Account
Minber News - ሚንበር ኸበር

Minber News - ሚንበር ኸበር

Username
@minberkheber
Subscribers8,706
Avg views per post, 7d1,245last 7 days
ERR14.30%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 25, 20261,367
Nov 26, 20261,330
Nov 27, 20261,282
Nov 28, 20261,075
Nov 29, 2026554

Most viewed this month

  1. አምነስቲ ኢንተርናሽናል እስራኤል በጋዛ ሆነ ብላ የልደት መጠን እንዲቀንስ አድርጋለች በሚል የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የዘር ማጥፋት ምርመራ እንዲያካሂድ ጠየቀ ዕለተ ረቡዕ ኅዳር 16 – 2019 ጁማደል ሣኒ 15 – 1448 አምነስቲ ኢንተርናሽናል እስራኤል በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ ልደትን የሚገቱ ወይም የሚከላከሉ እርምጃዎችን ወስዳለች በማለት፤ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) ጉዳዩን እንደ “የዘር ማጥፋት ድርጊት” አድርጎ እንዲመረምረው ጠይቋል። አምነስቲ ጥያቄውን ያቀረበው ዛሬ ረቡዕ ኅዳር 16፤ 2019 ‘አለም አቀፍ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን ማስወገድ’ ቀንን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት ነው፡፡ በዚህ ሪፖርት ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በእስራኤል ባለሥልጣናት የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲመረምር ጥያቄውን አቅርቧል። የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አግነስ ካላማር ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እስራኤላውያን ባለሥልጣናት የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል። ካላማር እንዳሉት ከጥቅምት 2016 ጀምሮ የተካሄደው ጦርነት በጋዛ ሴቶች አካላዊ፣ አእምሯዊና ስነ ተዋልዶ ጤና ላይ ጉዳት አስከትሏል። አክለውም እስከ 2019 ድረስ "የእስራኤል ድርጊቶች የመካንነት ሕክምና እንዳይገኝ፣ ለእርግዝና ችግሮች፣ ለፅንስ ማቋረጥና የሞተ ልጅ እንዲወልዱ አስተዋጽኦ አድርገዋል" ብለዋል። እንደ ፍራንስ 24 ዘገባ ከሆነ ሪፖርቱ ነፍሰጡር እናቶችና ልጃገረዶች የወሊድ እንክብካቤ እና የሕክምና ርዳታ ፍለጋ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በደረሱ ጥቃቶች መገደላቸውን፣ እንዲሁም የማደንዘዣ መድኃኒቶችና በወሊድ ወቅት የሚከሰት ከፍተኛ ደም መፍሰስን ለማከም የሚያገለግሉ መድኃኒቶች እጥረት መኖሩን ሰንዷል። በጋዛ የጤና ሚኒስቴር መረጃ መሠረት፣ እ.አ.አ በ2018 መጀመርያ አካባቢ የተመዘገበው በሕይወት ያሉ ሕፃናት ልደት ቁጥር ከ2015 ጋር ሲነጻጸር በግምት በ41 በመቶ ቀንሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም በ2019 መጀመርያ ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የወሊድ ቁጥር መቀነሱን መዝግቧል። አምነስቲ በሺዎች የሚቆጠሩ የተከማቸ ሽል፣ የወንድ ዘር እና እንቁላሎች መውደማቸውንም አመልክቷል። (ሚንበር ቲቪ)

