🔷ለበለጠ መረጃ የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮችን ይቀላቀሉ። 👇ቴሌግራም፡-👇 http://t.me/mkpublicrelation 👇ፌስ ቡክ👇 :-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/ 👇ዩ ቲዩብ፡-👇 http://www.youtube.com/user/EOTCMK ማኅበረ ቅዱሳን
Open in TelegramPosts of ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት በአርሲ ሃይማኖት ተኮር ጥቃት እና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። ማኅበረ ቅዱሳን በአርሲ ሃይማኖት ተኮር ጥቃት እና በልዩ ልዩ አካባቢ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ለመርዳት የሚያደርገውን የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጥሪ በመቀበል በአዲስ አበባ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት፣ የሰ/ት/ቤቱን አባላትና ተማሪዎችን በማስተባበር የ100ሺ ብር ድጋፍ አድርጓል። ሰ/ት/ቤቱ ከተመሠረተ 65 ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን በርካታ መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ማኅበረ ቅዱሳን ሰ/ት/ቤቱ ላደረገው ድጋፍና ትብብር እያመሰገነ በአገልግሎት በሚያገናኙ ተግባራት በጋራ ተባብሮ መስራቱን አጠናክሮ እንዲቀጠል ያሳስባል። ይህን አርአያ በማድረግ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያላችሁ ማኅበራት እና ሰ/ት/ቤቶች ሰብዓዊነት የሁላችንም ኃላፊነት ስለሆነ አጋርነታችሁን በማሳየት ድጋፍ እንድታደርጉ ሲል ጥሪውን ያቀርባል። ✝️ክርስቲያናዊና_ወገናዊ ድጋፍ ለማድረግ፡ 🔷CBE:1000309803648 #Ahadu Bank: 0025393810901 🔷Wegagen Bank: 0837331610101 #Bank of Abyssinia: 37235458 🔷Awash Bank: 01329817420400 #Dashen Bank: 5171156335011 🔷በመላው _ዓለም የምትኖሩ ፡- በወገን ፈንድ https://www.wegenfund.com/mknu #በተጨማሪ_ዜፊ (Zeffy) ሲስተምን ይጠቀሙ‼️ https://zeffy.com/en-US/donation-form/81579462-9df4-46a1-b801-01d1d2e69e0d
Open in Telegram🔷አሁኑኑ ለራስዎና ለቤተሰብዎ ዕጣ ትኬቱን በ100ብር ብቻ በመግዛት ዕድልዎትን ይሞክሩ፡፡ 🔷አካውንት ቁጥር-🔷 #ንግድ ባንክ_1000003774957 #አሐዱ ባንክ_0003488720301 #አቢሲኒያ ባንክ_15203196 #አዋሽ ባንክ_013040800017700 #ዳሽን ባንክ_0888872166011 ✝️ ባሉበት ሆነው ትኬት ለመቁረጥ ከላይ በተቀመጠ ስልክ ይደውሉልን! 🔷ለበለጠ መረጃ የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮችን ይቀላቀሉ። 👇ቴሌግራም፡-👇 http://t.me/mkpublicrelation 👇ፌስ ቡክ👇 :-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/ 👇ዩ ቲዩብ፡-👇 http://www.youtube.com/user/EOTCMK ማኅበረ ቅዱሳን
