Account

Posts of ምክረ ሃይማኖት

newest first

#9581Photo
Views569−74%vs avg
Forwards—
Reactions35
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h232
3 h523
8 h569
  1. After 1 hour232
  2. After 6 hours569
  3. Total to date569
#9580Photo
Views626−71%vs avg
Forwards—
Reactions33
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
5 h528
8 h626
  1. After 6 hours528
  2. Total to date626
#9578Video
Views1,310−40%vs avg
Forwards—
Reactions22
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
18 h1,130
24 h1,310
  1. After 24 hours1,310
  2. Total to date1,310
#9577Text

በአንድ ወቅት አንድ በጣም የሚናገርና "እግዚአብሔር የለም" ብሎ የሚያምን የጸጉር አስተካካይ ነበር። አንድ ቀን አንድ ትሁት ቄስ ጸጉራቸውን ሊስተካከሉ ወደዚህ ጸጉር ቤት ገቡ። አስተካካዩ ሥራውን እየሰራ፣ እንደ ልማዱ ወሬ ጀመረ፦ "አባቴ፣ እኔ እኮ እግዚአብሔር አለ የሚለውን ነገር አላምነውም!" አላቸው። ቄሱም በመገረም "ለምን ልጄ?" ብለው ጠየቁት። አስተካካዩም በኩራት እንዲህ አለ፦ "ወደ ውጭ ወጥተው መንገዱን ይመልከቱ! እግዚአብሔር ቢኖር ኖሮ ይሄ ሁሉ በሽተኛ ይኖር ነበር? ይሄ ሁሉ የታረዘና የተራበ ሕፃን ይታይ ነበር? ይሄ ሁሉ ግፍና መከራ በምድር ላይ ይፈጸም ነበር? አፍቃሪ የሆነ አምላክ ቢኖር ኖሮ ይሄን ሁሉ መከራ አይፈቅድም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር የለም!" ብሎ በድፍረት ተናገረ። ቄሱም በዚያ ሰዓት ክርክር ውስጥ ሳይገቡ ጸጉራቸውን ተስተካክለው፣ ክፍያቸውን ከፍለው ወጡ። ልክ ከጸጉር ቤቱ በር ላይ እንደወጡ፣ ቄሱ አንድ ሰው አዩ። ያ ሰው ጸጉሩ በጣም አድጎና ተንጨባርሮ፣ ጺሙም ተዘበራርቆ ፊቱ ሁሉ ተሸፍኖ ነበር። ቄሱ ወዲያውኑ ወደ ጸጉር ቤቱ ተመልሰው ገቡ። ቄሱም አስተካካዩን ጠርተው፦ "ልጄ ሆይ፣ አሁን አንድ እውነት ገባኝ። በዚህ ምድር ላይ 'የጸጉር አስተካካይ' የሚባል ነገር የለም!" አሉት። አስተካካዩ በሳቅ ፈረሰና "ምን ማለትዎ ነው አባቴ? እኔ እኮ እዚህ ቆሜ ጸጉርዎን አሁን አስተካክዬልዎት ወጣሁ። እንዴት የለም ይላሉ?" አላቸው። ቄሱም ወደ በሩ ጠቁመው፦ "አየህ፣ ጸጉር አስተካካይ ቢኖር ኖሮ ያ ሰውዬ ጸጉሩ እንደዛ ተንጨባርሮ በመንገድ ላይ ይሄድ ነበር? የጸጉር አስተካካይ ቢኖር ኖሮ እኮ ሁሉም ሰው ጸጉሩ የተስተካከለ ይሆን ነበር" አሉት። አስተካካዩም "ኧረ አባቴ! እኔ እኮ አለሁ። ችግሩ ያ ሰውዬ ወደ እኔ መጥቶ 'አስተካክለኝ' ስላላለን እንጂ እኔ እኮ ዝግጁ ነኝ" አለ። ቄሱም ፈገግ አሉና "በትክክል! እግዚአብሔርም አለ። ችግሩ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መጥተው 'ርዳን፣ ማረን' ስለማይሉት እንጂ፣ እግዚአብሔር እኮ ሁልጊዜም ዝግጁ ነው!" አሉት። አስተካካዩም አፉን ተዘጋ። *** በዓለማችን ላይ ላለው መከራ ሁሉ ተጠያቂው እግዚአብሔር አይደለም። እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ነፃ ፈቃድ ሰጥቶታል። ችግሩ ሰዎች ወደ ፈጣሪያቸው ከመቅረብ ይልቅ በራሳቸው መንገድ መጓዛቸው ነው። ወደ ጸጉር አስተካካዩ ያልሄደ ሰው ጸጉሩ እንደሚንጨባረር ሁሉ፣ ወደ እግዚአብሔር የማይቀርብ ሕይወትም ይዝረከረካል። ሼር ✞ @Mikre_haymanot ✞