    Text
    Views1.49K
    Forwards—
    Reactions8
    Comments—
  2. በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ ዕድምተኞች ዘንድ ትኩረትን እየሳበ የሚገኘው - “ሪጃሉል ፈጅር” ሀገሩ አልጄሪያ ነው፤ ሰጢፍ ግዛት በሀገሪቱ ካሉ ዋና ዋና ሕዝብ በብዛት ከሚኖርባቸው ግዛቶች አንዷ ነች፡፡ በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በኩል ደግሞ ዐይነል ከቢራ ከተማ ትገኛለች፡፡ በአንዱ ቀዝቃዛ ማለዳ፤ በአንድ የአካባቢው የቁርኣን መምሕር አነሳሽነት የፈጅር ሰላት የአዛን ጥሪ ከመሰማቱ በፊት እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕጻናትን በመቀስቀስ ለሰላት በጀመዐ መሄድ ተጀመረ፡፡ በመጀመርያው ቀን ስድስት ሕጻናት ተሳታፊ ሆኑ፡፡ የሕጻናቱ ቡድን ከእንቅልፋቸው ነቅተው ወደ መስጅድ በማቅናት በፈጀር ሰላት ከፊት ረድፍ መሰለፋቸው እንግዳ ነገር ነበር፡፡ የእነዚህ ሕጻናት በቡድን ሆነው ወደ መስጂድ ሲጓዙ የሚያሳዩ ቪድዮዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሠራጭ ግን አንዱ ለሌላው ብርታት ሆኖ በሌሎች የአልጄሪያ ግዛቶችም በተመሳሳይ ተነሳሽነቶች ተጀመሩ፡፡ በአሁኑ ወቅት የተሳታፊዎች ቁጥር በሺሕዎች ይቆጠራል፡፡ በቡርጅ ቡ አሬሪጅ ብቻ ከ80 በላይ ሕጻናት በመደበኛነት ይታደማሉ፡፡ በዚያ የተለየው ነገር አንድ የአካባቢው አስተባባሪ ዓብዱረሕማን ለተባለ ሕጻን በፈጅር ሰላት በመታደሙ የዑምራ ሽልማት ማበርከቱ ነው፡፡ ሽልማቱ በዓብዱረሕማን ብቻ አልቆመም፤ ሦስት ተጨማሪ የዑምራ ሽልማቶች ለሌሎች ሕጻናት ተሰጥቷል፡፡ ይህ ከአልጄሪያ የተነሳ ትዕይንት በማኅበራዊ ሚዲያ ተሠራጭቶ መላውን የሙስሊሙን ዓለም ልብ ነክቷል፡፡ ተነሳሽነቱ “ሪጃሉል ፈጅር” የሚል ሥያሜ የተሰጠው ሲሆን፤ በቀጥተና ትርጉሙ “የማለዳ ሰዎች” ወይም “የንጋት ጀግኖች” እንደማለትም ነው፡፡ ከአልጄሪያ ሲሻገር ሞሮካውያን ዘመቻውን የተቀላቀሉት “ፉርሳን አል ፈጅር” በሚል ሥያሜ ነው፡፡ “የንጋት ፈረሰኞች” የሚል ትርጉም በያዘው እንቅስቃሴ ሕጻናት ለንጋት ሰላት ተሰባስበው የሚያሳዩ ፎቶግራፍ እና ቪድዮ እያጋሩበት ለሌሎች ብርታት እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ግብጽ የአልጄሪያውን “ሪጃሉል ፈጅር” ስትጠቀም፤ በዮርዳኖስ ደግሞ “ነሻሚል ፈጅር” በመባል ይጠራል፡፡ ከሞሮኮ፣ ዮርዳኖስና ግብጽ ባሻገር በእኛዋ ጎረቤት ሱዳንም በርካታ ሕጻናት ለፈጅር ሰላት ሲገኙ የሚያሳዩ ቪድዮዎች እየተጋሩ ይገኛል፡፡ የዮርዳኖሱ ዘመቻ መስራች አይመን አል በለዊ እንደተናገሩት፤ በፈጅር ሰላት ወቅት የመስጂዱ ታችኛው ክፍል በሰጋጆች በመሙላቱ፣ አብዛኛውን ጊዜ ለጁመዐ አልያም ለረመዳን ካልሆነ በስተቀር የማይከፈተው ሁለተኛ ፎቅ እንዲከፈት ተገደዋል፡፡ የዚህ እንቅስቃሴ ፋይዳ ሰላት ከመስገድም በላይ ነው፡፡ ለሕጻናት ሰዓት አክባሪነትን፣ ሥነ ሥርዐትን፣ ንጽሕናንና ለሃይማኖታዊ ግዴታዎች ክብር መስጠትን ያስተምራል፡፡ ስለ መልካም ሥነ ምግባር በቃል ከማስተማር ይልቅ፣ በተግባራዊ ልምምድ በጎ ልማዶችን ያስተዋውቃቸዋል፡፡ “ዓለም አቀፉ የሙስሊም ሊቃውንት ኅብረት” ተነሳሽነቱን በሕጻናት ልብ ውስጥ የፈጅር ሰላት ፍቅርን የሚተክልና አዲሱን ትውልድ ከልጅነቱ ጀምሮ ከመስጂድ ጋር የሚያስተሳስር “የተባረከ ጥረት” ነው ሲል አወድሶታል፡፡ ኅብረቱ እንደገለጸው፤ ይህ ተነሳሽነት “በሁሉም የሙስሊም ሀገራት ሊስፋፋ የሚገባው” ነው፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያዎች በርካቶች ይህን እንቅስቃሴ “ትውልድን የማነጽ” መንገድ ብለውታል፡፡ አንዳንዶች ሕጻናቱ አጥንት የሚሰብር ቅዝቃዜን ተቋቁመው በፊት ረድፍ ላይ መሰለፋቸው አዋቂዎችን ጭምር እያነቃቃ መሆኑን ጽፈዋል፡፡ በርግጥ ተነሳሽነቱ ተቺዎችንም አላጣም፡፡ አንዳንድ ተችዎች ይህ እንቅስቃሴ “የሕጻናትን የእንቅልፍ ሰዓት ይሻማል” እንዲሁም “በትምህርታቸው ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል” ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ለዚህ ምላሽ የሚሰጡ ሐኪሞች፤ ሕጻናት ቀደም ብለው ከተኙና ወደ ዘጠኝ ሰዓት ያህል እንቅልፍ ካገኙ፣ በማለዳ መንቃት ትኩረትንና አካላዊ ንቃትን እንደሚሻሽል የሚያሳዩ ጥናቶችን አቅርበዋል፡፡ ክርክሩ የከረረው የአልጄሪያው ዕለታዊ ጋዜጣ “አል ፈጅር” ሥራ አስኪያጅ ሀዳ ሐዛም በቲክቶክ የቀጥታ ሥርጭት ተነሳሽነቱን ከተቹ በኋላ ነው፡፡ ሰውዬው በሕጻናት እንቅልፍና ትምህርት ላይ ይደርሳል ካሉት ጉዳት ባሻገር የሕጻናቱ ደኅንነት ጋር በተገናኘ ውንጀላ አቅርበዋል፡፡ ይሁን እንጂ “ኦሪየንት” የተባለ ሬድዮ የጋዜጣው ሥራ አስኪያጅ ካሉት ጉዳይ ጋር በተያያዘ የተመዘገበ ክስተት አልተገኘም ሲል ዘግቧል፡፡ ይህ ንግግር የፓርላማ አባላትን አስቆጥቶ ዑመር ማእመር የተባሉ የፓርላማ አባል ለፍትህ ሚኒስቴር ደብዳቤ እንዲጽፉ አድርጓል፡፡ የአልጄሪያ የሃይማኖት ጉዳዮችና አውቃፍ ሚኒስቴርም መስጂዶችና ኢማሞችን ሰድበዋል በሚል ክስ መስርቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመዳኘት ለፊታችን እሑድ ቀጠሮ ይዟል፡፡ ንጋት ላይ ፀሓይን ቀድመው መስጂድ የሚደርሱት ልጆች መንፈሣዊ ጀብድ፤ በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ዘንድ ትኩረትን እየሳበ አንዳንዶችም ዘመቻውን ተቀላቀሉን እያሉ ይገኛሉ፡፡ ስለ ጉዳዩ ዘለግ ያለ ጽሑፍ ያቀረበው ዳዕዋ24 ድረ ገጽ በጽሑፉ ማጠቃለያ ላይ ይህን አስፍሯል፡- የስክሪን ሱስና እስከ እኩለ ሌሊት ማምሸት በበዛበት በዚህ ዘመን፣ በማለዳ ነቅቶ ወደ መስጂድ መሄድን የሚለምድ ሕጻን ሰላትን ብቻ ሳይሆን ሥነ ሥርዐትን፣ ኃላፊነትንና የማኅበረሰቡ አካል የመሆንን ስሜትም ይማራል፡፡ ይሁን እንጂ ተነሳሽነቱ እንዲሳካ የወላጆችን ፈቃድ፣ ሕጻናት በሰዓቱ እንዲተኙ የሚያስችል ዝግጅት እንዲሁም በመስጂድ ውስጥ ለደኅንነታቸውና ለጤናቸው የሚደረግ ጥንቃቄን ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ነገሮች ከተሟሉ፣ “ሪጃሉል ፈጅር” ለእያንዳንዱ የሙስሊም ማኅበረሰብ ምሣሌ መሆን የሚችል ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

