ከሰሞኑ በቦሌ አየር ማረፊያ በታዩት ሰባት የሩሲያ ወታደራዊ የጭነት አውሮፕላኖች ዙርያ ህንድ ያሉ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ለአንድ የሀገሪቱ ጋዜጠኛ አነጋጋሪ ምላሽ ሰጡ ይህ ውዝግብ የተነሳው "ሪች ቴድ" የተባለ መረጃ ተንታኝ የቦሌውን ምስል መገኛ ቦታ በማረጋገጥ አውሮፕላኖቹ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሱዳን ድንበር አቅራቢያ ወደሚገኙ ሌሎች የኢትዮጵያ አውሮፕላን ማረፊያዎች በረራ ማድረጋቸውን መግለጹን ተከትሎ ነው https://www.meseretmedia.org/p/fd0
Open in TelegramPosts of Meseret Media
#የምርመራዘገባ የወር ደሞዛቸው ላይ 68,000 ሺህ ብር ጭማሪ ያረጉት ባለስልጣን እና አነጋጋሪው የመስሪያ ቤታቸው የሰራተኛ ቅጥር ጉዳዩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌዴራል ኦዲት ዋና መሥሪያ ቤት፣ ለሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዘርፍ፣ ለፌዴራል ፖሊስ፣ ለፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በግልባጭ ቢላክም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ ታውቋል https://www.meseretmedia.org/p/68000
Open in Telegramየመንግስት ጦር እና ተባባሪ ሀይሎች መስከረም ወር ላይ በአላማጣ የፈፀሙት የከባድ መሳርያ ጥቃት የጦር ወንጀልነት ምርመራ እንዲደረግበት አምነስቲ አሳሰበ ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው ኃይሎች በከተማዋ ዳግም ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በተለያዩ ትምህርት ቤቶችና ሰዎች በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ወታደራዊ ሰፈሮችን በማቋቋም ሲቪሎችን ለአደጋ ማጋለጣቸውን ምርመራው አመልክቷል https://www.meseretmedia.org/p/e9f
Open in Telegram#YouTube በሳምንት አንድ ቀን ቅዳሜ በዩትዩብ የምናቀርበው መረጃ ተለቋል፣ በቀጥታ ይከታተሉ https://youtu.be/NU-gm3I5kVs?is=YqCX-CIQK65dAboL
Open in Telegram#አስተያየት | እየተስፋፉ የመጡት ሽልማቶች እና በገንዘብ የማይገዛው እውነተኛው ክብር በአማኑኤል ተስፋሁን ለመሠረት ሚድያ "ሽልማት የብቃትና የስኬት ማሳያ ነው። ይህ ማሳያ ትርጉም የሚኖረው ለማግኘት ጥረትና ብቃት ሲጠይቅ ብቻ ነው። በአንድ የድግስ ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጡ እንግዶችን በመሰብሰብ ወይም ደግሞ የክብረ በዓልን ወይም የኮንሰርትን አዳራሽን ለመሙላት ብቻ ማንም ሊያገኘው የሚችል የክብር ስለተሸላሚው ብቃት ወይም አስተዋጽኦ ምንም አይነግረንም" https://www.meseretmedia.org/p/fe8
Open in Telegramኢትዮጵያ ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመው ግድያ “አስከፊ አዝማሚያ” እያሳየ መሆኑን የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር አስጠነቀቁ https://www.meseretmedia.org/p/620
Open in Telegramከእንጦጦ እስከ ፒኮክ ወንዝ ዳር ልማት ላይ የተሰማሩ ከ600 በላይ አነስተኛ ማህበራት ያጋጠማቸው ጉዳይ ምድን ነው? የወንዝ ዳር ልማቱን ከብድር እና ቁጠባ ተበድረው የሰሩ እነዚህ ጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት ከአንድ ቢልዮን ብር በላይ ክፍያ እንዲቀንስባቸው መደረጉን እያስረዱ ይገኛሉ፣ ዝርዝሩን ይዘናል https://www.meseretmedia.org/p/600-fc5
Open in Telegramበቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ አንዳንድ አመራሮች አማካኝነት ከ30 በላይ የመንግስት ቤቶች በፎርጅድ ዶክመንት ተወስደው ተገኙ ይህ የሀብት ዘረፋ ድርጊት የተጋለጠው ለከተማው ከንቲባ እና የሰላምና ፀጥታ ሃላፊ በቀጥታ በደረሰ ጥቆማ አማካኝነት መሆኑን መሠረት ሚድያ አረጋግጧል https://www.meseretmedia.org/p/30-c16
Open in Telegramየምርጫ አስፈፃሚዎች እና አሰልጣኞች የሰሩበትን ብር ሲጠይቁ "ሂዱልን!" ተብለው እየተባረሩ መሆኑን ተናገሩ "በምርጫው አብላጫ ድጋፍ ያገኘው አካል መንግሥት መስርቶ እና የበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት በተጠናቀቀበት ወቅት የምርጫ ቦርድ በጀት አልተለቀቀም ማለቱ ፍጹም አሳማኝ ሆኖ አላገኘነውም" https://www.meseretmedia.org/p/f62
