Views209−85%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#1826Text

የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከተቋቋመ ወዲህ ባሉት ዓመታት በቀያጭነት እና በመንግሥታዊ ቅርርብ/ድጋፍ ጥርጣሬዎች ውስጥ ሲተች ቆይቷል። ቴዎድሮስ ተጫንን የመሳሰሉ በሚዲያ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችም ይህንን ጨምሮ ብዙ ጉዳዮችን ሲተቹ ኖረዋል። ቴዎድሮስ ተጫን በተለይ ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ ሰዎችን ተችቷል (በትክክለኛም ይሁን በተሳሳተ ምክንያት)። አንዳንዱ ሲነካ ይመልሳል፤ ሌላው በዝምታ ያልፈዋል። በካውንስሉ ባይሆንም ከእኔ ጋርም ተጋጭተን እናውቃለን። እስከማውቀው ግን ክስ እና እስር ድረስ የደረሰ ምላሽ የሰጠ እንዳለ አላውቅም። አብዛኛው ሰው «ያልተግባባነው ወንድም ነው» ብሎ ቢያልፍ እንጂ ስምን ለማስከበር እና ለማፈን እዚህ ድረስ አይደርስም። ቴዲ አሁን ላይ በካውንስሉ ጉዳይ እስር ላይ እንዳለ እየሰማን ነው። ማንም አካል ወይም ተቋም ሕግ አጣቅሶ ስሙን የማስከበር መብት ቢኖረውም፣ የካውንስሉ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንደመሆኑ ከመደበኛ ሕግ በላቀ የሞራል ልዕልና እንዲያዝ እጠብቅ ነበር። በክርስቲያናዊ የሥነ ምግባር ልዕልና ቴዎድሮስ ኑፋቄ አላስተማረ፤ አሊያም የሥነ ምግባር ዝንፈት ውስጥ አልተገኘም ( የሚያደርገውንም ለርካሽ ዝና ያደርጋል ብዬ አላስብም)። ይልቁንም ካውንስሉን በእነዚህ ሁለት ወሳኝ ነገሮች መተቸቱ፣ እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያን ልጅ በሚችለው ማስረጃ መምጣቱ፣ ለዚህ እስር ሊዳርገው ይገባል? ቤተ ክርስቲያን በሙስና እና ምዝበራ በልጆቿ ስትተች ምላሿ ይህ መሆን አለበት? መቼስ ቃሉ ነው ለሁሉ መለኪያችን፤ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የዘር አድልዎ አለ ስትባል ምን አደረገች (ሐዋ. 6፥1-2)? ጴጥሮስ ሲሰብክ 3,000 የሚድነው፣ ጨርቁ ድውያንን የሚፈውሰው፣ መልአክ ከእስር የሚያስፈታው፣ ሙታንን የሚያስነሳው በቆርኔሌዎስ ጉዳይ በተነቀፈ ጊዜ ምን አደረገ (ሐዋ. 11፥2)? በግልጽነት የሆነውን ሁሉ አስረዳ። ጳውሎስም በ2ኛ ቆሮንቶስ 2፥14–7፥4 ያደረገው ያንኑ ነው፤ በትዕግሥት ንጽሕናን ማስረዳት። ንጹሕ ሆኖ ከተገኘ ደግሞ ለተቃዋሚዎች ሸብረክ አለማለት! ጥያቄው ቤተ ክርስቲያን እና መሪዎች የተነቀፉ ሲመስላቸው ቀድመው ወደ ፖሊስ፣ ደኅንነት እና መደበኛ ሕግ ነው መሄድ ያለባቸው? ክስ የቀረበባቸው መንፈሳዊ መሪዎች ንጹሕ ቢሆኑ እንኳን ንጽሕናቸውን በዋነኝነት የሚያረጋግጥላቸው ማን ነው? በቴዎድሮስ በታየው የካውንስሉ ድርጊት የሚለየው፣ ከማንም በላይ በውስጥ ምርመራ ይቋጫል ተብሎ ሲጠበቅ፣ ስሙን እና ሥልጣኑን ለማስጠበቅ እስከ ብረት እና ሰንሰለት ድረስ እንደሚሄድ ማሳየቱ ነው። ለምን? ክሱ ሐሰት መሆኑ ስለተረጋገጠ በቀል መሆኑ ነው? ወይስ ክሱ ማያወላዳ በመሆኑ ማምለጫ ለማድረግ? ምናልባትም ለቴዎድሮስ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም «ለተናገረኝ እንዲህ አደርጋለሁ» የሚል ማስጠንቀቂያ ለማስተላለፍ ይሆን? ካውንስሉ ተቃዋሚውን ሲያሳስር የመጀመሪያው እንዳልሆነ ሰምቻለሁ። በዚህ አጭር ተቋማዊ ዘመኑ የሰዱቃውያንን አካሄድ መከተሉ—ማለትም ከመንግሥት ጋር ተቀራርቦ ስጋትን የማስወገድ ዘዴ መላበሱ—ይታማል። ገና ከአሁኑ ቀና ብለህ የማታየው እና የማትናገረው አካል እየሆነ ነው። ይህ ድርጊት የካውንስሉን አባል አገልግሎቶች ስለ መብት እና ግዴታ እንዲያስቡ የሚያደርግ ነው (በተለይ ቴዎድሮስ አባል ከሆነ)። አባል አገልግሎቶች ግዴታቸውን ካደረጉ፣ መብታቸው እስከምን ድረስ ነው የሚለውን ማሰብ የሚጀምሩበት ወቅት ነው። ካውንስሉ ነገ ጉዳዩን የት ሊወስደው እንደሚችል ስላሳየ፣ የትኛውም ጥያቄ በሕግ አግባብ መደራጀት እንዳለበትም የሚያመላክት ነው። አባል ካልሆነ ደግሞ፣ እንደ ምክር፣ የካውንስሉ አባል ቢሆን የበለጠ የሚጠቅም ይመስለኛል። የመናገር መብቱን በአባልነት አውድ ውስጥ ቢጠይቅ የበለጠ የሚረዳው ይሆናል። ለማለት የፈለኩት ቴዲን ከመተቸት ጋር በማያያዝ ብቻ፣ መታሰሩን የሚጠበቅ አድርጎ ማየት ወይም ከዚያም ባለፈ «አብዝቶት ነበር፤ ይበለው» የሚል ምላሽ የሚያስከትለው አደጋ በጣም የገዘፈ ነው። ከቴዎድሮስ ጋር ድፍረት እና በግልጽ የመናገር ነጻነት አብረው ታስረዋል። ቴዲ እንደ ግለሰብ ነገ ይወጣል። እሱ ሲወጣ በዝምታ የደገፍነው ወይም ያለፍነው አካሄድ፣ ተቋሙ ነገ «ተራው የእናንተ ነው» (You are next) እያለን እንደሆነ ለማስታወስ ነው። አክሊሉ ኩማ

Open in Telegram
Views447−68%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#1824Text

የዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል ስል በእውነትና በጸጋው ወደ መሞላት መመለስ ይኖርባታል ማለቴ ነው። ይኽ ደግሞ ሊሆን የሚችለው በአቦሰጥ (randomly) አይደለም። ይኽ እንዲሆን በመጀመሪያ ደረጃ የቤተ ክርስቲያን ትኩረት ወደ ክርስቶስ ማንነትና አገልግሎት ምሳሌነት መመለስ አለበት። ክርስቶስን ምሳሌዋ ያላደረገች ቤተ ክርስቲያን የትም ጥሻ ውስጥ ናት። የሞተላትን እረኛዋን በመተው ሌላ ነገር የምትከተል ቤተ ክርስቲያን ስታለች። ሞቱንና ትንሣኤውን የስብከቷ አንኳር መልዕክት የማታደርግ ቤተ ክርስቲያን የርሱ አይደለችም። ተሃድሶ መንፈሳዊ መነቃቃት እንጂ አዕምሮአዊ ንቃት አይደለም። ለመንፈሳዊ መነቃቃት ደግሞ የሰውን ልብ የሚያዘጋጀው ወይም የሚከፍተው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። የምሁራን ትምህርት፥ የመንፈሳዊያን ልምምድ፥ የታላላቆች ምክር፥ የኃይማኖት መሪዎች ቅንዓት ቤተ ክርስቲያንን ያለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ ሊያነቃቃት አይችልም። አሁንም ልድገም ቤተ ክርስቲያንን ወደ ቃሉ ሥልጣን፥ ወደ ክብሩ፥ ሙላት፥ ወደ መንፈሱ አሠራር፥ ወደ ንስሓና ወደ ቅድስና ሕይወት ለመመለስ የሚያስችለው ቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ነው። ተሃድሶ ሰዎችን ወደ ሉተራዊነይ፥ ወደ ካልቪንስትነይ፥ ወደ ዌስሊያንነት፥ ወደ ጴንጤቆስጤያዊነት ማዘዋወር አይደለም። ወደ እግዚአብሔር ፍቅር፥ ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አገዛዝ፥ ለጌታ ወደሚኾን ታማኝነት፥ ለቃሉ ወደሚኾን ታዛዥነት ነው። ተሃድሶ ፕሮግራም አይደለም “reformation is not an event” የሚባለው ትክክለኛ መረዳት ነው። yes its not an event. ኮንፈራንስ አይደለም። ዝማሬና የአዳራሽ ውስጥ ጭፈራም አይደለም። ረጅም ጸሎት መቻል አይደለም። አቧራ ማጨስ መድረክ መሙላት አይደለም። የሚዲያ ጋጋታ የደጋፊ ብዛት አይደለም። የወረት ሰሞናዊ ግርግር አይደለም። ተሃድሶ የሕይወት ለውጥ ነው። የአካኼድ የአቅጣጫ ለውጥ ነው። ወደ መለኮታዊ አጀንዳ መመለስ ነው። ወደ እግዚአብሔር ደስታ መመለስ ነው። ቤተ ክርስቲያን በዚህች ምድር ባለችበት ዘመን ሁሉ እንድትሠራው ወደ ተሰጣት የምስዮናዊነት ተልዕኮ ወደ ነቢይነት ሚና መመለስ ነው። ወደ ቀደመው ክብሯ ወደ ነበራት ሥፍራዋ መመለስ ነው። መልካም የተሃድሶ መታሰቢያ ቀን ለፕሮቴስታንት ወንድሞችና እህቶች!! ብዬ ቋጨሁ። ወርቅነህ ዳዊት

Open in Telegram
Views2,940+112%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—
#1823Text