Open in Telegramበ1970 ዓ.ም በደብረ ፀሐይ ሳሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ያን የተመሠረተው ሐመረ ሕይወት ሰ/ት/ቤት የቃሊቲ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል በራሱ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እስከተመራበት 2005 ዓ.ም በጋራ ሁለቱም አድባራት ላይ መንፈሳዊ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ከምሥረታው ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያሉትን አባላት የቤ/ክን ትምህርት በተከታታይ የሚያስተምርበት የተደራጀ እና ዘመናዊ የአገልግሎት አዳራሽ አልነበረውም፡፡ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የቦታ ማጣት እንቅፋት ሆኖ ወጣቶችን ከሰ/ት/ቤት እንዳያጠፋቸዉ በማሰብ ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ በማቋቋም የሥነ ሕንጻ ባለሙያ የሆኑ አባላትን በማደራጀት በ2009 ዓ.ም ማገባደጃ ሥራውን በእግዚአብሔር ቸርነት አንድ ብሎ የጀመረው ሐመረ ሕይወት ሰ/ት/ቤት በወቅቱ ካዝናው ውስጥ 30,000 ብር ብቻ ነበረው፡፡ ታዲያ በዚች ትንሽ ገንዘብ መነሻነት ይህን የመሰለ እጅግ ውብ ሕንጻ ሠርቶ ለምርቃት ያበቃበትን ትልቁን ምሥጢር የሰ/ት/ቤቱ ዋና ጸሓፊ መ/ር ታደለ በሪፖርቱ ላይ እንዲህ ሲል አቅርቧል፡፡ሙያ ያለቸው አባሎቻችን ሙያቸውን በነጻ ሳይሰስቱ ባይሰጡን፣ ደመዎዝተኞች በየጊዜው የወር ደመወዛቸውን ለሕንጻው ገቢ ባያደርጉ ፣ነጋዴዎች ከትርፋቸው ከፍለው ባይለግሱ ፣ተማሪዎች ውድ ጊዜያቸውን እና ጉልበታቸውን ሳይነፍጉ ባይተባበሩን ኖሮ ከ65,000,000(ስድሳ አምስትሚሊዮን ብር) በላይ የሚያስፈልገውን ሕንጻ 32 ሚሊዮን ብር በማይሞላ አናጠናቅቅም ነበር በማለት ከእግዚአብሔር ቸርነት ባሻገር የበኩላቸውን የደረጉትን ሁሉ በማክበር የምስክር ወረቀት እና የማስታወሻ ስጦታ በመስጠት አመስግኗል፡፡ ✝️በዕለቱ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሕይወት አሽኔ መኮንን የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት በማስተላለፍ በሕንጻው ሦስተኛ ወለል ላይ ከ400-500 ሰው የሚችል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቀድሞ የሰ/ት/ቤት አባል የነበረች ነገር ግን በድንገተኛ አደጋ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ ሆና በምትሠራበት በድንገተኛ ያረፈች አያንቱ ግርማዬ (ዓመተ ገብርኤል) ስም መታሰቢያ ይሆናት ዘንድ ሙሉ ወጭ በመሸፈን ያሠሩትን ወላጆቿን በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የካናዳ እና የአሶሳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እጅ የክብር ካባ ሸልመዋል፡፡ አስተዳዳሪው በመልእክታቸው ላይ የሐመረ ሕይወት ሰ/ት/ትቤት አባላት በእውቀት የበሰሉ ፣በአመራር የዘመኑ፣በክርስትና ሕይወታቸው የተመሰከረላቸው መሆናቸውን በመግለጽ በሰ/ት/ቤት ውስጥ ማደግና ማገልገል ጥቅሙ ከቤ/ክን አልፎ ለሀገርና ለወገን የሚተርፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ ሰ/ት/ቤት ከማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ እና ከስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ጋር በመተባበር ከከፋና ኮንታ ሀገረ ስብከት የተመለመሉ 30 ሠልጣኞችን ለአንድ ወር በማሠልጠን ለገጠሪቱ ቤ/ክን የሚያደርገውን አጋርነት በተግባር ያሳየ አንጋፋ ሰ/ት/ቤት ነው፡፡ በዕለቱ የተመረቀው ሕንጻም ከዚህ የበለጠውን ለማገልገል የሚያተጋ መሆኑን በቦታዉ ከነበሩ ሥራ አመራር አካላት ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የካናዳና የአሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሰ/ት ቤቱ እስካሁን ለሠራዉ ሥራ አመስግነዉ በቀጣይም ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና ከክፍለ ከተማው መዋቅር አገልጋዮች ጋር በመተባበር ብርቱ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው በማስገንዘብ የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡ 🔷ለበለጠ መረጃ የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮችን ይቀላቀሉ። 