Account

Posts of Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

newest first

#51135Video

ያልተነገረ እንጂ ምን ያልተሠራ አለ⁉️ ====================== (አጋልጥ ⬅️ ክፍል  5️⃣8️⃣) (በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተገኘ ምሽግ!) || ✍️ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የጦር ስልጠና የተሰጠበት አለ፣ ምሽግ ተቆፍሮ ነበር፣ መነኩሴና ካህን ሳይቀር ከሃገር መከላከያ ሠራዊት ጋር ተዋግቷል… ስንል አንዳንዶች መረጃ አምጡ እያሉ ያገር መረጃዎችን አዝንበናል። በዚህ ፋና ባዘጋጀው ቪድዮ ላይ የደብረ ኢልያስ ገዳምን የጦር ማዘዣ ያስጎበኛናልና በጥሞና ተከታትላችሁ፤ ማን አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ፣ ተንኳሽ፣ ሲገረፍ ከሳሽ፣ አሸባሪ፣ ጽንፈኛ፣ አክራሪ፣ ባንዳ፣ የሃገር ስጋት፣ የሰላም ጠንቅ፣ ሐሳዊ ኃይማኖተኛ … እንደሆነ በግልፅ ትመሰክሩ ዘምድ ጋበዝኳችሁ። አሁንም ለተኙ ምእመናንና ምእመናት ማንቂያ ይሆን ዘንድ፤ ለሁሉም ሼር አድርጉላቸው። || t.me/MuradTadesse

Open in Telegram
Views7,800−33%vs avg
Forwards—
Reactions123
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h1,260
2 h7,800
  1. Total to date7,800
#51134Video

ግብፅ ለዘመናት ከበደለችን በደል አንዱ ይህ ነው። ለራሷ ከጁሙዓህ ውጭ ሌት ከቀን እየሠራች ወሳኝ የኢኮኖሚ አቅም ገንብታ ሳለ፤ የኛን ሃገር ዜጋ ግን ለወሩ 30 ቀን 44 ታቦት አከፋፍላ በዓል ነው ብላ ተጫውታብናለች። የሚያሳዝነው ነገር፤ ይህን በዓል ካከበሩም ራሳቸው የእምነቱ ተከታዮች ብቻ ማክበርና ከፈለጉ ሥራ መፍታት ሲገባቸው፤ ሙስሊሙም አብሯቸው በግደታ ካላከበረ «በዓል ተጥሷል፣ የጎርፍ አደጋና በረዶ ይከሰታል!…» እያሉ የሌላውን እምነት ተከታይም ማስገደዳቸው ነው። በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል በዚህና ከመለመዱ የተነሳ እንደ ባህል ተወስዶ ማስገደድ ሊቆም ይገባል። የፈለገ ሰው በፈለገው ቀን የመሥራት ነፃነት ሊሰጠው ይገባል። ዛሬ ማሪያም ናት፣ እርሻ እንዳታርስ፣ አጨዳ እንዳታጭድ… ወዘተ እየተባለ መገደድ የለበትም። ይህን በሌላው እምነት ተከታይ ላይ መጫን ኋላ ቀርነት ነው። ከፈለጉ ለራሳቸው የመቦዘን መብታቸው የተጠበቀ ነው። አምራቹ ገበሬና ሌላው ታታሪ ሠራተኛ በዚህ ባል ወይም የአንድ እምነት ዶግማነ ቀኖና መሰቃየት የለበትም። ይህን በዘዴ የሚያስፈፅሙ የመንግስት አካላትም ተጠያቂ ሊደረጉ ይገባል። ህዝብን ሥራ ብለው ማበረታታት ሲገባቸው፤ በማያምንበት እምነት ሊያስገድዱት አይገባም። || t.me/MuradTadesse

Open in Telegram
Views10,400−11%vs avg
Forwards—
Reactions255
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h2,140
2 h6,670
4 h10,400
  1. After 1 hour2,140
  2. Total to date10,400
#51133Photo

ዝግጁ⁉️ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኀ-ግብር ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር አሰላሙ ዓለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ! ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ከመጪው ጁምዓ፣ ኅዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ል. ጀምሮ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚያሳትፍ ሰፊ የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ በማኅበራዊ ሚዲያ ያካሂዳል። የዚህ ዘመቻ ዋና ዓላማ፣ ማዕከሉ ላለፉት 20 ዓመታት ሲያከናውናቸው የቆዩትን የትምህርት፣ የዳዕዋ፣ የሚዲያና የበጎ አድራጎት ሥራዎች የበለጠ ማጠናከር፣ ቀጣይነታቸውን ማረጋገጥና አገልግሎቶቹን ማስፋፋት ነው። ይህን ታላቅ ዓላማ ለማሳካት የሁሉም ወገኖች ትብብር፣ ተሳትፎና ድጋፍ ያስፈልገናል። ስለሆነም በዚህ የድጋፍ ዘመቻ ላይ ሁላችሁም በንቃት እንድትሳተፉ፣ በአቅማችሁ እንድትደግፉ፣ መልእክቱን ለሌሎች እንድታደርሱና በዳዕዋ ስራ ላይ አሻራ እንድታሳርፋ በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን። በመተባበር፤ የመልካም ሥራዎቻችንን ቀጣይነት እናረጋግጥ! አላህ ጥረታችንን የተባረከ ያድርግልን፣ ከሁላችንም ይቀበልልን። ባረከላሁ ፊኩም! ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

Open in Telegram
Views10,700−9%vs avg
Forwards—
Reactions182
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h5,030
4 h10,700
  1. After 1 hour5,030
  2. After 6 hours10,700
  3. Total to date10,700
#51132Text

በጉራጌ ዞን ብቻ የሚገኙ ከ45 በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መንፈሳዊ ተቋማትና አደረጃጀቶች‼ ============================= (ከአንድ ዞን ይህ ሁሉ መዋቅር?) || ✍️ በፈረንጆቹ 2021 የታተመ ሳይንሳዊ ጥናት በጉራጌ ዞን 339 የደብር ደን ቦታዎችን (በሳተላይት ምርመራ 394)፣ እንዲሁም የጉራጌ ሀገረ ስብከት በ2015 ያቀረበውን 417 አብያተ ክርስቲያናት (ከእነዚህም 13ቱ ገዳማት) እንደሚጠቅስ ያትታል። ከእነዚህ መካከል በሕዝብና በቤተክርስቲያን ምንጮች የተጠቀሱት ዝርዝሮች የሚከተሉት ናቸው፦ (ይህን መረጃ የምጠቅሰው ሰሞኑን በመቋቋም ላይ ያለ 1 የሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ያስገረማቸው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች፤ ከአንድ ዞን ብቻ መሬት ላይ የወረደ ስንት ተቋማት እንዳሏቸው ለማስታወስ በማሰብ ነው።) 1. የጉራጌ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት (መንበረ ጵጵስና — ወልቂጤ) — የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዞኑና የአካባቢው ከፍተኛ አስተዳደራዊ መዋቅር ሲሆን፣ ከጉራጌ ዞን ባሻገር በቤተክርስቲያን አደረጃጀት ምሥራቅ ጉራጌንና ማረቆ ልዩ ወረዳን ጭምር በአንድ ሀገረ ስብከት ያስተዳድራል። 2. የወረዳ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤቶች — በሀገረ ስብከቱ ሥር 9 ያህል ወረዳ ቤተ ክህነቶች እንዳሉ በ2017 E.C. (2025) ሪፖርት የተጠቀሰ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የመንበረ ጵጵስናና የቀቤና ልዩ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት (ወልቂጤ)፣ የቸሃ ወረዳ ቤተ ክህነት፣ የእኖር (እነሞር) እና ኤነር ወረዳ ቤተ ክህነት፣ የእዣ ወረዳ ቤተ ክህነት፣ የጉመር ወረዳ ቤተ ክህነት፣ የአበሽጌ ወረዳ ቤተ ክህነት እና የሶዶ ወረዳ ቤተ ክህነት ይገኙበታል። 3. የጉራጌ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ — በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን የሚያደራጅና ሥርዓተ ትምህርት የሚያዘጋጅ መንፈሳዊ አስተዳደር ክፍል። 4. የካህናት ዋና ክፍል እና የትምህርትና ሥልጠና ዋና ክፍል — በሀገረ ስብከቱና በወረዳ ቤተ ክህነቶች ደረጃ የአብነት ተማሪዎችንና አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ምዘናና ክህነት የሚያስተባብሩ ክፍሎች። 5. የጉራጌ ዞን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ — በዞኑ ሰላም፣ ልማትና ማኅበራዊ ትብብር ላይ የሚሠራ ሲሆን የጉራጌ ሀገረ ስብከት በሰብሳቢነት/አመራርነት ይሳተፍበታል። 6. ቅዱስ ዜና ማርቆስ ዘምሁር መንፈሳዊ ኮሌጅ — በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አማካኝነት የተመሠረተና በጉራጌ ሀገረ ስብከት ከመንበረ ጵጵስናው ጋር አብሮ የተመረቀ ከፍተኛ መንፈሳዊ የትምህርት ተቋም። 7. የምሁር ኢየሱስ ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት፣ የካህናት ማሠልጠኛና ቤተ መዘክር — በቅኔ፣ በድጓ፣ በቅዳሴና በመጻሕፍት ትርጓሜ ሊቃውንትን የሚያፈራ ጥንታዊ የከፍተኛ ትምህርት ማዕከል፣ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍትንና ንዋያተ ቅድሳትን የሚጠብቅ አመናዊ ቤተ መዘክር፣ እንዲሁም በሐዋርያትና በወልቂጤ ከተማዎች ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ 10ኛ ክፍል የሚደርሱ ዘመናዊ ት/ቤቶችን የሚያስተዳድር። 8. የቆጠር ገድራ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም የአብነት ትምህርት ቤት — በእዣ ወረዳ በሚገኘው ገዳም ውስጥ ደቀ መዛሙርትን የሚያስተምር የአብነት ት/ቤትና የካህናት ማሠልጠኛ። 9. መጋቢና አዳሪ የአብነት ትምህርት ቤቶች — በዘጠኙ የወረዳ ቤተ ክህነቶች ሥር በሚገኙ የተለያዩ ገዳማትና አድባራት ውስጥ ዲቁናና ቅስና የሚቀበሉ ደቀ መዛሙርትን የሚያዘጋጁ ት/ቤቶች። 10. ሳሌም ሚዲያ እና ፈለገ ቅዱሳን ሚዲያ — የጉራጌ ሀገረ ስብከትን እንቅስቃሴዎችና መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚዘግቡ የሚዲያ ክፍሎች። 11. ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ — የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የሚመሩት ቅርንጫፍ 12. ወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል (ደብረ ሲና ቅዱስ ገብርኤል) — በወልቂጤ ከተማ የሚገኝ ታላቅ ደብርና ካቴድራል። 13. ወልቂጤ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን — በወልቂጤ ከተማ የሚገኝ ደብር ወጣቶች አደረጃጀት። 14. ወልቂጤ ቅዱስ ሚካኤል ወገብርኤል ቤተክርስቲያን — በወልቂጤ ከተማ የሚገኝ ደብር አደረጃጀት። 15. ጉብሬ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን — በጉብሬ ክፍለ ከተማ የሚገኝና የመስኖና የእንስሳት እርባታ ልማት ሥራዎች የሚካሄዱበት ደብር። 16. ምሁር ኢየሱስ ገዳም (ምሁር ገዳመ ኢየሱስና ኤልያስ) — በምሁር አክሊል ወረዳ፣ ቆረር ቀበሌ (ከሐዋርያት ከተማ 3 ኪ.ሜ፣ ከወልቂጤ 52 ኪ.ሜ ርቀት) የሚገኝ፣ በአቡነ ዜና ማርቆስ የተመሠረተ ጥንታዊ የአርምሞ ገዳምና በሚያዝያ 2018 E.C. አዲስ ዘመናዊ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ያስመረቀ። 17. ገሽ አማኑኤል ቤተክርስቲያን — በምሁር አክሊል ወረዳ የሚገኝና በጥንታዊ የድንጋይ ደወል ቅርሱ የሚታወቅ። 18. ደንገዝ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን — በምሁር አክሊል ወረዳ የሚገኝ፣ የድንጋይ ደወልና መንበር ያለው ታሪካዊ ቤተክርስቲያን። 19. ቆጠር ገድራ መካነ ቅዱሳን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም — በእዣ ወረዳ ከ350 ሄክታር በላይ በሚሸፍነው ታሪካዊ የቆጠር ገድራ ጥብቅ ደን ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ገዳም። 20. አትርፎ ደብረ ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን — በእዣ ወረዳ የሚገኝና በጉራጌ ምድር ከተተከሉ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ። 21. ገጨ ቅዱስ ሩፋኤል አንድነት ገዳም — በእዣ ወረዳ የሚገኝ ገዳም። 22. ደረሬ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ወደብር — በእዣ ወረዳ የሚገኝ ገዳምና ደብር። 23. ምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን — በእዣ ወረዳ የሚገኝና በ2013 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ የተከበረ ሕንጻ ቤተክርስቲያን። 24. ጎበት ደሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን — በእዣ ወረዳ የሚገኝና በግንቦት 2017 E.C. (2025) የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የተከናወነ ደብር። 25. ኤነር አማኑኤል ገዳም — በእነሞርና ኤነር / ኤነር መገር ወረዳ የሚገኝ፣ ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በታሪክ የሚጠቀስ ጥንታዊ ገዳምና የአካባቢው ባህላዊ ሸንጎ መሰብሰቢያ ቦታም የነበረ። 26. ጠረደ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን — በእነሞርና ኤነር / ኤነር መገር ወረዳ የሚገኝ ቤተክርስቲያን። 27. የጆካ ደብረ ሰላም በዓለወልድ ቤተክርስቲያን — በቸሃ ወረዳ (እምድብር አካባቢ) የሚገኝ ደብር። 28. እምድብር የረሸዋ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን — በቸሃ ወረዳ (እምድብር አካባቢ) የሚገኝ ደብር። 29. አበኬ ኧጅ ኤበራ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን — በጉመር ወረዳ የሚገኝ ቤተክርስቲያን። 30. ዳርጌ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን — በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ «ዳርጌ» ቀበሌ/አካባቢ ከጉራጌ ሀገረ ስብከት ጋር ተያይዞ የሚጠቀስ ደብር 31. ዳግማዊ ደብረ ሊባኖስ፣ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም 32. አቡነ ዜና ማርቆስ ቤተክርስቲያን — በጻድቁ ስም የተሰየመና በጉራጌ ሀገረ ስብከት ምንጮች የተጠቀሰ። 33. አሳር ጊዮርጊስ — በጉራጌ ዞን ምንጮች የተጠቀሰ ቤተክርስቲያን 34. ጂገና ጊዮርጊስ — በጉራጌ ዞን ምንጮች የተጠቀሰ ቤተክርስቲያን 35. ፋቶ ባለወልድ ቤተክርስቲያን — በጉራጌ ዞን ምንጮች የተጠቀሰ ቤተክርስቲያን። 36. ዋሻ ሥላሴ ቤተክርስቲያን — በጉራጌ የታሪክ ትውፊት ከቀደምት አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ሆኖ የሚጠቀስ። 37. ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም — ከአዲስ አበባ 122 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተመሠረተ ጥንታዊ ገዳም፤ በአሁኑ የመንግሥት አስተዳደር በምሥራቅ ጉራጌ ዞን፣ ሶዶ ወረዳ ውስጥ ቢሆንም በቤተክርስቲያን አደረጃጀት ግን በጉራጌ ሀገረ ስብከት ሥር ነው። 38. ዶባ ጥሙጋ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን — በሶዶ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኝና በጉራጌ ሀገረ ስብከት የሚተዳደር ደብር። 39. አዳዲ ማርያም ውቅር ቤተክርስቲያን — በታሪክና በጉዞ ከጉራጌና ከምድረ ከብድ አካባቢ ጋር በቅርበት የምትነሳ ጥንታዊት ውቅር ቤተክርስቲያን ብትሆንም፣ በአስተዳደራዊ ወሰን በኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ቀርሳና ማሊማ ወረዳ ውስጥ ትገኛለች። 40. የወልቂጤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ተስፋ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት — በ1990 E.C. በወልቂጤ ከተማ የተመሠረተ፣ የርቀት ትምህርትና ዲጂታል መጽሔት ያለው ንቁ ሰንበት ት/ቤት። 41. የየጆካ ደብረ ሰላም በዓለወልድ ቤ/ክ ሰንበት ት/ቤት — በቸሃ ወረዳ የሚገኝ ሰንበት ት/ቤት። 42. ማኅበረ ቅዱሳን (የወልቂጤ/ጉራጌ እና የእምድብር ወረዳ ማዕከላት) — በምድረ ከብድና በቆጠር ገድራ ገዳማት የአብነት ትምህርት ቤቶችን፣ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶችንና የሰንበት ት/ቤቶችን ሥርዓተ ትምህርት በማዘጋጀት የሚያግዝ ማኅበር። 43. ማኅበረ ዜና ማርቆስ ዘሀገረ ምሁር አክሊል — በምሁር አክሊል ወረዳ ከምሁር ኢየሱስ ገዳምና ከመስቀል ጉባኤያት ጋር የተያያዙ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን የሚያስተባብር ማኅበር። 44. ማኅበረ ማርያም ዘባጃ — በጉንችሬ አካባቢ በበጎ አድራጎትና ለአረጋውያን መጠለያ በመሥራት ሥራ የተጠቀሰ ማኅበር። 45. በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያናት የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት ልብ በሉልኝ፦ ይህ ዝርዝር በኦፊሻል የሀገረ ስብከቱ ዘገባዎች፣ በመንግሥት የባህልና ቱሪዝም ጽሑፎች፣ በዜና አውታሮችና በጥናታዊ ጽሑፎች ላይ የተገኙ ሕዝባዊ መረጃዎችን ያጠቃለለ እንጂ በዞኑ የሚገኙትን ሁሉንም 417+ አብያተ ክርስቲያናት የያዘ ሙሉ መዝገብ አይደለም። እንዲሁም አንዳንድ ተቋማት በቅርቡ ከተደረገው የምሥራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደራዊ መዋቅር በኋላ በአስተዳደር ካርታ ከጉራጌ ዞን ቢለዩም፣ በቤተክርስቲያን ሀገረ ስብከት አደረጃጀት ግን አሁንም ከጉራጌ ሀገረ ስብከት ጋር የሚተዳደሩ መሆናቸውን ልብ ማለት ያስፈልጋል። ታዲያ ይህ ሁሉ መሬት የወረደ ተቋም በአንድ ዞን ውስጥ ብቻ ያለው ተቋም፤ ለምን ገና በመቋቋም ላይ በሚገኝ በአንድ የሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ላይ ቅናት ያድርበታል? ኧረ! ተው እንከባበር ወገን‼ || t.me/MuradTadesse