“Ecclesia semper reformanda est - ቤተ ክርስቲያን ሁሌም መታደስ አለባት (ይኖርባታል)።” በአሥራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተካኸደው የፕሮቴስታንት ተሃድሶ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን የእምነት አቋምና ልምምድ የፈተነ ወይም የፈተሸ ነበር። ጀርመናዊው ሉተር በ1517ዓ.ም ዘጠና አምስት ነጥቦች ያሉትን የተሃድሶ መግለጫ በዊተንበርግ የለጠፈው በዛሬው ቀን October 31 ነበር። ሉተር ቤተ ክርስቲያን የገባችበትን ግብረገባዊ ውድቀት በተለይም የኃጢአት ይቅርታ እንደ ሸቀጥ ለሽያጭ የሚቀርብበትን ሁኔታ በመቃወም ነበር የተሃድሶ ፈር ቀዳጅ በመኾን የተነሳው። ሁኔታው ተመችቶት ወይም እንደሌሎች መነኩሴዎች ዝምታን መርጦ መቀመጥ ቢችልም ይኽንን ማድረግ ምርጫው አልነበረም። በልዩነት አቋሙን ይዞ ወጣ። እንግዲህ ተሃድሶው በኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነቶችና ልምምዶች ላይ የተወሰደ የተቃውሞ እርምጃ ነበር። የአመጽ እርምጃ ሳይኾን የመንፈሳዊ መነቃቃት እርምጃ ነበር። የግብረገብ ውድቀት (Moral decay) በሚኖርበት ጊዜና ሁኔታ ሁል ጊዜም ተሃድሶ ግድ ነው። በዚያ ዘመን አማኙ ማኅበረሰብ ቃሉን ለማግኘትም ኾነ በቃሉ ሕይወቱን ለመምራት ዕድል አልነበረውም (lack of access to scripture ነበር) መጽሐፍ ቅዱስ ከላቲን ውጭ ባልነበረበት በዚያ ሁኔታ ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊው መንፈሳዊነት ትውልዱን ለመመለስ ሉተር ተነሳ። የሚከፈለውን መሥዋዕት ሁሉ የሚጠይቀውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ራሱን አዘጋጅቶ ወደ ሥራው ገባ። ድኅነት በጸጋው በእምነት አማካይነት ብቻ፥ የበላይ ባለ ሥልጣንና መለኮታዊ መገለጥ ቃሉ ብቻ፥ የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና ክብር ለርሱ ብቻ፥ ለሕትወታችን ድኅነት የተሰጠን ሥጦታ መካከለኛው የሕይወታችን ማዕከል ክርስቶስ ብቻ በሚል መንፈሳዊና ሥነ መለኮታዊ ተጽዕኖ ያሳደሩ አቋሞች በዚህ ወቅት ተገልጸው ነበር። በተለይ በጊዜው በተነሡ ሌሎችም አባቶች ታምነው በሂደት ጥርት ያለው የአምስቱ ብቻ አቋም (five solas) ድንቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘመን ዘለቅ የእምነት አቋም ነበር። ተሃድሶው ያስከተላቸው ሁለንተናዊ ተጽዕኖዎች ሊዘረዘሩ ይገባል። ቤተ ክርስቲያንን ከነበረችበት ሁኔታ ፈቀቅ ሊያደርግ የቻለ ብቻ ሳይሆን አውሮፓን በሁለንተናው የለወጠ ተሃድሶ ነበር። መንፈሳዊና ሥነ መለኮታዊ በረከቶችን ሁሉ አማኝ በእምነት አማካይነት በግሉ መጎናጸፍ እንደሚችል ያመለከተ & የእግዚአብሔርን ጸጋ ያለግዢ በነጻ በእምነት ቀርቦ መቀበል እንደሚችሉ ያሳየ እንቅስቃሴ ነበር። የቤተ ክርስቲያን እረኞች (የቄሳውስት) አገናኝ ጣልቃ ገብነት አማኝ እግዚአብሔርን በግሉ ማወቅና መከተል እንደ ጌታ ማገልገል እንደ አባት ማናገር እንደሚችል መልሶ ያሳሰበ ክርስቶስን ያመነ ሁሉ የንጉሡ ካሕን መኾኑን ያበሰረ ተሃድሶ ነበር። አማኞች የእግዚአብሔርን ቃል በግላቸው የማንበብ፥ የመረዳት፥ ለቃሉ የመታዘዝ መንፈሳዊ አቅም ያላቸው መኾኑን ያስገነዘበ ነበር። ከዚህ ሁሉ ጋር አማኞች የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ አማኞቹ መረዳት በሚችሉት ቋንቋ እንዲኖራቸው እንዲያጠኑና በሕይወታቸው እንዲተረጉሙ ያደረገ ነበር። ድኅነት ሰው በጥረቱ የሚያገኘው ሳይኾን የእግዚአብሔር ነጻ ሥጦታ መኾኑን በማወቅ እምነቱን በጌታ ብቻ እንዲያደርግ ያደረገ ነበር። መንፈሳዊ ጥገኝነትን ያስወገደ አማኞችን በግላቸው የተዘጋጀላቸውን የድኅነት በረከት እንዲያገኙ ያዘጋጀ የእምነት እጃቸውን ዘርግተው እንዲቀበሉ ያደረገ ነበር። በቄሳውስቶችና ካሕናት ዘንድ የነበረው የባለቤትነት ስሜት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከዛሬው በባሰ ነበር። ቤተ ክርስቲያንን እንደ ባለአደራ ሳይኾን እንደባለቤት ቆጥረው ያሻቸውን ያደርጉ ነበር። ይኽንን አስገባሪ ሁኔታ ተሃድሶው ሽሮአል። አንዳንዶች ራሳቸውን በተለየ ሁኔታ ለእግዚአብሔር የቀረበ በማስመሰል ሕዝቡን እንደ ዛሬው ለሸቀጥ አጋልጠው ያስጨንቁ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ በአውሮፓ ትምህርትና ሥልጣኔ እንዲስፋፋ ምክንያት የሆነ እንቅስቃሴ ነበር። የግለሰብ ነጻነትና ሰብዓዊ መብት በተመለከተም ተሃድሶ የራሱን አሻራ ያስቀመጠ ነበር። ነባሩን የሮማውያንን የፖለቲካ ሥልጣን የበላይነት ወደ ፖለቲካዊ ፕሉራሊዝም ወይም ሌሎች አማራጮችን የማየት ያስቻለ ነበር። መንፈሳዊና ግብረገባዊ ብቻ ሳይኾን የኢኮኖሚያዊ አውታርና የፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ሁሉ ዓይን ከፋች እንቅስቃሴ ነበር። ማኅብረሰቡ ከተለያዩ እሥራቶች በመፈታት ወደ ሕሊና ነጻነት እንዲመጣ የበኩሉን ጉልህ ድርሻ የተወጣ ነበር ተሃድሶው። በጊዜው በነበረው ማኅበረሰብ ዘንድ ብቻም ሳይኾን ሁል ጊዜም በየሥፍራው እውነት፥ እምነት፥ የሕሊና ሕግ ሊታደስ የሚገባ መኾኑን በግልጽ ያመለከተ ድንቅ ንቅናቄ ነበር። በርግጥ ተሃድሶው አዲስና መጤ አስተሳሰብ ሳይኾን ቤተ ክርስቲያንን ወደ ቀደመው አዲስ ኪዳናዊው ትምህርትና ልምምድ የመለሰ ነበር። ምሁራን ስለ ተሃድሶ በሰጡት ምስክርነት:- “The Reformation was essentially a revival of New Testament Christianity.” (J.I. Packer) ብለዋል። ይህ አባባል የማያግባባቸው አንዳንድ ዘመነኞች በዚህ ዘመን የተሃድሶ መሪዎችን ተሃድሶአዊ እንቅስቃሴና እርምጃ ሲያጣጥሉ እየሰማን ነው። ይኽ ደግሞ አሳዛኝ ክስተት ነው። እነዚህ ወጣቶች ወደ ጥንታዊው ክርስትና የመመለስን አስፈላጊነት ቢናገሩም ይኽንን ታላቅ ሥራ ግን የማጣጣል ምንም ሞራል አይኖራቸውም። ይኽንን የተሃድሶ አምድ ሳንለቅ ቅ በዚህ ዘመን የሚያየውን የቤተ ክርስቲያን ችግር እንቅረፍ ማለት እንጂ ይኽንን የተሃድሶ ሥራ በማጣጣል የሚጀመር ምንም እንቅስቃሴ ሊኖር አይገባም ብዬ አምናለሁ። ይህንን ያህል ለመግቢያ ካልኩ ወደ ዋናው ሃሳቤ ልግባ። ቤተ ክርስቲያን ሁሌም ለተሃድሶ ክፍትና ዝግጁ መኾን ይኖርባታል። የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችም ቤተ ክርስቲያንን ወደ እግዚአብሔር ቃል፥ ወደ እግዚአብሔር ጸጋ፥ ወደ እግዚአብሔር ክብር፥ ወደ ክርስቶስ ማዕከልነት፥ ወደ ተልዕኮው ትኩረት መጣራት ይኖርባቸዋል። የአዲስ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያን ዕለት ዕለት የምትታደስ ራሷን በቃሉ መርህ መሠረት የምትፈትሽ ድንገት ከሳተችም አቋሟን የምታስተካክል ናት እንጂ በገባችበት የሥነመለኮታዊና መንፈሳዊ ችግሮች ተውጣ የምትቀመጥ አይደለችም። ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ዘመን የሰው ባሕልና ልምድ የሰው ልምምድና ሥርዓት ሳይኾን ቃሉ በበላይነት የሚመራት በመንፈስ ቅዱስ አሠራር የምታምንና ፈቃዱን የምትከተል መኾን ይኖርባታል። ልኬቷ ተበላሽቶ መርከብ ያለ መሪ እንደሚጓዝ በምድር ባሕር ተለቅቃ መጓዝ የለባትም። ተሃድሶ አማኞችን ከከንቱ ኃይማኖታዊ ሥርዓት ይልቅ ከጌታ ጋር ሊኖር ወደሚገባው ግላዊ ግንኙነት የሚመራ፥ ሰዎች በክርስቶስ አማካይነይ የተዘጋጀላቸውን ጽድቅና ክብር ወደመጎናጸፍ እንዲመጡ የሚያደርግ መኾን ይኖርበታል። አማኞች ከእግዚአብሔር በነጻ ላገኙት ለጸጋው ሥጦታ ካላቸው ክብርና ምሥጋና ተነስተው በሙሉ መሰጠት ተቀድሰው እንዲኖሩ የሚያስችል መኾን ይኖርበታል። ተሃድሶ ከአጉል ወግ አጥባቂነትም ሆነ ከልቅ ለዘብተኛ ማንነት የሚያላቅቅ ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት የሚያስገዛ መሆን ይኖርበታል። በነገራችን ላይ እውነተኛ ተሃድሶ ትርጉሙ አጭርና ግልጽ ነው ይኼውም renewal through truth and grace ሊባል ይችላል። ክርስቶስ የምድርን ሁኔታ ለመለወጥ ሲመጣ የተሞላው በነዚህ በሁለቱ ነበር። truth and grace የማይገነጣጠሉ ነገሮች ናቸው።