    Text
    Views1.45K
    Forwards—
    Reactions29
    Comments—
  3. ልዩ ኸበር - “የንጋት ልጆች” ከመስጂዱ ደጃፍ ደርሰዋል ታዳጊ ሕጻናት በመስጂድ በመገኘት የፈጅር (የንጋት) ሰላት እንዲሰግዱ የሚያበረታታ እንቅስቃሴ በመላው የሙስሊሙ ዓለም ትኩረት ስቧል፡፡ በአልጄሪያ ተጀምሮ በሞሮኮና በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ ተነሳሽነቶች እንዲፈጠሩ መነሻ የሆነው ይህ ዘመቻ፤ “ከልጅነት ጀምሮ መልካም ልማዶችን ጠንካራ የሥነ ምግባር እሴቶችን ማዳበር” የሚል መልዕክት ያዘለ ነው፡፡ በአልጄሪያ “ሪጃል አል ፈጅር” (የንጋት ሰዎች እንደማለት) በመባል የሚታወቀው ይህ ተነሳሽነት፣ ታዳጊ ወንዶች ፀሓይ ከመውጣቷ በፊት ከአልጋቸው ተነስተው በአካባቢያቸው በሚገኙ መስጂዶች በጀመዐ ሰላት እንዲሳተፉ ያበረታታል፡፡ በጥቂት ሕጻናት እንደተጀመረ የሚነገርለት ይህ እንቅስቃሴ፣ በማኅበረሰቡ ተሳትፎና በማኅበራዊ ትስስር ገጾች በተደረገ ቅስቀሳ እያበበ መጥቷል፡፡ ሞሮካዊያን ይህ ተመሳሳይ ዘመቻ የተቀላቀሉት “ፉርሳን አል ፈጅር” በሚል ሥያሜ ነው፡፡ የንጋት ፈረሰኞች የሚል ትርጉም በያዘው እንቅስቃሴ ሕጻናት ለንጋት ሰላት ተሰባስበው የሚያሳዩ ፎቶግራፍ እና ቪድዮ እያጋሩበት ለሌሎች ብርታት እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ የዚህ እንቅስቃሴ ፋይዳ ሰላት ከመስገድም በላይ ነው፡፡ ለሕጻናት ሰዓት አክባሪነትን፣ ሥነ ሥርዐትን፣ ንጽሕናንና ለሃይማኖታዊ ግዴታዎች ክብር መስጠትን ያስተምራል፡፡ ስለ መልካም ሥነ ምግባር በቃል ከማስተማር ይልቅ፣ በተግባራዊ ልምምድ በጎ ልማዶችን ያስተዋውቃቸዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