Open in Telegram
Views10,000−15%vs avg
Forwards—
Reactions157
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h3,570
2 h7,820
4 h10,000
  1. After 1 hour3,570
  2. Total to date10,000
#51131Text

በሃይማኖት ስም የሚካሄድ የፖለቲካ ንግድ‼ ========================== በአሕመዲን ጀበል ~~~ ✊በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሃይማኖት ስም የሚካሄደው የጥላቻ ዘመቻ ሁሉ ከእምነት ቅንዓት የመነጨ አይደለም። አንዳንዶች ሃይማኖትን ለፖለቲካ ፍላጎታቸው ይጠቀሙበታል፤ በእምነት ስሜት ተደብቀው ተከታይ፣ ዝናና ተጽዕኖ ይፈልጋሉ። ያለፉ ሥርዓታት ታሪክ በሰነድ ሲመረመር፣ «ሃይማኖታችን ተነካ» የሚል ጩኸት ይሰማል። በዚህ ጩኸት ውስጥ ግን የታሪክ ማስረጃውን የመመርመር ፍላጎት አይታይም፤ ይልቁንም ሕዝቡን በስሜት አነሳስቶ የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት የሚደረግ ጥረት ይታያል። የዚህ ዘመቻ መጀመሪያ ፍርሃት ነው። አንድ ሙስሊም ጸሐፊ የታሪክ ሰነድ ሲያቀርብ ወይም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ መብቱን ሲጠይቅ፣ «እምነታችሁ ሊጠፋ ነው፤ ታሪካችሁ ሊፋቅ ነው» በማለት ሰዎችን ለማስደንገጥ ይሞክራሉ። ከዚያም ራሳቸውን የእምነቱ ጠባቂ አድርገው ያቀርባሉ። ሰው በፍርሃት ሲዋጥ ማስረጃን በጥሞና ለማንበብ ይቸገራል። የተጻፈውን ከመመርመር ይልቅ የሚያስደነግጠውን ጩኸት ይከተላል። የዘመቻው አቀናባሪዎችም የሚፈልጉት ይህንኑ ነው፤ የሕዝብን ስሜት አነሳስተው የራሳቸውን አጀንዳ ማስኬድ። ይህ ዘዴ ያለፉ መንግሥታዊ በደሎችንም ከተጠያቂነት ለማስመለጥ ይጠቅማል። የቀድሞ ገዥዎችን ድርጊት ከመመርመር ይልቅ፣ የፖለቲካ ልሂቃኑን ስህተት በተራው አማኝ ላይ ያላክካሉ። «የቀድሞ መንግሥት አስተዳደር ተተቸ» ማለት ያለና የሚኖር ዜጎች ስለሀገራቸው መንግሥት የሚኖራቸው እይታ ዉጤት ነው። «ቤተ ክርስቲያን ተነካች» ወይም "እምነታችን ተሰደበ" ማለት የብዙዎችን ስሜት በቀላሉ ያነሳሳል። ከዚህ የተነሳ እንደ አርዓያ ለማቅረብ እየተጉ ያለውን ስርዓት ለመከላከል ሃይማኖትን እንደ ጋሻ ይይዛሉ። በእርግጥ ሃይማኖትን ለፖለቲካ ሽፋን ማዋል ግን እምነቱን ማክበር አይደለም። በማኅበራዊ ሚዲያ በሞዓ ተዋህዶ አባላትና በደጋፊዎች የሚዘራው ጥላቻ የሀገርን ሰላም ያናጋል፤ አብረው የኖሩ ሰዎችንም እርስ በርስ በጥርጣሬ እንዲተያዩ ያደርጋል። የስም ማጥፋት ዘመቻው ተከታይና ዕይታ ያስገኝላቸዋል፤ እነርሱም ያንን ወደ ዝናና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ይቀይራሉ። የሚጎዳው ግን በጥላቻው መካከል የሚገኘው ሕዝብና አብሮነታችን ነው። የሃይማኖት አባቶችና ለእምነታቸው የሚቆረቆሩ ዜጎች ይህን ነገር በጥሞና ሊመለከቱት ይገባል። ሃይማኖት የፍቅር፣ የእውነትና የፍትሕ መሠረት ነው፤ ለፖለቲካ ነጋዴዎች መሸሸጊያ መሆን የለበትም። የታሪክ ሰነድን በማሰረጃ መመርመርና ተቃራኒውን ማሳየት ለሃይማኖት ጠላት መሆን አይደለም። አደገኛው የጥፋት ተግባር ሆነ ተብሎ እየተደረገ ያለው በሃይማኖት ስም ጥላቻን መንዛት፣ በሕዝቦች መካከል ጥርጣሬን መዝራትና የሕዝብን ስሜት ለፖለቲካ ጥቅም መዘወር ናቸው። ለአሁኑ አበቃሁ።ቸር እንሰንብት!

Open in Telegram
Views13,300+13%vs avg
Forwards—
Reactions200
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h5,260
4 h10,900
8 h13,300
  1. After 1 hour5,260
  2. After 6 hours10,900
  3. Total to date13,300
#51130Text
Views12,600+7%vs avg
Forwards—
Reactions271
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h3,520
2 h8,000
4 h10,400
7 h12,600
  1. After 1 hour3,520
  2. After 6 hours12,600
  3. Total to date12,600
#51129Video
Views12,000+2%vs avg
Forwards—
Reactions191
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h4,720
5 h10,700
6 h12,000
  1. After 1 hour4,720
  2. After 6 hours12,000
  3. Total to date12,000
#51128Photo
Views11,400−3%vs avg
Forwards—
Reactions72
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h4,720
5 h10,100
6 h11,400
  1. After 1 hour4,720
  2. After 6 hours11,400
  3. Total to date11,400
#51127Photo

በፖለቲካው መድረክ እና በጦር ግምባር ክፉኛ የተዘረረው የጽምዶ ቡድን፤ የመጨረሻ ሙከራው ወደሆነው የኃይማኖት ጉዳይ መምጣቱ አንድ የጠቀመን ነገር፤ የኃይማኖት አባቶቻቸው ጭምር በህቡዕና በይፋ ምን ያክል ግጭት ጠማቂ፣ ለጦርነት ቀስቃሽ፣ ያልተነቃባቸው ፖለቲከኛ፣ ጽንፈኛና የአጼው ስርዓት ናፋቂ መሆናቸውን የሚያሳዩ የቪድዮና የምስል ማስረጃዎችን በነፃነት እንድንለቅ ሰበብ ሆነውናል። በዚህም አብዛሃኛው ማኅበረሰብና የነርሱ ተከታይ ጭምር እንዲታዘባቸውና እንዲያፍርባቸው ማድረግ ችለናል። አሁንም ካላረፉ ገና በብዙ እጥፍ ይጨመርላቸዋል። ተከታዮቻቸውን ሌላውን ጠላት በማድረግ ለመሰብሰብ ቢሞክሩም፤ የበለጠ የሚያጋጭና ለትዝብት የሚዳርጋቸው ነው። እኛም ቀድመው ስለተነኮሱን፤ ሳንደርስባቸው ስለደረሱብን… ያለ ምንም ሼምና ኃፍረት ልክ ልካቸውን ያለ ማጋነን ከራሳቸው በተገኙ መረጃና ማስረጃዎች በአደባባይ ትክክለኛ ጭምብላቸውን ለማውለቂያነት ግሪን ላይት ሆኖናል። وَإِنْ عُدتُّمْ عُدْنَا ۘ

Open in Telegram
Views11,7000%vs avg
Forwards—
Reactions213
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h4,210
5 h10,200
6 h11,700
  1. After 1 hour4,210
  2. After 6 hours11,700
  3. Total to date11,700
#51126Photo
Views11,200−4%vs avg
Forwards—
Reactions236
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h5,170
7 h11,200
  1. After 1 hour5,170
  2. After 6 hours11,200
  3. Total to date11,200
#51125Voice message
Views10,900−7%vs avg
Forwards—
Reactions43
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h5,740
7 h10,900
  1. After 6 hours10,900
  2. Total to date10,900
#51124Text

ይሄው ነው‼ ======== ✔ ሁሉም ማህበረ ቅዱሳን ፅን"ፈኞች ናቸው ማለት ህገ ወጥ ነው። አይባልም! ግን የፅን:ፈኛው ልሳኖች ኡጋንዳም ይኑሩ አሜሪካ ሁሉም በአንድ ወቅት የማህበረ ቅዱሳን አባላት ነበሩ!! ✔ ሁሉም ማህበረ ቅዱሳን ሞዓ ተዋህዶ አባል ናቸውና አይባልም ። ነውር ነው! ግን ሁሉም የሞዓ ተዋህዶ አባላት ግን ማህበረ ቅዱሳን የነበሩ ናቸው ✔ ሁሉም ፋኖዎች ሞዓ ተዋህዶዎች ናቸው አይባልም። ግን ሁሉም ሞዓ ተዋህዶዎች ፋኖዎች ናቸው!! ✔ ሁሉም ፋኖዎች ሳልሳዊ ቴዎድሮድና ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን አባላት ናቸው አይባልም። ሁሉም የሳልሳዊ ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን አባላት ግን ፋኖዎች ናቸው!! ✔ መንግስትን ተቃውመው ጫካ የገቡትም በከተማ ያሉት ሁሉ የፅምዶ ደጋፊና አካል ሆነው የኢትዮጵያን መንግሥት ለመጣል በሚል ከግብፅ፣ ከሱዳንና ከኤርትራ ጋር ተሰልፈዋል ባይባልም። ሁሉም ከሱዳን ኤርትራና ግብፅ ጋር ሆነው የተሰለፉት በሙሉ ግን ባን: ዳዎች ናቸው ። ✔ ሁሉም የኦርቶዶክስ ማህበራት ይሄ መንግሥት የእስላም መንግስት ነው ባይሉም ሁሉም ይህ መንግስት የእስላም መንግስት ነውና ተነስ ታጠቅ፣ ዝመት፣ ጥለህ ውደቅ የሚሉት በሙሉ የኦርቶዶክስ ማህበራት አባላት ወይም መሪ የሆኑ ቀሳውስቶች ናቸው!! ✔ በኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት የትኛው ሃይል በቋሚነት በፕሮፓጋንዳም፣ በትርክትም፣ በነፍጥም መንግሥት እንዳይረጋ፣ ሠላም እንዳይመለስ በይፋም በስውርም እየሰራ እንደሆነ እንኳን ለመንግስት ለማንም የሚሰወር አይደለም!! ✔ የሽብርን ተግባር ማን እንደሚፈፅመው መንግስት ጠፍቶት ነው? የእስላም ሲሰግድም ሲበላም ሲስቅም ሲቀመጥም ፎቶ እያነሳህ "አሸ-ባሪ ውሃ'ቢያ!" እያልክ በመለጠፍ ከመንግስት ጋር ሙስሊሙን ለማጋጨት የምትደክመው? ይህንማ ክ1987-2004 አጥብቃችሁ ሰራችሁትኮ!! እና ደግሞ ✔ ሁሉም በአርሲ የሞቱት ኦርቶዶክሶች ብቻ ናቸው አይባልም። ግን በአርሲ የተጨ: ፈጨፉትን ኦርቶዶክሶች በሙሉ ከጨፈ 'ጨፋቸው የሸኔ ቡድን ጋር ጥምረት የፈፀሙት በሙሉ የኦርቶዶክስ አፊሌትድ ታጣቂ የትግራይና የአማራ ሃይሎች ናቸው!! ©: ዐብዱ-ል-ጀሊል ሸይኽ ዓሊ ካሳ

Open in Telegram
Views11,500−2%vs avg
Forwards—
Reactions213
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h6,650
7 h11,500
  1. After 6 hours11,500
  2. Total to date11,500
#51121Video

ይሄ መዝሙር ሲዘመርለት የጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር Abiy Ahmed የፊቱን reaction የሚያሳይ ሌላ ቀረፃ ካለ ላኩልኝ እስኪ?! በሳቅ ፈንድቶ ከመድረክ ተነስቶ አልሄደም ወይ¿ ወዳጄ! አንዳንዱ ቄስ ከርሱ የበለጠ ትጥቅ አለን፣ ከፈለግን አንበርክከነው በ24 ሰዓት የአባታችንን የአጼ ሚኒልክን ቤተ መንግስት እንረከባለን… ይላል እንጂ፤ እንደዚህ ዘምሮ መኖር ነው የሚያዋጣቸው¡ ★ ኧረ! ቢስሚላህ! ዘመረው'ኮ አንተ¡ ይሄ ነው አኗኗሩ የገባው¡ ዝም ብለህ «ኧረ! እነ አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ እነ በላይ ዘለቀ፣ እነ አጼ ሚኒሊክ… ኧረ! ከመቃብር ውጡና ኑልን!» ከምትነፋረቅ፤ በጊዜው ካለ መሪ ጋ ተስማምተህ፣ ሲያሻህም እየዘመርክለት መኖር¡ (ከጎኑ ያለው ባለ መነፅሩ ግን የመጀመሪያው አመለካከቱ ገዳይ ነው። እይታውን ያነሳው በሳቅ ፈንድቶ ላለመታሰር ነው መሰል¡

Open in Telegram
Views11,600−1%vs avg
Forwards—
Reactions322
Comments—
#51120Photo

ሽብርን ቀድመን እንከላከል‼ ================== ✍️ ጠቅላይ ሚኒስተሩ በድብቅ ከነ አሕመዲን ጀበል ጋር ሆኖ በሙስሊም ወንድማማቾች አማካኝነት ቱርክ ላይ የወሃ•ቢያ ስልጠና ሲወስዱ ከርሞ እስላማዊ መንግስት የመመስረት እቅዳቸው አሁን በግልፅ ፍጥጥ ብሎ መጣ። የራሷን ፊደል የቀረፀችውን የአገራችንን ቋንቋን በመናቅ በእስላም ቋንቋ ቤተመንግስቱን እና የክርስታን ደሴት የሆነችዋን ኢትዮጵያን አራከሷት። ጠሚው ክርስቲያን መስለው እንዳታለሉን ቀደም ብለንም ተናግረን ነበር። ድሮም አሕመድ የሚል የአባት ስም ይዘው እንዴት ይታመናሉ? ይህ ነው እንግዲህ የወሃ*ቢያ አለማ። ወሃ°ቢያ የሆኑትን ጠቅላይ ሚ/ሩን እና አሕመዲን ጀበል አገራችን ኢትዮጵያን ከመናዳቸው በፊት ለፍርድ በማቅረብ ሽብርን ቀድመን እንከላከል። ልብ ያለው ልብ ይበል! Isak Yasin

Open in Telegram
Views12,200+4%vs avg
Forwards—
Reactions323
Comments—
#51119Text
Views12,900+10%vs avg
Forwards—
Reactions220
Comments—
#51116Text

እነዚህን የ"ትኩረት ጠለፋ" ስልቶች መረዳት፣ ጥቃቱ ሲሰነዘር በስሜት ከመነዳት ይልቅ በዕውቀት ለመመከት ያስችላል። መብት የችሮታ ውጤት ሳይሆን የዜግነት መገለጫ መሆኑን ማመን የጽናታችን ምንጭ ሊሆን ይገባል። ይህ ለምን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ያሳስባል? ✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅ የታርጋ ፖለቲካና የጅምላ ፍረጃ ዛሬ በአንድ ወገን ላይ ቢሰነዘርም፣ ነገ ግን መላውን ሀገርና የዜግነት መብትን የሚንድ የጋራ ጠላት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይህንን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ መመከት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን፣ ለፍትሕና ለሰው ልጅ ክብር የሚቆሙ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀገራዊ ግዴታ ነው። ለዘመናት የጸናው የአብሮነትና የሰላም እሴታችን በጥቂት አንቂዎች የፈጠራ ትረካና በዲጂታል ሴራ ፈጽሞ ሊፈርስ አይችልም። በመሆኑም እውነትን በማንገብ የሐሰትን ወጥመድ በመበጣጠስ ፣ የሁላችንም መሸሸጊያ የሆነችውን ኢትዮጵያን ከፍረጃና ከጥላቻ ፖለቲካ ነፃ ማውጣት ታሪካዊ ኃላፊነታችን ነው። ለዛሬ አበቃሁ። ቸር እንሰንበት!