Open in Telegram
Views1,310−6%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#1821Text

የዛሬ 509 ዓመት፣ በዛሬዋ ዕለት፣ በኦክቶበር 31፣ 1517 አመተ እግዚ አንድ ብዙም የማይታወቅ የአውገስጢኖስ ገዳም መነኩሴ፣ በአንዲት ትንሽ የጀርመን ዩኒቨርስቲ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ፕሮፌሰር የነበረ ሰው በዩኒቨርስቲው ቅጥር ውስጥ በሚገኘው የቤተ ክርስትያን በሮች ላይ የተወሰኑ ወረቀቶችን ለመለጠፍ መዶሻ አነሳ። እነዚያን ወረቀቶች በቤተ ክርስትያን አደባባይ ላይ የለጠፈበት ምክንያት የቤተ ክርስትያኑ አደባባዩ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንደ ማስታወቅያ ሰሌዳ ያገለግል ስለነበር በርከት ያለ ሰው እንዲመለከተውና ውይይት እንዲያጭር አስቦ ነበር። በለጠፈው ወረቀት ውስጥ 95 አናቅጽት በዋናነት የሰውን ድኅነት እንደ ቁስ መገዛቱን በማውገዝ ነበር። ሰው ከፑርጋቶሪ ይወጣ ዘንድ የኅጢአት ይቅርታ ሰነድ በመኸከለኛ ዘመኗ ካቶሊክ ለጉድ ይቸበቸብ ነበር። ይህ ሰነድ ወይም 'ኢንደንጀልስ' በወረቀት የሰፈረና የቤተ ክርስትያንን ይሁንታ አግኝቶ መግዛት ለቻለ ሁሉ የቀረበ ነበር። ህዝቡም ኢንደልጀንሱን ይገዛ ዘንድ 'በቅቤ አቅልጥ' ደላላ አሻሻጮች ይጎተጎት ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ይሁንታዋን ሰጥታ ነበር። ህዝቡ ለራሱ፣ ለዘመዱና ለወዳጁ ይገዛ ነበር፤ በሞቱት ስም እንኳን ሳይቀር ይቸረቸራል። ሉተር 95 አናቅጽቱን ጽፎ ሲለጥፋቸው ዩኒቨርስቲ ውስጥ ባሉት ፕሮፌሰሮች መሃል ውይይት እንዲፈጥር በማሰብ ነበር። ነገር ግን ዘጠና አምስቱ አናቅጽት ከቪተንበርግ ማኅበረሰብ በዘለለ በመላው የጀርመን ግዛቶችና በጠቅላላው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዘንድ ታላቅ ሁካታን ለመፍጠር በቃ። በአጭር ጊዜ ውስጥም ብዙ ህዝብ የዚህን መነኩሴ ስም ማወቅ ጀመረ፣ በቪተንበርግ ዩኒቨርስቲ የሥነ መለኮት ዶክተሩን ማርቲን ሉተርን። ህዝብን በማወክና ባለመታዘዝ ቤተክርስትያን ከሰሰቸው፣ በጀርመን ንጉስ ፊትም ራሱን እንዲከላከልና ያደረገው ሃሰት መሆኑን አውቆ እንዲያስወግድ ታዘዘ። ያደረገው ስህተት መሆኑን ባለመቀበሉና ህሊናው ለቅዱሳት መጽሐፍት ተገዢነታቸውን በማጽናቱ ምክንያት የውጤቱን ስሜት 500 አመታትን ተሻግሮ ዛሬ እኛም ይሰማናል። . «ስቻለሁ የምለው አንዳች ነገር የለኝም፤ ኅሊናዬ ከሚያዘኝ ውጪ መሆን ትክክልም ሆነ አግባብ አይደለም። እነሆ፤ እዚሁ ቆሜያለሁ፤ ከዚህ ውጪ ምንም ላደርግም አይቻለኝም። እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ። አሜን።» . ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እንዳሉት፣ "አሕይዎና ተሐድሶ (Revival and Renewal or Reformation) ተደላድሎና ተመቻችቶ በተቀመጠ ሥርዐት (Establishement) ውስጥ የዛገና የሚራገፍ ነገር የሚያይ የአእምሮ ችሎታና የተፈጥሮ ተሰጥዎ ካላቸው ታላላቅ ሰዎች ዘንድ የሚመጡ ሐሳቦች ናቸው።" በዚህ ሰው ለመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት በታማኝነት መታዘዝና መሰጠት ምክንያት የቤተክርስቲያን መልክ እንደ ቀደሞው ላይሆን ተለውጧል። . ተሐድሶ ብቻ መቆምን ይጠይቃል። ዘመንን መረዳትን፣ መጽሐፍትን መመርመርን፣ ለእግዚአብሔርና ለህሊናችን ታማኝ መሆንን ይጠይቃል። ተሐድሶ ወደ አባቶችና አያቶች ለመንፀሪያ መመልከትን አንደ ቄንጥ አያይም። የድነትን መኸከለኛ፣ የእምነትን ፈፃሚ፣ የእግዚአብሔርን መገለጥ፣ ትምሕርተ ክርስቶስን አደብዛዥን ሁሉ ለመቃወም ሁለቴ አያስብም። ተሐድሶ ቃለ–እግዚአብሔር ማሕደረ–ክርስቶስ በተባለችው ቤተክርስቲያን ሲደፈጠጥ ጥሪውን በማማ ላይ ያሰማል፤ እነሆኝ ለህሊናዬም ለቃሉም ቆሜያለሁ ይላል። እግዚአብሔር ልጁን በገለጠበት ቃል በኩል ለኅሊናዬ ብቻዬን እንኳን ቢሆን እቆማለሁ የሚል እውነትና ፅናት ያድለን። . የዛሬ 509 ዓመት የተለኮሰውን የተሐድሶውን እሳት ነገ በቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቤተክርስቲያን ከቀኑ 9:00 ጀምሮ እናስበዋለን! ወደ ተተሓድሶው እሳቤዎች መመለስ ከእምነት ድንጋጌ እና ከእምነት መግለጫዎች ስልጣን ሥፍራ አንጻር እንቃኛለን። መልካም ዕለተ ተሐድሶ ማስታወሻ! አማኑኤል አሰግድ

Open in Telegram
Views2,270+63%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#1818Photo
Views2,140+54%vs avg
Forwards—
Reactions30
Comments—
#1817Photo

የ16ኛው ክፍለ ዘመን ተሓድሶ አዲስ ሃይማኖት አዋላጅ አልነበረም። የቀደመውን መንገድ ወደ ኋላ አሽቀንጥሮ በተለየ ጎዳና ላይ ክርስትናን የወሰደም ተደርጎ አይቆጠርም። ይልቁንም ተሓድሶው ተመላሽ ነበር። ወደ ሐዋርያዊቷ ቤተክርስቲያንና እምነት፣ ወደ አባቶች አስተምህሮና አቋም ተመላሽ ነው። የእምነት ድንጋጌዎችንም ሆነ የእምነት መግለጫዎችን የተቀዱት ከቅዱሳት መጽሐፍት ምስክርነት መሆኑን እያጸና ወደ ኋላ ይመለሳል። እውነተኛ ተሓድሶ ወደ ኋላ በመመለስ እውነተኛውንና የቀናውን መንገድ ለመያዝ ይጥራል። ቤተክርስቲያን አንድም በሰብዐዊ ድካም ወይም በዘመን ብዛት በሚከሰት ብዥታ አልያም በቸልታ ለእውነተኛው መንገድ ማደር ሲያቅታት እግዚአብሔር በተሓድሶ ንፋስ እያጸዳ በቃሉ ብርሃን ያጸዳታል። የሆነውም ይህ ነው። የፊታችን እሁድ ከቀኑ 9:00 ላይ በቅዱስ ማቴዎስ አንጌሊካን ቤተክርስቲያን ብቅ ብትሉ ተሓድሶውን እያወሳን ስለ እምነት ድንጋጌዎች፣ ስለ እምነት መግለጫዎች እንዲሁም ተዋስኦዊ ሥልጣን በተሓድሶው እንዴት እንደነበር እናያለን። ወደ ተሓድሶው መመለስ አለብን ብለን እንጮኸለን። ከቻላችሁ ተገኙ!

Open in Telegram
Views1,820+31%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#1815Text
Views2,190+58%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#1813Text