👇ቴሌግራም፡-👇 http://t.me/mkpublicrelation 👇ፌስ ቡክ👇 :-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/ 👇ዩ ቲዩብ፡-👇 http://www.youtube.com/user/EOTCMK ማኅበረ ቅዱሳን
Open in Telegramወጣት ኦርቶዶክሳውያን መንፈሳዊ እውቀት ተመግበው የሚታነጹበት የሰ/ት ቤት ሕንጻ ተመረቀ። ✝️በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክን ሐመረ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ወጣቶችን በሥነ ምግባር ኮትኩቶ የሚያሳድግበት ሁለገብ ባለ ሦስት ወለል ሕንጻ ኅዳር ፲፫ 2019 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የካናዳ እና የአሶሳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣የሀገረ ስብከቱ መምሪያ ኃላፊዎች እና የተለያዩ የክፍለ ከተማው ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ፣የሰንበት ት/ቤቱ አመራሮች ምእመናን በተገኙበት በድምቀት አሥመርቋል፡፡
Open in Telegramየገና ስጦታ ለየኔታ እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!! 🔷ማኅበረ ቅዱሳን ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶችን ለማጠናከር የሚውል በየዓመቱ የገና ስጦታ ለየኔታ በሚል ልዩ የድጋፍ ማሰባሰቢያ እና የስጦታ መርሐ ግብር ከኅዳር 15 - ታኅሣሥ 30 ቀን 2019 ዓ.ም አዘጋጅቷል፡፡ እርስዎም በዚህ ድጋፍ በመሳተፍ የድርሻዎትን እንዲወጡ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ✝️ ኑ አብረን እንስራ ለውጥም እናመጣለን ማኅበረ ቅዱሳን 🔷ድጋፍዎን፡- #ኢ/ን/ባንክ ፡- 1000003549805 ✝️አሐዱ ባንክ ፡- 0025344310901 # አቢሲኒያ ባንክ ፡- 15376007 ✝️ ወጋገን ባንክ ፡- 0042921130101 # አዋሽ ባንክ፡- 013521172004500 🔷ለበለጠ መረጃ 0963010101 ይደውሉ!!
Open in Telegram🔷አሁኑኑ ለራስዎና ለቤተሰብዎ ዕጣ ትኬቱን በ100ብር ብቻ በመግዛት ዕድልዎትን ይሞክሩ፡፡ 🔷አካውንት ቁጥር-🔷 #ንግድ ባንክ_1000003774957 #አሐዱ ባንክ_0003488720301 #አቢሲኒያ ባንክ_15203196 #አዋሽ ባንክ_013040800017700 #ዳሽን ባንክ_0888872166011 ✝️ ባሉበት ሆነው ትኬት ለመቁረጥ ከላይ በተቀመጠ ስልክ ይደውሉልን! 🔷ለበለጠ መረጃ የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮችን ይቀላቀሉ። 👇ቴሌግራም፡-👇 http://t.me/mkpublicrelation 👇ፌስ ቡክ👇 :-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/ 👇ዩ ቲዩብ፡-👇 http://www.youtube.com/user/EOTCMK ማኅበረ ቅዱሳን