Open in Telegram
Views15,100+29%vs avg
Forwards—
Reactions175
Comments—
#51115Text

የፍረጃው መሪ ተዋናዮች እና አጀንዳዎቻቸው 🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨 በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ "ወሃቢ"፣ "አክራሪ" ወይም "አሸባሪ" የሚሉ የፍረጃ ቃላትን ደጋግመው በሚለጥፉ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ በብዙ አጋጣሚዎች የሚስተዋል አንድ ተደጋጋሚ ድርጊት አለ፤ ይኸውም አንዳንድ የተደራጁ አካላት በብሔርና በእምነት ፖለቲካ ስም የተቀነባበሩ የዲጂታል ዘመቻዎችን ሲያካሂዱ ይስተዋላል። እነዚህን የፍርጃ ቃላት የሚፈጥሩ፣ መልእክቶችን የሚለጥፉና የሚያጋሩ ጥቂት ግለሰቦችን የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ስንመለከት የሚከተሉትን ሁለት ግልጽና ልዩ መለያዎችን እናያለን፦ 1. የፖለቲካ አርማ ፦ 🏀🏀🏀🏀🏀 በብዙዎቹ የእነዚህ አካላት ገጾች ላይ የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ ምልክቶች አሉ፤ ለምሳሌ የፋኖ ደጋፊነትን የሚያሳዩ ምልክቶችና የጽንፈኛ ብሔርተኝነት መፈክሮች በስፋት ሲንጸባረቁ ይታያል። 2. ሃይማኖታዊ ሽፋን ፦ 🚛🚛🚛🚛🚛🚛 ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ጋር የተቆራኙ ምልክቶችን እንደ መሸፈኛ በመጠቀም፣ የእምነቱን የሰላምና የአብሮነት እሴቶች የማይወክል የፖለቲካ ጥላቻን የሚረጩ ናቸው። በፍርሃት ላይ የተመሠረተ የሕዝብ ንቅናቄ 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 እነዚህ አካላት የጋራ መለያቸው ማንኛውንም ሃይማኖታዊና ብሔራዊ ስሜት ቀስቃሽ ጉዳዮችን በመጠቀም በሕዝብ ዘንድ ፍርሃትን መፍጠር እና በዚያ ፍርሃት አማካኝነት ሕዝብን ለራሳቸው ስውር አጀንዳ ማሰለፍነው። በዚህ አካሄድ ላይ ተሰማርተው የምናገኛቸው ሦስት ተዋናዮች ናቸው። እነርሱም፦ 1. ጽንፈኛ የብሔር ፖለቲከኞች ፦ 💥💥💥💥💥💥💥💥💥 በብዙዎቹ የእነዚህ አካላት ገጾች ላይ የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ ምልክቶች አሉ፤ ለምሳሌ፦ የፋኖ ደጋፊነትን የሚያሳዩ አርማዎች፣ ፎቶዎችና የጽንፈኛ ብሔርተኝነት መፈክሮች በስፋት ሲንጸባረቁ ይታያሉ። ይህም ፖለቲካዊ አጀንዳን ከሃይማኖታዊ ፍረጃ ጋር በማቀላቀል ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለጥቃት ኢላማ የማድረግ ስልት አካል ይመስላል። እነዚህ አካላት በዛ የሚሉቱ በአማራ በተለይ በፋኖ ጉዳይ እንንቀሳቀሳለን የሚሉ ሲሆኑ ስልታቸውም ሙስሊሙን ማህበረሰብ "የኦሮሞ ብልጽግና ስርዓት ስልታዊ አጋር" አድርጎ በመፈረጅ ለጥቃት ኢላማ ሲያደርጉት ይታያሉ።ከዚህ የተነሰ «ኦሮሙማ» እና «ስልጤ» የሚሉ ታፔላዎችን በመለጠፍ ሲፈርጁም ይታያል። 2. በእምነት ስም የሚንቀሳቀሱ አክራሪዎችና፦ 🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀 እነዚህ አካላት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ምልክቶችን እንደ መስቀልና የቅዱሳን ሥዕላትን እንደ መሸፈኛ በመጠቀም፣ የእምነቱን የሰላምና የአብሮነት እሴቶች የማይወክል የፖለቲካ ጥላቻን ይረጫሉ። ዋና ዓላማቸውም ታሪካዊ የበላይነትን ለማስጠበቅ ሲሉ የሙስሊሙን ማህበረሰብ መሠረታዊ የመብት ጥያቄዎች እንደ "ሕልውና ስጋት" አድርጎ ማቅረብ ሲሆን፣ ይህም ሙስሊሙን እንደ "መጤ" ወይም "የባዕድ አስተሳሰብ ተላላኪ" አድርጎ በመፈረጅ ከሀገር ባለቤትነት የማግለል ስልታዊ አካሄድ ነው። እነዚህ አካላት ቤተ ክርስቲያንን እንደ ብቸኛ የሀገር ባለቤት አድርገው በመሳል የሚረጩት ይህ መርዛማ ትርክት፣ ተራው አማኝ የጥላቻ መልእክቱን እንደ ሃይማኖታዊ እውነት እንዲቀበለው በማድረግ ለዘመናት የቆየውን የሕዝቦች አብሮነት የሚሸረሽርና በዜጎች መካከል የጥርጣሬ ግንብ የሚገነባ አደገኛ ስልት ነው። 3. ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የ አካውንቶች ፦ 🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎 በውጭ ሀገር የሚገኙና በዛ ያሉ ተከታዮች ያሏቸው የቲክቶክ፣ የቴሌግራም እና የፌስቡክ «መምህር»ና «አንቂዎች» የሚባሉ የዘመቻው ሞተሮች ናቸው። እነዚህ አካላት የተከታዮቻቸውንና የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ "በኢትዮጵያ የእስልምና አክራሪነት ስጋት ደቅኗል" የሚል አጀንዳ በመቅረጽ የጥላቻ ንግግሮችን በማቀናበር ሙስሊሞች ላይ ጥርጣሬና ፍርሃት እንዲነግስ ይተጋሉ። የጠላት ፈጠራ ፋብሪካ፦ ስልታዊ ኪሳራ እና የማግለል ሴራ 🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡 የእነዚህ አካላት ሌላኛው አደገኛው ጠባይ ይታይባቸዋል።ማንም ይሁን ማን በማህበራዊ ሚዲያ ምህዳር ዉስጥ እነርሱ የሚያዜሙትን ካላዜመ፥ በለቅሶ ፖለቲካቸው ላይ ከእነርሱ ጎን ተሰልፎ አብሮ ካላለቀሰ፥ ወይም ደስታውንም ሆነ ሀዘኑን እነርሱ ካሰመሩት አካሄድ ወጥቶ በራሱ መንገድ ጉዳዩ ላይ አቋሙን ከገለጸ ወይም ጥያቄ ካነሳ ፥አልያም ስልታዊ አካሄዳቸውንና ሴራቸውን ካወቁባቸው ወይም ድጋፍ ካነፈጓቸው ወዲያውኑ "የአማራ ጠላት" ወይም "የኦርቶዶክስ ጠላት" የሚሉ የታፔላዎች ተመዘው ይለጠፍበታል። በዚህ አካሄዳቸው የተነሳ ለአማራ ሕዝብ እና ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን በቀንና በሌሊት በርካታ «ጠላቶችን» እየፈጠሩ ይገኛሉ። ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻቸው እንደታዘብኩት በርካታ አካላትን ጠላት በሚል ፈርጀው ዘምተውባቸዋል። በአማራ ክልል ውስጥ የቅማንትን፣ የአገውን፣ የወሎ ኦሮሞን፣ አማራ ሙስሊሙንና የክልሉን መንግሥት (በብአዴን ስም)፤ በወሎ ሕዝብ ጉዳይ የሚንቀሳቀሱ አካላትን፥ ከክልል ውጭ ደግሞ መላው የኢትዮጵያ ሙስሊምን ("ወሃቢ" በሚል)፣ የትግራይ ኤሊትንና ፓርቲን፣ እንደሕዝብ የኦሮሞንና የስልጤን ሕዝብ፣ በመተከል ያሉ የቤኒሻንጉል ብሔረሰብ አባላትን፥ከፓርቲ ደግሞ የብልጽግና ፓርቲን፥ኢዜማን፥ በጠላትነት ፈርጀዋል። በግለሰብ ደረጃ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን፥ ጀውሃር መሀድን፥ እኔ አሕመዲን ጀበልን ጨምሮ በርካቶችን ሲፈርጁ ታዝቤያለሁ። እዚህ ላይ አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ማንሳት ያስፈልጋል። ለመሆኑ በቀን 24 ሰዓት ስድብን፣ ፍረጃንና ጠላትን ማምረት እነርሱ ቆመንለታል ለሚሉት ለአማራም ሆነ ለኦርቶዶክ እምነት ተከታይ ሕዝብ ምን ጥቅም ያስገኝላቸዋል? የሕዝቡን ዘላቂ ችግሮች ይፈታል ወይስ ይበልጥ ያባብሳል? ከወዳጅ ይልቅ ጠላትን ማምረት የፖለቲካ ብስለት ሳይሆን ስልታዊ ኪሳራ ነው። ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ትክክለኛው ስልታዊ ጥቅም የሚገኘው ከሌሎች ማህበረሰቦች ጋር አጋርነትና ጥምረትን በመፍጠርና ድጋፍ በማሰባሰብ እንጂ ጠላትን በማብዛት አልያም ስድብ የሚያዋጡ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመፍጠር አይደለም። ከየትኛውም ወገን ይሁን ከየት የሚሰነዘርባቸውን ጥቃቶች ለመመከትና የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ትኩረትና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ የሌሎችን ወገኖች አጋርነትና ድጋፍ ማግኘት እጅግ ወሳኝ ነው። በተጨማሪም ሁሉንም ወገን በጠላትነት መፈርጅና ማግለል የፍትሕ ጥያቄያቸው ድጋፍ እንዳያገኝ በማድረግ ለብቻቸው ተነጥለው ለጥቃት እንዲጋለጡ በማድረግ የከፋ ጉዳት ያመጣል። እነዚህን የጥላቻ ትረካዎች የሚያመርቱ፣ በጅምላ የሚፈርጁና በየቀኑ ጠላት የሚፈጥሩ አካላት በማንኛውም መልኩ ሊደገፉ፣ ሊበረታቱ ወይም የትግሉ አካል ሊደረጉ አይገባም። የእነሱ ድርጊት የሕዝቡን ስቃይ የሚያራዝም እንጂ መፍትሔ የሚያመጣ ባለመሆኑ፣ ይህ አካሄድ የጠላት ተግባር እንጂ የወዳጅ እርምጃ ሊባል አይችልም። ከዚህም ባለፈ፣ በሌሎች ሃይማኖታዊ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ተቋማትና እንቅስቃሴዎች ላይ በማተኮር እነሱን ለማጥቃት ጊዜን ማጥፋት ፈጽሞ ትክክለኛ አካሄድ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም በሌሎች ላይ ስታተኩር ሌሎችም በአንተ ላይ እንዲያተኩሩ በሩን እየከፈትክ መሆኑን መዘንጋት የለብህም። ሌሎች ላይ በከፈትከው ግንባር ልክ አጸፋው ወደ አንተ እንደሚመለስና ለራስህ ተቋማትና እሴቶች ስጋት እንደሚሆን የታወቀ ነው። የጥቃቱ ኢላማዎች እና ስልታዊ ስኬቶች 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ይህ የተቀነባበረ ዘመቻ በዘፈቀደ የሚሰነዘር ሳይሆን፣ ማህበረሰቡን 'መሪ አልባ' በማድረግ በምሁራንና በተቋማት ላይ እምነት በማሳጣት ስልታዊ ውድመት ለማድረስ የታለመ ነው። ፕሮፓጋንዳ ነጋዴዎቹ የሚከተሉትን ሦስት ዋና ዋና ስኬቶች ለመቀዳጀት ይጥራሉ፦ 1. መጤ አድርጎ የመሳል ሴራ 🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺 እስልምናን እንደ 'ባዕድ አስተሳሰብ' በመሳል ሙስሊሙን ከሀገሩ ታሪክ ጋር ያለውን ትስስር ለመበጠስ ይሰራሉ። ዓላማው ማህበረሰቡን በመበታተን በገዛ ሀገሩ እንደ እንግዳ እንዲቆጠር ማድረግ ሲሆን፣ ይህም ሙስሊሙ መሠረታዊ መብቱን ሲጠይቅ እንደ 'የባዕድ አጀንዳ' ተቆጥሮ ውድቅ እንዲደረግና ለማህበረሰባዊ አንድነት እንቅፋት እንዲሆን ታስቦ የሚከናወን ነው። 2. ከፍረጃ ወደ ፈቃድ ማውጫ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 ንጹሐን ሙስሊሞች ላይ የሚፈጸሙ ዘግናኝ ጥቃቶችን 'ጽንፈኞችን የማጽዳት እርምጃ' አስመስሎ በማቅረብ፣ ለጥላቻና ለጥቃት ማኅበራዊ ፈቃድ ለማግኘት ይጣራል።ግፍ ሕጋዊ ከመደረጉ በፊት፣ ጥላቻ ማህበራዊ ተቀባይነት እንዲያገኝ ይደረጋል። ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ሰለባው በጥርጣሬ እንዲታይ ይደረጋል። 3. የዓለም አቀፍ ድጋፍ መሸጫ 'ወሃቢዝም' እና 'ሽብርተኝነት' የሚሉ ስሜት ቀስቃሽ ቃላትን እንደ መሸጫ መሣሪያ በመጠቀም፣ ከምዕራባውያንና ከዓለም አቀፍ አካላት ዘንድ የፖለቲካና የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት የሐሰት ትርክት ይሰራሉ። ይህ ስሌት በሀገር ውስጥ ያሉ ምሁራንና ተቋማት ላይ ዓለም አቀፍ ጫና እንዲፈጠር በማድረግ፣ ማህበረሰቡን የሚመራበት አስተማማኝ አቅጣጫ በማውጣት ለጥላቻ ነጋዴዎች ስውር የፖለቲካ ፍላጎት ተገዢ እንዲሆን ያደርገዋል። ሂደቱ በሚከተለው መልኩ ወደ አደገኛ ደረጃ ይሸጋገራል፦ ተደጋጋሚ ክስ → ማኅበራዊ መላመድ → የሞራል ድንዛዜ → የማግለል ፈቃድ ይህ የጥፋት ጉዞ የሚከተሉትን ደረጃዎች ይይዛል፦ 1. ተደጋጋሚ ክስ ✅✅✅✅✅✅ አንዱን ወገን ኢላማ ያደረጉ የሐሰት ትርክቶችና ፍረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያና በተለያዩ አውታሮች ደጋግመው ይለቀቃሉ። 2. ማኅበራዊ መላመድ 📶📶📶📶📶📶📶 ክሱ በየቀኑ ሲደጋገም፣ መጀመሪያ ላይ "እውነት አይደለም" ብሎ ሲሞግት የነበረው ማህበረሰብ ቃላቱንና ትረካዎቹን እንደ ተራ ወሬ መልመድ ይጀምራል። 3. የሞራል ድንዛዜ 🌲🌲🌲🌲🌲 ማህበረሰቡ ፍረጃውን ሲለምደው፣ በተበዳዩ ወገን ላይ ለሚፈጸሙ ግፎችና መገለሎች ያለው ርኅራኄ እየቀነሰ ይሄዳል። "ሊደረግበት የሚገባው ነው" የሚል የሞራል ድንዛዜ ውስጥ ይገባል። 4. የማግለል ፈቃድ 📦📦📦📦📦📦 በመጨረሻም፣ ግለሰቡን ወይም ማህበረሰቡን ከሀገራዊና ማኅበራዊ ተሳትፎ ማግለል፣ አልፎም ጥቃት መፈጸም በዝምታ የሚታለፍ አልፎም የሚደገፍ "ሕዝባዊ ይሁንታ" ያገኛል። የሥነ-ልቦና ሽባነት እና የውስጥ ክፍፍል 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 የዚህ ስልታዊ ዘመቻ ስር የሰደደ ግብ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሥነ-ልቦና ደካማ፣ በውስጥ የተከፋፈለ እና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ድምፅ አልባና የተገለለ (Marginalized) ማድረግ ነው። ይህ ግብ የሚሳካው ማህበረሰቡን ለሚከተሉት ሶስት አደገኛ ጫናዎች አሳልፎ በመስጠት ነው፦ 1. ራስን መገደብ 🍎🍎🍎🍎🍎 የፍረጃው ቀዳሚ ውጤት ሙስሊሙ ዜጋ "ጽንፈኛ፣ ወሃቢ ወይም አክራሪ ልባል ነው" በሚል ስጋት ራሱንና ሃሳቡን እንዲገታ ማድረግ ነው። ለምሳሌ፦ አንድ ሙስሊም በሥራ ቦታው፣ በዩኒቨርሲቲው ወይም በፖለቲካው መድረክ መሠረታዊ መብቱን ሲያስከብር ወይም ሙያዊ ብቃቱን ሲያሳይ "ታርጋ ይለጠፍብኛል" በሚል ስጋት እንዲሸማቀቅ ይደረጋል። ይህ ሥነ-ልቦናዊ ሽባነት ግለሰቡ በሀገሪቱ የለውጥና የልማት ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዳይሆን በማድረግ፣ የማህበረሰቡን ሀገራዊ አበርክቶ ያኮላሻል። 2. የገጽታ ጥቃት 📣📣📣📣📣 ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚያነሳቸውን ፍትሐዊና አመክንዮአዊ ጥያቄዎች በሐቅ መመለስ ሲያቅታቸው፣ ብቸኛው መሸሸጊያቸው ጥያቄውን ሳይሆን ጠያቂውን ማጥቃት ነው። ይህም በኡስታዞችና በመሪዎች ላይ የተመረዙ ትረካዎችን በመርጨት ስማቸውን ማጠልሸት ነው። የዚህ የገጽታ ግድያ ስልት ዋና ዓላማ በመሪውና በተከታዩ መካከል ያለውን "የመተማመን ድልድይ" በመስበር፣ ማህበረሰቡን መሪ አልባና አቅጣጫ የለሽ አድርጎ ማስቀረት ነው። 3. የውስጥ ክፍፍል (ከፋፍለህ ግዛ) ♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦ ማህበረሰቡን በ"ነባር" እና "መጤ" ወይም በ"ሱፊ" እና "ወሃቢ"/«ሰለፊ» በሚሉ ጎራዎች ተቧድኖ በውስጥ ንትርክ እንዲጠመድ የማድረግ ፍላጎትና አካሄድ እንዳላቸው በተደጋጋሚ ተስተውሏል። የሙስሊሞችን ጉዳዮችን በዚህ መነጽር ብቻ እንዲታይ ደጋፊ ሚዲያዎቻቸው ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ታዝበናል። ይህም ፍላጎታቸውን አላረካ ሲልም አንዱን ቡድን ደግፈው በመጅሊስ ጉዳይና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ይመለከተናል በሚል ቃና በግልጽ ሲታገሉም ታይተዋል። ማህበረሰቡ በውስጣዊ ልዩነቶች ላይ እንዲያተኩር ሲደረግ፣ በጋራ በሚሰነዘሩበት በደሎችና ስልታዊ አደጋዎች ላይ አብሮ የመቆም አቅሙ ይዳከማል። ይህ የውስጥ መከፋፈል ማህበረሰቡን ለውጭ ጥቃትና ለፖለቲካዊ መጠቀሚያነት ተገላጭና ምቹ ያደርገዋል። በአጠቃላይ እነዚህ ስልቶች ሲቀናጁ ማህበረሰቡ በገዛ ሀገሩ ላይ ባይተዋርነት እንዲሰማው፣ ለጋራ ጥቅሙ እንዳይቆም እና በሥነ-ልቦና ተሸንፎ ለሌሎች ፍላጎት ተገዥ እንዲሆን የተሰናዱ የወጥመድ ፖለቲካ መገለጫዎች ናቸው። ያልተደነገገው «ወንጀል» እና የቃላት ላቦራቶሪ 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢 በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ውስጥ "ወሃቢ"፣ "አክራሪ" ወይም "ጽንፈኛ" የሚባል የወንጀል ዓይነትም ሆነ ድንጋጌ የለም። እነዚህ ቃላት በሕግ መጻሕፍት ውስጥ የማይገኙ፣ ነገር ግን በፕሮፓጋንዳ ነጋዴዎች ላቦራቶሪ ውስጥ ለሥነ-ልቦና ጦርነት መሣሪያነት የተፈበረኩ የፖለቲካ ማጥቆሪያ ታርጋዎች ናቸው። ዓላማቸውም ማህበረሰቡን በህግ ጥላ ስር ሳይሆን በፕሮፓጋንዳ ጥላቻ ስር እንዲወድቅ በማድረግ የሞራል ልዕልናውን መንካት ነው። የጥላቻ ትረካ ስርጭት ወቅታዊ ስሌቶች 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 የፕሮፓጋንዳ ነጋዴዎቹ የጥላቻ መርዛቸውን የሚረጩባቸው ወቅቶች በዘፈቀደ የሚመረጡ ሳይሆኑ፣ ከፍተኛ ሥነ-ልቦናዊ ድንጋጤ ለመፍጠር ታስበው በሚከተሉት ሦስት ስሌቶች የሚሰናዱ ናቸው፦ 1. የፀጥታ ችግሮችን ለሴራ መጠቀም 🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀 በሀገሪቱ የትኛውም አካባቢ የፀጥታ መታወክ ሲከሰት፣ ያለ ምንም ማስረጃ "የወሃቢ እጅ አለበት" የሚሉ ትረካዎችን በማሰራጨት ሙስሊሙን ከስጋት ጋር በማቆራኘት በሕዝብ ዘንድ ጥርጣሬን መዝራት። 2. የፖለቲካ ጦስ 📦📦📦📦📦 ሀገራዊ የፖለቲካ ውጥረቶች ሲበረቱና የሕዝብ ጥያቄዎች ሲገዝፉ፣ የሕዝቡን ትኩረት አቅጣጫ ለማስለወጥ ሙስሊሙን ማህበረሰብ እንደ ማላከኪያ በመጠቀም የጥላቻ ግንባር መክፈት። 3. በሃይማኖታዊ በዓላት ላይ የሚሰነዘር ጥቃት 📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶 የጁምዓ ተቃውሞዎች፥ እንደ ረመዳን እና ኢድ ባሉ ታላላቅ በዓላት ወቅት የሚከናወኑ በጎ አድራጎቶችን እንኳ "ለጽንፈኝነት ምልመላ" እንደዋሉ በመሳል፣ በበዓላቱ ድምቀት ላይ የጥርጣሬና የፍርሃት ድባብ መፍጠር።የወጣቶች ካውንስል የአባልነት ምዝገባም ሆነ የአደባባይ ኢፍጣሮችም በዚሁ መልኩ ፈርጀዋቸዋል።