"የተነሳው ውዥንብር፣ ቄስ ደረጄንም ይነካል!" የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ፣ መጋቢ ጌትነት ለማን በተመለከተ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተነሳው ጥያቄ ሄዶ ሄዶ እዚህ ደርሷል። በAI (አርቴፊሺየል አስተውሎት) ተላክኮ የነበረው እና AI ራሱ፣ "የእኔ እጅ የለበትም!" ብሎም ሳይታመን የቆየው ጉዳይ ህያው ባለቤት አግኝቷል። ዛሬ፣ በወዳጄ ቴዎድሮስ ተጫን Tewodros Techan የኅዋ ሰሌዳ ላይ ተለጥፎ በተመለከትሁት፣ "የካውንስሉ ካንሰር" የሚል ርዕስ በተቸረው ቪዲዮ ውስጥ፣ ካውንስሉ ቢሮ ለመቀጠር ከመጋቢ ጌትነት ለማ ጋር የገንዘብ ድርድር ሲያደርግ የነበረው ግለሰብ ተከስቶ፣ "እኔ ነኝ!" ብሏል። የመረጃውን፣ "ከዬት መጣ፣ ከዬት ወጣ?" ጥያቄም መልሷል። መቶ ሺህዎችን ጉቦ ከፍሎ በካውንስሉ ቢሮ ተቀጥሮ ለሰባት ወራት የቆየው፣ መጋቢ ጌቱ በቀለ የሚባለው ይህ ሰው በቃለ ምልልሱ ስለ ጠቅላይ ጸሐፊው ብዙ ብሏል። ቀደም ብሎ በእርሱ ቦታ ስለነበሩት እና አሁን ላይ የካውንስሉ ፕሬዚዳንት ስለሆኑት ቄስ ደረጄ ጀንበሩ የተናገረውም ቢሆን በጣም ይከነክናል። "ሥራ ለመቀጠር እጅ መንሻ በመስጠቴ ተሳስቻለሁ፣ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ጭምር ሠርቻለሁ!" የሚል ኑዛዜ ያሰማው ጉቦ ከፋዩ መጋቢ ከሰባት ወር በፊት ሥራውን ለመልቀቅ ያበቃው ምክንያትና ከጠቅላይ ጸሐፊው ጋር የፈጠረው ግጭት እርሱ እንደነገረን ይሁንም አይሁንም ስለዚያ ቤት ማወቅ ያለብንን እንድናውቅ ግን አደርጎናል። እናም በካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ጌትነት ለማ ጉዳይ የተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ስለ ፕሬዚዳንቱ የተባለውንም አብሮ ማየት እንዳለበት ተሰምቶኛል። ከድምጽ ወደ ፊደል ቀይሬም ከሥር እንደወረደ አኑሪያለሁ፤ የቪዲዮውን መስፈንጠሪያ ደግሞ በአስተያየት መስጫ ሳጥን ውስጥ አስቀምጫለሁ። "አሁን በካውንስሉ ውስጥ የተነሳው ውዥንብር፣ [የካውንስሉን ፕሬዘዳንት] ቄስ ደረጄን የማይነካ ዓይደለም። በዋናነት ተጠያቂ እሳቸው ናቸው።...ለጌቱ ከለላ እየሰጡ ያሉት እሳቸውም የጥቅም ተናጋሪ ስለሆኑ ብዬ አስባለሁ። ለምሳሌ የቀድሞ ፕሬዘዳንቶች፣ ፕሮፌሰር እያሱ፣ ዶ/ር ጣሰው፣ ፕሬዘዳንት በነበሩበት ወቅት አንድ ሲም ካርድ አላቸው፣ ስብሰባ ሲኖር እና የተለያዩ ፕሮግራሞች ሲኖር ሰው ተልኮ በመኪና ያመጣቸዋል። "ቄስ ደረጄ ግን [ከቀድሞ ቦታቸው ተነስተው ፕሬዘዳንት ከሆኑ በኋላ] መኪና አልተወሰደባቸውም፣ ቢሮ አለቀቁም፣ በወር 60,000 ብር ይከፈላቸዋል፣ የመኪና ነዳጅ 30,000 ብር ይሰጣቸዋል፣ የወንበር 30,000 ሺህ ብር፣ በጠቅላላው በወር 120,000 ብር ያገኛሉ። ሥራ አስፈጻሚው ይኼን አያውቅም፣ መተዳደሪያ ደንቡም ይኼን አይፈቅድም። ስለዚህ አጣሪ ኮሚቴው ይህንንም ማጣራት አለበት።" ብሏል። © ሽመልስ ይፍሩ

Open in Telegram
Views2,630+89%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#1812Text

ቃሉ የሚለውና በግልጽ የሚነግረን ይህንን እንጂ ሴት ባጠቃላይ መቼም-መች አትመራም አታስተምርም የሚል እንዳይደለ ይረዳል፡፡ . የዚህ ቁ 12 ነገር የሚጀምረውም ከቁ 8 ነውኮ። ከዚያ ጀምሮ ነው መነበብ ያለበት። ቁ8 ወንዶችን ሁሉ ሰለአምልኮ ሥርአት ይመክራል፤ ከቁ 9 ጀምሮ ድግሞ ሴቶችን ይመክራል፡፡ አንዱ ምክር ሴቶቹ "በሹሩባና በወርቅ ወይም በዕንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ" ይላል፡፡ እናሳ? ይህ በታሪካዊ ዳራ ካልተፈታ እና ቃሉ ለዚያ ዘመን እንደተናገረ ካላመንን፤ ይህንንም እንደ ቁ12 ሁሉ ያለምንም ማንገራገር ሴቶቻች መተግበር አለባቸው!? ሰዎቹ ወንዶቹ ሰባኪዎቻችስ፡- ይህንን ለልጅ ሚስቶቻቸው ያደርጉታል? ያ ምርጡ ነገር ዕንቁ ዳይመንድ ጌጥ ላይ ያስጨክኑ? አያደርጉትም፡፡ እንደምናውቀው ደግሞ ዛሬ የጨዋ ሴቶች መገለጫ ሹሩባ ነው፤ ይህንን የኛዎቹ እህቶች ተስማምቷቸው አምሮባቸው ነው ያየነው፡፡ በቤተከርሰቲያን ውስጥ በጉባኤ የሚያገለግሉም ዘማሪም ሰባኪ ሴቶች ሲዋቡበት ሳይ ደስተኛ ነኝ፡፡ በቅርቡም ጊዜ ቢሆን በሀገራችንም ሴቶች አለባበስ ላይ የነበረው ጥብቅ አቋም እናውቃለን (ሹሩባ ሲከለከል እንደነበረ ባላውቅም)፡፡ ጥያቄው፡- ያኔ በነ ጳውሎስ ጊዜ ሹሩባ ምን ቢሆን ነው ተከለከለው? ይህን ክፍል ለመረዳት ታሪካዊ ዳራ ወሳኝ ነው፡፡ አርጤምስ እና በመቅደስዋ የሚያገለግሉት ሴት ካህናት ደግሞም የከተማዋ ዘማዊያን የአለባበስ እና ጸጉር ስታዬል መታዬት አለበት፡፡ ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን? አምናለሁ፤ ያነሳኋቸውን ነጥቦች መረዳት ቁጥር 12ን እና ትክክለኛውን ስለሴቶች አገልግሎት ያለውን አመለካከት ለመቀበልም ለማረቅም ጥሩ መነሻ እንደሚሆን፡፡ . . ..... ይቀጥላል (በሚቀጥለው ከፍል 2፡- በመጀመሪያ ኣዳም መፈጠሩን መጠቀሱ፤ ስለመጋቢያን መልእክቶች፤ ሴቶች ስለተከለከሉበት እና ስለተፈቅደላቸው አገልግሎት ዘርፎች ከታሪካዊ ዳራ ጋራ አጣምረን እንመለከታለነ፡፡ በ1ጢሞ 2 እና በ1 ቆሮንቶስ ላይ ስለሴቶች አገልግሎት ላይ እጅግ የተከበሩ የነገረመለኮት መምህራን ምን እንደሚሉም እናያለን፡፡ . . ዋቢ፡ Craig Keener. ‘Was Paul For Or Against Women In Ministry?’ https://news.ag.org/en/article-repository/news/2001/02/was-paul-for-or-against-women-in-ministry https://craigkeener.com/.../EJ_2001_02_Spring_Keener-1.pdf በቪዲዮ ለሚወዱ፡ https://www.youtube.com/watch?v=xyZr-K3STsU Cynthia Long Westfall, The Meaning of αὐθεντέω in 1 Timothy 2.12, Journal of Greco-Roman Christianity and Judaism 10 (2014): 138-73. Douglas Moo, “1 Timothy 2:11-15: Meaning and Significance” in Trinity Journal 1, no. 1 (Spring 1980): 62–83): 82. Gordon Fee, 1 and 2 Timothy (San Francisco: Harper & Row, 1984), 37 ሰለ ሴት አገልግሎት ተቋዋሚዎች አንዳንድ አስገራሚ ነጥቦታቸውን ማወቅ ከፈለጋችሁ፤ https://plymouthbrethren.org/article/511 John MacArthur፣ The MacArthur Bible Commentary፣ 1 Timothy 2:15 የፕሮፌሰር ኪነር ትምህርት በቪዲዮ፦ https://www.youtube.com/watch?v=xyZr-K3STsU አፈወርቅ ኃይሉ (ዶ/ር)

Open in Telegram
Views1,410+2%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#1811Text

