Account

Posts of ይሰግዱ ሎቱ YSEGDU LOTU

newest first

#8214Text
Views30+62%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
19 h18
31 h30
  1. After 24 hours18
  2. Total to date30
#8213Text
Views29+57%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
19 h19
31 h29
  1. After 24 hours19
  2. Total to date29
#4586Photo
Views13,100×708vs avg
Forwards—
Reactions28
Comments—
#2402Photo
Views13,200×714vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#2400Text

ሕማማተ ረቡዕ ✝️ በዚህ ቀን ፀሐፍት ፈሪሳውያን ጌታችንን ለመያዝ ፣ ይዘውም ለመስቀል የመከሩበት ቀን ነው ✝️ በዚህ ቀን ሦስት ታላላቅ ነገሮች እንደተከናወኑ መጽሐፍ ቅዱሳችን ይነግረናል ፩. ምክረ አይሁድ ➻ በዚህች ዕለት አይሁድ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ኢየሱስን ለመያዝ የመከሩበት፣ ምክራቸውንም ያጸኑበትና ሰቅለው ይገድሉት ዘንድ የወሰኑበት ነው " በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፥ ኢየሱስንም በተንኰል ሊያስይዙት ሊገድሉትም ተማከሩ።" ማቴ.፳፮፥፫-፬ /26፥3-4/ ➻ ጊዜው የፋሲካ በዓልን የሚያከብሩበት ወቅት በመሆኑና ብዙ ሕዝብ በትምህርቱ የተማረኩ በመሆናቸው እንዴት እንደሚይዙት ተጨነቁ ➻ ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም በገንዘብ ፍቅር የወደቀው የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን ስሞ ሊሰጣቸው ለዚያም ሠላሳ ብር ሊከፍሉት ተስማሙ ➻ ይሁዳም የነበረባቸውን ጭንቀት አስወገደላቸው ጌታውን በገንዘብ ለወጠ ፪. የመልካም መዓዛ ቀን ➻ ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ተቀምጦ ሳለ ዘመንዋን በሙሉ በዝሙት ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት "ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ውድ ሽቱ ገዝታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ቀባችው " ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግር ቀባች፤ በጠጕርዋም እግሩን አበሰች፤ ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ።" ዮሐ.፲፪፥፫ /12፥3/ ➻ በዚህም ዕለቱ "የመልካም መዓዛ ቀን" ተባለ ➻ ማርያም እንተ እፍረትም በዚህ በጎ ተግባርዋ መልካም መዓዛ ያላት ሆና ወደ ቤትዋ ተመልሳለች ፫. የዕንባ ቀን ➻ በዚያው ቀን ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መለሠ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እያነባች ጠየቀች ➻ በዕንባዋ እግሩን እያጠበች በፀጉሯም እግሩን እያበሰች ሥለ ኃጢአቷ ሥርየት ተማፅናዋለችና ቀኑ "የዕንባ ቀን" ተባለ ዛሬም በማወቅም ይሁን ሳናው የሰራነውን ኃጢአት ይቅር የሚል አምላክ አለንና በንስሐ እየታጠብን ይቅርታን እንጠይቅ።

Open in Telegram
Views6,790×367vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—
#2319Photo
Views7,520×406vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#2027Photo
Views11,400×616vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#1791Photo
Views8,410×455vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#1319Audio
Views7,190×389vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#1318Audio
Views4,850×262vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#1284Photo
Views4,280×231vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#1283Photo
Views5,250×284vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#1233Link preview