Open in Telegram
Views13,600+16%vs avg
Forwards—
Reactions62
Comments—
#51114Text

1. መጤ አድርጎ የመሳል ሴራ 🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺 እስልምናን እንደ 'ባዕድ አስተሳሰብ' በመሳል ሙስሊሙን ከሀገሩ ታሪክ ጋር ያለውን ትስስር ለመበጠስ ይሰራሉ። ዓላማው ማህበረሰቡን በመበታተን በገዛ ሀገሩ እንደ እንግዳ እንዲቆጠር ማድረግ ሲሆን፣ ይህም ሙስሊሙ መሠረታዊ መብቱን ሲጠይቅ እንደ 'የባዕድ አጀንዳ' ተቆጥሮ ውድቅ እንዲደረግና ለማህበረሰባዊ አንድነት እንቅፋት እንዲሆን ታስቦ የሚከናወን ነው። 2. ከፍረጃ ወደ ፈቃድ ማውጫ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 ንጹሐን ሙስሊሞች ላይ የሚፈጸሙ ዘግናኝ ጥቃቶችን 'ጽንፈኞችን የማጽዳት እርምጃ' አስመስሎ በማቅረብ፣ ለጥላቻና ለጥቃት ማኅበራዊ ፈቃድ ለማግኘት ይጣራል።ግፍ ሕጋዊ ከመደረጉ በፊት፣ ጥላቻ ማህበራዊ ተቀባይነት እንዲያገኝ ይደረጋል። ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ሰለባው በጥርጣሬ እንዲታይ ይደረጋል። 3. የዓለም አቀፍ ድጋፍ መሸጫ 'ወሃቢዝም' እና 'ሽብርተኝነት' የሚሉ ስሜት ቀስቃሽ ቃላትን እንደ መሸጫ መሣሪያ በመጠቀም፣ ከምዕራባውያንና ከዓለም አቀፍ አካላት ዘንድ የፖለቲካና የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት የሐሰት ትርክት ይሰራሉ። ይህ ስሌት በሀገር ውስጥ ያሉ ምሁራንና ተቋማት ላይ ዓለም አቀፍ ጫና እንዲፈጠር በማድረግ፣ ማህበረሰቡን የሚመራበት አስተማማኝ አቅጣጫ በማውጣት ለጥላቻ ነጋዴዎች ስውር የፖለቲካ ፍላጎት ተገዢ እንዲሆን ያደርገዋል። ሂደቱ በሚከተለው መልኩ ወደ አደገኛ ደረጃ ይሸጋገራል፦ ተደጋጋሚ ክስ → ማኅበራዊ መላመድ → የሞራል ድንዛዜ → የማግለል ፈቃድ ይህ የጥፋት ጉዞ የሚከተሉትን ደረጃዎች ይይዛል፦ 1. ተደጋጋሚ ክስ ✅✅✅✅✅✅ አንዱን ወገን ኢላማ ያደረጉ የሐሰት ትርክቶችና ፍረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያና በተለያዩ አውታሮች ደጋግመው ይለቀቃሉ። 2. ማኅበራዊ መላመድ 📶📶📶📶📶📶📶 ክሱ በየቀኑ ሲደጋገም፣ መጀመሪያ ላይ "እውነት አይደለም" ብሎ ሲሞግት የነበረው ማህበረሰብ ቃላቱንና ትረካዎቹን እንደ ተራ ወሬ መልመድ ይጀምራል። 3. የሞራል ድንዛዜ 🌲🌲🌲🌲🌲 ማህበረሰቡ ፍረጃውን ሲለምደው፣ በተበዳዩ ወገን ላይ ለሚፈጸሙ ግፎችና መገለሎች ያለው ርኅራኄ እየቀነሰ ይሄዳል። "ሊደረግበት የሚገባው ነው" የሚል የሞራል ድንዛዜ ውስጥ ይገባል። 4. የማግለል ፈቃድ 📦📦📦📦📦📦 በመጨረሻም፣ ግለሰቡን ወይም ማህበረሰቡን ከሀገራዊና ማኅበራዊ ተሳትፎ ማግለል፣ አልፎም ጥቃት መፈጸም በዝምታ የሚታለፍ አልፎም የሚደገፍ "ሕዝባዊ ይሁንታ" ያገኛል። የሥነ-ልቦና ሽባነት እና የውስጥ ክፍፍል 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 የዚህ ስልታዊ ዘመቻ ስር የሰደደ ግብ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሥነ-ልቦና ደካማ፣ በውስጥ የተከፋፈለ እና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ድምፅ አልባና የተገለለ (Marginalized) ማድረግ ነው። ይህ ግብ የሚሳካው ማህበረሰቡን ለሚከተሉት ሶስት አደገኛ ጫናዎች አሳልፎ በመስጠት ነው፦ 1. ራስን መገደብ 🍎🍎🍎🍎🍎 የፍረጃው ቀዳሚ ውጤት ሙስሊሙ ዜጋ "ጽንፈኛ፣ ወሃቢ ወይም አክራሪ ልባል ነው" በሚል ስጋት ራሱንና ሃሳቡን እንዲገታ ማድረግ ነው። ለምሳሌ፦ አንድ ሙስሊም በሥራ ቦታው፣ በዩኒቨርሲቲው ወይም በፖለቲካው መድረክ መሠረታዊ መብቱን ሲያስከብር ወይም ሙያዊ ብቃቱን ሲያሳይ "ታርጋ ይለጠፍብኛል" በሚል ስጋት እንዲሸማቀቅ ይደረጋል። ይህ ሥነ-ልቦናዊ ሽባነት ግለሰቡ በሀገሪቱ የለውጥና የልማት ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዳይሆን በማድረግ፣ የማህበረሰቡን ሀገራዊ አበርክቶ ያኮላሻል። 2. የገጽታ ጥቃት 📣📣📣📣📣 ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚያነሳቸውን ፍትሐዊና አመክንዮአዊ ጥያቄዎች በሐቅ መመለስ ሲያቅታቸው፣ ብቸኛው መሸሸጊያቸው ጥያቄውን ሳይሆን ጠያቂውን ማጥቃት ነው። ይህም በኡስታዞችና በመሪዎች ላይ የተመረዙ ትረካዎችን በመርጨት ስማቸውን ማጠልሸት ነው። የዚህ የገጽታ ግድያ ስልት ዋና ዓላማ በመሪውና በተከታዩ መካከል ያለውን "የመተማመን ድልድይ" በመስበር፣ ማህበረሰቡን መሪ አልባና አቅጣጫ የለሽ አድርጎ ማስቀረት ነው። 3. የውስጥ ክፍፍል (ከፋፍለህ ግዛ) ♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦ ማህበረሰቡን በ"ነባር" እና "መጤ" ወይም በ"ሱፊ" እና "ወሃቢ"/«ሰለፊ» በሚሉ ጎራዎች ተቧድኖ በውስጥ ንትርክ እንዲጠመድ የማድረግ ፍላጎትና አካሄድ እንዳላቸው በተደጋጋሚ ተስተውሏል። የሙስሊሞችን ጉዳዮችን በዚህ መነጽር ብቻ እንዲታይ ደጋፊ ሚዲያዎቻቸው ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ታዝበናል። ይህም ፍላጎታቸውን አላረካ ሲልም አንዱን ቡድን ደግፈው በመጅሊስ ጉዳይና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ይመለከተናል በሚል ቃና በግልጽ ሲታገሉም ታይተዋል። ማህበረሰቡ በውስጣዊ ልዩነቶች ላይ እንዲያተኩር ሲደረግ፣ በጋራ በሚሰነዘሩበት በደሎችና ስልታዊ አደጋዎች ላይ አብሮ የመቆም አቅሙ ይዳከማል። ይህ የውስጥ መከፋፈል ማህበረሰቡን ለውጭ ጥቃትና ለፖለቲካዊ መጠቀሚያነት ተገላጭና ምቹ ያደርገዋል። በአጠቃላይ እነዚህ ስልቶች ሲቀናጁ ማህበረሰቡ በገዛ ሀገሩ ላይ ባይተዋርነት እንዲሰማው፣ ለጋራ ጥቅሙ እንዳይቆም እና በሥነ-ልቦና ተሸንፎ ለሌሎች ፍላጎት ተገዥ እንዲሆን የተሰናዱ የወጥመድ ፖለቲካ መገለጫዎች ናቸው። ያልተደነገገው «ወንጀል» እና የቃላት ላቦራቶሪ 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢 በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ውስጥ "ወሃቢ"፣ "አክራሪ" ወይም "ጽንፈኛ" የሚባል የወንጀል ዓይነትም ሆነ ድንጋጌ የለም። እነዚህ ቃላት በሕግ መጻሕፍት ውስጥ የማይገኙ፣ ነገር ግን በፕሮፓጋንዳ ነጋዴዎች ላቦራቶሪ ውስጥ ለሥነ-ልቦና ጦርነት መሣሪያነት የተፈበረኩ የፖለቲካ ማጥቆሪያ ታርጋዎች ናቸው። ዓላማቸውም ማህበረሰቡን በህግ ጥላ ስር ሳይሆን በፕሮፓጋንዳ ጥላቻ ስር እንዲወድቅ በማድረግ የሞራል ልዕልናውን መንካት ነው። የጥላቻ ትረካ ስርጭት ወቅታዊ ስሌቶች 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 የፕሮፓጋንዳ ነጋዴዎቹ የጥላቻ መርዛቸውን የሚረጩባቸው ወቅቶች በዘፈቀደ የሚመረጡ ሳይሆኑ፣ ከፍተኛ ሥነ-ልቦናዊ ድንጋጤ ለመፍጠር ታስበው በሚከተሉት ሦስት ስሌቶች የሚሰናዱ ናቸው፦ 1. የፀጥታ ችግሮችን ለሴራ መጠቀም 🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀 በሀገሪቱ የትኛውም አካባቢ የፀጥታ መታወክ ሲከሰት፣ ያለ ምንም ማስረጃ "የወሃቢ እጅ አለበት" የሚሉ ትረካዎችን በማሰራጨት ሙስሊሙን ከስጋት ጋር በማቆራኘት በሕዝብ ዘንድ ጥርጣሬን መዝራት። 2. የፖለቲካ ጦስ 📦📦📦📦📦 ሀገራዊ የፖለቲካ ውጥረቶች ሲበረቱና የሕዝብ ጥያቄዎች ሲገዝፉ፣ የሕዝቡን ትኩረት አቅጣጫ ለማስለወጥ ሙስሊሙን ማህበረሰብ እንደ ማላከኪያ በመጠቀም የጥላቻ ግንባር መክፈት። 3. በሃይማኖታዊ በዓላት ላይ የሚሰነዘር ጥቃት 📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶 የጁምዓ ተቃውሞዎች፥ እንደ ረመዳን እና ኢድ ባሉ ታላላቅ በዓላት ወቅት የሚከናወኑ በጎ አድራጎቶችን እንኳ "ለጽንፈኝነት ምልመላ" እንደዋሉ በመሳል፣ በበዓላቱ ድምቀት ላይ የጥርጣሬና የፍርሃት ድባብ መፍጠር።የወጣቶች ካውንስል የአባልነት ምዝገባም ሆነ የአደባባይ ኢፍጣሮችም በዚሁ መልኩ ፈርጀዋቸዋል። እነዚህን የ"ትኩረት ጠለፋ" ስልቶች መረዳት፣ ጥቃቱ ሲሰነዘር በስሜት ከመነዳት ይልቅ በዕውቀት ለመመከት ያስችላል። መብት የችሮታ ውጤት ሳይሆን የዜግነት መገለጫ መሆኑን ማመን የጽናታችን ምንጭ ሊሆን ይገባል። ይህ ለምን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ያሳስባል? ✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅ የታርጋ ፖለቲካና የጅምላ ፍረጃ ዛሬ በአንድ ወገን ላይ ቢሰነዘርም፣ ነገ ግን መላውን ሀገርና የዜግነት መብትን የሚንድ የጋራ ጠላት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይህንን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ መመከት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን፣ ለፍትሕና ለሰው ልጅ ክብር የሚቆሙ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀገራዊ ግዴታ ነው። ለዘመናት የጸናው የአብሮነትና የሰላም እሴታችን በጥቂት አንቂዎች የፈጠራ ትረካና በዲጂታል ሴራ ፈጽሞ ሊፈርስ አይችልም። በመሆኑም እውነትን በማንገብ የሐሰትን ወጥመድ በመበጣጠስ ፣ የሁላችንም መሸሸጊያ የሆነችውን ኢትዮጵያን ከፍረጃና ከጥላቻ ፖለቲካ ነፃ ማውጣት ታሪካዊ ኃላፊነታችን ነው። ለዛሬ አበቃሁ። ቸር እንሰንበት!ትት! ወሃቢያ!፦ ውሸትን እውነት የማስመሰል የፕሮፓጋንዳ ወጥመድ 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢 በአሕመዲን ጀበል ✅✅✅✅✅✅ መልዕክቱ በስፋት እንዲዳረስ በሁሉም መንገድ ሼር ያድርጉ። 📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶 በኢትዮጵያ ዲጂታል ምኅዳር የሚታዩት 'ወሃቢያ'፣ 'አክራሪ' እና 'አሸባሪ' የሚሉ የጅምላ ፍረጃዎች ተራ የስድብ ቃላት ሳይሆኑ፤ በጥናት ላይ የተመሠረቱና አእምሮን ለመቆጣጠር የታለሙ የሥነ-ልቦና ጦርነት መሣሪያዎች ናቸው። ይህ ስልታዊ አካሄድ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎችና የታሪክ ባለቤትነት ፍለጋን በማጠልሸት፣ ማህበረሰቡን በሀገር ግንባታ ውስጥ ተገፊና ድምፅ አልባ (Marginalized) ለማድረግ በብዙ አጋጣሚዎች በስፋት የሚታይ የተቀነባበረ ስልት ነው። እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው እውነት፦ ይህ ትንታኔ በሃይማኖቶች መካከል ያለን ነፃ የሐሳብ ልዩነት ወይም ትምህርታዊ ክርክር የሚቃወም አይደለም። ይልቁንም ትኩረቱ ቃላት ከመንፈሳዊ ይዘታቸው ተነጥለው እንደ ፖለቲካዊ የማጥቆሪያ ታርጋ ለሥነ-ልቦና ጦርነት ጥቅም ላይ በሚውሉበት አደገኛ አካሄድ ላይ ነው። የዚህ ስልታዊ ዘመቻ ዋና ዋና ግቦች የሚከተሉት ናቸው፦ 1. አመክንዮአዊ ሽባነትን መፍጠር 🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲 ማህበረሰቡ የቀረበለትን መረጃ በምክንያት ከመመርመሩ በፊት፣ በውስጡ ስር የሰደደ 'የህልውና ስጋት' እና ፍርሃት እንዲነግሥ በማድረግ የማሰብ አቅሙን ማደንዘዝ። በዚህ ስልት፣ የፕሮፓጋንዳው ሰለባ የሆነ ሰው ከእውነት ይልቅ ለስሜታዊ ትረካዎች ተገዥ እንዲሆን ይደረጋል። 2. ጥቃትን ማጽደቅና ማኅበራዊ ፈቃድ ማውጣት፦ ♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦ ተጠቂውን አካል 'አደገኛ' አድርጎ በመሳል፣ ግፍና በደል ሲፈጸምበት ሕዝቡ በዝምታ እንዲያልፍ ወይም የጥቃቱ ደጋፊ እንዲሆን የሚያደርግ የሞራል ድንዛዜ የመፍጠር ሴራ ነው። 3. የማህበረሰቡን ስነ-ልቦናዊ በራስ መተማመን መሸርሸር፦ 🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀 ሙስሊሙ ዜጋ መሠረታዊ መብቶቹን ሲጠይቅ 'ታርጋ ይለጠፍብኛል' በሚል ስጋት ራሱን እንዲያገልና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለው ተሳትፎ እንዲቀጭጭ የሚያደርግ ስውር የባርነት ቀንበር ነው። ይህ የፍረጃ ፖለቲካ ዛሬ በሙስሊሙ ላይ ቢሰነዘርም፣ ሰለባው ግን መላው የኢትዮጵያ ህዝብና የሀገሪቱ አንድነት ነው። ምክንያቱም ጥላቻና ፍረጃ ቦታ ባገኙበት ምድር፣ የዜግነት መብትና የህግ የበላይነት ሊከበር አይችልም። በመሆኑም ይህንን የሐሰት ትርክት መመከት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ድርሻ ብቻ ሳይሆን፣ ለፍትህና ለሰው ልጅ ክብር የሚቆሙ የሁሉም እምነት ተከታዮችና ኢትዮጵያውያን የጋራ የዜግነት ኃላፊነት ሊሆን ይገባል። የጥቃቱ ስልታዊ ይዘት እና የምልክት ጦርነት 🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺 ይህ የሥነ-ልቦና ጦርነት የሚካሄደው የማሰብ ሂደትን በማዛባት "ውሸትን እውነት" የማስመሰል ስልታዊ ተንኮልን በመጠቀም ነው። ሂደቱ ማስረጃን በፍረጃ የመተካት ጥበብ ሲሆን፤ የሚከተሉትን ሦስት የጥፋት ደረጃዎች ይከተላል፦ 1. መረጃን መቆንጸል (Selective Filtering)፦ 🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎 አንድን ክስተት ሙሉ በሙሉ ከመተንተን ይልቅ፣ ለፍረጃው የሚመቸውን ክፍል ብቻ ነጥሎ በመውሰድና አውዱን በማዛባት የጥላቻ ትርጉም መስጠት። ይህም ተደራሲው ግማሽ እውነትን ይዞ ሙሉ ስዕል ላይ እንዲደርስ የሚያደርግ የአእምሮ ጠለፋ ነው። 2. የምልክት ጦርነት ፦ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 በምልክት ጦርነት ውስጥ፣ ሙስሊምነትን የሚገልጹ ሃይማኖታዊ ምልክቶች ከመንፈሳዊ ይዘታቸው ተላቀው የ"አደጋ"፣ የ"ጽንፈኝነት" ወይም የ"መጤነት" መለያ ተደርገው ዳግም ይተረጎማሉ። 3. የሐሰት ስምምነት ማመንጨት ፦ 🍗🍗🍗🍗🍗🍗🍗🍗🍗🍗 በብዙ አጋጣሚዎች እንደሚስተዋለው፣ ጥቂት ግለሰቦች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመጠቀምና በተፅዕኖ ፈጣሪዎች በመታገዝ እነዚህን የፍረጃ ትረካዎች በስፋት እንዲሰራጩ ያደርጋሉ። ይህም ፍረጃው በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ለማስመስል የሚደረግ የተቀነባበረ የዲጂታል ዘመቻ አካል ይመስላል፤ በዚህም ሌሎች "ብዙሃኑ ከተቀበለው ትክክል ቢሆን ነው" በሚል ስሜት ተነድተው የጥላቻው አካል እንዲሆኑ በር ይከፍታል። እነዚህ የፕሮፓጋንዳ ስልቶች ተቀናጅተው በሚሠሩበት ጊዜ፣ ሂደቱ አብዛኛውን ጊዜ የሚከተለውን ግልጽ የሥነ-ልቦና ቅደም ተከተል ይከተላል፦ ፍረጃ → ፍርሃት → ጥርጣሬ → መገለል → ዝምታ → ወደ ዳር መገፋት ይህ ሂደት የሚከተሉትን ደረጃዎች ያልፋል፦ 1. ፍረጃ ፦ 📺📺📺📺 በመጀመሪያ በአንድ ማህበረሰብ ወይም በወካዮቹ ላይ አንድ ስያሜ/ታርጋ ይለጠፋል። 2. ፍርሃት ፦ 🏡🏡🏡🏡 የተለጠፈው ታርጋ በማህበረሰቡ ውስጥ ስር የሰደደ ፍርሃትን ይፈጥራል። 3. ጥርጣሬ፦ 📣📣📣📣 ፍርሃቱ ቀስ በቀስ ወደ እርስ በርስና ወደ ውጭ ጥርጣሬ ይቀየራል። 4. መገለል ፦ 🎁🎁🎁🎁 ጥርጣሬው ማህበረሰቡ ከሌላው ወገን ጋር ያለው ግንኙነት እንዲቋረጥና ማህበራዊ መገለል እንዲፈጠር ያደርጋል። 5. ዝምታ ፦ 🆔🆔🆔 መገለሉ በማህበረሰቡ ውስጥ የራስ-ሳንሱርንና ድምፅን የማጥፋት (ዝምታን የመምረጥ) ስሜት ይወልዳል። 6. ማግለልና ወደ ዳር መገፋት ፦ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 በመጨረሻም ኢላማ የተደረገው ማህበረሰብ ከሀገራዊ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ተገፍቶ ወደ ዳር እንዲወጣ ይደረጋል። የፍረጃ ፖለቲካው ታሪካዊ ዳራ እና አዲሱ አካሄድ 🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒 'ወሃቢያ' የሚለው ፍረጃ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ምኅዳር ውስጥ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን፣ ሙስሊሙን ከሀገራዊ ባለቤትነት ለማግለል ሲለጠፉ የቆዩት ጥረቶች ቅጥያ ነው። ይህ ሂደትም ሁለት ዋና ዋና ምዕራፎችን አልፏል፦ 1. ባዕድ የማድረግ ጥንታዊ ስልት፦ 🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮 ቀደም ባሉ ዘመናት ሙስሊሙን እንደ 'መጤ' ወይም 'ሰርጎ ገብ' አድርጎ የመሳል ስራ ይከናወን ነበር። ዓላማው ሙስሊሙ ከሀገሩ ጋር ያለውን ትስስር እና ለሀገሩ የከፈለውን መስዋዕትነት በመካድ ከሀገራዊ ውሳኔ ሰጪነት የማግለል ጥረት ነው። 2. ዓለም አቀፋዊ ፍረጃን የማላመድ ስልት፦ 🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀 በዚህ ዘመን ደግሞ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚጠቀሰውን 'የጸረ ሽብርተኝነት ጦርነት' አውድን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም፣ የቀድሞው 'ባዕድ የማድረግ' ስልት ከዘመኑ ጋር በሚመች መልኩ በ'ወሃቢዝም'፥ “አክራሪ”፥ “ጽንፈኛ”፥ “አይሲ ስ” ወዘተ በሚሉ ተለውጦ ይተገበራል። ይህ ስያሜ ሙስሊሙን ከሀገር በቀል ማንነቱ ነጥሎ 'የባዕድ አጀንዳ ተላላኪ' አስመስሎ ለጥቃት የሚያመቻች ስልታዊ ጥረት ነው።