    Photo
    Views1.45K
    Forwards—
    Reactions17
    Comments—
  4. ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ፤ ኤሚሬትስ ኢስላሚክን ሙሉ በሙሉ በአክሲዮን ልውውጥ ሥምምነት ሊገዛ ነው ዕለተ ሐሙስ ኅዳር 17 – 2019 ጁማደል ሣኒ 16 – 1448 ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ፤ ኤሚሬትስ ኢስላሚክ የተሰኘውን ባንክ ሙሉ ለሙሉ በአክሲዮን ልውውጥ ስምምነት ለመግዛት ተሥማምቷል፡፡ ግብይቱ ያለ ጥሬ ገንዘብ በአክስዮን ልውውጥ ብቻ የሚፈጸም ነው፡፡ ሥምምነቱ ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ 100 በመቶ የኤሚሬትስ ኢስላሚክን ካፒታል ለመውሰድ በምትኩ ለኤሚሬትስ ኤን.ዲ.ቢ አዲስ መደበኛ አክስዮኖችን መስጠትን ያካትታል፡፡ ይህ ሥምምነት በሐብት መጠን በዓለም ሁለተኛውን ትልቅ በአክሲዮን የተመዘገበ እስላማዊ ባንክን ይፈጥራል ተብሏል፡፡ ሁለቱ ባንኮች በሰጡት የጋራ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ሥምምነቱ ሲጠናቀቅ ኤሚሬትስ ኤን.ቢ.ዲ በዱባይ ኢስላሚክ ውስጥ ትልቅ ባለድርሻ ይሆናል፡፡ ሆኖም ባንኮች የግብይቱን አጠቃላይ ዋጋ፣ ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ የሚያወጣውን የአክሲዮን የአክሲዮን ብዛት ወይም የኤሚሬትስ ኤን.ቢ.ዲ የሚኖረውን የድርሻ መጠን ይፋ አላደረጉም፡፡ ገልፍ ኒውስ እንደዘገበው፤ አበዳሪዎች የአክስዮን ግዥ ሥምምነቱን ከመፈራረማቸው በፊት የሁለቱም ባንኮች የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥምምነቱን አጽድቀዋል፡፡ ነገር ግን ሥምምነቱ አሁንም የባለአክስዮኖችን ይሁንታ እንዲሁም ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ማዕከላዊ ባንክ፣ ከካፒታል ገበያ ባለሥልጣን እና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ፈቃድ ይፈልጋል፡፡ ባንኮቹ ሥምምነቱ የሚጠናቀቅበትን ቀን አልገለጹም፡፡ እስከ መስከረም ድረስ ባለውና ኦዲት ባልተደረገ የፋይናንስ መረጃ መሠረት፣ አበዳሪዎቹ ከተጣመረ ሐብታቸው ወደ 159 ቢሊዮን ዶላር ገደማ እንደሚሆን ገምተዋል፡፡ ይህ አኃዝ ከግብይቱ በኋላ የሚደረጉ የሒሳብ ማስተካከያዎችን የማያካትት ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውም የባንኮቹን ግምት የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ ይህ ሥምምነት ዱባይ ኢስላሚክ ቀደም ሲል “ኑር ባንክ”ን በመግዛት በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የእስልምና ባንክ እንቅስቃሴውን ካሰፋ በኋላ የተደረገ ነው፡፡ እ.አ.አ በ1975 የተመሠረተውና በዱባይ የፋይናንስ ገበያ የተመዘገበው ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ በፓኪስታን እና በኬንያ ቅርንጫፍ ባንኮች ያሉት ሲሆን፣ በኢንዶኔዥያ እና በቱርክ ደግሞ በእስልምና እና በዲጂታል ባንክ ዘርፎች ላይ ኢንቨስትመንቶች አሉት፡፡ በዚህ ጥምረት ውስጥ ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ የትላልቅ ኩባንያዎች የባንክ አገለግሎት አቅሙን ይዞ የሚመጣ ሲሆን፣ ኤሚሬትስ ኢስላሚክ ደግሞ የተደራጀ የግለሰብ/ችርችሮ የባንክ አገለግሎትና የተቀማጭ ገንዘብ መሠረትን ይጨምራል፡፡ እ.አ.አ በ2004 የተመሠረተው ኤሚሬትስ ኢስላሚክ በመላው የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች 36 ቅርንጫፎች አሉት፡፡ ለግለሰቦችና ለንግድ ተቋማት ከሸሪዓ ሕግ ጋር የተጣጣመ የፋይናንስ፣ የቁጠባ እና የሌሎች የባንክ አገለግሎቶች ይሰጣል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