Open in Telegramመሠረት ሚድያ ለህዝብ የሚያቀርባቸው መረጃዎችን የሚያዘጋጁ 6 ጋዜጠኞች እና 8 ተባባሪ ፀሀፊዎች አሉት። ሚድያችን ማስታወቂያም ሆነ ድጋፍ ከየትኛውም አካል ስለማይቀበል የአንባቢዎችን ድጋፍ ይፈልጋል። ስለዚህ ዛሬውኑ የመሠረት ሚድያ የፕሪሚየም አባል በመሆን ስራችንን ይደግፉ፣ ለሁለት ሳምንት ብቻ በ30% የክፍያ ማስተካከያ አባል ይሁኑ። ሊንክ ⤵️ https://www.meseretmedia.org/subscribe?coupon=fdecd213
Open in Telegram#YouTube በሳምንት አንድ ቀን ቅዳሜ በዩትዩብ የምናቀርበው መረጃ ተለቋል፣ በቀጥታ ይከታተሉ https://youtu.be/U8FXbl8FGYo?is=kbeUZll8NdyrqhY_
Open in Telegram#አስተያየት | መንግስት በቅርቡ ያደረገው የኢኮኖሚ እድገት ክለሳ እና ከቁጥሮቹ ጀርባ የተደበቁት መጪዎቹ መሠረታዊ የምጣኔ ጫናዎች በዳግማዊ ተገኝ ለመሠረት ሚድያ "ማኅበረሰቡ ከመብላት ይልቅ እያጠራቀመ ነው የሚል የተዛባ ድምዳሜ ላይ መደረሱ መንግሥት በመሰረታዊ ሸቀጦች ማለትም በነዳጅ፣ በማዳበሪያ፣ በመብራትና በውኃ ላይ የሚያደርጋቸውን ድጎማዎች ያለምንም ርኅራኄ እንዲያነሳ መንገድ ይከፍታል" https://www.meseretmedia.org/p/196
Open in Telegramትንታኔ: ሹመትና የስራ እድገት የሚያሰጠው የሚድያ ሰራተኞች ስልጠና ስልጠናው ሲጠናቀቅ ተሳታፊች አራቱን የመደመር መጻህፈትን ተፈትነው ከፍተኛ ውጤት ያመጣ ሰልጣኝ ጀማሪ ባለሙያ ቢሆንም የመደመር ፍልስፍና ገብቶታል ተብሎ እድገትና ሹመት ያገኛል መባሉ በሰራተኞች ዘንድ ቅሬታ እና ግርምትን ፈጥራል https://www.meseretmedia.org/p/092
Open in Telegramፓስተር ጥበቡ ወርቅዬን ከለሚ ኩራ ነዋሪዎች ጋር ያጋጨው ጉዳይ ምንድን ነው? ግንባታው በሚካሄድበት ወቅት የፀጥታ አካላት አካባቢውን ከበው ለሶስት ቀናት ያህል ሲጠብቁ ነበር የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ይህም ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል ይላሉ https://www.meseretmedia.org/p/3c5
Open in Telegramኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት የፕሮቶኮል ሀላፊነት ያጨቻቸው አነጋጋሪ ግለሰብ ማናቸው? https://www.meseretmedia.org/p/d19
Open in Telegramቲክቶክ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች እና ይዘት ፈጣሪዎች እገዳ ዙሪያ ለመሠረት ሚድያ ማብራርያ ሰጠ https://www.meseretmedia.org/p/107
Open in Telegram#YouTube በሳምንት አንድ ቀን ቅዳሜ ምሽት በዩትዩብ የምናቀርበው መረጃ ተለቋል፣ በቀጥታ ይከታተሉ https://youtu.be/9fOeStjPT0A?is=WuseJWSMQTUwPTQb
Open in Telegramበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ቡልዲግሉ ወረዳ በታጣቂዎች በተሰነዘረ ድንገተኛ ጥቃት ከ105 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ "በክልሉ እንዲህ አይነት ክስተት አዲስ ባይሆንም በዚህ መጠን ሰው ተጎድቶ አይቼ አላውቅም" https://www.meseretmedia.org/p/105
Open in Telegramየኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ በአርሲ እና በሌሎች አካባቢዎች በንጹሐን ላይ የተፈጸመውን ግድያ እና ውድመት አወገዘ ጳጳሳቱ የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ እና የሕግ አካላት የዜጎችን ሕይወት የመታደግ፣ ንብረት የማስጠበቅ እንዲሁም የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት በአስቸኳይ የመመለስ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አጥብቀው ጠይቀዋል https://www.meseretmedia.org/p/3cb
Open in Telegramበምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ በዛሬው ዕለት ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ዜጎች መገደላቸው ታወቀ፣ የ34 ምዕመናን አስከሬን መገኘቱ ተሰምቷል በስፍራው የተፈጸመው ጥቃት እጅግ አሰቃቂ እና ድንገተኛ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር አሁንም ሊያሻቅብ እንደሚችል ተጠቁሟል https://www.meseretmedia.org/p/34-6a5
Open in Telegram