እንደነገሩ "ቃሉ ይላል፤ በቃ ታዘናል" ብሎ ማለፍ ለማን ቢጠቅም ነው? ፍታቴ ከመቼ ወዲህ በጠደፍ-ጠደፍ ቃሉን ማቅረብ ሆነ? ታሪካዊ ዳራ ከተናቀ፤ እነ አርጤምስ አይነሱ ከተባለ ... ይህ በምን ይፈታል ይዳፈናል እንጂ! ሴቶች ፓስተር አይሆኑም አያስተምሩም ከሚሉቱ አንዳንዶቹ ጥሩ የቃሉ አዋቆች ሆነው ሳለ፤ ታሪካዊ ዳራ አሰፈላጊነት ብዙ ጊዜም ሲያስተምሩ እየታዩ፤ ያው ባጠቃላይ 1 ጢሞ 2 ላይ ሲደርሱ... የሚገዳደራቸው ነገር አለ፡፡ የሚቀበሉት ቤተክርስቲያን ባህል ቅድመ-እሳቤ ሳይጫናቸው አልቀረም። ቃሉን እዚህ ክፍል ላይ እንዲያው እንደነገሩ መነካካታቸው ቢደንቀኝም፤ ዐውዱን አክብረው ስለአርጤምስ የሚያብራሩትን መወራረፋቸው እና በእነሱ ላይ መሳለቃቸን ግን ደግ አይደለም እላለሁ፡፡ ስለሴቶች አገልግሎት የቤተክርስቲያን ወግ እና ሥርዐትንም ልዩ ልዩ እንደሆነ ለሰሚዎቻቸው በጥቂቱም ቢሆን ያለማስረዳትም ተገቢም አልነበረም። . 1 ጢሞ 2 በቁ 15 ላይ ሴት "በመውለድ ትድናለች" ይላልምኮ፡፡ ሴት "በመውለድ ትድናለች" ይላል፤ ይህም ያኔ እውነትኛ እና አስፈላጊ ምክር ነበረ! ግን አንዳንድ መምህራኖቻችን ለክፍሉ ቀድሞውኑ የታሪካዊ ሐይማኖታዊ ባህላዊ ማህበራዊ ዳራዎች አስፈላጊነት ትኩረት ሰለነሱት... ይህን በምን ያስረዱት ታዲያ! ጳውሎስ ይህን የሚለው የዚያን ጊዜ ችግር መፍትሔ ነው ብለው ካላሉ "መዳን በኢየሱስ ነው" የሚለው ለ"መውለድ" መሰጠታቸው ነው፤ መዳን ደግሞ ‹ለመውለድ› እንዲሰጥ ስለማይፈልጉ ነው ለኮፍ ለኮፍ አድርገው ማለፋቸው፤ ይመስለኛል፡፡ ያ በ"መውለድ መዳን"ስ መልዕክት ለሁሉም ሴትና ለዘላለሙ እውነት እንዴት ይሆናል? ለደጋጉም ሆነ በሐሰት ትምህርት ለከነፉ፣ ቤት ለቤት እየዞሩም ለሚያውኩ፣ ነፍስ አጥፊ መንፈስ ለያዛቸውም? ያላገቡ ሴቶችስ እንዴት ይዳኑ? አንዳንዶቹ እንዲያውም... ዛሬም ቢሆን ሴት በመውለድ ከተጣለባት ገደብ የምትድነው ልጅ ወልዳ ልጅዋ ስባኪ እና መሪ ስለሚሆንላት ክገደብዋ ያኔ ነው የምትድነው ይላሉ፤ ይህን "substitutionary multiplier" / "generational rectification ይሉታል እነሱ። ሴትዋ የቤተክርስቲያን "አገልጋይ እና መሪ" የምትሆነው በልጆችዋ ነው የሚል የምር አቋም አላቸው፡- "While a woman may have led the human race into sin, women have the privilege of leading many out of sin to godliness. ... Her primary ministry is that of childbearing and the rearing of children who will become godly adults and leaders.” / "አንዲት ሴት የሰውን ዘር ወደ ኃጢአት መርታ ሊሆን ቢችልም፣ ሴቶች ግን ብዙዎችን ከኃጢአት አውጥተው ወደ እግዚአብሔር አምልኮ (ቅድስና) ለመምራት ታላቅ ዕድል አላቸው። ... ዋነኛ አገልግሎቷም ልጆችን መውለድ እንዲሁም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ጎልማሶችና መሪዎች እንዲሆኑ አድርጎ ማሳደግ ነው።" ይህን ያለው ላንዳንድ ወዳጆቻቸን ተወዳጃችው የሆነ ሰባኪና ፓስተር ማክአርተር በጢሞቴዎስ 2 ማብራሪያ መጽሐፍ ቅዱሱ ላይ ነው ይህን ያለው የሚለውን ስታነቡ ... ያው በጸጋ መዳን ጠፍቶት አይደል መቼሰ። በሱ ባፕቲስት ቤተከርስቲያን ውስጥ ያሉ ሴቶች ለተጣለባችው የአገልግሎት ገደብ ማስታገሻ እንዲሆንላቸው... መርፌ መውጋቱ ነው መሰለኝ፡፡ እኛም ሀገር ሴትን በጉባኤ ለመለጎም ያለው ፍለጎት ዬት ድረስ ይሄድ ይሆን እላለሁ፡፡ ወገን፦ ሴትን ሲመክሩ ውለዱ ልጅ አሳድጉ ወንድ ልጃችሁ ሰባኪ ሲሆን በዚያ ነው የናንተ የመሪነት አገልግሎት የሚል አቋም ያላቸውም አሉኮ፤ ሲያመሰጥሩም "Her position is to rear her family in the fear and admonition of the Lord. If she and her husband continue in the faith, she may one day have sons to preach and teach the Word." / "የእሷ ድርሻ (ኃላፊነት) ቤተሰቧን በጌታ ምክርና በተግሣጽ ማሳደግ ነው። እሷና ባሏ በእምነት ከጸኑ፣ አንድ ቀን የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰብኩና የሚያስተምሩ ወንዶች ልጆችን ልታፈራ (ልትወልድ) ትችላለች።" ያው የቤተክርስቲያን ባህል አይነቱ ብዙ ነው እንደምታውቁት፤ እነዚህም... ስለሴት አስተምህሮ ከሆነ አንድ ነጥብ ተነስተው አስፍተው ነው... ወዲህ የደረሱት፡፡ እንዲያውም፥ በምድራችንም ይህ ትምህርት በተለያዬ መንገድ ሲተገበር የነበረ ስለሆነ ብዙም የማይደንቃቸውና "ታዲያስ ልክ አይደለም ወይ?" የሚሉ ቢኖሩም... ሰዎቹ ይህ ባህል እንዴት እንደተመቻቸው ለማሰብ እንኳ ገና አልተቻለኝም፡፡ ስለ ሴቶች የአደባባይ አገልግሎት የየፔንተኮስታሎቹ/የካሪዝማቲኮች እና ነጻ አብያተክርስቲያናት መንገድ ግልጽ ቢሆንም፤ ያንን የሚያበረታቱ ከተለያዬ ባህል ውስጥ ያሉ ጎምቱ የነገረ መለኮት አዋቆች የሚስማሙበት ነው (ሰለ እነ ክሬግ ኪነር፡ ጆን ስቶት ዳግላስ ሙ... ተመሳሳይ አመለከከት ቀጣይ ቁ ላይ በተጠቀሱ ተያያዥ ዋቢ ጽሁፎች ላይ ታገኛላችሁ)፡፡ ይህም፦ 1 ጢሞቴዎስ መዕ 2 በጥሩ ነገረመለኮታዊ ትንታኔ ሲኬድበት... ታሪካዊ ዳራውም ትኩረት ሲሰጥ... ሴቷ ማንና ምን እንደሆንች ይገባናል፤ ክፉ የሐሰት ትምህርት አመንጪ፤ አጋንንትን ከድማጭ፣ ያገባች ነገር ግን ባል ምክር የማይመከርበት፣ የገዢነት መንፈስ ያላት፤ ባል እያለ 'የሌለ' የሚመስል መንገድ የሚትኖር፡ ቆፍጥናም ወንዱን ወዳፈለጋት ነጂ ነች፤ ባል ቢኖርም ምክረ ቃሉ የማይፈለግበት ሆኖ የሚኖርበት ቤት (እንደ የዘፍጥረቷ ሔዋን እና አዳም ኑሮ ነው የታዬው)፤ እናም ያ 'በመውለድ መዳን' ምክሩ ያኔ ልክ ነበረ፡፡ ባሏን መስማት ነበረባት። መስከን ማረፍ፤ ጋብ ማለት ነበረባት፡፤ መውለድ ደግሞ በራሱ ብዙ ገደብ ጣይ መሆኑን ሚስት እናቶቻችሁን ጠይቁ፡፡ ታዲያ በዚያች ቤተክርስቲያን የታየውን የፍጥረት ተቃራኒ የሆነ የሴቷ ልቅ መልክ እና ምልልስ በቁጥር ካስገባን ነው... ይህ ክፍል ግልጽ የሚሆንልን፡፡ በኤፊሶን ሴቶች መመከር ነበረባቸው፤ ለባሏ "ትገዛ" የተባለችውም አግብተው ሰለነበረ ነው፡፡ ይህም ምክር መጽሐፍ ቀዱሳዊ መሠረት ባለው ሁኔታ ቀረበልን፡፡ አዳም እና ሔዋን፡፡ መጀመሪያ የተፈጠረው አዳም ሆኖ ሳለ፤ ነገር ቢገባት እንኳ ለአዳም ከአምላክ የተሰጠውን ምክር መጠየቅ ሲገባት፤ ከዲያብሎስ ጋር አውርታ ሳተች፡፡ የራሷን ደረሰች፤ የአዲስ ሃሳብ ደራሲ author ሆነች (የግሪኩን ስርወቃል ማብራሪያ ተመልከት)፡፡ የራስ መንገድ ነው፤ መለኮታዊ ምክር የሌለበት፡፡ ለወንዱ የተሰጠ የአምላክ ምክር በሷ ዘንድ ሥፍራ ያልነበረው፡፡ ሔዋንም ሆነች የኤፌሶኗ ሴት/ሴቶች፡ ትውልድ ገዳይ ሳይሆን አሳቢ መሆን ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ ተገደበች፡፡ ሰለ ብዙ ሌሎች ውድ የጌታ አገልጋይ ሴቶች (ስለ እነ ፌቤን፡ ጵርስቅላ፡ ማርያ፡ ዩሊያን: ፕሮፍምና ጢሮምፍሳ፡ ጠርሲዳ፡ ዩሊያ... ጳውሎስ ያንን አይልም፤ ማለትም አይችልም! የሚለው አብረውኝ ለጌታ "የሚሰሩ... የሚደክሙ" "እናት" ሰለሆኑት ሴቶች ነው የሚናገረው (ሮሜ 16፡1፣ 3፤ 6፤ 7፤ 12፤ 13፡ 15 )፡፡ እናም፤ ማንም አዲስ የቃሉ አንባቢ ሰው የተገሰጹትን የኤፌሶን ሴትን/ሴቶችን ቢያይ፤ ደግሞም ታሪካዊ ዳራ ግልጽ ቢሆንለት እና ቢማር ከዚያም 1ጢሞ ምዕ 2ን ቢያነብ...

Open in Telegram
Views1,130−19%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#1810Text

