Posts of Mizan Tepi University Students Union Channel
በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ካምፓስ የ2019 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የGC Birthday መርሐ ግብር በተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ክንውኖች ተከበረ። መርሐ ግብሩ ተማሪዎቹ በቆይታቸው የነበራቸውን አንድነትና አብሮነት ይበልጥ ያደመቁበት እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲውና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ያላቸውን አክብሮት የገለጹበት ድንቅ አጋጣሚ ነበር። The GC Birthday program for the 2019 E.C. graduating class at Mizan-Tepi University, Tepi Campus, was celebrated with various entertaining and educational activities. The event was a wonderful occasion where the students further highlighted the unity and togetherness they shared during their stay, as well as expressed their respect for the university and the local community.
Open in TelegramForwarded from MTULSU(Mizan Tepi University Law students Union👩🎓👨🎓
📢 አዲስ ነገር የክርክር መድረክ ዝግጅት ተጠናቋል! የ4ኛ ዓመት የሕግ ተማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ያዘጋጁትን የክርክር መድረክ ዝግጅት አጠናቀው፣ የክርክሩን ቀን ማለትም ሰኞን በታላቅ ጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ። በዚህ አጋጣሚ በተለይ የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት የሕግ ተማሪዎች ከዚህ የክርክር መድረክ ልምድና እውቀት እንድታገኙ፣ እንዲሁም የሕግ እውቀታችሁን እንድታሳድጉ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን። የሕግ እውቀትን ለማስፋት፣ የአመክንዮ አቅማችንን ለማጠናከር እና ሐሳባችንን በማስረጃ ለመደገፍ ጉጉት ያላችሁ እርሶም ከዚህ ወሳኝ መድረክ እንዳትቀሩ ተጋብዘዋል! ሰዓቱንና ቦታውን በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል። ⚖️ ሕግን በእውቀት! መልካም ምሽት! Join us @MTULSU
Open in TelegramForwarded from Mizan Tepi University MTU
የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ከቴፒ ካምፓስ አስተዳደር ሠራተኞች ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው ። ሚቴዩ፣ ህዳር 18/2019 ዓ.ም ክቡር ዶ/ር ዋቆ ገዳ ከዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ሠራተኞች ጋር የጀመሩትን ተከታታይ ውይይት ዛሬም በመቀጠል፣ በቴፒ ካምፓስ ከሚገኙ አስተዳደር የሥራ አስፈጻሚዎች፣ የቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ጋር እየመከሩ ሲሆን በዚህ መድረክ ፕሬዚዳንቱ በተቋሙ አበይት የሥራ እንቅስቃሴዎች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በማተኮር ከካምፓሱ ማኅበረሰብ ጋር በሰፊው ይነጋገራሉ።
Open in TelegramAnnouncement We urge all students at M.T.U. Main Campus who have registered for the sports competition across various sports categories, as well as students who wish to register, to be present at the stadium tomorrow, Saturday, 19/03/2019 (Ethiopian calendar) at 3:00 AM (local time / 9:00 AM standard time). Reminder / Notice We announce that any student who does not show up tomorrow will not participate in the competition.
Open in Telegramማስታወቂያ በሚ.ቴ.ዩ main campus ምትገኙ ተማሪዎች በሙሉ ለእስፖርት ውድድር በተለያዩ እስፖርት ዘርፎች የተመዘገባቹ እና መመዝገብ ምትፈልጉ ተማራዎች ነገ ቅዳሜ ማለትም በቀን 19/03/2019 ከጥዋቱ 3:00 ላይ እስታድየም እንድትገኙ እናሳስባለን:: ማሳሰቢያ ነገ ያልተገኘ ማነኛውም ተማሪ ውድድሩ ላይ የማይሳተፍ መሆኑን እንገልፃለን::
Open in Telegram