Account

Posts of ምክረ አበው

newest first

#13535Text
Views493−82%vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—
#13534Text
Views1,210−57%vs avg
Forwards—
Reactions22
Comments—
#13533Text
Views1,490−47%vs avg
Forwards—
Reactions18
Comments—
#13530Photo
Views1,370−51%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#13526Text
Views1,540−45%vs avg
Forwards—
Reactions21
Comments—
#13525Text
Views1,780−36%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#13524Text
Views1,890−32%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—
#13523Text

+ አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +   እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡     ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡     በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ ‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6 ‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10 ‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’  መዝ. 90፡7 እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡ ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡ ‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12 ‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5 ‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31   የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን  መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’  ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡  /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24   አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]   ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ  ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18   ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡   የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡ ’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’  1ዮሐ 1፡9 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Open in Telegram
Views1,860−33%vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—
#13520Photo

በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት «ሚካኤል» የሚለውን እያንዳንዱ ፊደል ሲተረጎም ‹‹ሚ›› ማለት «መኑ» ማለት ነው፤ «ካ» ማለት «ከመ» ማለት ነው፤ «ኤል›› ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ሲሆን ሲገጣጠም «መኑ ከመ አምላክ — ማን እንደ አምላክ/እንደ እግዚአብሔር» ማለት ነው፡፡ ዳን ፲፪፥፩ ፤ ራእ ፲፪፥፯ ይሁዳ ፱ ኅዳር አሥራ ኹለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኀይላት ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ ነው:: ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምላል በታላቅ ክብር ሆኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው። "ከእኛ ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" ባለው ጊዜ:- ❝እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ መጥቻለሁ❞ — አለው። ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና "በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል?" አለው፡፡ የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን:- ❝የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ!❞ — አለው፤ ኢያሱም እንዳለው አደረገ:: ያም መልአክ ኢያሱን:- ❝በውስጧ ያለውን ንጉሧን፣ ከኃያላንና ከአርበኞቹ ጋር ኢያሪኮን በእጃችሁ አስገባታለሁ❞ — ብሎ ተራዳኢነቱን ገልጦለታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የአርምሞና የትሕትና መልአክ ነው:: ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከሚፈጽሙ ድረስ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው እርሱ ነው:: ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ ፲፪ ቀን ለመታሰቢያው በዓል እናደርጋለን፤ እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲያወርድልን፤ የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን፤ ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲያደርግልን፤ ሁሉንም የተስተካከለ እንዲያደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በክንፈ ረድኤቱ ጋርዶ ችግራችንን አስወግዶ ከፈጣሪው እንደሚያስታርቀን ሊቁ በዜማው ሲያመሰጥር:- ❝እስመ ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኀይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ይስአል ለነ ረዳኢ ይኩነነ አመ ምንዳቤነ ሰፊሖ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤሁ — ሚካኤል የኀይል መልአክ ነውና እርሱ ታላቅ ነው። ሥልጣኑም ታላቅ ነው። በችግራችን ጊዜ ይለምንልን ዘንድ ረዳትም ይሆነን ዘንድ ክንፎቹንም ዘርግቶ በላዩ ይጋርዳል❞ — በማለት ዘምሯል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የነፍስም የሥጋም መጋቢ በመሆኑ በቃል ኪዳኑ ታምነው አማላጅነቱን ደጅ ጸንተው ስሙን የጠሩ ሁሉ በነፍስም በሥጋም የሚጠቀሙ ሆነዋል:: (ታሪክ ... ) የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ «ዱራታዎስ» የሚባል አንድ ሰው ነበረ። ሚስቱ ቴዎብስታ ትባላለች። ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የቅዱስ የሚካኤልን የበዓሉ መታሰቢያ ያደርጉ ነበር። በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ። ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትም አንዳች አጡ። ዱራታዎስም የበዓሉ መታሰቢያ መታጎል የለበትም ብሎ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ሊሽጥ ወደ ገበያ ይዞ ወጣ። ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት፤ ወደ ባለበጎች ሄዶም በእርሱ ዋስ በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ ዳግመኛም ወደ አሣ አጥማጅ ሄዶ አንድ አሣ እንዲወስድ አዘዘው። ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ። ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ቤቱ በበረከት ተመልቶ አገኘው:: እጅግም አደነቀ የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደው አደረገ:: የተራቡ ድሆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸው:: ከዚህም በኋላ አሣውን ቢሰነጥቀው ፫፻ የወርቅ ዲናር በአሣው ሆድ ውስጥ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው:- ❝ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውን ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ:: በኋለኛውም መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል❞ አላቸው። እነርሱም ይህን ሲሰሙ ደነገጡ፡፡ እርሱም:- ❝ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ መሥዋዕታችሁንና ምፅዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም❞ አላቸው:: ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ። እስራኤል ዘሥጋን ከግብፅ የባርነት ኑሮ ነጻ አውጥቶ፣ መና አውርዶ፣ ደመና ጋርዶ፣ አለት ሰንጥቆ፣ ውኃ አፍልቆ፣ ጠላት ገድሎ፣ ባሕር ከፍሎ እየመራ ምድረ ርስት ያስገባቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው:: በዚህም ‹‹መጋቤ ብሉይ» የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ስለዚህ ገናና መልአክ:- ❝መርሖሙ መዓልተ በደመና ወኵሎ ሌሊተ በብርሃነ እሳት ወአውፅኦሙ ለሕዝቡ በትፍሥሕት ፈነወ መልአኮ ወአድኀኖሙ እንዘ ሚካኤል የሐውር ቅድመ ትዕይንቶሙ ለእስራኤል — ሚካኤል ቀን በደመና ሌሊት በብርሃነ እሳት መራቸው፣ በእስራኤል በጎዳናቸው ፊት ፊት እየሔደ ሕዝቡን በደስታ አወጣቸው፤ መልአኩን ላከ አዳናቸው❞ — በማለት ታዳጊነቱን ዘምሯል፡፡ ዳግመኛም ቅዱስ ሚካኤል እስራኤል ሲበድሉ እያማለደ፤ ሲራቡ እየመገበ ሲደክሙ እያበረታ፤ ልብሳቸውና ጫማቸው እንዳያልቅ አድርጎ ዐርባ ዓመት ሙሉ ተንከባክቦ እንደ ጠበቃቸው ቅዱስ ያሬድ በድጓው እንዲህ ይገልጠዋል:- ❝ባሕረ ግርምተ ገብረ ዐረፍተ ወበውስቴታ አርአየ ፍኖተ በእደ መልአኩ አቀቦሙ በገዳም ለሕዝቡ አርብዐ ዓመተ ወሲሳዮሙ መና ኅብስተ ኪነ ጥበቡ ዘአልቦ መሥፈርተ — ለጥበቡ መስፈርት የሌለው አምላክ አስፈሪ ባሕርን ግድግዳ አደረገ፤ በውስጧም መንገድን አሳየ፤ በመልአኩ እጅ ጠበቃቸው፤ አርባ ዓመት ሙሉ በዱር ኅብስተ መናን መገባቸው❞ — በማለት ተናግሯል፡፡ ነቢዩ ዳንኤልም ስለወገኖቹ ስለእስራኤል ነጻነት ሲል ከፋርስ ንጉሥ በሚያደርገው ትግል ቅዱስ ሚካኤል ሊረዳው እንደመጣ መስክሯል። ነቢዩ ዳንኤል የተናገረውንም የምስክርነት ቃል ሊቁ እንዲህ ሲል በዜማ ይገልጠዋል:- ❝ይቤ ነዋ ሚካኤል አሐዱ አመላእክት እምቅዱሳን ቀደምት መጽአ ይርድአኒ አጽንዐኒ ወይቤለኒ ኢትፍራህ ብእሴ ፍትወት አንተ ሰላም ለከ ጽናዕ ወተዐገሥ ወእንዘ ይትናገረኒ ፀናዕኩ ወእቤሎ ንግረኒ እስመ አጽናዕከኒ ወይቤለኒ ሶብ ተአምር ዳዕሙ ሚካኤል መልአክ — ቀደምት ከሆኑ ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ አለ፤ አፀናኝ አትፍራም አለኝ፤ ብእሴ ፍትወት ዳንኤል ሆይ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ጽና፤ ታገሥ ብሎ ሲናገረኝ ጸናሁ፣ መልአኩ ሚካኤል ሆይ አጽንተኸኛልና ንገረኝ አልኩት❞ — በማለት ዘምሯል፡፡ «ብእሴ ፍትወት» የሚለው ስም ለነቢዩ ለዳንኤል የተሰጠው ሰማያዊ መጠሪያ ነው:: ነቢዩ ዳንኤል እስራኤል ከአምላካቸው ጋር በተጣሉ ጊዜ በአምላኩ ፊት ሞገስን ያገኘ ሰው ነው፤ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ተቀምጦ ከጾም ከጸሎት ያልተለየ፤ በፍጹም እምነት አላውያን ነገሥታትን የተቋቋመ፤ ያለፍርሃት እውነትን የተናገረ፤ በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅ ሰው ነውና መልአኩ ❝የተወደድክ ዳንኤል ሆይ!❞ ብሎ ጠርቶታል — (ዳን ፲፥፲፫)። ነቢዩ ዳንኤል ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃ ለሰው ምሕረትን ሲለምንና የክብር ንጉሥ በአዕላፍ መላእክት ታጅቦ ወደ እርሱ ሲመጣ ማየቱን ቅዱስ ያሬድ:- (፩/፪) የዚህ ጽሑፍ ቀጣይ ክፍል ከስር ባለው ጽሑፍ ይቀጥላል:- ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