Open in Telegram
Views11,200−4%vs avg
Forwards—
Reactions71
Comments—
#51113Text

ትት! ወሃቢያ!፦ ውሸትን እውነት የማስመሰል የፕሮፓጋንዳ ወጥመድ 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢 በአሕመዲን ጀበል ✅✅✅✅✅✅ መልዕክቱ በስፋት እንዲዳረስ በሁሉም መንገድ ሼር ያድርጉ። 📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶 በኢትዮጵያ ዲጂታል ምኅዳር የሚታዩት 'ወሃቢያ'፣ 'አክራሪ' እና 'አሸባሪ' የሚሉ የጅምላ ፍረጃዎች ተራ የስድብ ቃላት ሳይሆኑ፤ በጥናት ላይ የተመሠረቱና አእምሮን ለመቆጣጠር የታለሙ የሥነ-ልቦና ጦርነት መሣሪያዎች ናቸው። ይህ ስልታዊ አካሄድ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ሕጋዊ የመብት ጥያቄዎችና የታሪክ ባለቤትነት ፍለጋን በማጠልሸት፣ ማህበረሰቡን በሀገር ግንባታ ውስጥ ተገፊና ድምፅ አልባ (Marginalized) ለማድረግ በብዙ አጋጣሚዎች በስፋት የሚታይ የተቀነባበረ ስልት ነው። እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው እውነት፦ ይህ ትንታኔ በሃይማኖቶች መካከል ያለን ነፃ የሐሳብ ልዩነት ወይም ትምህርታዊ ክርክር የሚቃወም አይደለም። ይልቁንም ትኩረቱ ቃላት ከመንፈሳዊ ይዘታቸው ተነጥለው እንደ ፖለቲካዊ የማጥቆሪያ ታርጋ ለሥነ-ልቦና ጦርነት ጥቅም ላይ በሚውሉበት አደገኛ አካሄድ ላይ ነው። የዚህ ስልታዊ ዘመቻ ዋና ዋና ግቦች የሚከተሉት ናቸው፦ 1. አመክንዮአዊ ሽባነትን መፍጠር 🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲 ማህበረሰቡ የቀረበለትን መረጃ በምክንያት ከመመርመሩ በፊት፣ በውስጡ ስር የሰደደ 'የህልውና ስጋት' እና ፍርሃት እንዲነግሥ በማድረግ የማሰብ አቅሙን ማደንዘዝ። በዚህ ስልት፣ የፕሮፓጋንዳው ሰለባ የሆነ ሰው ከእውነት ይልቅ ለስሜታዊ ትረካዎች ተገዥ እንዲሆን ይደረጋል። 2. ጥቃትን ማጽደቅና ማኅበራዊ ፈቃድ ማውጣት፦ ♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦ ተጠቂውን አካል 'አደገኛ' አድርጎ በመሳል፣ ግፍና በደል ሲፈጸምበት ሕዝቡ በዝምታ እንዲያልፍ ወይም የጥቃቱ ደጋፊ እንዲሆን የሚያደርግ የሞራል ድንዛዜ የመፍጠር ሴራ ነው። 3. የማህበረሰቡን ስነ-ልቦናዊ በራስ መተማመን መሸርሸር፦ 🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀🔀 ሙስሊሙ ዜጋ መሠረታዊ መብቶቹን ሲጠይቅ 'ታርጋ ይለጠፍብኛል' በሚል ስጋት ራሱን እንዲያገልና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለው ተሳትፎ እንዲቀጭጭ የሚያደርግ ስውር የባርነት ቀንበር ነው። ይህ የፍረጃ ፖለቲካ ዛሬ በሙስሊሙ ላይ ቢሰነዘርም፣ ሰለባው ግን መላው የኢትዮጵያ ህዝብና የሀገሪቱ አንድነት ነው። ምክንያቱም ጥላቻና ፍረጃ ቦታ ባገኙበት ምድር፣ የዜግነት መብትና የህግ የበላይነት ሊከበር አይችልም። በመሆኑም ይህንን የሐሰት ትርክት መመከት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ድርሻ ብቻ ሳይሆን፣ ለፍትህና ለሰው ልጅ ክብር የሚቆሙ የሁሉም እምነት ተከታዮችና ኢትዮጵያውያን የጋራ የዜግነት ኃላፊነት ሊሆን ይገባል። የጥቃቱ ስልታዊ ይዘት እና የምልክት ጦርነት 🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺 ይህ የሥነ-ልቦና ጦርነት የሚካሄደው የማሰብ ሂደትን በማዛባት "ውሸትን እውነት" የማስመሰል ስልታዊ ተንኮልን በመጠቀም ነው። ሂደቱ ማስረጃን በፍረጃ የመተካት ጥበብ ሲሆን፤ የሚከተሉትን ሦስት የጥፋት ደረጃዎች ይከተላል፦ 1. መረጃን መቆንጸል (Selective Filtering)፦ 🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎 አንድን ክስተት ሙሉ በሙሉ ከመተንተን ይልቅ፣ ለፍረጃው የሚመቸውን ክፍል ብቻ ነጥሎ በመውሰድና አውዱን በማዛባት የጥላቻ ትርጉም መስጠት። ይህም ተደራሲው ግማሽ እውነትን ይዞ ሙሉ ስዕል ላይ እንዲደርስ የሚያደርግ የአእምሮ ጠለፋ ነው። 2. የምልክት ጦርነት ፦ 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 በምልክት ጦርነት ውስጥ፣ ሙስሊምነትን የሚገልጹ ሃይማኖታዊ ምልክቶች ከመንፈሳዊ ይዘታቸው ተላቀው የ"አደጋ"፣ የ"ጽንፈኝነት" ወይም የ"መጤነት" መለያ ተደርገው ዳግም ይተረጎማሉ። 3. የሐሰት ስምምነት ማመንጨት ፦ 🍗🍗🍗🍗🍗🍗🍗🍗🍗🍗 በብዙ አጋጣሚዎች እንደሚስተዋለው፣ ጥቂት ግለሰቦች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመጠቀምና በተፅዕኖ ፈጣሪዎች በመታገዝ እነዚህን የፍረጃ ትረካዎች በስፋት እንዲሰራጩ ያደርጋሉ። ይህም ፍረጃው በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ለማስመስል የሚደረግ የተቀነባበረ የዲጂታል ዘመቻ አካል ይመስላል፤ በዚህም ሌሎች "ብዙሃኑ ከተቀበለው ትክክል ቢሆን ነው" በሚል ስሜት ተነድተው የጥላቻው አካል እንዲሆኑ በር ይከፍታል። እነዚህ የፕሮፓጋንዳ ስልቶች ተቀናጅተው በሚሠሩበት ጊዜ፣ ሂደቱ አብዛኛውን ጊዜ የሚከተለውን ግልጽ የሥነ-ልቦና ቅደም ተከተል ይከተላል፦ ፍረጃ → ፍርሃት → ጥርጣሬ → መገለል → ዝምታ → ወደ ዳር መገፋት ይህ ሂደት የሚከተሉትን ደረጃዎች ያልፋል፦ 1. ፍረጃ ፦ 📺📺📺📺 በመጀመሪያ በአንድ ማህበረሰብ ወይም በወካዮቹ ላይ አንድ ስያሜ/ታርጋ ይለጠፋል። 2. ፍርሃት ፦ 🏡🏡🏡🏡 የተለጠፈው ታርጋ በማህበረሰቡ ውስጥ ስር የሰደደ ፍርሃትን ይፈጥራል። 3. ጥርጣሬ፦ 📣📣📣📣 ፍርሃቱ ቀስ በቀስ ወደ እርስ በርስና ወደ ውጭ ጥርጣሬ ይቀየራል። 4. መገለል ፦ 🎁🎁🎁🎁 ጥርጣሬው ማህበረሰቡ ከሌላው ወገን ጋር ያለው ግንኙነት እንዲቋረጥና ማህበራዊ መገለል እንዲፈጠር ያደርጋል። 5. ዝምታ ፦ 🆔🆔🆔 መገለሉ በማህበረሰቡ ውስጥ የራስ-ሳንሱርንና ድምፅን የማጥፋት (ዝምታን የመምረጥ) ስሜት ይወልዳል። 6. ማግለልና ወደ ዳር መገፋት ፦ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 በመጨረሻም ኢላማ የተደረገው ማህበረሰብ ከሀገራዊ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ተገፍቶ ወደ ዳር እንዲወጣ ይደረጋል። የፍረጃ ፖለቲካው ታሪካዊ ዳራ እና አዲሱ አካሄድ 🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒 'ወሃቢያ' የሚለው ፍረጃ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ምኅዳር ውስጥ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን፣ ሙስሊሙን ከሀገራዊ ባለቤትነት ለማግለል ሲለጠፉ የቆዩት ጥረቶች ቅጥያ ነው። ይህ ሂደትም ሁለት ዋና ዋና ምዕራፎችን አልፏል፦ 1. ባዕድ የማድረግ ጥንታዊ ስልት፦ 🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮🏮 ቀደም ባሉ ዘመናት ሙስሊሙን እንደ 'መጤ' ወይም 'ሰርጎ ገብ' አድርጎ የመሳል ስራ ይከናወን ነበር። ዓላማው ሙስሊሙ ከሀገሩ ጋር ያለውን ትስስር እና ለሀገሩ የከፈለውን መስዋዕትነት በመካድ ከሀገራዊ ውሳኔ ሰጪነት የማግለል ጥረት ነው። 2. ዓለም አቀፋዊ ፍረጃን የማላመድ ስልት፦ 🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀🏀 በዚህ ዘመን ደግሞ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚጠቀሰውን 'የጸረ ሽብርተኝነት ጦርነት' አውድን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም፣ የቀድሞው 'ባዕድ የማድረግ' ስልት ከዘመኑ ጋር በሚመች መልኩ በ'ወሃቢዝም'፥ “አክራሪ”፥ “ጽንፈኛ”፥ “አይሲ ስ” ወዘተ በሚሉ ተለውጦ ይተገበራል። ይህ ስያሜ ሙስሊሙን ከሀገር በቀል ማንነቱ ነጥሎ 'የባዕድ አጀንዳ ተላላኪ' አስመስሎ ለጥቃት የሚያመቻች ስልታዊ ጥረት ነው። የፍረጃው መሪ ተዋናዮች እና አጀንዳዎቻቸው 🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨🚨 በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ "ወሃቢ"፣ "አክራሪ" ወይም "አሸባሪ" የሚሉ የፍረጃ ቃላትን ደጋግመው በሚለጥፉ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ በብዙ አጋጣሚዎች የሚስተዋል አንድ ተደጋጋሚ ድርጊት አለ፤ ይኸውም አንዳንድ የተደራጁ አካላት በብሔርና በእምነት ፖለቲካ ስም የተቀነባበሩ የዲጂታል ዘመቻዎችን ሲያካሂዱ ይስተዋላል። እነዚህን የፍርጃ ቃላት የሚፈጥሩ፣ መልእክቶችን የሚለጥፉና የሚያጋሩ ጥቂት ግለሰቦችን የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ስንመለከት የሚከተሉትን ሁለት ግልጽና ልዩ መለያዎችን እናያለን፦ 1. የፖለቲካ አርማ ፦ 🏀🏀🏀🏀🏀 በብዙዎቹ የእነዚህ አካላት ገጾች ላይ የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ ምልክቶች አሉ፤ ለምሳሌ የፋኖ ደጋፊነትን የሚያሳዩ ምልክቶችና የጽንፈኛ ብሔርተኝነት መፈክሮች በስፋት ሲንጸባረቁ ይታያል። 2. ሃይማኖታዊ ሽፋን ፦ 🚛🚛🚛🚛🚛🚛 ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ጋር የተቆራኙ ምልክቶችን እንደ መሸፈኛ በመጠቀም፣ የእምነቱን የሰላምና የአብሮነት እሴቶች የማይወክል የፖለቲካ ጥላቻን የሚረጩ ናቸው። በፍርሃት ላይ የተመሠረተ የሕዝብ ንቅናቄ 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 እነዚህ አካላት የጋራ መለያቸው ማንኛውንም ሃይማኖታዊና ብሔራዊ ስሜት ቀስቃሽ ጉዳዮችን በመጠቀም በሕዝብ ዘንድ ፍርሃትን መፍጠር እና በዚያ ፍርሃት አማካኝነት ሕዝብን ለራሳቸው ስውር አጀንዳ ማሰለፍነው። በዚህ አካሄድ ላይ ተሰማርተው የምናገኛቸው ሦስት ተዋናዮች ናቸው። እነርሱም፦ 1. ጽንፈኛ የብሔር ፖለቲከኞች ፦ 💥💥💥💥💥💥💥💥💥 በብዙዎቹ የእነዚህ አካላት ገጾች ላይ የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ ምልክቶች አሉ፤ ለምሳሌ፦ የፋኖ ደጋፊነትን የሚያሳዩ አርማዎች፣ ፎቶዎችና የጽንፈኛ ብሔርተኝነት መፈክሮች በስፋት ሲንጸባረቁ ይታያሉ። ይህም ፖለቲካዊ አጀንዳን ከሃይማኖታዊ ፍረጃ ጋር በማቀላቀል ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለጥቃት ኢላማ የማድረግ ስልት አካል ይመስላል። እነዚህ አካላት በዛ የሚሉቱ በአማራ በተለይ በፋኖ ጉዳይ እንንቀሳቀሳለን የሚሉ ሲሆኑ ስልታቸውም ሙስሊሙን ማህበረሰብ "የኦሮሞ ብልጽግና ስርዓት ስልታዊ አጋር" አድርጎ በመፈረጅ ለጥቃት ኢላማ ሲያደርጉት ይታያሉ።ከዚህ የተነሰ «ኦሮሙማ» እና «ስልጤ» የሚሉ ታፔላዎችን በመለጠፍ ሲፈርጁም ይታያል። 2. በእምነት ስም የሚንቀሳቀሱ አክራሪዎችና፦ 🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀🚀 እነዚህ አካላት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ምልክቶችን እንደ መስቀልና የቅዱሳን ሥዕላትን እንደ መሸፈኛ በመጠቀም፣ የእምነቱን የሰላምና የአብሮነት እሴቶች የማይወክል የፖለቲካ ጥላቻን ይረጫሉ። ዋና ዓላማቸውም ታሪካዊ የበላይነትን ለማስጠበቅ ሲሉ የሙስሊሙን ማህበረሰብ መሠረታዊ የመብት ጥያቄዎች እንደ "ሕልውና ስጋት" አድርጎ ማቅረብ ሲሆን፣ ይህም ሙስሊሙን እንደ "መጤ" ወይም "የባዕድ አስተሳሰብ ተላላኪ" አድርጎ በመፈረጅ ከሀገር ባለቤትነት የማግለል ስልታዊ አካሄድ ነው። እነዚህ አካላት ቤተ ክርስቲያንን እንደ ብቸኛ የሀገር ባለቤት አድርገው በመሳል የሚረጩት ይህ መርዛማ ትርክት፣ ተራው አማኝ የጥላቻ መልእክቱን እንደ ሃይማኖታዊ እውነት እንዲቀበለው በማድረግ ለዘመናት የቆየውን የሕዝቦች አብሮነት የሚሸረሽርና በዜጎች መካከል የጥርጣሬ ግንብ የሚገነባ አደገኛ ስልት ነው። 3. ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የ አካውንቶች ፦ 🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎🍎 በውጭ ሀገር የሚገኙና በዛ ያሉ ተከታዮች ያሏቸው የቲክቶክ፣ የቴሌግራም እና የፌስቡክ «መምህር»ና «አንቂዎች» የሚባሉ የዘመቻው ሞተሮች ናቸው። እነዚህ አካላት የተከታዮቻቸውንና የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ "በኢትዮጵያ የእስልምና አክራሪነት ስጋት ደቅኗል" የሚል አጀንዳ በመቅረጽ የጥላቻ ንግግሮችን በማቀናበር ሙስሊሞች ላይ ጥርጣሬና ፍርሃት እንዲነግስ ይተጋሉ። የጠላት ፈጠራ ፋብሪካ፦ ስልታዊ ኪሳራ እና የማግለል ሴራ 🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡🏡 የእነዚህ አካላት ሌላኛው አደገኛው ጠባይ ይታይባቸዋል።ማንም ይሁን ማን በማህበራዊ ሚዲያ ምህዳር ዉስጥ እነርሱ የሚያዜሙትን ካላዜመ፥ በለቅሶ ፖለቲካቸው ላይ ከእነርሱ ጎን ተሰልፎ አብሮ ካላለቀሰ፥ ወይም ደስታውንም ሆነ ሀዘኑን እነርሱ ካሰመሩት አካሄድ ወጥቶ በራሱ መንገድ ጉዳዩ ላይ አቋሙን ከገለጸ ወይም ጥያቄ ካነሳ ፥አልያም ስልታዊ አካሄዳቸውንና ሴራቸውን ካወቁባቸው ወይም ድጋፍ ካነፈጓቸው ወዲያውኑ "የአማራ ጠላት" ወይም "የኦርቶዶክስ ጠላት" የሚሉ የታፔላዎች ተመዘው ይለጠፍበታል። በዚህ አካሄዳቸው የተነሳ ለአማራ ሕዝብ እና ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን በቀንና በሌሊት በርካታ «ጠላቶችን» እየፈጠሩ ይገኛሉ። ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻቸው እንደታዘብኩት በርካታ አካላትን ጠላት በሚል ፈርጀው ዘምተውባቸዋል። በአማራ ክልል ውስጥ የቅማንትን፣ የአገውን፣ የወሎ ኦሮሞን፣ አማራ ሙስሊሙንና የክልሉን መንግሥት (በብአዴን ስም)፤ በወሎ ሕዝብ ጉዳይ የሚንቀሳቀሱ አካላትን፥ ከክልል ውጭ ደግሞ መላው የኢትዮጵያ ሙስሊምን ("ወሃቢ" በሚል)፣ የትግራይ ኤሊትንና ፓርቲን፣ እንደሕዝብ የኦሮሞንና የስልጤን ሕዝብ፣ በመተከል ያሉ የቤኒሻንጉል ብሔረሰብ አባላትን፥ከፓርቲ ደግሞ የብልጽግና ፓርቲን፥ኢዜማን፥ በጠላትነት ፈርጀዋል። በግለሰብ ደረጃ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን፥ ጀውሃር መሀድን፥ እኔ አሕመዲን ጀበልን ጨምሮ በርካቶችን ሲፈርጁ ታዝቤያለሁ። እዚህ ላይ አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ማንሳት ያስፈልጋል። ለመሆኑ በቀን 24 ሰዓት ስድብን፣ ፍረጃንና ጠላትን ማምረት እነርሱ ቆመንለታል ለሚሉት ለአማራም ሆነ ለኦርቶዶክ እምነት ተከታይ ሕዝብ ምን ጥቅም ያስገኝላቸዋል? የሕዝቡን ዘላቂ ችግሮች ይፈታል ወይስ ይበልጥ ያባብሳል? ከወዳጅ ይልቅ ጠላትን ማምረት የፖለቲካ ብስለት ሳይሆን ስልታዊ ኪሳራ ነው። ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ትክክለኛው ስልታዊ ጥቅም የሚገኘው ከሌሎች ማህበረሰቦች ጋር አጋርነትና ጥምረትን በመፍጠርና ድጋፍ በማሰባሰብ እንጂ ጠላትን በማብዛት አልያም ስድብ የሚያዋጡ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመፍጠር አይደለም። ከየትኛውም ወገን ይሁን ከየት የሚሰነዘርባቸውን ጥቃቶች ለመመከትና የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ትኩረትና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ የሌሎችን ወገኖች አጋርነትና ድጋፍ ማግኘት እጅግ ወሳኝ ነው። በተጨማሪም ሁሉንም ወገን በጠላትነት መፈርጅና ማግለል የፍትሕ ጥያቄያቸው ድጋፍ እንዳያገኝ በማድረግ ለብቻቸው ተነጥለው ለጥቃት እንዲጋለጡ በማድረግ የከፋ ጉዳት ያመጣል። እነዚህን የጥላቻ ትረካዎች የሚያመርቱ፣ በጅምላ የሚፈርጁና በየቀኑ ጠላት የሚፈጥሩ አካላት በማንኛውም መልኩ ሊደገፉ፣ ሊበረታቱ ወይም የትግሉ አካል ሊደረጉ አይገባም። የእነሱ ድርጊት የሕዝቡን ስቃይ የሚያራዝም እንጂ መፍትሔ የሚያመጣ ባለመሆኑ፣ ይህ አካሄድ የጠላት ተግባር እንጂ የወዳጅ እርምጃ ሊባል አይችልም። ከዚህም ባለፈ፣ በሌሎች ሃይማኖታዊ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ተቋማትና እንቅስቃሴዎች ላይ በማተኮር እነሱን ለማጥቃት ጊዜን ማጥፋት ፈጽሞ ትክክለኛ አካሄድ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም በሌሎች ላይ ስታተኩር ሌሎችም በአንተ ላይ እንዲያተኩሩ በሩን እየከፈትክ መሆኑን መዘንጋት የለብህም። ሌሎች ላይ በከፈትከው ግንባር ልክ አጸፋው ወደ አንተ እንደሚመለስና ለራስህ ተቋማትና እሴቶች ስጋት እንደሚሆን የታወቀ ነው። የጥቃቱ ኢላማዎች እና ስልታዊ ስኬቶች 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ይህ የተቀነባበረ ዘመቻ በዘፈቀደ የሚሰነዘር ሳይሆን፣ ማህበረሰቡን 'መሪ አልባ' በማድረግ በምሁራንና በተቋማት ላይ እምነት በማሳጣት ስልታዊ ውድመት ለማድረስ የታለመ ነው። ፕሮፓጋንዳ ነጋዴዎቹ የሚከተሉትን ሦስት ዋና ዋና ስኬቶች ለመቀዳጀት ይጥራሉ፦