Open in Telegram
Views1,510−30%vs avg
Forwards—
Reactions50
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
21 h1,360
27 h1,510
  1. After 24 hours1,360
  2. Total to date1,510
#9576Photo
Views1,480−32%vs avg
Forwards—
Reactions79
Comments—
#9575Photo
Views1,680−23%vs avg
Forwards—
Reactions69
Comments—
#9573Photo
Views1,860−14%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
65 h1,840
68 h1,860
  1. Total to date1,860
#9569Text

በአንድ ሀገር ለንጉሡም ለሕዝቡም ያስቸገረ ሌባ ነበር። ንጉሡ ሕዝቡን ሰብስቦ ሌባውን መዘው እንዲሰጡት ቢያባብልም ሌባውን የሚያውቅ በመጥፋቱ ሊሆን አልቻለም፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ንጉሡ በሀገሩ ካለ ሰፊ ሜዳ ላይ ሕዝቡ ሁሉ እንዲኮለኮል አደረገ፡፡ እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ሕዝቡ ሌባውን እንዲያ ጋልጥና እንዲሰጠው ተናገረ፡፡ ግን ምንም ፍንጭ የለም። በዚህ ጊዜ በአካባቢው ካለ አንድ ጨለማ ቤት ውስጥ አንድ አህያ እንዲታሰር አደረገና ለሕዝቡ የሚከተለውን መመሪያ አስተላለፈ እንዲህ ሲል «እዚያች ትንሽ ቤት ውስጥ አንድ አህያ ታስሯል፡፡ ሁላችሁም በተራ ወደዚያች ክፍል እየዘለቃችሁ የአህያውን ጭራ ትጨብጣላችሁ፡፡ በዚህ ጊዜ አህያው ሌባው ሲነካው ያናፋል ያኔ ሌባውን እናው ቀዋለን፡፡» ይላል፡፡ በሌባው ምክንያት ሊታወክ የሰነበተው ሕዝብ ደስ አለውና ሒደቱ ቀጠለ፡፡ ሕዝቡም ሁሉ በየተራ እየገባ የአህ ያዋን ጭራ እየጨበጠ ይወጣ ጀመር፡፡ ኹኔታው ቀጥሎ የሌባው ተራ ይደርስና ወደጨለማው ቤት ይዘልቃል ከቤቱ ውስጥ ከአህያዋ በስተቀር ምንም የለም፡፡ ሌባው ግራና ቀኙን ዐይቶ ተመልካች ስለሌለው የአህያውን ጭራ ቢነካ ያጋልጠኛል ብሎም ስላሰበ አንተ አህያ ሞኝህን ፈልግ ይልና ጭራውን ሳይጨብጥ እንዲሁ ይወጣል፡፡ በልቡም ሠራሁለት ይኽ ጅል ንጉሥ ይላል። ሕዝቡ ሁሉ ድርጊቱን ፈጽሞ ሲያበቃ ንጉሡ ዙሪያውን ካስከበበ በኋላ እያን ዳንዱን ሰው ወደዙፋኑ እንዲቀርብ እያደረገ የሁሉንም እጅ እጃቸውን ማሽተት ይጀምራል፡፡ ይህንን ያደረገው ያለምክንያት አልነበረም:: የአህያውን ጭራ ውድና ልዩ የሆነ ሽቱ ቀብቶት ስለነበር እንጂ፡፡ ሌባው ሆዬ ሀገር ሰላም ብሎ መዳፉን ለንጉሡ ይሰጥና ሲሸተት ባዶ ሆኖ ይገኛል...ከዚያማ ያው እርምጃ ይወስ ድበትና ሀገሪቷ በንጉሡ ብልኀት ከመታወክ ዳነች ይባላል፡፡ *** አበው ሲናገሩ «እውነተኛ ፍርድ እውነተኛ ዳኛ እስኪገኝ ይዘገያል» ይላሉ፡፡ በዚህ ታሪክ በኃይል መጠቀምን በጥበብ ማስተዳደር ሲለቀውም እናያለን፡፡ ሁልጊዜ አጭበርባሪ እንደሆኑ አይዘልቅምና ራሳችንን ወቅሰን ንስሐ መግባቱ ብልህነት ነው፡፡ ✞ @Mikre_haymanot ✞                ✞⌲                       ˢʰᵃʳᵉ