Open in Telegram
Views2,640−6%vs avg
Forwards—
Reactions27
Comments—
#13519Text

ዘመነ አስተምሕሮ ከኅዳር ፮ እስከ ታኅሣሥ ፲፫ ያለው ወቅት ሲሆን ቃሉ "አስተምሕሮ"  ፪ ትርጉም አለው። ይኸውም፦ ፩. በሐመሩ «ሐ» (አስተምሕሮ) በሚለው ከተጻፈ ምሕላ፣ ምልጃና ልመና ይቅርታ ማለት ነው፡፡ ይህም «መሐረ» ይቅር አለ፣ በደልን ተወ፣ ወይም «አምሐረ» አስማረ፣ ይቅር አሰኘ፣ አራራ ከሚለው ሥርወ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ዘመነ አስተምሕሮ ስለ እግዚአብሔር ቸርነትና ርኅራኄ የምንመሰክርበት እርሱ በደላችንን ሁሉ ይቅር ብሎ ሊታረቀን ከስማይ መውረዱን ከድንግል ማርያም መወለዱን የምናዘክርበት እንዲሁም እርሱ ይቅር እንዳለን ተገንዝበን እኛም እርስ በእርሳችን ይቅር መባባል እንደሚገባን ትምህርት የሚሰጥበት ወቅት ነው፡፡ በተለይ ይህ ዘመነ አስተምሕሮ ቤተክርስቲያን ስለ ልጆቿ ምልጃ የምታቀርብበት፤ ምእመናንንም ስለ በደላቸው ይቅርታ የሚጠይቁበት ዘመን ነው፡፡ ፪. በሃሌታው «ሀ» (አስተምህሮ) በሚለው ከተጻፈ ትምህርት ሥርዓት ማለት ነው። አስተምህሮ የሚለው ቃል «መሀረ» አስተማረ፣ መከረ፣ ዘከረ ከሚለው ሥርወ ግሥ የተገኘ ነው። ይኸውም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ ርኅራኄ፣ ትዕግሥትና የማዳን ሥራው በቤተክርስቲያን በስፋት የሚሰበክበት ጊዜ ስለሆነ ወቅቱ ዘመነ አስተምህሮ ተብሏል፤ የሥርዓትና የትምህርት ወቅት ማለት ነው፡፡ "ፊደል አይቀነስም" ብለው ሊቃውንቱ የሚሟገቱት ከዚህ የተነሣ ነው፤ እነዚህ ተመሳሳይ ድምፅ ያላቸው ፊደላት በአገባባቸው ሰፊ የትርጉም ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉና! ፊደላት ጥበብ ከመሆናቸውም በላይ ያለ ድርሻና ያለዓላማ እንዲሁ ለጌጥ የተቀመጡ ፊደላት የሉም። እያንዳንዳቸው በአገባባቸው የትርጉም የምሥጢር ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉበት ድርሻ አላቸው። በተለይ በልሳነ ግዕዝ አጠቃቀም የፊደላት አገባብ ትልቅ የትርጉም ለውጥና ተፋልሶ ያመጣሉ። ለምሳሌ፦ «ሠረቀ እና ሰረቀ» በእነዚህ ግሦች ከአንድ ፊደል የተነሣ መሠረታዊ የትርጉም ልዩነት አላቸው። «ሠረቀ» ሲል ወጣ፤ ተወለደ ማለት ሲሆን ፤ «ሠረቀ ለነ ፀሐየ ጽድቅ - የጽድቅ ፀሐይ ወጣልን፤ «ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ዘእበለ ዘርአ ብእሲ ወአድኃነነ፤ ያለወንድ ዘር ከድንግል በሥጋ ተወለደ» ይላል፡፡ «ሰረቀ» ሲል ደግሞ ሰረቀ፣ ዘረፈ የሚል ትርጉም አለው። ❝ኢትስርቁ ትብል ወለሊከ ትስርቅ — አትስረቁ ትላለህ አንተ ግን ትስርቃለህ❞ — እንዲል ሮሜ ፪፥፳፩። ሌላ ምሳሌ ብንወስድ፦ «ዓመት እና አመት» በሚሉት ቃላት