Open in Telegram
Views10,700−9%vs avg
Forwards—
Reactions119
Comments—
#51112Text
Views10,400−11%vs avg
Forwards—
Reactions362
Comments—
#51111Video

ቤተ ክርስቲያን በቅኝ ግዛት ተይዛለች‼ ======================= (ፓትሪያሪኩ እውነታውን አፈረጡት!) (አጋልጥ ⬅️ ክፍል: 5️⃣6️⃣) || ✍️ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለአመታት አፍነው የያዙትን እውነታ በአደባባይ አስጥተውታል። በሲኖዶሱ ጉባዔ ላይ ቤተ ክርስቲያን በቅኝ ግዛት ስር እንደምትገኝና፤ ቀኝ ገዢዋም በስሟ የተዋቀረው ማኅበር (በዋናነት ማኅበረ ቅዱሳን) እንደሆነ ተናግረዋል። ቡድኑ የቤተ ክርስቲያኗን ንብረትና ክብር ዘርፏል ብለዋል። አቡነ ማትያስ ይህን እውነታ በአደባባይ ካሰጡት በኋላ፤ በርካታ ሰዎች ቂም ይዘውባቸዋል። ይህን እውነታ ከተናገሩ ቆይተዋል፤ ዛሬ ላይ ስለነ ሞዓ ተዋህዶ፣ ክርስቲያን ህብረት፣ የዓለም ብርሐንና ስለመሳሰሉት የተለያዩ ማኅበራት እውነታውን ቢያፈርጡት ደግሞ፤ ከኃላፊነታቸው ያነሷቸዋል። ▫️ አቡነ ማትያስ በነዚህ ማኅበራትና ጽንፈኛ ብሔርተኞች፤ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከባድ ጫና አሁንም እየተደረገባቸው ነው። ያኔ በትግራይ ጦርነት ወቅት የትግራይን ሲኖዶስ እንዲያወግዙ ጫና ተደርጎባቸዋል። በጎድን ለምን ለትግራዋዮች ድምፅ ሆናችሁ፣ ዘረኛ ናችሁ… እያሉ በአደባባይም ዘልፈዋቸዋል። ▫️ በአሁኑ ወቅትም ከባድ ጫና እንዳለባቸው የውስጥ ምንጮች ይናገራሉ። ይሄውም ያኔ ለትግራዩ ጦርነት ድምፅ እንደሆንከው ሁሉ፤ ዛሬ በአማራ ክልል ጦርነት ጊዜ ለምን ዝምታን መረጥክ? ተብለው በዘረኝነት እያሙ ጫና እያደረጉባቸው እንደሆነ እያዬን ነው። ከርሳቸውም ባሻገር እንደ ጥቅል ሲኖዶሱን ያለመቀበል ሰበካና ዘመቻ ውስጥ ለውስጥና አልፎ አልፎም በይፋ ሲነገር እያየን ነው። በተለይም የዓለም ብርሐንና መሰል ማኅበራት፤ የሲኖዶሱ ተጠሪ መንፈስ ቅዱስ መሆን ሲገባው፤ ከጊዜ በኋላ ለፓትሪያሪኩ ተደርጓልና ሰው አናመልክም፣ ለሰው አንመራም የሚል ተቃውሞ እየተስፋፋ ነው። ታዲያ መንግስት እነዚህን ከሲኖዶሱም፣ ከፓትሪያሪኩም በላይ የሆኑ ጠርዘኛ ሰዎችን ለምን አደብ አያሲዛቸውም⁉️ ጳጳሱ አሁንም በይፋ ቢቃወሙ፤ ምናልባትም ሌላ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ሊከቷቸው ይችላል። ጥበቃ ይደረግላቸው‼ በዚህ ንግግራቸው ራሱ እንደ አዲስ ብዙ ግልምጫ ሳያደርሱባቸው አይቀሩም። || t.me/MuradTadesse

Open in Telegram
Views12,600+7%vs avg
Forwards—
Reactions194
Comments—
#51110Text

በዚያ መሬት ት/ቤት ቢከፈት የአካባቢው ኗሪ ሙስሊም ስለሆነ የመማር እድል ያገኛል ብለው አስበው ነበር። ለአብነትም በጅማ ዞን ‹‹ደነባ›› ከተማ ላይ ት/ቤት ይከፈትበት ዘንድ ‹‹አባ ቦረና አባመጫ›› በ1960 ዓ.ል 25 ሺህ ካሬ ሜትር መሬታቸውን ለትምህርትና ሥነ-ጥበብ ሚኒስቴር በነጻ ሰጥተው ነበር። (አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ታህሳስ 12 ቀን 1960) የሃይማኖት ነጻነትን በጠበቀ መልኩ ትምህርትን የማግኘት ጥያቄ ከዋንኛዎቹ የሙስሊሞች ጥያቄዎች መካከል አንዱ ነበር። ለዚህም ነበር በሚያዝያ 1 ቀን 1966 ዓ.ል ለጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ እንዳልካቸው መኮንን እንዲህ ሲሉ ያመለከቱት፡- ‹‹በየትምህርት ቤቱ የሚሰጠው የሃይማኖት የሞራል ትምህርት የአንዱን ክፍለ ሃይማኖት የተከተለ እንደመሆኑ እስላሞች ልጆቻቸው ሃይማኖታቸውን እንዳይለውጡ በመፍራት ወደየትምህርት ቤቶቹ ሳይልኳቸው በመቅረቱ በዘመናዊ ትምህርት ያለንን ተካፋይነት አዳክሞታል፡፡›› (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም፣ ማኅደር ቁጥር I.E.S 2400/01/4) ለሙስሊሙ ትምህርት ተገቢውን ሥፍራ ሳይሰጡ አፄ ኃይለ ሥላሴ በ1966 የሕዝቡና ተማሪው ንቅናቄ ግብዓተ መሬቱ ተፈፀመ። ሙስሊሙን ከትምህርት ለማራቅ የነበረው የሤራና የእቀባው መልኩን ቀይሮ በአለባበስና በሰላት እያመካኘ በየስድስት ወሩ የሚነሳ እንቅፋት ሆኖ እንደቀጠለ ነው።

Open in Telegram
Views12,200+4%vs avg
Forwards—
Reactions162
Comments—
#51109Text