Open in Telegram፭.ጾመ ፊልጶስ፡-ሐዋርያው ፊልጶስ በአፍራካ አውራጃዎች በመዘዋወር ወንጌልን እየሰበከና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ፣ ያመኑትን እያጸና፣ ያላመኑትን እየመለሰ ቆይቶ በሰማዕትነት ዐረፈ። ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ቢሹ አጡት፤ ተሰውሮባቸው ነበርና። እግዚአብሔር እንዲገልጥላቸው ሱባኤ ይዘው በጾም በጸሎት ቢለምኑት በሦስተኛው ቀን ተገልጦላቸዋል። እነሱም በክብር አሳረፉት። ጾሙን ግን እስከ ጌታ ልደት ቀን ድረስ ጹመውታል። በዚህም ምክንያት ጾመ ፊልጶስ እየተባለ ይጠራል። ፮. ጾመ ማርያም፡-እመ አምላክ፣ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ወልደ እግዚአቤሔርን እንደምትወልደው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቢያበሥራት ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ፀንሼ፣ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ›› በማለት በትሕትና ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጹማ ነበርና ጾመ ማርያም ተብሏል። እንግዲህ ከላይ ያየናቸው ቀደምት ቅዱሳን በዚህ ጾም ተጠቅመውበታል። እኛም አምላካችን ምሕረት ይሰጠን ዘንድ እንዲሁም ከቅዱሳኑም በረከት እናገኝ ዘንድ ልንጾመው ግድ ነው። ✝️ውድ ኦርቶዶክሳውያን ስንጾም እነዚህን ነገሮች ልብ ማለት ይገባል። ሀ. በእምነት ሁነን መጾም፦ እግዚአብሔር ይሰማኛል፤ ዋጋ አገኝበታለሁ ብለን እያመንን መሆኑን ማስተዋል ይገባል። ለ. በፍቅር መጾም፦ ከወንድሞችና ከእኅቶች ጋር በመስማማትና በአጠቃላይ ክፋት በማይታሰብበት ልቡና ሆኖ መጾም ያስፈልጋል። ሐ. ንስሓን፣ ጸሎትን፣ ምጽዋትን፣ ይቅርታን ገንዘብ በማድረግ መጾምን አለብን። መ. ከክፉ ነገር ሕዋሳቶቻችንን ዐቅበን (ጠብቀን) መጾም፦ ዐይን፣ ጆሮ፣ እጅ፣ እግር፣ አፍ ይጹም ብሎ እንደነገረን ቅዱስ ያሬድ እኛም ከክፉ ሁሉ ተከልክለን እንዲህ ባለው አኳኋን ከጾምን ቸሩ አምላካችን ምሕረቱን ይልክልናል። በመጨረሻም ስንጾም በመከራ ውስጥ ስላሉት ወገኖቻችን እያሰብን እንዲሁም ሁሉም ነገር መልካም የሚሆነው ሀገር ሰላም ሲሆን ነውና ለሀገራችን ሰላምን፣ ለሕዝቦቿም ፍቅር፣ አንድነትን እያሰብን አምላካችንን እንለምነው። የራሔልን ዕንባ የተቀበለ አምላካችን ጾማችንን ይቀበልልን፤ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር! 🔷ለበለጠ መረጃ የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮችን ይቀላቀሉ። ቴሌግራም፡- http://t.me/mkpublicrelation ፌስ ቡክ :-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/ ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK ማኅበረ ቅዱሳን
Open in Telegramጾመ ነቢያት በድጋሜ የተለጠፈ ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውን ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ድረስ ይጾማል። እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን ሲል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ ከንጽሕተ ንጹሓን፣ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም መወለዱን፣ ወደ ግብጽ መሰደዱን፣ በዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርተ ወንጌልን ማስታማሩን፣ በመጨረሻም በሞቱ ሞትን ማጥፋቱን፣ ትንሣኤውንና ዕርገቱን ሁሉ አስቀድመው የተነሡ ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ትንቢት በተናገሩት መሠረት ተፈጽሟል፡፡ ነቢያቱም ትንቢታቸው እንዲፈጸም ‹‹አንሥእ ኀይለከ ፈኑ እዴከ፤ኃይልህን አንሳ እጅህንም ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው መምጫውን በጊዜ እየለኩ ሲጠባበቁ ኑረዋል። ትንቢቱም ጊዜው ሲደርስ ተፈጽሟል፡፡ እኛም ከዚህ በመነሣት ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሠረት ልንጾም ይገባናል፡፡ ✝️ጾሙ የሚጠራባቸው ስያሜዎች ፩.