ልብ በሉ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ቦታ ስለሥልጣን ይናገራል፡፡ ሰለ የህዝብ አለቆች ሥልጣን፤ ስለ ነቢያት ሰለ ኢየሱስ፤ ስለሐዋርያቱ፤ ስለ ሽማግሌዎች ስለ ኤጲስቆጶሳት "ሥልጣን" እና ሹመት ይናገራል፤ ጳውሎስም ለማስተማር እንደተሾመ ደጋግሞ ይናገራል። ሴቷ ዲቦራ በህዝቡ ላይ ሥልጣን የነበራት ሰፋኒት judge ነበረች፡፡ ብሉዩም አዲሱም ሰለሥልጣን እና ሹመት ይናገራል፡፡ በቃሉ ውስጥ ከመቶ ቦታ በላይ ተጠቅሷል። በ1 ጢሞ 2 ስለ ሴት "መሰልጠን"/ አዩቴንቴዎ የሚናገረው ለመጽሐፍ ቅዲስ የተነገረው ብቸኛ ቃል ነው። አዲስ ኪዳን ውስጥ የለም፤ ብሉይ ኪዳንም ውስጥ የለም! 66ቱ ውስጥ የለም! ይህ የግሪክ ቃል "ያው እንደ ሽማግሌዎች እንደ ሐዋርያት እንደ አስተማሪ ስልጣን አይኑራት"፤ ... ፓስተርም ሥልጣን አለውና "ፓስተር አትሆንም" ማለት ነው የሚለው ልክ አይደለም፡፡ ቃሉ "ያው" ሳይሆን “ለዬት ያለ ነው” መባል ያለበት፤ በእውነት ለቃሉ ታማኝ ከሆንን። 1ጢሞ 2 ላይ ያለው መሰልጠን ልዩ፤ በሌላ መጻህፍት እንኳ ቢፈለግ ተጠቅሶ የሚገኘው ክአዲስ ኪዳን በፊት ባለ በ intertestamental period ከተጻፈው Wisdom of Solomon 12:6 ላይ ያለ ነው (ከግዕዙ ጥበበ ሰለሞን ጋር ለማስተያዬት ጊዜም ፍላጎቱም የለኝም፤ የምትችሉ ግን እርዱን)፡፡ አገባቡም ፍጹም የበላይነትና የጭከና አገዛዝ ነው፤ ሊተረጎምም የሚገባው በዚህ መነጽር ነው (አንዳንድ የአዲስ ኪዳን ሀሳቦች የሚፈቱት በብሉይ ኪዳን ብቻ ሳይሆን በኪዳናቱ መሐል በተጻፉ መጻሕፍትም ነው የምንለው ለዚህም ነው)። ጥቅሱ የሴትዋ በጌታ እና በቤተክርስቲያን ሥልጣን ስር ስለማገልገል የሚናገር አይደለም። ቃሉ በራስ ሃይል የመሰልጠን የdomineer መንፈስ ነው! ያ ነው ፍቺው፡፡ ከባድ አገዛዝ ነው፤ ያ ነው በዚያች የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ሴት (ሴቶች) ላይ የታየው፡፡ ይህ መሰልጠን ይለያል፤ ያው የሚባል አይደለም! በዚህ ጥቅስ እና በቆሮንቶሱ የክልክላ ጠቅስ ላይ ተሞርኩዞ ኤግስት አንድ የማስተርስ ቴሲስ እንደተሰራ አውቃለሁ፡ ዶ/ር አለም ባዘዝ የተባሉ ከሙሉ ወንጌል የመጀመሪያዎቹ አማኞች ውስጥ አንዱ ሰው ናቸው ያን ጥናት ያጠኑት፡፡ (እዚህ የቴሲሱን ርዕስ በጸፍኩ፤ አንዱ አንባቢ ላይብረሪ አግኝቶት በኮሜንት ላይ ያጋራን ይሆናል)፡፡ ያ ጥቅስ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ሌላ ጥናት ታች ዋቢ አድርጌ አስቀምጨአለሁ፤ ይህ ቃል እኮ ለዬት ያለና ብቸና ነው፤ 'its to assume full control' "act in a self-assertive and forceful manner rather than neutrally exercising official leadership/ "ይህም እንደማነኛውም መሪነት ሥልጣን መለማመድ ሳይሆን፣ ፍጹም ሥልጣንን በመጠቅለል፣ አምባገነንነትና በሃይል መጋፋትን ያሳያል" ነው፡፡ ይህ ለሴትዋ የተነገረውን እንደሌላው ዐይነት "ሥልጣን" ማዬት... የቃሉን ዋና መልዕክት ማሳነስ ነው! ያ እኮ ለእግዚአብሔር መታዘዝ የሌለበት (እንደ ሔዋን የራስ መንገድ ፣ ውድቀት ጥፋት ያለበት፣ ለባል እና ለጌታ መገዛት የሌለበት 'እውነት የሚመስልን ውሸት ፈጣሪነት') ነው። ለዚያ ነው ሔዋን የተጠቀሰችው፡፡ ለሆነው ነገር ብቸኛ ገላጭ ያ የዘፍጥረት ከክፍል ነው፡፡ ልክ የሔዋን መንገድ ነው ኤፌሶን ቤተክርስቲያን ውስጥ የታየው፤ የተገሰጸው። ስለዚህ ይህ መሰልጠን "according to earlier usage, one who with his own hand kills either others or himself. [...] in later Greek writings one who does a thing himself the author [....] one who acts on his own authority, autocratic, equivalent to [...] an absolute master; [...] to govern one, exercise dominion over one"/ ይህ ወደ አማርኛ እንዲው ለመመለስ ከተሞከረ፡- "ልትሰለጥን" (αὐθεντέω / authenteō የሚለው ቃል "በቀደመው የቃሉ አጠቃቀም መሠረት ከሆነ፣ በገዛ እጅ ሌሎችን ወይም ራስን መግደል ሰው። [...] በኋለኞቹ የግሪክ ጽሑፎች ደግሞ አንድን ነገር ክራስ የሚያመነጭ፣ ፈጠራ ደራሲነት [....] በራስ ሥልጣን ብቻ መንቀሳቀስ፣ ‘አምባገነንነት’፣ [...] ከ‘ፍጹማዊ ጌታ’ ጋር እኩል፤ [...] በራስ ስልጣን የሚያደርግ፣ በሰው ላይ ፍጹም የበላይነትን ማሳየት።" ቃሉ በየዘመናቱ እያደገ የተለያዬ ትርጉም ቢያገኝም፤ እኛ መተርጎም ያለብን በ1ኛ ክ/ዘ እና ቀደም ባሉት አመታት ትርጉሙ ነው፡፡ "The Greek Septuagint, the Greek translation of the OT, written 100-300 years before Paul, includes Wisdom of Solomon 12:6 where authentas is used for the murderous parents sacrificing their children in a context of idolatry and witchcraft that parallels the pagan cults in Ephesus."/ "ከጳውሎስ ከ100 እስከ 300 ዓመታት በፊት የተጻፈውና የብሉይ ኪዳን የግሪክ ትርጉም የሆነው ‘ሰብአ ሊቃናት’ (ሴፕቱአጄንት) [መጽሐፍ ቅዱስ] ውስጥ ያለው ጥበበ ሰሎሞን 12፡6 ላይ ነው ‘አውቴንተስ’ (authentas) የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው፣ በኤፌሶን ከነበሩት ጣዖት አምላኪዎች ጋር በሚመሳሰል የጣዖት እና የሟርት አውድ ውስጥ፣ ልጆቻቸውን መሥዋዕት ለሚያደርጉ ነፍሰ ገዳይ ወላጆች ለመግለጽ ነው።" ይህ ደግሞ የከባድ ድርጊቶች ገላጭ ቃል ነው፡፡ ጳወሎስ እንደ ብርቱ አንባቢነቱ ያንን ልዩ ቃል ቢያውቅ ነው ወደዚህ ያመጣው፡፡ ይህ ቃል ሌላውንም ራስንም (በራስ) ማጥፋትን የሚገልጽ ነው፡፡ ልክ እንደሔዋን አጋንንትን ማድመጥ ነው፡፡ እርስዋ ወንዱ ላይ ሰልጥና ምን እንዳስተማረች እናውቃለን፡፡ በጥንቃቄ ስናዛምደውም፦ እንዲያ አይነት ገዥነት እና ጥፋት ከታዬ (በጉባኤያቸው ውስጥ ሊኖሩ ከቻሉ፤ ዛሬም አሉና)፤ ለተመሣሣይ ባህሪይ እና ዝንባሌ ላላት ሴት ልክ የሆነ ተግሳጽ ነው። ያ ነው ልክ፤ ለሁሉም ቅዱሳን ሴቶች የእግዚአብሔር አጀንዳ ደግሞ ብዙ ሴቶች በወንዱም በሴቱም ጉባኤ ላይ በተሰጣቸው ጸጋ ተሾመው እንዳገለገሉት ነው፡፡ መሪዎችም ምናልባት እንዲህ አይነት ሴቶች ካዩ ወደ ጎን ወስደው ይምከሩ ሥርዐት ያስይዙ እንጂ ለሁሉም ቅዱሳን ሴቶች ላይ አጠቃላይ ገደብ ጣይ አድርገው ቃሉን ባያቀርቡ ጥሩ ነው፡፡ ስለሆነም በጌታ ስልጣንና ሀይል በታች፤ ከጌታ በተሰጡ መሪዎች በምትመራ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚያገለግሉ እረኛ/ፓስተር እና አስተማሪ ... ሴቶች የአገልግሎት ክልከላ መናገሩ ነው ቢሉ... መታመን እንዴት ይሆናል? ቁ12 እየተነበበ እረኛ / ኤጵስቆጶስ / ሽማግሌ የሚለውስ ሃሳብ ከዬት መጣ? ሴት እንዳታስተምር ተከለከለች ከተባለ "ምን ቢያስተምሩ ነው?" አይባልም? የሔዋን አይነት ከቃሉ ትዕዛዝ የወጣ መከራን ፍዳን ያመጣ ትምህርት አስተምረው ከሆነ የሚገልጣቸው ዘፍጥረት ላይ ያለው የሔዋን የአርጤምስን ሴት ካህናት የመሰለ፡ ከፍጥረት ግልብጥ የሆነ ሐይማኖት ስርዐት የውሸት እምነት ፈጣሪነት ስለታየባቸው ነውና፡፡ ዛሬም ያ ከታዬ ነው ቃሉ ማዛምድ፤ በኤፌሶን ቤተክርስቲያን የታየውን ነው ጳውሎስ ያስተካከለውና። በታሪካዊ ዳራ ብቻ ሊፈታ የሚችልን ጉዳይ ...

Open in Telegram
Views1,220−12%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#1809Text