    Text
    Views1.44K
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—

Latest posts

#5746Photo
Views554−55%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#5742Photo
Views1,140−8%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
23 h876
33 h1,140
  1. After 24 hours876
  2. Total to date1,140
#5739Photo

ያጉት ፔይ እና ዳሽን ባንክ የዓለም አቀፍ ማስተርካርድ ክፍያ አገልግሎትን በይፋ አስጀመሩ ያጉት ፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ አ.ማ. ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር በይፋ ያስጀመረው የማስተርካርድ (MPGS pay fac)አገልግሎት ይፋ የተደረገው ዛሬ ቅዳሜ ኅዳር 19/2019 ነው። ስለ አገልግሎቱ የተናገሩት የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተሾመ ዓለማየሁ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን በውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ በማስቻል ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልፀዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው በአገልግሎቱ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ማብራሪያ፣ አዲሱ የክፍያ ሥርዓት ባለሀብቶች ግብይታቸውን በቀላሉ እና በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲያከናውኑ ከማገዙም ባለፈ ለዓለም አቀፍ ጎብኝዎች ምቹ የክፍያ አማራጭ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል። ነጋዴዎች ወይም ተቋማት ከደንበኞቻቸው የሚመጡ የካርድ ክፍያዎችን ማስተርካርድ በመጠቀም በኦንላይን ወይም በፖስ ማሽን አማካኝነት ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲያስተናግዱ ያደርጋል። አገልግሎቱ ለሀገሪቱ ተጨማሪ የፋይናንስ አማራጭ በመሆን ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን እንደሚያጠናክር የጠቆሙት አቶ ተሾመ፣ ይህም በአጠቃላይ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ አስረድተዋል። የዳሽን ባንክ ተወካይ አቶ ዮሐንስ ሚሊዮን አገልግሎቱ ባንኩ ደንበኞቹ ጥራት እና ቀለል ባሉ አሰራሮች ክፍያቸዉን እንዲያሳልጡ እንደሚያስችል ገልፀዋል። (ሚንበር ቲቪ)

Open in Telegram
Views1,010−19%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#5736Text

በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ ዕድምተኞች ዘንድ ትኩረትን እየሳበ የሚገኘው - “ሪጃሉል ፈጅር” ሀገሩ አልጄሪያ ነው፤ ሰጢፍ ግዛት በሀገሪቱ ካሉ ዋና ዋና ሕዝብ በብዛት ከሚኖርባቸው ግዛቶች አንዷ ነች፡፡ በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በኩል ደግሞ ዐይነል ከቢራ ከተማ ትገኛለች፡፡ በአንዱ ቀዝቃዛ ማለዳ፤ በአንድ የአካባቢው የቁርኣን መምሕር አነሳሽነት የፈጅር ሰላት የአዛን ጥሪ ከመሰማቱ በፊት እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕጻናትን በመቀስቀስ ለሰላት በጀመዐ መሄድ ተጀመረ፡፡ በመጀመርያው ቀን ስድስት ሕጻናት ተሳታፊ ሆኑ፡፡ የሕጻናቱ ቡድን ከእንቅልፋቸው ነቅተው ወደ መስጅድ በማቅናት በፈጀር ሰላት ከፊት ረድፍ መሰለፋቸው እንግዳ ነገር ነበር፡፡ የእነዚህ ሕጻናት በቡድን ሆነው ወደ መስጂድ ሲጓዙ የሚያሳዩ ቪድዮዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሠራጭ ግን አንዱ ለሌላው ብርታት ሆኖ በሌሎች የአልጄሪያ ግዛቶችም በተመሳሳይ ተነሳሽነቶች ተጀመሩ፡፡ በአሁኑ ወቅት የተሳታፊዎች ቁጥር በሺሕዎች ይቆጠራል፡፡ በቡርጅ ቡ አሬሪጅ ብቻ ከ80 በላይ ሕጻናት በመደበኛነት ይታደማሉ፡፡ በዚያ የተለየው ነገር አንድ የአካባቢው አስተባባሪ ዓብዱረሕማን ለተባለ ሕጻን በፈጅር ሰላት በመታደሙ የዑምራ ሽልማት ማበርከቱ ነው፡፡ ሽልማቱ በዓብዱረሕማን ብቻ አልቆመም፤ ሦስት ተጨማሪ የዑምራ ሽልማቶች ለሌሎች ሕጻናት ተሰጥቷል፡፡ ይህ ከአልጄሪያ የተነሳ ትዕይንት በማኅበራዊ ሚዲያ ተሠራጭቶ መላውን የሙስሊሙን ዓለም ልብ ነክቷል፡፡ ተነሳሽነቱ “ሪጃሉል ፈጅር” የሚል ሥያሜ የተሰጠው ሲሆን፤ በቀጥተና ትርጉሙ “የማለዳ ሰዎች” ወይም “የንጋት ጀግኖች” እንደማለትም ነው፡፡ ከአልጄሪያ ሲሻገር ሞሮካውያን ዘመቻውን የተቀላቀሉት “ፉርሳን አል ፈጅር” በሚል ሥያሜ ነው፡፡ “የንጋት ፈረሰኞች” የሚል ትርጉም በያዘው እንቅስቃሴ ሕጻናት ለንጋት ሰላት ተሰባስበው የሚያሳዩ ፎቶግራፍ እና ቪድዮ እያጋሩበት ለሌሎች ብርታት እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ግብጽ የአልጄሪያውን “ሪጃሉል ፈጅር” ስትጠቀም፤ በዮርዳኖስ ደግሞ “ነሻሚል ፈጅር” በመባል ይጠራል፡፡ ከሞሮኮ፣ ዮርዳኖስና ግብጽ ባሻገር በእኛዋ ጎረቤት ሱዳንም በርካታ ሕጻናት ለፈጅር ሰላት ሲገኙ የሚያሳዩ ቪድዮዎች እየተጋሩ ይገኛል፡፡ የዮርዳኖሱ ዘመቻ መስራች አይመን አል በለዊ እንደተናገሩት፤ በፈጅር ሰላት ወቅት የመስጂዱ ታችኛው ክፍል በሰጋጆች በመሙላቱ፣ አብዛኛውን ጊዜ ለጁመዐ አልያም ለረመዳን ካልሆነ በስተቀር የማይከፈተው ሁለተኛ ፎቅ እንዲከፈት ተገደዋል፡፡ የዚህ እንቅስቃሴ ፋይዳ ሰላት ከመስገድም በላይ ነው፡፡ ለሕጻናት ሰዓት አክባሪነትን፣ ሥነ ሥርዐትን፣ ንጽሕናንና ለሃይማኖታዊ ግዴታዎች ክብር መስጠትን ያስተምራል፡፡ ስለ መልካም ሥነ ምግባር በቃል ከማስተማር ይልቅ፣ በተግባራዊ ልምምድ በጎ ልማዶችን ያስተዋውቃቸዋል፡፡ “ዓለም አቀፉ የሙስሊም ሊቃውንት ኅብረት” ተነሳሽነቱን በሕጻናት ልብ ውስጥ የፈጅር ሰላት ፍቅርን የሚተክልና አዲሱን ትውልድ ከልጅነቱ ጀምሮ ከመስጂድ ጋር የሚያስተሳስር “የተባረከ ጥረት” ነው ሲል አወድሶታል፡፡ ኅብረቱ እንደገለጸው፤ ይህ ተነሳሽነት “በሁሉም የሙስሊም ሀገራት ሊስፋፋ የሚገባው” ነው፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያዎች በርካቶች ይህን እንቅስቃሴ “ትውልድን የማነጽ” መንገድ ብለውታል፡፡ አንዳንዶች ሕጻናቱ አጥንት የሚሰብር ቅዝቃዜን ተቋቁመው በፊት ረድፍ ላይ መሰለፋቸው አዋቂዎችን ጭምር እያነቃቃ መሆኑን ጽፈዋል፡፡ በርግጥ ተነሳሽነቱ ተቺዎችንም አላጣም፡፡ አንዳንድ ተችዎች ይህ እንቅስቃሴ “የሕጻናትን የእንቅልፍ ሰዓት ይሻማል” እንዲሁም “በትምህርታቸው ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል” ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ለዚህ ምላሽ የሚሰጡ ሐኪሞች፤ ሕጻናት ቀደም ብለው ከተኙና ወደ ዘጠኝ ሰዓት ያህል እንቅልፍ ካገኙ፣ በማለዳ መንቃት ትኩረትንና አካላዊ ንቃትን እንደሚሻሽል የሚያሳዩ ጥናቶችን አቅርበዋል፡፡ ክርክሩ የከረረው የአልጄሪያው ዕለታዊ ጋዜጣ “አል ፈጅር” ሥራ አስኪያጅ ሀዳ ሐዛም በቲክቶክ የቀጥታ ሥርጭት ተነሳሽነቱን ከተቹ በኋላ ነው፡፡ ሰውዬው በሕጻናት እንቅልፍና ትምህርት ላይ ይደርሳል ካሉት ጉዳት ባሻገር የሕጻናቱ ደኅንነት ጋር በተገናኘ ውንጀላ አቅርበዋል፡፡ ይሁን እንጂ “ኦሪየንት” የተባለ ሬድዮ የጋዜጣው ሥራ አስኪያጅ ካሉት ጉዳይ ጋር በተያያዘ የተመዘገበ ክስተት አልተገኘም ሲል ዘግቧል፡፡ ይህ ንግግር የፓርላማ አባላትን አስቆጥቶ ዑመር ማእመር የተባሉ የፓርላማ አባል ለፍትህ ሚኒስቴር ደብዳቤ እንዲጽፉ አድርጓል፡፡ የአልጄሪያ የሃይማኖት ጉዳዮችና አውቃፍ ሚኒስቴርም መስጂዶችና ኢማሞችን ሰድበዋል በሚል ክስ መስርቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመዳኘት ለፊታችን እሑድ ቀጠሮ ይዟል፡፡ ንጋት ላይ ፀሓይን ቀድመው መስጂድ የሚደርሱት ልጆች መንፈሣዊ ጀብድ፤ በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ዘንድ ትኩረትን እየሳበ አንዳንዶችም ዘመቻውን ተቀላቀሉን እያሉ ይገኛሉ፡፡ ስለ ጉዳዩ ዘለግ ያለ ጽሑፍ ያቀረበው ዳዕዋ24 ድረ ገጽ በጽሑፉ ማጠቃለያ ላይ ይህን አስፍሯል፡- የስክሪን ሱስና እስከ እኩለ ሌሊት ማምሸት በበዛበት በዚህ ዘመን፣ በማለዳ ነቅቶ ወደ መስጂድ መሄድን የሚለምድ ሕጻን ሰላትን ብቻ ሳይሆን ሥነ ሥርዐትን፣ ኃላፊነትንና የማኅበረሰቡ አካል የመሆንን ስሜትም ይማራል፡፡ ይሁን እንጂ ተነሳሽነቱ እንዲሳካ የወላጆችን ፈቃድ፣ ሕጻናት በሰዓቱ እንዲተኙ የሚያስችል ዝግጅት እንዲሁም በመስጂድ ውስጥ ለደኅንነታቸውና ለጤናቸው የሚደረግ ጥንቃቄን ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ነገሮች ከተሟሉ፣ “ሪጃሉል ፈጅር” ለእያንዳንዱ የሙስሊም ማኅበረሰብ ምሣሌ መሆን የሚችል ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