አፄ ኃይለ ሥላሴና ለሙስሊሙ ቦታ ያልነበረው የትምህርት ሥርዓታቸው 💥💥💥🔴🔴🔴⭕⭕⭕💥💥💥🔴 በአሕመዲን ጀበል፥ ክፍል 3 ✅✅✅✅✅✅✅✅ ኢትዮጵያዊም ሙስሊምም መሆን ሳይቻል ሲቀር 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢 በአገር ውስጥ የመማር እድል ያላገኙት ሙስሊሞች ስደትን መረጡ። የዜግነት ፓስፖርት ተነፍገው በእግር ወደ ሱዳን፣ ከዚያም ወደ ግብጽ አቀኑ። በዚያም በአል-አዝሐር ዩኒቨርሲቲ የመማር እድል አገኙ። በገዛ አገራቸው ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ የተነፈጉትን የመማር እድል በባዕድ አገር በግብጽ አገኙ። ሆኖም ፓስፖርት የላቸውም። ድጋፍም የሚያደርግላቸው የለም። ለክርስቲያኑ ተማሪዎች መንግሥት ፓስፖርትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ይሰጥ ነበር። መብት በልመናና በልምምጥ ስለማይገኝ ለመታገል ወሰኑ። ‹‹እንደሌሎች ተማሪዎች እኛም መብት ይኑረን›› የሚል ጥያቄ ይዘው ግብጽ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አመሩ። በወቅቱ ለነበረው የኤምባሲው ጉዳይ አስፈጻሚ አቶ ደመቀ ጥያቄያቸውን አቀረቡ። ጥያቄውን ካቀረቡት መካከል የነበሩት ሐጂ በሽር ዳዉድ እንዲህ ይተርኩልናል፡- ‹‹ፊቱን ጥቁር ጭምድድ አድርጎ ከእግራችን እስከ አናታችን ተመለከተን። ማመልከቻውን መልከት አለና ወዲያው ሁለት እጆቹን በሁለት ጆሮዎቹ ላይ ጠቀጠቀ። ‹ግሩም! ግሩም! ጆሮ የማይሰማው የለም! እስላም ለመንግሥት ግብር ይከፍላል እንጂ እንዴት መንግሥትን ቀለብ ይክፈለን ብሎ ይጠይቃል?!› አለና የቢሮውን ዘበኛ ወዲያው በደውል ጠራ። ‹እባክህ እነዚህን ምንነታቸው ያልታወቀ ፍጡሮች በቶሎ አስወጣልኝ!› አለው።›› (ሐጂ በሽር ዳውድ፣ በሕይወቴ ሂደት ዙሪያ፤ ገጽ 105) ተማሪዎቹ በንዴት ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመለሱ። ጉዳዩ በሁሉም ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ዘንድ ተሰማ። ሁሉም በንዴት ለመታገል ወሰኑ። ወዲያውኑ ዐብደላ ዐብዱረህማን የኢኽዋነል ሙስሊሚንን ጋዜጠኞች ጠራና በተማሪዎች መኝታ ክፍል ፎቶ ግራፍ አስነሳቸው። ዜናው ከነጎስቋላ ገጽታቸው ጋር በጋዜጣ ታተመ። የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት መሸበር ያዘ። የኤምባሲው ጉዳይ አስፈፃሚ ከስፍራው ተነሳ። በ1949 ፊታውራሪ ታፈሰ ዋና አምባሳደር ሆኖ መጣ፤ አሁንም ተማሪዎቹ ጥያቄያቸውን ይዘው ከኤምባሲው ተገኙ። ሳይሸበሩና አጎንብሰው ሳይሰግዱለት ቆፍጠን ብለው ወደ ውስጥ ዘለቁ። የአምባሳደሩን ምላሽ ሐጂ በሽር እንዲህ ይተርኩልናል፡- ‹‹‹እኔ እኮ በኢትዮጵያ ዘውድ መጫን እንጂ ሌላ ሥልጣን ምንም አልቀረኝም። ታዲያ እነዚህ ምንነታቸው ያልታወቁ እስላሞች መሬት ሳይስሙ በድፍረት እንዴት ያነጋግሩኛል?› በማለት ዘበኛውን ጠራ። ‹አስወጣልኝ!› አለው። ቀጠል አድርጎ ‹ስለጥያቄያችሁ ከአስር ቀን በኋላ እዚያው ባላችሁበት እንድታውቁ ይደረጋል። እዚህ ግን እንዳትመጡ› አለን።›› (ሐጂ በሽር ዳውድ፣ በሕይወቴ ሒደት ዙሪያ፣ ገጽ 107) አምባሳደሩ ካሰናበታቸው በኋላ ሁሌም እንደ ሚደረገው ‹‹ዋና አንቀሳቃሽ ናቸው›› ያላቸው ላይ እርምጃ እንዲወስድ ለፖሊስ ጻፈ። እነርሱም፡- 1ኛ) በሽር ዳዉድ 2ኛ) ዐብዱልከሪም ሙሐመድ ኑር 3ኛ) ዐብዱረሒም ዩሱፍ 4ኛ) ዐሊ ሐይደር 5ኛ) ሸኽ ዐብዱል ሐዲ ነበሩ። የግብጽ ፖሊስ ግለሰቦቹን ጠራቸው። ቃልም ተቀበላቸው። ጉዳዩን ቀደም ብሎ በጋዜጣ አንብበው ነበርና ጉዳዩን በዝርዝር ሲሰሙ ‹‹ይህስ አነስተኛ ጥያቄ ነው፤ ሕግን ተከትላችሁ በሰላም ጠይቁ›› ብለው አሰናበቷቸው። የተማሪዎቹ ቁጥር ጨምሮ መቶ ገደማ ሆነው ኤምባሲ ደረሱ። ዉዱእ አድርገው እዚያው በኤምባሲው ሳሎን ውስጥ ሶላት በጀማዓ (በሕብረት) እየሰገዱ አምባሳደሩን ይጠብቁት ያዙ። አምባሳደሩ ማምሻውን መጣ። ሲያያቸው ደንገጥ አለ። እየተንቀጠቀጠ፡- ‹‹እናንተ ልጆች ስሙ! አሁን በፖሊስ ባስይዛችሁ የግብጽ ፖሊሶች መጥፎዎች ናቸው። የአገራችንን ስም ያጠፋሉ፤ ጥያቄያችሁን እኔ ብቻዬን ልፈጽምላችሁ አልችልም። የአስር ቀን ጊዜ ስጡኝና ጃንሆይን በቴሌግራም ልጠይቅ። እርሳቸው ስጥ ካሉኝ እሰጣችኋለሁ። በአጠቃላይ ውሳኔውን እነግራችኋለሁ። አሁን እባካችሁ ከኤምባሲው ውጡልኝ›› አለ። ወጡ። ሙስሊም ተማሪዎች በሰገዱበት ክፍል በማግስቱ በግብጽ የነበሩትን ኢትዮጵያዉያን ቀሳውስት ጠርተው ‹‹የረከሰውን ለማጥራት›› በሚል ጸበል ረጩ። ዕጣንም አጨሱ። ተማሪዎቹም በሆነው ነገር ተናደዱ። ሆኖም በ10ኛው ቀን በቀጠሮው ለመሄድ ወሰኑ። በጠዋት ሄደው ኤምባሲውን ሞሉት። መቶ ይሆናሉ። ፊታውራሪ ታፈሰ (አምባሳደሩ) ሊያነጋግራቸው ፈቃደኛ አልሆነም። ከጸሐፊዎቹ አንዱን ‹‹ሂድና አናግራቸው›› ሲል ላከ። የካይሮው ኤምባሲ ፍጥጫ ⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕ ተማሪዎቹ ተናደዱ። ጸሐፊው ሊያናግራቸው ሲመጣ ኡስታዝ ዓሊ ሐይደር በጥፊ አጮለው። ጸሐፊው በጩኸትና በእምባ ታጅቦ ወደ አምባሳደሩ ተመለሰ። ኡስታዝ ዓሊ ሐይደር በኤምባሲው የነበረውን ቴሌፎን አንስቶ ወለል ላይ ሰባበረው። ረብሻ ተፈጠረ። ፖሊስ ተጠራ። መቶ የሚደርሱ ፖሊሶች በሦስት ኮሎኔሎች እየተመሩ መጡ። ኤምባሲውን ከበቡ። ኮሌኔሎቹ በቁጣ ‹‹ውጡ!›› ሲሉ ተማሪዎቹን ተቆጡ። ሐጅ በሽር እንዲህ ይተርኩልናል፡- ‹‹እኛም በድፍረት ‹አንወጣም! ለአምባሳደራችን የፓስፖርትና ቀለብ ጥያቄ አቅርበናል። መልስ እሰጣችኋለሁ ስላለን ነው የመጣነው። መልስ ካልሰጠን አንወጣም፤ ይኸው እንደምታዩን መልስ ከመጠበቅ ሌላ ሰው አልገደልንም፤ ረብሻ አልፈፀምንም፤ ይህም የኛ የመንግሥት ቢሮ ነው፤ እናንተ ለምን ገባችሁ?› አልናቸው። (ሐጂ በሽር ዳውድ፤ ገጽ 110) ኮሎኔሎቹ ደንገጥ አሉና ሊያሸማግሉን ፈለጉ። ወደ አምባሳደሩ ገቡና ‹ክቡር ሆይ! እነዚህ ልጆች ናቸው። ደህና ቃል እንኳን ሰጥተህ መልሳቸው!› አሉት። እርሱም ‹እኔ የጠራኋችሁ እንድ ታስወጡልኝ እንጂ እንድታደራድሩኝ አይደለም። ከነዚህ ጋር ለመደራደር ማዕረጌ አይፈቅድም፤ አልቀበላችሁም ከቢሮዬ ውጡልኝ!› አላቸው። ወጡ። ፖሊሶቹ ተማሪዎቹን ‹እናንተ ምንም ጥፋት የለባችሁም። ጥያቄያችሁ ሕጋዊ ነው። አምባሳደራችሁ ደንቆሮና የማይረባ ሰው ነው። አስወጡልኝ ብሎ ጠርቶን መጥተናል። ሕግ ያስገድደናል፤ እባካችሁ ውጡልን› ሲሉ ጠየቋቸው። ተማሪዎቹ በፖሊስ ታጅበው ‹የኢትዮጵያ ሕዝብና የሙስሊሙ ጠላት የሆነው ኃይለ ሥላሴ ከነአጫፋሪዎቹ ይውደም! ንጉሥ ፋሩቅ ለዘላለም ይኑሩ!› እያሉ ወጡ። ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዱ። አምባሳደሩ ‹አምስቱ ዋና አስተባባሪዎች ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ይላኩልኝ› ሲል ጠየቀ። አምስቱ ሲቀሩ ሌሎቹ ተለቀቁ። የተፈቱት ተማሪዎች ጉዳዩን በአዝሐር ዩኒቨርሲቲ የውጭ ተማሪዎች ጉዳይ ኃላፊ ለሆኑት ሸኽ ዐብዱል ሐሚድ ነገሩ። ሼኹም ወደፖሊስ ጣቢያ መጡና፡- ‹‹ወንጀሌ ሙስሊም መሆኔ ነው!›› 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ‹‹አል-አዝሐር እንደ ቫቲካን ራሱን የቻለ መንግሥት ነው። ለነዚህ ተማሪዎች መታወቂያ፣ መኖሪያ ቤትና ቀለብ መድቦ በነፃ የሚያስተምራቸው አል-አዝሐር ነው እንጂ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አይደለም። እንዲሁም ፓስፖርት ስጠን ሲሉት እምቢ ማለት ኢትዮጵያዉያን አይደላችሁም ማለት ነው። ኢትዮጵያዉያኖች ካልሆኑ ደግሞ ምኔ ናቸው ብሎ ነው ይያዙልኝ የሚለው?›› በማለት በቁጣ ተናገሩ። የተለያዩ ባለስልጣናት በልጆቹ ጉዳይ ላይ ከተነጋገሩ በኋላ ቃል እንዲሰጡ ተደረገ። ‹‹ወንጀለኛ ነህ? አይደለህም?›› በሚል ተጠየቁ። አራቱ ‹‹ወንጀለኛ አይደለሁም!›› ሲሉ መለሱ። አምስተኛ ሐጅ በሽር ዳዉድ ነበሩ። እንዲህ ይተርካሉ፡- ‹‹የኔ ተራ ደረሰና ከመርማሪው ኮሎኔሎች አንዱ ወደኔ እያመለከተ ‹ያ ወለድ (አንተ ልጅ) ወንጀለኛ ነህ አይደለህም?