ስብከትም አመራርም ትምህርትም በተግባር አልከለከሉምኮ፡፡ ነገሩ duplicity እንዳይሆን መጠንቀቀ ተገቢ ነው፤ ብልጠት ጥበብን እንዳይከዳ፡፡ ፍርሐቴ፦ ይህቺን ደግሞ አንብበው በዘማሪዎችችን እና ጸሎት መሪዎች ላይ ማዕቀብ እንዳይጥሉ ነው፤ መከልከሉ ወደ እነዚህም አገልግሎት እንዳይሄድ እንጸልያለን፡፡ "በአለም አልተደረገም እኛ ጋር እንዴት ይሆናል?" አንልምና፤ በኋላ ላይ ላሳይ እንደምሞክረውም ይህ አይሆንም ብሎ ማለት ተላላነት ነው፤ እንደ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2ቱ ሌላው መከራ ያየውን ጥቅስ (1 ቆሮ14፡34) እየጠቀሱ ሴቶች በዋና ጉባኤያቸው በፍጹም የማያሳትፉ አንዳንድ አሉ ተብለናልና፤ እንደሚያምኑትም "women should not speak, pray audibly, or sing out loud during specific formal worship meetings" / "ሴቶች በተለዩ መደበኛ የአምልኮ ስብሰባዎች ወቅት መናገር፣ ድምፅ አውጥተው መጸለይ ወይም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው መዘመር የለባቸውም" የሚሉ አሉኮ! እንዳልኩት፥ ሁሉም የኔ የሚለውን የቤተክርስቲያናን ወግ እንደየወገኑ መከተሉ ጥሩ ነበረ፣ ግን ደግሞ ነገሩ ተነስቷልና አንዳንድ ወሳኝ ጉዳዮች በአመክንዮ ብቻ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችን ማጥራትም አለብን። ይህ ደግሞ በቅድሚያ ለፔንቴኮስታሎች ካሪዝማዊያን እና "ነጻ" አብያተክርስቲያናትን ይጠቅማል ባይ ነኝ (የማቀርበው በባፕቲስት እና ሪፎርምድ ባህል ውስጥ ያሉትን ብዙዎችን የሚጠቅም ባይሆንም 'አንዳንድ' የሴቶችን የፓስተርነት አገልግሎት የሚቀቀበሉትንም ይረዳ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ያልኩትም፡ አንዳንዶቹ የሴትን ማስተማር እና በአመራር ማገልገል ስለሚቀበሉ ነው (ለምሳሌ Saddleback Church: የ 'አላማ-መር ህይወት' መጽሐፍ ጸሃፊ Rick Warren በፓስተርነት የሚያገለግልባት ቤተክርስቲያን ከ3 ዓመታት በፊት ከዋናው 'ማህበር' ከSouthern Baptist Convention የተወገደችው የሴቶችን በፓስተርነት በአመራርና ማስተማር አገልግሎት ሰለተቀበለች ነው)፡፡ ሴት ፓስተር አትሆንም የሚል አቋም እንደ አንድ የቤተክርስቲያን ባህል የማየው ቢሆን፤ የቃሉን እውነት እንጠብቃለን ደግሞም ቃሉን በጥንቃቄ በዐውድ መፍታት አለብን የሚሉ ተወዳጆቻችን 1ጢሞቴዎስ በመሳሰሉ ክፍሎች ላይ ይህ አቋማቸው በትንሹም ቢሆን ሲከዳቸው በማዬቴ መገረሜን ማዘኔንም አልደብቅም። ቃሉን ሊፈቱ የወደዱ ወዳጆቻችን፦ አንዱ ችግራቸው፥ 1 ጢሞቴዎስ ምዕራፍ 2ን በምዕራፍ 3 መነጽር መፍታታቸው ነው፡፡ 'እንዲያስተምሩ የታዘዙ ኤጲስቆጶሳት ናቸው (3፡2)... ሴት ደግሞ በምዕ 2፡12 ላይ ማስተማር ስለተከከለች... ሴት ፓስተር እንድትሆን ተከለክሏል' ይላሉ፡፡ ኤጲስቆጶስ ክሽማግሌነት ሆነ ከፓስተርነት ጋር አንድ እንደሆነ ቀድሞውኑ በአዕምሮአቸው ውስጥ ወስነዋል ማለት ነው፡፡ ሴት በጉባኤ እንዳታስተምር የተከለከለችው "በክፍሉ እንደ የተጠቀሱት ኤጲስቆጶስ (እንዲያስተምሩ የታዘዙቱ) አይነት ጸጋ ስለማይኖራት ነው".... ያሉበት አግባብ ልክ አይደለም፡፡ ምክንያቱስ? ፓስተርነት/እረኝነት በ1 ጢሞ (በቲቶም ጭምር!) ውስጥ ምንም አልተጠቀሰም። የሌለውንና ያልተጠቀሰውን አምጥተው ለመድፈቅና ለማስወገድ መፈለጋችው ነው ችግራቸው፣ በምንም መልኩም ቢሆን ያልተገለጸውን የእረኛ ጸጋ ስጦታ (በኤፌ 4:11 ላይ የተጠቀሰው እረኞች/ ποιμένας / poimenas / ፖይመናስ፤ singular form: እረኛ ποιμήν / poimēn) ልክ በ1ኛ ጢሞቴዎስ ውስጥ ያገኙት አስመስለው እያነሱ-መጣላቸው ነው ችግሩ። ያ ነው የንባባቸው መጀመሪያ ድካም። እውነታው፦ ፖይመን / ፖይመናስ የሚለው ቃሉም ሆነ የቃሉ ዝርያ በ1ኛ እና 2ኛ ለጢሞቴዎስም ሆነ ለቲቶ በተላኩ መልዕክታት ውስጥ ጭራሽ የለም! እናም፥ ሰዎቹ በክፍሉ ውስጥ የሌለን የፓስተር/እረኛ አገልግሎት በሀሳብ ፈጥሮ መደብደብ ነው ስህተታቸው። የሌለ ጣምራ ፈጥሮ (እረኛን ከኤጲስቆጶስ ጋር አዋስቦ) አጋብቶ ያልተገባ ድምዳሜ ላይ መድረስ ነው ችግሩ እያልኩ ነው። ምክንያቱም ኤጲስቆጶስ እና ሽማግሌ በራሱ እረኛ/ፓስተር አይደለምና! ይህን በሚቀጥለው ሁለተኛ ክፍል ልጥፌ ላይ አሳያለሁ፡፡ ልብ በሉ፡ ሽማግሌዎች እና ኤጲስቆጶሳት/ጳጳሳት የእረኝነት ሥራን ቢሰሩም (ሐዋ 20)፤ ይህ እኮ... ጴጥሮስ ሐዋርያ ሆኖ ሳለ በጎቹን እንዲጠብቅ በጌታ እንደታዘዘው ያለ አይነት እረኝነት ነው (ዮሐ 21፡16)፤ በሁለቱም ስፍራዎች የግሪኩ የቃሉ የግስ አገባብ የእረኝነትን ሃላፊነት መውጣት ποιμαίνειν / poimainein ነው፡፡ ሐዋርያ ደግሞ እረኛ አይደለም (ኤፌ 4፡11)፡፡ ድሮም ዛሬም እንደምናውቀው ከሆነ ደግሞ፡ ሐዋርያ የእረኛነት ተግባር ይወጣል እንጂ እረኛ/ፓስተር አይደለም፡፡ ለኤጲስቆጶስም ሆነ ለሽማግሌ ይህ እውነት ነው፡፤ እረኛነትን ሥራ ይሰራሉ እንጂ እረኛ/ፓስተር አይደሉም፡ . በ1ጢሞ 2፡12 ላይ ጳውሎስ ሴት "ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም" ሲል፣ "አልፈቅድም" የሚለው ቃል በዘለዓለማዊ መልኩ የተሰጠ ትዕዛዝ ስለሆነ "እኛም ዛሬ ልንታዘዝ ይገባል" ለማለት ሲደፍሩ፣ ሁሉን እውነት እያስተማሩ እንዳልሆነ ልባቸው ሳያውቀው ቀርቶ ነው? እላለሁ። ወይስ ለተነሱለት አቋም ታማኝነታቸው ተገቢ ትኩረትን ነስቷቸው? በተለይ ቲዎሎጂ በሚገባ ተማርን ለሚሉ ነው ጥያቄዬ፡፡ ሌላው ቢናገር ወሬው 'እዳው ገብስ ነው'፡ አይጎዳም፡፡ ወይም፡ እውነትም ቃሉን በሚገባ ባያዩት ነው? እላለሁ፡፡ ምክንያቱም፥ "አልፈቅድም" (በግሪኩ፦ ἐπιτρέπω / ኤፒትረፖው epitrpwo) በግልጽ በ present active indicative ያለ ያሁን ጊዜ ገላጭ በመሆኑ... በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሁሌም (ሁሌም!) ለዘለዓለማዊ እውነት ማጽኛነት የሚውል ትዕዛዝ የሚቀርብ ሳይሆን.... በዚህ ጥቅስ ላይ ይልቁኑ እዚያ ኤፌሶን ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረ ችግርን ለማስቆም የተሰጠ የቃሉ "የአሁን" ትዕዛዝ ነውና! "ችግሩ ምን ነበረ? ብሎ ይጠየቃል፡፡ የኤፌሶን ሴቶችን/ሴቷን ችግሩ ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች ማሳየት እንደሞከርኩት... ጉዳዩ የዚያን ጊዜ ችግር ነው... የጳዉሎስ መፍትሔም እንደዚያው ለዚያ ዘመን ነው እያልኩ ነው፡፡ የ"መልዕክታት" ትርጓሜ እና ቃሉን የማዛመድ ዘይቤ ደግሞ... ያንኑ የኤፌሶን ቤተክርስቲያን ችግር የሚመስል ተግዳሮት ዛሬ በመካከላችን ሲታይ ብቻ ነው ማዛመድ የሚገባ ባይ ነኝ፡፡ ያንን የሚመስል ችግር ደግሞ በየዘመናቱ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሊታይ ይችላል፡ ያኔ ምክሩ ይሰራል፡፡ ግልጹ እውነት ግን ይህ ነው፤ οὐκ ἐπιτρέπω ን.... "እኔ መቼም መች አልፈቅድም" እንደሚል አይነት አድርጎ ማስተማር ተገቢ አይደለም አይደለም የሚል ነው፤ ያን ደግሞ በተለይ ከአንዳንድ ተወዳጅ ወንድሞቼ አልጠብቅም ነበረ። . "ሴት በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም" ማለቱ "ያው ሥልጣን አይኑራት ማለቱ ነው፣ ምንም ሌላ ትርጉም የለውም" የሚለውም ታማኝ አይደለም። ልክም አይደለም! "ልትሰለጥን" (αὐθεντέω / authenteō/ አዩቴንትዎ) ያው የተለመደ 'ሥልጣን' አይነት ሆኖ....ለሴት ያልተፈቀደ "ሥልጣን" የሚባልለት አይነት አይደለም፡፡

Open in Telegram
Views1,120−19%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1808Text