Forwarded from ✟ ጋሜል- ዘ ኦርቶዶክስ ✟

💮 ​​​​✝️ ጾመ ነብያት ✝️ 💮      ➡️ ጾመ ነቢያት የገና ጾም ከልደት አስቀድሞ የሚጾም ጾም ነው፡፡ ከህዳር ፲፭ 15 ጀምሮ ለ ፵፫ 43 ቀናት የሚጾም ሲሆን ፋሲካው ፍቺው በልደት በዓል ነው፡፡ ይህም ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳንና ምዕመናን ጾመውታል፡፡ ➡️ ጾመ ነብያት ስያሜውን ያገኘው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት ነው፡፡ በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምስጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ ፣ የረቀቀው ገዝፎ ጎልቶ እየተመለከቱ ትንቢት ተናገሩ ፤ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ጾሙ ጸለዩ፡፡ ➡️ ነቢያት ከእመቤታችን ስለ መወለዱ ፥ ወደ ግብፅ ስለ መሰደዱ ፥ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ ፥ ብርሃን በሆነው ትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ ፥ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ ፥ ስለ ትንሣኤው ፥ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፡፡ ለአዳም የተሠጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው ፦ "አንሥእ ኃይልከ ፣ ፈኑ እዴከ" እያሉ ጮኹ፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም እግዚአብሔር ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት ፣ በሳምንታት ፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ፬፵፮ ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡ ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር ፦ "አያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር" ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩ እነ ነቢዩ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም፡፡ ኢሳ.፶፰፥፩፡፡ በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለተፈጸመበት ይህ ጾም "የነቢያት ጾም" ይባላል፡፡ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ስለሆነም "ጾመ ስብከት" ይባላል፡፡ ➡️ ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፦ ✨፩. ጾመ አዳም ✨፪. ጾመ ነቢያት ✨፫. ጾመ ሐዋርያት ✨፬. ጾመ ማርያም ✨፭. ጾመፊልጶስ ✨፮. ጾመ ስብከት ✨፯. ጾመ ልደት ➦ ጾመ አዳም፦ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገነት ከተባረረ በኋላ በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ ፤ አለቀሰ እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ፣ በደጅህ ድኼ ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡" የሚል ነው፡፡ ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት "ጾመ አዳም" ይባላል፡፡ ➦ ጾመ ነቢያት፦ ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው ፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች : ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም : ቅዱስ ሙሴ : ቅዱስ ኤልያስ ፣ ቅዱስ ዳንኤልና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: ዘዳ.፱፥፲፱ ፣ ነገ.፲፱፥፰ ፣ ዳን.፱፥፫ መዝ.፷፰፥፲ ፻፰፥፳፬ ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል:: ➦ ጾመ ሐዋርያት፦ ሐዋርያት "ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን ፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?" ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡ ➦ ጾመ ማርያም፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና "ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?" ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና "ጾመ ማርያም" ይባላል፡፡ ➦ ጾመፊልጶስ፦ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት ፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡ ➦ ጾመ ስብከት፦ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት ፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡ ➦ ጾመ ልደት ፦ የጾሙ መጨረሻ መፍቻ በዓለ ልደት ስለሆነ "ጾመ ልደት" ይባላል፡፡ ጾሙን የኃጢአታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን። ❤️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❤️

Open in Telegram
Views4,950×268vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#1058Audio

ኪዳነ ምሕረት ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ ✞ ኪዳነ ምሕረት ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ/፪/ እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ ኧኸ እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ/፪/ የነፍሴ ትምክሕት ሁኚኝ ጥላዬ እያማለድሽኝ ከቸር ጌታዬ ማዕረጌ ጌጤ የልቤ ቅኔ ሳመሰግንሽ ይለፍ ዘመኔ ኪዳነ ምሕረት እናቴ የነፍሤ መጽደቂያ ሁኚኝ/፪/ እንደ ለመንኩሽ አንቺም ተለመኚኝኝ/፪/ አለሽ ቃል ኪዳን የማይታጠፍ ትውልድ የሚያስምር ለዓለም የሚተርፍ በክብር ያለሽ በእግዚአብሔር ቀኝ ለጻድቅ አይደል ለሐጥዕ ለምኝ ኪዳነ ምሕረት ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ/፪/ እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ/፪/ ነፍሴ ከቅጽርሽ ተጠግታለች በፍቅር ሥምሽ ትማልላለች ልቤን አኑሬ በብርታትሽ ላይ ከአንቺ ጋር ልኑር ሞትን እንዳላይ ኪዳነ ምሕረት እናቴ የነፍሴ መጽደቂያ ሁኚኝ /፪/ እንደ ለመንኩሽ አንቺም ተለመኝኝ/፪/ በርሕራሔው በቸርነቱ በፍቅር እንዲያየኝ በምሕረቱ ብለሽ ንገሪው መሐር ወልድየ የኃጢአቴ ቀንበር ይውረድ ከላየ ኪዳነ ምሕረት ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ/፪/ እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ /፪/

Open in Telegram
Views3,990×216vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#1046Photo
Views2,860×155vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—