Open in Telegram
Views1,870−14%vs avg
Forwards—
Reactions41
Comments—
#9568Text

የአባ ሎጥ ደቀ መዝሙር አባ ጴጥሮስ ስለ አባ አጋቶን እንዲህ ብሏል። «አንድ ጊዜ በአባ አጋቶን በኣት እያለሁ አንድ ወንድም መጣና አባ አጋቶንን «ከወንድሞች ጋር መኖር እሻ ነበር፣ እስቲ እንዴት አብሬያቸው መኖር እንዳለብኝ ምከረኝ» ሲል ጠየቀው፡፡ አባ አጋቶንም «በኑሮህ ሁሉ የአንግዳ ሰው ዓይነት ልቡና ይኑርህ፤ ልክ በመጀመሪያ ያገኘሃቸው ቀን የምትሆነውን ዓይነት፡፡ በጣምም አትቅረባቸው፤ በጣምም አትራቃቸው፡፡» አለው በዚህ ጊዜ አባ መቃርዮስ «ይህ መቀራረብ ምን ይስከትላል?» ሲል ጠየቀው፡፡ አባ አጋቶንም «ያማ እንደ ኃይለኛ ዐውሎ ነፋስ ያለ ነው፤ ሊንሳፈፍ የሚችለውን ሁሉ እያነሣ የዛፎችን ፍሬ ያበላሽባቸዋል»፡፡ አባ መቃ ርዮስም «ያለ መጠን መናገር ይህን ያህል ይጐዳል እንዴ» ብሎ ጠ የቀ። አባ አጋቶንም «የማይቆጣጠሩትን ምላስ ያህል መጥፎ ፆር የለም፣ እርሷ የፈተና ሁሉ እናት ናት። ስለሆነም አውነተኛ የሥራ ሰው አይጠቀምባትም! አንዲት ትንሽ አልጋ የነበረችው አንድ ወን ድም አውቃለሁ፤ እርሱ በበኣቱ ለረዥም ዘመናት ከኖረ በኋላ «ያችን ትንሽ አልጋ ላልጠቀምባት ከበኣቴ ወጣሁ፣ ምክንያቱም እዚያ መኖርዋን የነገረኝ ሰው አልነበረምና» ይል ነበር፡፡ ✞ @Mikre_haymanot ✞                ✞⌲                       ˢʰᵃʳᵉ

Open in Telegram
Views2,140−1%vs avg
Forwards—
Reactions53
Comments—
#9566Photo
Views3,080+42%vs avg
Forwards—
Reactions71
Comments—
#9565Text