ትልቅ የትርጉም ልዩነት አላቸው። «ዓመት» ከሆነ ዘመን የሚል ትርጉም ሲኖረው፤ «አመት» ሲል ደግሞ ገረድ/አገልጋይ ማለት ነው። ❝ነየ አመቱ ለእግዚአብሔር - እነሆ የእግዚአብሔር አገልጋዩ በፊቱ አለሁ❞ እንዳለች እመቤታችን። ሌላ ምሳሌ ብንወስድ፦ «በዓል እና በአል» የሚለውን ቃል ብንመለከት ሁለት ትርጉም ይሰጡናል። «በዓል» በሚለው ከሄድን ክብረ በዓል፣ ዓመታዊ የመታሰቢያ ቀን ማለት ነው፤ «በአል» በሚለው ብንመለከት ደግሞ ጣዖት የሚል ትርጉም ይሰጠናል። በዚህ መልኩ ተመሳሳይ ድምዕ ያላቸው ነገር ግን በአካላዊ ገጽታ የሚለያዩ ፊደላት የራሳቸው አገባብ ስላላቸው ሰዎች ማወቅ አውቆም መጠቀም ሲከብዳቸው ይቀነስልን የሚሉ 'ዘመናዊ' ሰዎችን ማየት ትንሽ ምቾት የማይሰጥ አሳፋሪ ጉዳይ ነው፡፡ አባቶቻችን ለእነዚህ ፈደላት ሲሉ ነው ደማቸውን ያፈሰሱት አጥንታቸውን የከሰከሱት፡፡ እኛ ዘመን አድርሰውልናል እንግዲህ መጠበቅና ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ የእኛው ዕዳ ነው። በቤተክርስቲያናችን የዘመን አከፋፈል መሠረት ከኅዳር ፮ ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ፯ ወይም ፲፫ ቀን ድረስ ያለው ወቅት ዘመነ አስተምሕሮ ተብሎ ይጠራል። በዘመነ አስተምህሮ የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ ታጋሽነትና ይቅር ባይነት በየጊዜው የሰዎችን በደል ሳይመለከት የቸርነቱን ሥራ መሥራቱን፣ ለሰዎች የዕረፍት ቀን እንዲሆን ሰንበትን መቀደሱ ይታሰባል፡፡ በተለይ ደግሞ ቅዱሳን ነቢያት ስለ ክርስቶስ መምጣት የቆጠሩት ሱባኤ የመሰሉት ምሳሌ የተናገሩት ትንቢት፣ የጸለዩት ጸሎት፣ የጾሙት ጾም የሚዘከርበት ሰሞን ነው። ይቀጥላል ..... ዲ/ን ኃይለራጉኤል

Open in Telegram
Views3,300+18%vs avg
Forwards—
Reactions22
Comments—
#13514Text

#ኅዳር_6 #ደብረ_ቁስቋም ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡ ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡ እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡ ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ። (ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር ፮)

Open in Telegram
Views4,130+48%vs avg
Forwards—
Reactions38
Comments—
#13511Text
Views4,650+66%vs avg
Forwards—
Reactions28
Comments—
#13510Photo
Views4,320+55%vs avg
Forwards—
Reactions20
Comments—
#13509Photo

የመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ስለምን ጥቅምት ፳፯ ይከበራል❓❓❓ ጥቅምት ፳፯ ቀን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የመድኃኔዓለም (የኢየሱስ ክርስቶስ) ዓመታዊ የ«ጥንተ ስቅለት» መታሰቢያ በዓል ሆኖ በደማቁ ይከበራል። ይህ በዓል በጥቅምት ፳፯ ቀን እንዲከበር የተደረገበት ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦ ፩./ የበዓል መዛወር (የለውጥ በዓል)፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በቀራንዮ መስቀል ላይ የተሰቀለውና ደሙን ያፈሰሰው መጋቢት ፳፯ ቀን ነው። ነገር ግን ይህ ቀን አብዛኛውን ጊዜ በዐቢይ ጾም (በሁዳዴ ጾም) ወቅት ይውላል። በዐቢይ ጾም ወቅት ደግሞ የሐዘንና የጸሎት እንጂ ከበሮ የሚመታበት፣ እልልታና የደስታ ዝማሬ የሚሰማበት የንግሥ በዓል ማክበር በቤተክርስቲያን ሥርዓት አይፈቀድም። ስለዚህ ምእመናን የበዓሉን በረከት በደስታና በምስጋና እንዲያከብሩት አባቶች ሊቃውንት መጋቢት ፳፯ የሚውለውን የጥንተ ስቅለት በዓል ወደ ጥቅምት ፳፯ ቀን አዙረው እንዲከበር ሥርዓት ሠርተዋል። ፪./ የማዳን ሥራውን ለማሰብ፦ በዚህ ዕለት ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል የተቀበላቸው ዐሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል፣ መከራውና በሞቱ ሞትን ሽሮ ዓለምን ነጻ ማውጣቱ በሰፊው ይታሰባል። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን አሜን።

Open in Telegram
Views4,180+50%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#13508Text
Views3,860+38%vs avg
Forwards—
Reactions36
Comments—
#13506Text
Views4,540+62%vs avg
Forwards—
Reactions36
Comments—
#13504Text

አንዳንድ ሰው ነሐስን ቀጥቅጦ እጅግ ውብ ቅርጽ እንዲኖረው፣ በላዩ ላይም የተለያየ ዓይነት ሐረግ በማውጣት የማሳመር ችሎታ አለው፡፡ ሌላው ሰው ደግሞ ጥቃቅን ዕንጨቶችን አገጣጥሞ በመሥራት ማንም ሰው ሊሰብረው የማይችል ውብ ጠረጴዛ የመሥራት ችሎታ አለው፡፡ ሦስተኛው ሰው እጅግ ውብ የኾነ ክር የመፍተል ችሎታ አለው፡፡ አራተኛው ሰው ደግሞ ይህን የመሸመን ችሎታ አለው፡፡ አምስተኛው ሰው ድንጋይ በድንጋይ ላይ በማኖር ቤት የመገንባት ችሎታ አለው፡፡ ስድስተኛው ሰው ደግሞ በተገነባው ቤት ላይ ጣሪያ የመክደን ችሎታ አለው፡፡ እዚህ ልንዘረዝራቸው የማንችላቸውና እነርሱን ለመማር ብዙ ዓመታትን የሚፈጁ ሌሎች ሙያዎችም አሉ፡፡ ባለጸጎች ሊኖራቸው የሚገባ ችሎታስ ምንድን ነው? ነሐስ መቀጥቀጥ፣ ወይም ዕንጨቶችን መገጣጠም፣ ወይም ቤቶችን መሥራት የሚችሉበት ሙያ አያስፈልጋቸውም፡፡ እነርሱ ሊማሩት የሚገባው ሙያ ሀብታቸውን እንደ ምን ሊጠቀሙበትና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችንም እንዴት ሊጠቅሙ እንደሚገባ ነው፡፡ አንድ እደ ጥበበኛ “ይህን መማር’ማ ቀላል ነው” ብሎ ሊያስብ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከኹሉም ይልቅ እጅግ ከባዱ ሙያ ይኼ ነው፡፡ ይህን ማወቅ ከፈለጋችሁም ስንት ባለጸጎች ይህን ማድረግ እንዳቃታቸውና ወደ ጽድቅ ሕይወት የሚመጡት እጅግ ጥቂቶች እንደ ኾኑ ተመልከቱ፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች መጽሐፍ) @mekra_abaw

Open in Telegram
Views5,340+91%vs avg
Forwards—
Reactions22
Comments—