Account

Posts of 👼 AnyሐበሻThought 😈

newest first

#34863Text

በሰቆጣ ከተማ የተጣለው ቅጣት‼️ አማራ ክልል ዋግኸምራ ሰቆጣ ከተማ አላስፈላጊ ወጪዎችንና ጎጂ ልማዶችን ለመቀነስ አዳዲስ ክልከላዎችና ለማስቆም የተወሰኑ ውሳኔዎች። ​1. ከጋብቻ (ሰርግ) ጋር የተያያዙ ውሳኔዎች ​በእጮኝነት ጊዜ ልብስ ለማልበስ ከ5 ሰዎች በላይ ይዞ መሄድ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። ​በሰርግ ዋዜማ ለጥሎሽ/ልብስ ከ5 ሰዎች በላይ ይዞ መሄድ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። ​ከሰርግ በኋላ ለትውውቅ/ምላሽ (ቅልቅል) ከሰርግ ያልተናነሰ ድግስ መደገስ በሴቷም በወንዱም ወገን እያንዳንዳቸው 50,000 ብር፤ የባረከ ቄስ 10,000 ብር ቅጣት። ​በሰርግ ጊዜ ከ25 ሰው በላይ መዝመት ወይም ለተለያዩ ፕሮግራሞች ዩኒፎርም (ተመሳሳይ ልብስ) መልበስ ዋናው ባለጉዳይ 30,000 ብር፤ ለብሰው የሚገኙ አካላት እያንዳንዳቸው 10,000 ብር ቅጣት። ​ለሰርግ በኪራይ ወይም በግዥ የሚዘጋጅ ስቴጅ (መድረክ) እና ከልክ ያለፈ ዲኮሬሽን መጠቀም 20,000 ብር ቅጣት የማይገኝ ሀብት/ማጫ በሐሰት መናገር ማጫ በተጨባጭ ታይቶ መባል አለበት (በዳስ አባቶች ይረጋገጣል)። ​2. ከልዩ ልዩ ድግሶችና በዓላት ጋር የተያያዙ ​በሠርግ እና በክርስትና ዕለት ቡፌ እና ኬክ ማዘጋጀት 50,000 ብር ቅጣት ​የተማሪዎች ከKG ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ የምረቃ ድግስ ማዘጋጀት 30,000 ብር ቅጣት። ​የቤቢ ሻወር (Baby Shower) እና የጋብቻ ዓመታዊ በዓል (Anniversary) ማክበር 10,000 ብር ቅጣት የጽዋ ማህበራት ዩኒፎርም መልበስ እና ታይታ ያለበት ድግስ ማዘጋጀት እያንዳንዱ አባል 10,000 ብር ቅጣት። ​በማንኛውም ፕሮግራም (ክርስትና፣ ልደት፣ ምንኩስና፣ ቤት ሲሰራ ወዘተ) አረቄ ይዞ መሄድ  ፈጽሞ የተከለከለ ነው፤ ተቀብሎ ያስተናገደ ባለቤት 20,000 ብር ይቀጣል። ​3. ከሀዘንና ከፍትሃት ጋር የተያያዙ ​በፍትሃት ጊዜ ከፍተኛ ድግስ መደገስ፣ በ40 ቀን መቃብር ላይ ሻማ ማብራትና ዳቦ መቁረስ 20,000 ብር ቅጣት በሃዘን ጊዜ ውሃ ይዞ መሄድ የተከለከለ ነው (በምትኩ ገንዘብ፣ ስኳር እና ቆሎ ጋብቻ እንዲወስዱ ተገልጧል። ይሄ ውሳኔ የመንግስት ውሳኔ ሳይሆን ማህበረሰቡ ከሁሉም ሀይማኖት አባቶች እና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር በመምከር መጤ ባህሎችን መከላከል እና የማህበረሰቡን አላስፈላጊ ወጭዎች ለመከላከል የተወሰነ የስምምነት ውሳኔ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፅዋል ። በተለይ አሁን ላይ ሽምግልና፣ ቅልቅልና መልስ ከሰርግ ያልተናነሰ ወጭ እያስወጡ ማህበሰቡን እያማረሩ ያሉ ጎጂ ባህሎች ናቸው። ከመጤ ባህል ራሳችንን ለመከላከል የተደረገ በጎ አላማ ያለው የማህበረሰብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮች ገልፅዋል ። @Seledadotio @Seledadotio

Open in Telegram
Views113+13%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—