Account

Posts of ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ

newest first

#3725Text

ሁሉም ያልፋል ትዝብት ይቀራል። እልህና ዲን ሲቀላቀሉ ነገራቶች ከቀን ወደ ቀን ውስብስብ እየሆኑ ይሄዳሉ እንጂ አይስተካከሉም! ጉዳዩን ከእልኸኝነት ከስሜታዊነት ወጥታችሁ ከዲን አንጻር ብቻ ብትመለከቱት በቀላሉ አንድ ሰአት ባልሞላ ውስጥ መስተካከል የሚችል ጉዳይ ነው። يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا [📗 ሱረቱ አል-ኒሳእ - 59 ] እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡ :-ወደ ራሳችሁ ተመለሱ የካፊሮች መሳለቂያ ከመሆን ራሳችሁን ጠብቁ ሙሥሊም አጀንዳ አቀባይ እንጂ አጀንዳ ተቀባይ አይደለም። ✍https://t.me/mukamil12

Open in Telegram
Views1,080−15%vs avg
Forwards—
Reactions31
Comments—
#3702Video
Views1,970+55%vs avg
Forwards—
Reactions58
Comments—
#3699Text
Views1,710+34%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#3693Text

የተመለስነው ልባችን ተሰብሮ ነው! - ባለፉት ጥቂት ቀናት በጉራጌ ዞን እነሞርና ኤነር ወረዳ ጉስባጃ፣ ኤግዶሳይ፣ ቦርጠኖ፣ ኬኤንድ፣ ተርሆኝና እገበኝ ተዘዋውረን ሙስሊም ወገኖቻችንን ማነጋገር የቻልንበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር ። ወደድንም ጠላንም  ልንቀበለው ማንችለው ሽንፈት ነው ያለው፡፡ 1.  በአንዲት ትንሽ መንደር ኤግዶሳይ ብቻ 300 የሚጠጉ ልጆቻችን ከፍረዋል። 2. በቦርጠኖ ከነበሩት 90 ሙስሊም ቤተሰቦች  50ው ሙሉ በሙሉ ከፍሯል ፤ ቀሪ 40 ቢሆኑ ቤቶች ውስጥ እስልምናቸውን ጠብቀው የቀጠሉት በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ብቻ ናቸው። በአንድ በቤት ውስጥ  8 ልጆች ካሉ 6ቱ ወይም 7ቱ ከፍረዋል፡፡ 3. አንድ የ80 ዓመት አባት ስምንቱም ልጆቻቸው ከፍረውባቸው  ለዓመታት ብቻቸውን ላለመክፈር  ታግለዋል። በመጨረሻ ሲሞቱ አስከሬናቸው እንኳ ወደ ተወለዱበት መንደር አልተመለሰም። 4. ሌላ አንድ አባት በልጆቻቸው  የሚደርስባቸው የክፈር ጫና ሲበረታ  «ማንቆርቆሪያዬንና መስገጃዬን ይዤ ዛሬ አንድ መስጂድ ነገ አንድ መስጂድ እያልኩ የቀረኝን እድሜ እጨርሳለሁ» አሉ። 5. አንድ ዩኒቨርሲቲይ  የተመረቀ ልጅ  ቤተሰቦቹ በሙሉ ከፍረው አልቀው እናቱ እንዳትከፍርበት ብቻ ከተማ በተሸለ ደሞዝ መስራት እየቻለ ገጠር ተቀምጧል፡፡ ለምን ከተማ ወጥተህ አትሰራም ስንለው  እናቴን ይወስዱብኛል ሲል መልሷል፡፡ እውነት ለመናገር  ብዙ ህፃናት አሊፍ-ባና ቁል ሁወላሁ አሀድ እንኳ በወጉ ሳያውቁ ያድጋሉ። በብዙ መንደሮች ቋሚ ኡስታዝ የለም። በእገበኝ ከ10 መስጂድ 8ቱ ተዘግተዋል።  አ  2 ወይም 3 ኪሎ ዱቄ ከአክፍሮ ሀይሎች  ለማግኘት ሲባል በረመዳን እናቶች ሙሉ ቀን ይሰለፋሉ፡፡  ምክንያቱ ግልፅ ነው፡ ከ10 ሰው 7ቱ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይኖራል፤ ልጆች ዲን የሚያስተምራቸው አካል አጥተዋል፤ እኛም  ርቀናቸዋል። በአካባቢው ያሉ ወላጆቹ በአንድ ድምፅ « እርዱን፣ ቋሚ ኡስታዝ ብቻ ስጡን፣ ልጆቻችንን ከስራ አስቀርተን እንልካለን» ብለውናል። ኡስታዝ አብዱራህማን ሲሸኙን ያሉን ቃል «ሄዳችሁ ሄዳችሁ ቆም አትበሉ፤ በአንድ ጊዜ ብልጭ ብላችሁ ድርግም አትበሉ።» ወገኖቻችን የሚጠይቁት ብዙ አይደለም፡ ለልጆቻቸው ኡስታዝ፣ የሚማሩበት መድረሳና በችግር ጊዜ ከጎናቸው የሚቆም ወንድም ነው። ምን ይደረግ? ✍ ኡስታዝ ቃል አሚን

Open in Telegram
Views1,490+17%vs avg
Forwards—
Reactions29
Comments—