✝ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል በመከራ ውስጥ ይመጣል ። አንድ ሰው መፍትሔ የሌለው የሚመስል መከራ ሊገጥመው ይችላል ። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ መከራው የገጠመው ጥቂት ኃጢአቶችን ስለ ፈጸመ መሆኑን ከማስጠንቀቂያ ጋር ይነግረዋል ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቃሉ ንስሓ ከገባህ መከራው ፍጻሜ ያገኛል እያለ ውስጡን ሲመክረው ይሰማል ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ንስሓው ሲል ለሰውየው ይራራለታል ። የእግዚአብሔር ድምፅ አንድ ሰው ሲ ታመም ወይም እርሱ የሚወደው ሌላ ሰው ሲታመም ሊመጣ ይችላል ። በዚህ ጊዜ እንዲጸልይ ወይም ስእለት እንዲሳል የሚመክረውን ድምፅ ከውስጡ ይሰማል ይህ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው ። የዮሴፍ ወድሞች እህል ሊገዙ ወደ ግብጽ ከወረዱ በኋላ በዚያ ችግር ሲገጥማቸው እርስ በእርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋግረው ነበር ፦ " በእውነት ወድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውና ። ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን ።"/ ዘፍ 42*21/ ። ከዚህ በኋላ ለዮሴፍ እንዲህ ብለውታል ፦ " ለጌታዬ ምን እንመልሳለን ? ምንስ እንናገራለን ? ወይስ በምን እንነጻለን ? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ ..."/ዘፍ 44*16/ ኃጢአታቸውን እንዲያስታውሱ ኀላም እንዲገሰጹ ያደረጋቸው የእግዚአብሔር ድምፅ ነው ። ነቢዩ ዳዊት የጌራ ልጅ በሆነው በሳሚ ሲሰደብ የእግዚአብሔር ድምፅ ውስጡን ስላለፈ ኃጢአቱ  እየወቀሰው መሆኑን አዳምጧል ። ስለሆነም በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች " "እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎታልና ይርገመኝ ። / 2ኛ ሳሙ 16*10/ በማለት በግልጽ ተናግሯል ። ረሀብና የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም ሲደርስ የእግዚአብሔር ድምፅ በመላው ዓለም ውስጥ ይሰማል ። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ የሚናገረን " ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ።" / ሚል 3*7/ እያለ ነው ። ይህ ድምፅ በረሀቡ ወይም በመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት ለደረሰባቸው ሀገሮች የሚሆን የእርዳታ ጥሪ ለማሰማት ወይም ሌሎቹ ከእነርሱ ትምህርት በመውሰድ ንስሓ እንዲገቡ ለማድረግ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኝት ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው ። ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ስትገቡ ከውስጣችሁ ያለውን የእግዚአብሔር ድምፅ አድምጡት እርሱ ለእናንተ ሊነግራችሁ የሚወደው ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁና ። ብጹዕነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ Share ✞ @Mikre_haymanot ✞

Open in Telegram
Views3,030+40%vs avg
Forwards—
Reactions46
Comments—
#9563Photo
Views2,920+35%vs avg
Forwards—
Reactions53
Comments—
#9562Text
Views3,050+41%vs avg
Forwards—
Reactions83
Comments—
#9560Text