ጾመ ነቢያት ፡- ይህ ጾም ከላይ ለመግለጥ እንደሞከርነው ሁሉ ነቢያት የእግዚአብሔርን ሰው መሆንና ዓለሙን የሚያድነበትን ጊዜ እየተጠባበቁ የጾሙት በመሆኑ ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም) ተብሏል። ፪. ጾመ አዳም ፡- ለአዳም የተነገረው የድኅነት ተስፋ ስለመፈጸሙ የተሰጠው ስያሜ ነው። ፫. ጾመ ስብከት፡- ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት በመሆኑ ጾመ ስብከትም እየተባለ ይጠራል። ፬. ጾመ ሐዋርያት፡-ሐዋርያት በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እንፈታለን፤ በዓለ ልደትንም ይህን ጾም ጾመን እንፍታ ብለው ሲጾሙት ስለነበር ጾመ ሐዋርያት ይባላል።
Open in Telegram🔷አሁኑኑ ለራስዎና ለቤተሰብዎ ዕጣ ትኬቱን በ100ብር ብቻ በመግዛት ዕድልዎትን ይሞክሩ፡፡ 🔷አካውንት ቁጥር-🔷 #ንግድ ባንክ_1000003774957 #አሐዱ ባንክ_0003488720301 #አቢሲኒያ ባንክ_15203196 #አዋሽ ባንክ_013040800017700 #ዳሽን ባንክ_0888872166011 ✝️ ባሉበት ሆነው ትኬት ለመቁረጥ ከላይ በተቀመጠ ስልክ ይደውሉልን! 🔷ለበለጠ መረጃ የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮችን ይቀላቀሉ። 👇ቴሌግራም፡-👇 http://t.me/mkpublicrelation 👇ፌስ ቡክ👇 :-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/ 👇ዩ ቲዩብ፡-👇 http://www.youtube.com/user/EOTCMK ማኅበረ ቅዱሳን
Open in Telegramበክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማሰብ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ዓለም አቀፍ ዘመቻ እያካሄዱ ነው። በመላው ዓለም በእምነታቸው ምክንያት ስደትና መከራ የሚደርስባቸውን ክርስቲያኖች ለማሰብ የሚካሄደው ዓመታዊው የ"ቀይ ሳምንት" ዘመቻ በፓሪስ ከሚገኘው የኖትር ዳም ካቴድራል ጀምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በመካሄድ ላይ ይገኛል። ከኅዳር 6 እስከ 13 በሚቆየው በዚህ ዘመቻ 130 ታዋቂ ካቴድራሎች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናት፣ ሐውልቶች እና የሕዝብ ሕንፃዎች በቀይ ብርሃን ይታያሉ። እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ ቀዩ ብርሃን ስለ ክርስቶስ ሲሉ ሕይወታቸውን የሰጡ ሰማዕታትን ደም የሚወክል ሲሆን በሳምንቱ ውስጥም በተለያዩ ስፍራዎች የጸሎት ሥነ-ሥርዓቶች እና ሕዝባዊ ስብሰባዎች ለማካሄድ በዓለም ዙሪያ ከመቶ ሺዎች በላይ የሚሆኑ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል። ዘመቻውን ከተቀላቀሉት የፈረንሳይ ዋና ከተማ አንዱ የሆነው የኖትር ዳም ካቴድራል ባወጣው መግለጫ፣ መርሐ-ግብሩ በስደት እና በመከራ ላይ ባሉ ክርስቲያኖች ዙሪያ ያለውን ዝምታ ለመስበር እና ዓለም እንዳልረሳቸው ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አሳውቋል። መረጃው የ Christian devotion ነው