Open in Telegram
Views1,450+17%vs avg
Forwards—
Reactions29
Comments—
#5734Photo

ልዩ ኸበር - “የንጋት ልጆች” ከመስጂዱ ደጃፍ ደርሰዋል ታዳጊ ሕጻናት በመስጂድ በመገኘት የፈጅር (የንጋት) ሰላት እንዲሰግዱ የሚያበረታታ እንቅስቃሴ በመላው የሙስሊሙ ዓለም ትኩረት ስቧል፡፡ በአልጄሪያ ተጀምሮ በሞሮኮና በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ ተነሳሽነቶች እንዲፈጠሩ መነሻ የሆነው ይህ ዘመቻ፤ “ከልጅነት ጀምሮ መልካም ልማዶችን ጠንካራ የሥነ ምግባር እሴቶችን ማዳበር” የሚል መልዕክት ያዘለ ነው፡፡ በአልጄሪያ “ሪጃል አል ፈጅር” (የንጋት ሰዎች እንደማለት) በመባል የሚታወቀው ይህ ተነሳሽነት፣ ታዳጊ ወንዶች ፀሓይ ከመውጣቷ በፊት ከአልጋቸው ተነስተው በአካባቢያቸው በሚገኙ መስጂዶች በጀመዐ ሰላት እንዲሳተፉ ያበረታታል፡፡ በጥቂት ሕጻናት እንደተጀመረ የሚነገርለት ይህ እንቅስቃሴ፣ በማኅበረሰቡ ተሳትፎና በማኅበራዊ ትስስር ገጾች በተደረገ ቅስቀሳ እያበበ መጥቷል፡፡ ሞሮካዊያን ይህ ተመሳሳይ ዘመቻ የተቀላቀሉት “ፉርሳን አል ፈጅር” በሚል ሥያሜ ነው፡፡ የንጋት ፈረሰኞች የሚል ትርጉም በያዘው እንቅስቃሴ ሕጻናት ለንጋት ሰላት ተሰባስበው የሚያሳዩ ፎቶግራፍ እና ቪድዮ እያጋሩበት ለሌሎች ብርታት እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ የዚህ እንቅስቃሴ ፋይዳ ሰላት ከመስገድም በላይ ነው፡፡ ለሕጻናት ሰዓት አክባሪነትን፣ ሥነ ሥርዐትን፣ ንጽሕናንና ለሃይማኖታዊ ግዴታዎች ክብር መስጠትን ያስተምራል፡፡ ስለ መልካም ሥነ ምግባር በቃል ከማስተማር ይልቅ፣ በተግባራዊ ልምምድ በጎ ልማዶችን ያስተዋውቃቸዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