ሴት ፓስተር አትሆንም? . (ክፍል 1) ከሰሞነኛ አጠቃላይ ርዕስ አንዱ ስለሴቶች ነበረ። በፕሮቴስታንቶች ዘንድም "ሴቶች ፓስተር እንዲሆኑ አልተፈቀደም" የሚሉ በርክት እያሉ ነው፤ አገልግሎቱ በብቻነት exclusively የወንዶች ነው የሚል አስተምህሮ መነሻው "ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትለጥን አልፈቅድም" (1ጢሞ 2:12) በሚለው ትዕዛዝ ላይ ተመርኩዞ የተሰጠ ትንታኔ ነው። እንደሚሉት፡- ሴት ሌሎች አገልግሎቶች አሏት፤ ብታስተምር ደግሞ በሰንበት ትምህርት ልጆችን ታስተምር፡፡ ለዚህ ድምዳሜ ትንተና መንገዱ እድሜ ጠገብ ቢሆንም፣ ለመከራከሪያው ብዙ በመጽሐፍ የተጻፈ እና በብዙ ድረገጾች እና ዩቲዩብ ቪዲዮዎች ላይ ያለ ቢሆንም (ለእኛም ሀገር ፍጆታ ቃል በቃል በአማርኛ ተተርጉሞ በውይይትም በስብከትም በጽሁፍም ተደጋግሞ የቀረበልን ቢሆንም)፣ የዚህ አመለካከት ባደባባይ አቅራቢዎች እንድሚያስቡት... ሁሉም ሰው ሀሳቡን በቀላሉ የሚገዛላቸው አይደለም፤ አይገባምም፡፡ ሴቶች ፓስተር እንዲሆኑ አልተፈቀደም የሚለው ሀሳብ "በቂ ባልሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንተና" ላይ የተመሰረተ መሆኑ ቀድሞውኑ በሚገባ የተሞገተ ነውና፤ እኔም አሁንም ያንን መስመር እክተላለሁ፡፡ አውቃለሁ ትምህርታቸውን የሚያጸኑ አብያተክርስቲያናት አሉ፤ ትምህርቱም በውጪዎቹም ሆነ በእኛም መሐል ሲሰማ የነበረ ነው፤ የኛዎች አንዳንዶቹን ያው "ቴዎሎጂ ስለማያውቁ አውዱን ስተዋል" ተብለው በትእግሥት የተያዙ ነበሩ፤ ቅንንቱም ጌታን መውደዱም ስላለ ሲያውቁና ሲረዱ ደግሞ አቋማቸውን ይቀይራሉና (ወደ ጌታ እንደሄዱት እንደ ፓ/ር ግርማ ያሉ፤ በተቃውሞ ቆይተውም ቢሆን አንድ ወቅት ፓስተር ሆንው በተላኩባት የአየርጤና በሙሉወንጌል አጥቢያ ላይ ሴት ሰባኪ በጉባኤ እንድትሰብክ እንደጋብዙት፤ ሴት አገልጋይ እንደ'ባረኩት፤ እኔም የዐይን እማኝ እንደሆንኩት)፡፡ የአሁኑ "ሴት አታገለግልም፤ ፓስተር አስተማሪ አትሆንም" የሚለው ዘመቻ ግን ጨዋዎቹንም ሆነ አውቀናል የሚሉ ተወዳጅ የቲዎሎጂ ተማሪዎቻችንም ያካተተ ነውና በሚገባ ማብራራት ተገቢ ሆኗል፡፡ ሴት "ፓስተር አትሆንም" የሚለውን ጳውሎስም ራሱ ያላስተማረው ከሆነስ? ይህም ሊብራራ ይገባል፡፡ "ሴት ፓስተር አትሆንም" የሚለው አቋም የአንዳንድ አብያተክርስቲያናት “ሥርዓትና ወግ” ከሆነስ? ይህም መታዬት አለበት፡፡ ያ ከሆነ ደግሞ ትምህርቱ ለባህሉ ተከታዮች እንጂ ሌላው ላይ የሚጫን መሆን የለበትም እላለሁ፡፡ እናም እነሱ ጉዳዩን ደጋግመው ካነሳሱት አይቀር፥ በአመክንዮም በቃሉም ማጠየቁንና ውይይቱን ሰፋ ማድረጉ ተገቢ ነው። ሁሉም የየራሱን የቤተክርስቲያን ባህልና ወግ ተከትሎ ወንዶችን ሴቶችን በሚገባቸው የአገልግሎት ሥፍራ ማሰማራት ተገቢ ነው እላለሁ። ያንን አምናለሁ፤ ትክክልም ነው እላለሁ። ይህን የምለው በ complementarian (ተደጋጋፊነት) እና egalitarian (እኩልነት) አቋሞች መሀል ያለው የአመለካከት ውጥረት ጠፍቶኝና ነገሩን አቅልዬ አይደለም። ይልቁኑ ያን የማይታረቅ ውጥረት መኖሩን በመረዳት ነው የአቋም ምርጫውን ለየባለቤቶቹ መተው ጥሩ ነው ማለትን የወደድኩት (እንደምታውቁት complementarianism የሴት እና ወንድ ከአንድነታቸው በላይ በተግባር እና በሥራ functionally ልዩ ልዩ መሆናቸውን ማጽናት፣ እና egalitarianism ደግሞ ሁለቱ የተለያዩ መሆናቸውን ቢረዱም በፍጹም እኩልነት ሁሉም አገልግሎት እኩል ተሳተፎ ላይ ትኩረት የሚሰጡ ናቸው)። ይህ የቆዬ የአመለካከት ባህል ልዩነት ነው። የመጀመሪያው አቋም ጎራ ያሉ ሰዎች ሽማግሌነትን አስተማሪነትን ጨምሮ (አሁን የማነሳውን) የፓስተርነት አገልግሎትን ለሴት አይሰጡም፤ የኋለኞቹ ደግሞ "ሴት ሁሉንም ዓይነት አገልግሎት ማገልገል ትችላለች" ይላሉ። የሁለቱም አቋም እንደየራሳቸው ወግ እና ባህል ጠቃሚ ሃሳቦች ቢኖራቸውም፤ ውስጣቸው ግን አንዳንድ ጽንፍ የረገጠ ነጥቦች ካሉም መስተካከል አለበት ባይ ነኝ፤ እናም "በተሻለ ሌላ አቋም" ሊገሩ ይገባልም ብዬ አምናለሁ። ማጠየቅ ስጀምር፥ complementarian አቋም አጥባቂ የሆኑ (በተለይ አንዳንድ ሪፎርምድ እና ባፕቲስት የሆኑ አብያተክርስቲያናት) እልል! ያለች ጥበብም እንዳላቸው አያለሁ፤ ሴቶችን ፓስተር አድርገው ባይሾሙም፥ ግን በልጆች አገልግሎት ላይ ያሰማራሉ፡፡ የነሱን ተቃርኖን አስታርቆ የመቀጠል ጥበባቸውን ብወደውም፡ ሴቶችን "ወንዶች ልጆችን ማስተማር" እንደሚችሉ ሲናገሩ ወንዶች ልጆቻችን... "ወንድ" የሚሆኑትስ መቼ ነው? እላለሁ፡፡ ያው ለሴቶች 'ወጣት ሴቶችን' ለማስተማር ምክር ስላለ ነው (ቲቶ 2፡ 3-4)፡፡ ወንድን አታስተምር ተብሏል ካሉ ያንኑ 'ለወንድ' ሁሉ ማጽናት ነበርኮ፤ ግን ጥበብስ! ለምን በልጆች ጉባኤ ሴቶች እንዲያስተምሩ ፈቀዱ? እውነታው፦ የመፍቀዳቸው ዋና ምክንያቱ ሲገባን.... ነገሩ ግልጽ ይሆንልናል (ይህን በሰፊው መተንተኑ ለአሁኑ ይቅር)፣ እንዲያው ... ለአገልግሎታቸው እንዲመች የተፈጠረ የራሳቸው የቤተክርስቲያናቸው "ባህል ነው፣ ወግ ነው" የሚለውን እንያዝ። ብቻ በዘመናዊውም የቤተክርስቲያን "የጉልበት እና የሥራ አስተዳደር" ዘይቤም ከታዬ ውጤታማ ነው ባይ ነኝ። ወንዶቹ ሰዎቹ፦ ፓስተርነት እና ሽማግሌነት... እና ተያያዥ አስተዳደሩን ከያዙ በኋላ፥ ከቤተክርስቲያን ሥራ ሰፊነት አንጻር ሴቶችን በልጆች ማስተማር ላይ ሲያሰማሩ ስታዩ፤ ይልቁኑ ልጆች ከትላልቆቹ ተለይተው (ሰንበት-ትምህርት በሚል ዘይቤ ከዋናው ጉባኤ ተለይተው) parallel በተመሳሳይ ሰዐት እንዲሰበሰቡ የጀመረበትን ጊዜ ስታውቁ... እና ሴቶች እንዲያስተምሩ እንደተመደቡባቸው ስትረዱ.... አሁን የምለው ግልጽ ነው። ካለበለዚያ፥ ወንዶች ልጆችን ‘ማስተማር' አገልግሎት ለሴቶችም ባልሰጡ ነበረ (በነገራቹ ላይ፡ ከልጅነትም ቢሆን ሴት ወንድን አታስተምር የሚሉ ቆፍጠን ያሉም አንዳንድ አብያተክርስቲያናት አልጠፉም)። ግን እንደእውነቱ ከሆነ፡ የኛዎቹ እንደዚያም ሆኖ ፈልገው... ፈልገው... ለሴት የሆነች ቦታ መስጠታቸውም ጥሩ ነው። ደግሞም የማንኛውም ቤተክርስቲያን ባህልና ወግ ከዬትኛውም በልጦ እንዳልተገኘ አውቃለሁና ደግ አድርገዋል፤ ያብዛላቸው፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም፤ በቤተክርስቲያን (ጉባኤ) ፊት እንዳያስተምሩ ሴቶችን ቢከለክሉም የነገረ-መለኮት ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲያስተምሩ ይፈቅዳሉ፥ በክፍል ውስጥ ወንዶች ተማሪዎች ቢኖሩም! ጳውሎስ "ሴት ግን እንድታስተምር አልፈቅድም" ቢልም! ድንቅ ጥበብ ነው። ይህ በውጪዎቹ የተለመደ ነው፤ በእኛም ሀገርም ያየሁት የማውቀው ነው፡፡ እናም በውጭውም በሃገራችንም ሴት አታስተምር የሚሉት አንዳንዶቹ፤ ሴት ነገረ-መለኮት አስተማሪዎች ስር የተማሩም ናቸው፡፡ በኤግስት በተማሪነትም ዋና በየአመቱ "ሰቃያቹ" ብዙ ሴቶች እንደነበሩ አውቃለሁ፤ ማሰብ ማስተማሩም የተመሰከራቸው ሴቶች ዛሬ አሉ መቼስ፡፡ ሴቶች ዘማሪዎችም አሉን፤ ሰማዩን ከምድሩ ያገናኙ ባለብዙ ጸጋ በረከቶቻችን፡፡ ዘማሪዎችም በአደባባይ በጉባኤም እንጂ ከመጋረጃ ጀርባ በድምጽ ብቻ ስለማይዘምሩ፤ ዝማሬው ደግሞ ትምህርትም ማነጽም ነው፡፡ አይደለም ወይ? ፕሮግራምም ስለሚመሩ (በነገራችን ላይ ይህም ማስተማር አለው)፤ በጸሎትም ሰለሚመሩ፦ ከመሩ ደግሞ አስተማሩ! በጉባኤ ከዘመሩምኮ አስተማሩ! "ሴት ፓስተር አትሁን፣ አታስተምር" የሚሉትን ሰዎች ጉባኤያቸውን አዬት አዬት አድርጉ፡፡ ሴቶቻቸው አያደርጉትም? አመራር እና ስብከት በአዋጅ ቢከለክሉም...

Open in Telegram
Views1,270−9%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—