በበአትህ ተቀመጥ ልብህን ሰብስብ፣ ዕለተ ሞትህን አዘክር፣ አሟሟትህ ምን ሊሆን እንደሚችል አስብ፡ መንፈስህ ጽኑ ይሁን ሕማማትን ተቀበል፣ የዓለምን ከንቱ ነገር ናቀው፤ ያን ጊዜ ያለ ድካም በሰላም መኖር ትችላለህ፡፡ በሲዖል ምን እንዳለ አስብ፣ በዚያ ያሉ ነፍሳትን ሁኔታ አስብ፣ አሰቃቂ የሆነውን ዝምታ፣ መሪር የሆነውን ጩኸት፣ ፍርሃታቸዉን ሁከታቸውን፣ በዚያ የሚኖሩበት ዘመን ማለቂያ እንደሌለው አስበው፡፡ ፍጻሜ የሌለውን ሐዘናቸዉንና ዘለዓለማዊውን የነፍሳቸዉን ልቅሶ አስብ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የትንሣኤን ዕለት አስበው፤ በእግዚአብሔር ፊት መቆምንም አትርሳ፡፡ አስፈሪውንና አስደንጋጩን ፍርድ አስብ፣ ለኃጥኣን የተጠበቀላቸዉን መከራ፣ በፈጣሪ ፊት በሊቃነ መላእክት፣ በመላእክትና በጻድቃን ሁሉ ፊት የሚከናነቡትን ሃፍረት አስብ፣ ያም ቅጣቱ፣ ዘለዓለማዊው እሳት፣ የማያንቀላፋው ትል፣ጨለማው፣ጥርስ ማፋጨቱ፣ ፍርሃቱና ሰቀቀኑ ናቸው፡፡ ለጻድቃን የታሰበላቸዉን መልካም ነገርም አስብ፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ፊት፣ በሊቃነ መላእክት በመላእክትና በሰዎች ሁሉ ፊት የሚኖራቸውን ክብር አስብ፡ መንግሥተ ሰማያትን በዚያ ያለውን ጸጋ፣ ደስታና ብፅዕና አትርሳ፡፡ እነዚህን ሁለት እውነታዎች በልቡናህ አኑር፤ በኃጥኣን ላይ ስለ ሚመጣው ፍርድ ስትል አልቅስ፤ ምናልባት አንተም እነዚያን ስቃዮች እንደምትቀበል አድርገህ ለራስህ እዘን፡፡ በጻድቃን ዕጣ ፈንታ ደግሞ ደስ ይበልህ፡፡ እነዚያን ጸጋዎች ለማግኘት ተጋደል፡፡ ነገር ግን ለእነዚያ ስቃያት እንግዳ ሁን። በበኣትህ ውስጥም ሆነ ከበኣትህ ውጭ እነዚህን ነገሮች ማሰብ ከአንተ እንዳይለይ ተጠንቀቅ፡፡ ያንጊዜ ክፉውንና አሳፋሪውን ሃሳብ ከአንተ ታርቀዋለህና። ኢቫግሪስ ✞ @Mikre_haymanot ✞                ✞⌲                       ˢʰᵃʳᵉ

Open in Telegram
Views3,750+73%vs avg
Forwards—
Reactions61
Comments—
#9559Text

"ለሰው ልጅ ከፈሪሃ እግዚአብሔር በቀር ሌላ የሚያስፈራው ነገር ሊኖር አይገባም። ፈሪሃ እግዚአብሔር ካለህ ከእሳት፣ ከባሕር፣ ከሰይፍ፣ ከንጉሥ ቁጣ ወይም ከማንኛውም መከራ በላይ ትሆናለህ። ​እግዚአብሔርን መፍራት ካለህ፣ ከቤትህ ሳትወጣ ሌላ ሀብት ሳታከማች አንተ ከባለጸጎች ሁሉ ትበልጣለህ። ምክንያቱም እግዚአብሔርን መፍራት የማይጠፋና የማይሰረቅ ሰማያዊ መዝገብ ነውና። ነገር ግን እግዚአብሔርን መፍራት ከሌለህ፣ በቤተ መንግሥት ውስጥ ብትኖርና የዓለምን ሀብት ሁሉ ብትሰበስብ አንተ ከደሆች ሁሉ የደኸየህ ነህ። ​ሰውን መፍራት ሰውን ባሪያ ያደርገዋል፤ እግዚአብሔርን መፍራት ግን ሰውን ነፃ ያወጣዋል። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ዓለት የጸና ነው፤ ማዕበል ቢመጣበት፣ ነፋስ ቢነፍስበት አይናወጥም። ሌላው ዓለም ሁሉ ሲንቀጠቀጥ እርሱ ግን በሰላም ይተኛል። ባለጸጋው ሀብቱን እንዳይሰረቅ ይፈራል፣ ባለሥልጣኑ ሥልጣኑን እንዳያጣ ይሰጋል፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ግን ሊቀማው የሚችል ማንም የለም።" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ➛ በእንተ ሐውልታት ድርሳን 15)

Open in Telegram
Views3,900+80%vs avg
Forwards—
Reactions87
Comments—