Open in Telegram
Views1,450+17%vs avg
Forwards—
Reactions17
Comments—
#5733Text

ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ፤ ኤሚሬትስ ኢስላሚክን ሙሉ በሙሉ በአክሲዮን ልውውጥ ሥምምነት ሊገዛ ነው ዕለተ ሐሙስ ኅዳር 17 – 2019 ጁማደል ሣኒ 16 – 1448 ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ፤ ኤሚሬትስ ኢስላሚክ የተሰኘውን ባንክ ሙሉ ለሙሉ በአክሲዮን ልውውጥ ስምምነት ለመግዛት ተሥማምቷል፡፡ ግብይቱ ያለ ጥሬ ገንዘብ በአክስዮን ልውውጥ ብቻ የሚፈጸም ነው፡፡ ሥምምነቱ ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ 100 በመቶ የኤሚሬትስ ኢስላሚክን ካፒታል ለመውሰድ በምትኩ ለኤሚሬትስ ኤን.ዲ.ቢ አዲስ መደበኛ አክስዮኖችን መስጠትን ያካትታል፡፡ ይህ ሥምምነት በሐብት መጠን በዓለም ሁለተኛውን ትልቅ በአክሲዮን የተመዘገበ እስላማዊ ባንክን ይፈጥራል ተብሏል፡፡ ሁለቱ ባንኮች በሰጡት የጋራ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ሥምምነቱ ሲጠናቀቅ ኤሚሬትስ ኤን.ቢ.ዲ በዱባይ ኢስላሚክ ውስጥ ትልቅ ባለድርሻ ይሆናል፡፡ ሆኖም ባንኮች የግብይቱን አጠቃላይ ዋጋ፣ ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ የሚያወጣውን የአክሲዮን የአክሲዮን ብዛት ወይም የኤሚሬትስ ኤን.ቢ.ዲ የሚኖረውን የድርሻ መጠን ይፋ አላደረጉም፡፡ ገልፍ ኒውስ እንደዘገበው፤ አበዳሪዎች የአክስዮን ግዥ ሥምምነቱን ከመፈራረማቸው በፊት የሁለቱም ባንኮች የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥምምነቱን አጽድቀዋል፡፡ ነገር ግን ሥምምነቱ አሁንም የባለአክስዮኖችን ይሁንታ እንዲሁም ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ማዕከላዊ ባንክ፣ ከካፒታል ገበያ ባለሥልጣን እና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ፈቃድ ይፈልጋል፡፡ ባንኮቹ ሥምምነቱ የሚጠናቀቅበትን ቀን አልገለጹም፡፡ እስከ መስከረም ድረስ ባለውና ኦዲት ባልተደረገ የፋይናንስ መረጃ መሠረት፣ አበዳሪዎቹ ከተጣመረ ሐብታቸው ወደ 159 ቢሊዮን ዶላር ገደማ እንደሚሆን ገምተዋል፡፡ ይህ አኃዝ ከግብይቱ በኋላ የሚደረጉ የሒሳብ ማስተካከያዎችን የማያካትት ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውም የባንኮቹን ግምት የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ ይህ ሥምምነት ዱባይ ኢስላሚክ ቀደም ሲል “ኑር ባንክ”ን በመግዛት በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የእስልምና ባንክ እንቅስቃሴውን ካሰፋ በኋላ የተደረገ ነው፡፡ እ.አ.አ በ1975 የተመሠረተውና በዱባይ የፋይናንስ ገበያ የተመዘገበው ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ በፓኪስታን እና በኬንያ ቅርንጫፍ ባንኮች ያሉት ሲሆን፣ በኢንዶኔዥያ እና በቱርክ ደግሞ በእስልምና እና በዲጂታል ባንክ ዘርፎች ላይ ኢንቨስትመንቶች አሉት፡፡ በዚህ ጥምረት ውስጥ ዱባይ ኢስላሚክ ባንክ የትላልቅ ኩባንያዎች የባንክ አገለግሎት አቅሙን ይዞ የሚመጣ ሲሆን፣ ኤሚሬትስ ኢስላሚክ ደግሞ የተደራጀ የግለሰብ/ችርችሮ የባንክ አገለግሎትና የተቀማጭ ገንዘብ መሠረትን ይጨምራል፡፡ እ.አ.አ በ2004 የተመሠረተው ኤሚሬትስ ኢስላሚክ በመላው የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች 36 ቅርንጫፎች አሉት፡፡ ለግለሰቦችና ለንግድ ተቋማት ከሸሪዓ ሕግ ጋር የተጣጣመ የፋይናንስ፣ የቁጠባ እና የሌሎች የባንክ አገለግሎቶች ይሰጣል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

Open in Telegram
Views1,440+16%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—

All posts

Connections

Mentioned by