Open in Telegramስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለምልጃ ከሚቆሙ ቅዱሳን መላእክት አንዱ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር (፲፪) ዓሥራ ሁለት ቀን በዓሉ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ “ በሰማይም ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም ከነሰራዊቱ ተዋጋቸው አልቻላቸውምም ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም…” እኔ ፈጣሪያችሁ ነኝ የሚል ትዕቢትና ትምክሕት ልቡን ሠወረበት ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ጭፍራውን ይዞ ላይመለስ ወደ ጥልቁ ሲወርድ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃ በመሆን ተሾመ (ራእ፲፪፤፯)፡፡ ለነዌ ልጅ ኢያሱ በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሲገለጥ ኢያሱም “ከእኛ ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ” ባለው ጊዜ እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ” በማለት አለቅነቱም በዓለመ መላእክት ብቻ ሳይሆን በሕዝበ እስራኤል (እግዚአብሔርን በሚያመልኩ ሰዎች) ላይ ጭምር መሆኑን ተናግሯል፡፡ መጋቤ ብሉይ የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ቅዱስ ሚካኤል እስራኤል ዘሥጋን ከግብፅ የባርነት ኑሮ እግዚአብሔር ነፃ ሲያወጣቸው መና አውርዶ፣ ደመናን ጋርዶ፣ ከዓለት ውኃን አፍልቆ እያበላ እያጠጣ የእግራቸው ጫማ እንኳ ሳያልቅ ሲመራቸው የነበረ መልአክ መሆኑን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሲመሰክር “መርሖሙ መዓልተ በደመና ወኩሎ ሌሊተ በብርሃነ እሳት ወአውፅኦሙ ለሕዝቡ በትፍሥሕት ፈነወ መልአኮ ወአድኀኖሙ እንዘ ሚካኤል የሐውር ቅድመ ትዕይንቶሙ፤ እስራኤልን ቅዱስ ሚካኤል ቀን በደመና ሌሊት በብርሃን እሳት መራቸው በእስራኤል በጎዳናቸው ፊት ፊት እየሔደ ሕዝቡን በደስታ አወጣቸው መልአኩን ልኮ አወጣቸው፡፡” በማለት የእግዚአብሔርን ነፃ አውጭነት የቅዱስ ሚካኤልን ረዳትነት በዝማሬው ገንጧል(ድጓ ዘቅዱስ ሚካኤል)፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብፅ ባርነት ወደ ከነዓን በሚመራቸው ጊዜ እግዚብሔር ለሙሴ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ነበር “ በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እልካለሁ በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፡፡ ” በማለት ቅዱስ ሚካኤል እኛን እስራኤል ዘነፍስን ጭምር ከምድር ወደ ሰማይ፣ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ፣ ከመከራ ወደ ዕረፍት የሚመራን መልአክ መሆኑን እና መንገድ በተባለች ሃይማኖት ስንኖር እግዚአብሔርን እየበደልን የመልአኩን ቃል ባለማድመጥ ካስመረርነው መልአኩ ይቅር እንደማይለን በግልጽ አስጠንቅቋል (ዘፀ፳፫፣፳)፡፡ ✝️በዚህ መከራ ለይቶ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በበዛበት ዘመን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእነ ዱራታዎስ፣ ለእነ አፎሚያ ወዳጅነቱን በመግለጥ ፈጥኖ እንደደረሰላቸው ለእኛም በስደት በመከራ ላሉ ወገኖቻችንም በማያሳፍር ምልጃው ይድረስልን አሜን፡፡ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮችን ይቀላቀሉ። 👇ቴሌግራም፡-👇 http://t.me/mkpublicrelation 👇ፌስ ቡክ👇 :-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/ 👇ዩ ቲዩብ፡-👇 http://www.youtube.com/user/EOTCMK ማኅበረ ቅዱሳን
Open in Telegram