› ብሎ በፈገግታ ጠየቀኝ። ቃል ተቀባዮቹ ሦስት ኮሎኔሎች ነበሩ። የውጭ ተማሪዎች ኃላፊ የሆነው ሸኽ ዐብዱልሐሚድም ለኛ ዋስ ለመሆን መጥቶ ከመርማሪዎች አጠገብ ተቀምጧል። እኔም በእልህ እየተንቀጠቀጥኩና እምባ እየፈሰስኩ ‹እኔ ወንጀለኛ ነኝ› አልኩት። መርማሪ ፖሊሶቹና ሸኽ ዐልዱልሐሚድ እጅግ ደነገጡ።ወደኔ አፍጥጠው ብዕራቸውን አሾሉ። ወረቀታቸውን እያመቻቹ ‹‹ምንድነው ወንጀልህ?› አሉኝ። እኔም ‹ወንጀሌ ኃይለ ሥላሴና የሱ አጫፋሪዎች ታላቅ ኃጢአት ነው የሚሉት ወንጀል ነው - ሙስሊም መሆኔ!›› አልኳቸው›› (ሐጂ በሺር ዳውድ፣ በሕይወቴ ሒደት ዙሪያ፣ ገጽ 111) ፖሊሶቹና ሼኹ ስሜታቸው ተነክቶ በእጅጉ አለቀሱ። እምባቸውን በመሐረብ እየጠረጉ ወደ (ወጣት) በሽር ዳዉድ ሄደው አቀፉት፤ ሳሙት። በአንድነት ሆነው ‹‹በአላህ ስም እንምላለን፤ ወንጀለኛው ኃይለ ሥላሴ ነው እንጂ አንተ አይደለህም›› አሉ። በሸኹ ዋስትና ሁሉም ተፈቱ። (ሐጂ በሺር ዳውድ፣ በሕይወቴ ሒደት ዙሪያ፣ ገጽ 111) ተማሪዎቹ በመፈታታቸው አምባሳደሩ ተናደደ። ሆኖም ምንም ማድረግ ሳይቻል ቀረ። ሳይማሩና ሳይነቁብን በልዩነት ባሕር ውስጥ እንዲዋኙ አድርጓቸው 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢 አፄ ኃይለ ሥላሴ ሙስሊሙን በትምህርት ብቻ ሳይሆን በሁለንተናዊ መልኩ እንዴት መምታት እንደሚቻል የሚያጠና ኮሚቴ በ1948 ዓ.ል አዋቅረው ነበር። ኮሚቴው ጥናት አድርጎ ሪፖርት አቀረበ። ሪፖርቱም ከውጭ ሲታይ የሕዝብን የኑሮ እድገት የሚያሻሽል የሚመስል፣ ነገር ግን ዓላማው ሙስሊሙን ከትምህርት የሚያርቅ፣ ከኢስላም አውጥቶ ወደ ክርስትና የሚያስገባ፣ ኢስላማዊ ደዕዋን የሚገታና ሁለገብ ሤራ የሚዶለትበት ተቋም በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ደረጃ እንዲቋቋም ተወሰነ። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጥር 21 ቀን 1949 ‹‹የሕዝባዊ ኑሮ እድገት ሚኒስቴር›› ተብሎ ተቋቋመ። በቦርድ አባልነትም ለኢስላም ባላቸው ጥላቻና ለንጉሡ ባላቸው ታማኝነት ባለሥልጣናት ተመረጡ። ከመካከላቸውም አቡነ ቴዎፍሎስ የተሰኙ ጳጳስን ጨምሮ የአገሪቷ የጦር ኤታማዦር ሹም፣ የተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚኒስትር ዴኤታዎች በቦርድ አባልነት ተካትተዋል። (ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጽሐፍት ኤጀንሲ፣ ማህደር ከተ.14.02) ቦርዱ ሙስሊሙን ሃይማኖት ለማስለወጥ ከሥላሴ ኮሌጅ ጋር በትብብር መሥራት ጀመረ። የትምህርት ሚኒስቴር ቦርዱ ሰብሳቢ የነበሩትና በፀረ-ሙስሊም አቋማቸው የሚታወቁት አቶ አካለ ወርቅ ሐብተ ወልድ የሕዝባዊ ኑሮ እድገት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ተደርገው ተሾሙ። ሙስሊሙ በወሳኝ የአገሪቱ ጉዳዮች ሚና እንዳይኖረው፣ እንዳይማር፣ ከተማረም በሙስሊምነቱ አንገቱን ደፍቶ፣ ሃይማኖቱን ደብቆ ተሸማቆ እንዲማር ተደረገ። ‹‹ሙስሊሙ ቢማርና በሃይማኖቱ የሚኮራ ከሆነ የክርስቲያኑን የበላይነት ለማስቀጠል በግልጽም ሆነ በሥውር ለሚያደርጉት ዘመቻዎች እንቅፋት ይሆናል›› ብለው ስለሠጉ ሳይማር እንዲሁ እንዲኖር ተወሰነ። ይህም ብቻ ሳይሆን እንዲሁ ከሚኖር እርስ በርስ እየተጣላ፣ አንድነት ሳይኖረው፣ ግራ ተጋብቶና እየተጠራጠረ እንዲኖር ሤራ ተሸረበ። ሙስሊም የሆኑት የአፋር እና የኢሳ ጎሳ አባላት እርስ በርስ እየተጣሉ ይገዳደላሉ። ሐጂ በሽር ዳዉድ (አላህ ይማራቸውና) ወደ አካባቢው ገዢ ዘንድ ሄደው ለምን መፍትሔ እንደማይፈለግ ሲጠይቁ እንዲህ የሚል ምላሽ ነበር የተሰጣቸው፡- ‹‹ከሰሜን ቀይ ባህር ከምዕራብ በሱዳን ድንበር አድርጎ በመንዝ ተራራ ሥር አልፎ እስከ ኬኒያ በሚያደርሰው ረባዳና ቆላማ ምድር ላይ ሰፍሮ የሚኖረው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠረው ሕዝብ በሙሉ እስላም ነው። ይህ ሕዝብ መጋደሉ ቀርቶ ሰላም ቢሆን፣ ቢማርና ዘላን መሆኑ ቢቀር እርስ በእርሱ አንድነትን እየፈጠረ በዙሪያው ካሉት እስላም አገሮች ጋር ግንኙነት ያደርጋል። ክርስቲያን ለሆኑት ነገሥታትና የክርስቲያን ደሴት ለሆነችው ኢትዮጵያ እጅግ አደገኛ ይሆናል። እንዲሁ እየተጋደሉ ሳይማሩና ተከፋፍለው በዘላንነት ብቻ ግብር እየከፈሉ እንዲኖሩ ከነገሥታትና ከበላይ ባለሥልጣኖች ተጠንቶ የተሰጠ መመሪያ አለ። ጋዜጠኛ ነኝ እያልህ ይህን እንዴት አታውቅም?›› (ሐጂ በሽር ዳውድ በሕይወቴ ሒደት ዙሪያ፣ 2003፣ ገጽ 38) ለዚህም ነበር በሙስሊሙ ላይ የተሸረበባቸውን ሴራ የተረዱ ሙስሊሞች ባገኙት አጋጣሚ ስለአንድነቱ ተረድቶ በሕብረት እንዲቆም ያስተምሩ የነበሩት፡፡ ሙስሊሙን ለማነቃቃትና እንዲጠናከር በመሞከሩ ኢስላማዊ መንግስት በመመስረትና በሀገሪቷ ላይ አደጋ ለማድረስ በማሴር ተወንጅሎ የተዘጋው ‹‹የሰላም ማህበር›› ይህንን አጀንዳ ትኩረት ከሰጠባቸው ነጥቦች ውስጥ ነበር፡፡ ማህበሩ በሐምሌ 14 ቀን 1956 ባዘጋጀው የመዉሊድ በዓል ዝግጅቱ ላይ ፊታውራሪ አመዴ ለማ ስለአንድነት ትኩረት በመስጠት እንዲህ ሲሉ ተናግረው ነበር፡- ‹‹አንድነት ሀብት ነው፤ አንድነት ኃይል ነው፤ አንድነት ዕውቀት ነው፤ አንድነት ሃይማኖት ነው፤ በጠቅላላው አንድነትና ሕብረት ለሰው ልጆች ለዛሬም ሆነ ለነገው አስፈላጊ የሆኑ ጠቃሚ ነገሮች ሁሉ የሚገኙበት ምንጭ መሆኑን ነብዩ ሙሐመድ ደህና አድርገው አስተምረውናል፡፡ የሰው ልጆች መብት በትክክል እንዲጠበቅ፣ አንዱ የሌላውን መብት አክብሮ በዲሞክራሲ መንፈስና በእኩልነት ችሎታውና ዝንባሌው በሚፈቅደው መጠን በሐቅ እየሠራ እንዲኖር አስፈላጊ የሆኑት መብትና ነፃነት በዚያ ታሪካዊ በሆነ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ሰፍረው ሙሐመዳዉያን (ሙስሊሞች) ሁሉ ሕገ-ፉርቃን እንዲሆኑ ለተወዳጁ ነብይ ሙሐመድ ከአላህ ተሰጥተዋል፡፡› (ፊታውራሪ አመዴ ለማ፣ የሕይወት ታሪኬ፣ ገጽ 272) በአገር ውስጥ የመማር ዕድል ያገኙት ጥቂት ሙስሊሞች ብቻ ነበሩ። እነርሱም ቢሆኑ በሙስሊምነታቸው አንገታቸውን ደፍተው የሃይማኖት ነፃነት ተነፍገው ቀጠሉ። በየትምህርት ቤቱ መስገድ ከባድ ኃጢአት ነበር። ጅልባብ እንኳ ማድረግ የማይታሰብ ነበር። ምክንያቱም የነበረው መንግሥት ጸረ-ኢስላም እና ሙስሊሞች ሃይማኖታቸው እንደሚያዛቸው እምነታቸውን ጠብቀው እንዲማሩ የማይፈቅድ ነበርና። የተወሰኑ ወላጆች ወንዶች ልጆቻቸውን ከነጫናው እየተሳቀቁ ለማስተማር ተገደው ነበር። ሴቶቹን ግን ያለ ኢስላማዊ አለባበስ ማስተማር ከባድና የማይሞከር ነበር። በወቅቱ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩት ሼኽ ኸሊፋ ዐብደላህ እንዲህ ብለው ነበር ‹‹እኔ የሦስት ወንዶችና የሰባት ሴቶች ልጆች አባት ነኝ።ወንዶች ልጆቼን በሚገባ አስተምሬያለሁ። ሴቶች ግን አልተማሩም። ምክንያቱም ኢስላም ተገላልጦ መማርን ስለማይፈቅድ ነው።›› "የሃይማኖት ነጻነት እንዳከበርኩ እወቁልኝ!" 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 የሚገርመው ይህን ሁሉ ግልጽና ሥውር ጸረ-ኢስላም ሤራ እየፈፀመ የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የሃይማኖት ነፃነትን እንዳከበረ ይለፍፍ ነበር። ‹‹የሃይማኖት ነፃነት በኢትዮጵያ›› የሚል መጽሐፍም በዚያው በጭቆና ዘመን በዓረብኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ አሳትሟል። ጭቆናውና ሙስሊሞችን መግፋት በግልጽ እየታየ ‹‹የሃይማኖት ነጻነት አከበርኩ›› እያሉ ይለፍፉም ነበር። ‹‹በተለያየ የሙስሊሙ አካባቢ ት/ቤት ቢከፈትና ሙስሊሙ የሃይማኖት ነፃነት ኖሮት ቢማር›› የሚለው የሁሉም ጥያቄ ነበር። አንዳንድ ሙስሊሞች መሬታቸውን ለትምህርት ሚኒስቴር በነፃ ሰጥተው ትምህርት ቤት ይከፈትበት ዘንድ ይጠይቁ ነበር።

Open in Telegram
Views14,000+19%vs avg
Forwards—
Reactions168
Comments—
#51108Text
Views14,900+27%vs avg
Forwards—
Reactions121
Comments—