Account

Posts of ለልጄ - LeLije

newest first

#450Photo

የሕጻናት አመጋገብ (ከ6 እስከ 8 ወር) (ሊንክ፦ ሕጻናት ምግብ ለመጀመር ዝግጁ ሲሆኑ በምን ይታወቃል?) (ሊንክ፦ የሕጻናት አመጋገብ እስከ 6 ወር ዕድሜ) በቀን ምን ያህል እና እንዴት መመገብ ያስፈልጋል? 👉🏾 በዚህ ጊዜም የሕጻናት ዋና ምግብ የጡት ወተት (ካልተቻለ ደግሞ የሕጻናት ወተት/ “ፎርሙላ) ቢሆንም፣ ጠጣር ምግብ መጀመር አለባቸው። 👉🏾 ልጅሽ በመጀመሪያ ሙከራ አልበላ ካለች፣ ጥቂት ቀናት ቆይተሽ ደግመሽ ሞክሪ። 👉🏾 ምግብ ሲጀምር ቅይጥ ነገሮችን ከመመገብ ይልቅ፣ በአንድ ዓይነት ነገር መጀመር ይሞከራል። እንዲህ ማድረጉ ምናልባት ልጅሽ አለርጂ ይኖርባት እንደሁ በቀላሉ ለመለየት ያስችላል። 👉🏾 መጀመሪያ ሰሞን በትንሹ (ከአንድ ወይ ሁለት የሻይ ማንኪያ ያልበለጠ) ምግብ መጀመር ይመከራል። 👉🏾 ቀስ በቀስ መጠኑን ወደ አንድ ወይ ሁለት የሾርባ ማንኪያ ከፍ ማድረግ፣ ምግቡንም እየቀየጡ መሄድ ይቻላል። 👉🏾 ሕጻናት ምግብ ይበልጥ እየለመዱ ሲሄዱ፣ ዓይነቱን እያበዙ እና በቀን ለበርካታ ጊዜ እየመገቡ መሄድ ይቻላል። 👉🏾 አዲስ ምግብ ሲያስጀምሩ ሁልጊዜም በትንሽ መጠን (በአንድ ወይም ሁለት የሻይ ማንኪያ) መጀመር ይመከራል፤ ይህም ልጅሽ አዲሱን ጣዕም እንድትላመድ ያግዛታል። 👉🏾 ሕጻናት እስከ 8 ወር ዕድሜያቸው በአብዛኛው አንድ ወይ ሁለት ጊዜ ብቻ በቀን ሊበሉ ይችላሉ። ከምን ምግቦች መጀመር ይሻላል? 👉🏾 የደቀቀ ፍራፍሬ (በተለይ ሙዝ እና አቮካዶ) 👉🏾 የደቀቀ እና የበሰለ አትክልት 👉🏾 የላመ እና በደንብ የበሰለ ሥጋ 👉🏾 የእህል ገንፎ #አራስ #አራስ_ልጅ #ሕጻን #አመጋገብ #6_ወር #7_ወር #8_ወር #አንደኛ_ዓመት Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views76−72%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#449Photo

ለወሊድ ወደ ጤና ተቋም ስሄድ ምን ልያዝ? እርግዝናሽ 36 ወይ 37 ሳምንት ከሆነው በኋላ፣ ድንገት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ቢኖርብሽ የሚከተሉትን ይዞ ለመሄድ አዘጋጅቶ መቆየት ይመከራል፦ 👉🏾 መታወቂያ 👉🏾 ምቹ ልብስና ጫማ (ከወለድሽ በኋላ ለመልበስ የሚመችሽ ለቀቅ ያለ ፒጃማ፣ ምቹ የሆነ “ታይት”፣ ካልሲ፣ ሰፋ የሚልሽ ጫማ (እግርሽ ሊያብጥ ስለሚችል)፣ ሻሽ 👉🏾 የመኝታ ጋወን 👉🏾 ጋቢ/ፎጣ 👉🏾 የሚመችሽ ትራስ 👉🏾 የጥርስ ብሩሽና ሳሙና፣ የሚስማማሽ ቅባት/ክሬም/ቫዝሊን፣ ቻፕስቲክ እና የመሳሰሉት 👉🏾 ስልክ እና ቻርጀር (እንዲሁም ለፎቶ/ቪዲዮ በቂ የሆነ “ሜሞሪ”) 👉🏾 የወር አበባ መጠበቂያ “ፓድ” (ከወሊድ በኋላ ለሚኖር ማንኛውም ከማኅጸን የሚወጣ ፈሳሽ) 👉🏾 የአዋቂ ዳይፐር (ለማንኛውም) 👉🏾 ለማንኛውም ሌላ ጉዳይ እየወሰድሽ ያለሽው ማቋረጥ የሌለብሽ መድኃኒት ካለ 👉🏾 ጥሬ ገንዘብ ወይም “የኤቲኤም” ካርድ (በጥንቃቄ የሚያዝ፣ አብሮ ያለ ሰው ቢይዘው የሚሻል) ለመጪው ሕጻን፦ 👉🏾 የአራስ ዳይፐር እና መጥረጊያ “ዋይፕ” 👉🏾 ጡጦ (ለማንኛውም - በተለይ በኦፕራሲዮን የምትወልጂ ከሆነ) 👉🏾 የአራስ ሕጻን ልብስ (ለማልበስ የማያስቸግር) 👉🏾 መጠቅለያ እና መታቀፊያ የምትወልጂበት ተቋም የሚያቀርበው ተጨማሪ ነገር ይኖር ከሆነ ቀድሞ በማጣራት (ለምሳሌ ዳይፐር እና ዋይፕ የሚያቀርብ ከሆነ) አንዳንድ ነገሮችን መያዝ ላያስፈልግሽ ይችላል። ምን ቀረ? ምን ይጨመር? አስተያይት መስጫው ላይ በማከል ያሳውቁን👇🏾 #እርግዝና #ወሊድ #ጤና_ተቋም Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views104−62%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#448Photo

ሕጻናት ምግብ ለመጀመር ዝግጁ ሲሆኑ በምን ይታወቃል? ሕጻናት 6 ወር እስኪሞላቸው ድረስ የሚመከረው የጡት ወተት ብቻ እንዲጠቡ (ካልተቻለም የሕጻናት ወተት/ፎርሙላ እንዲጠቡ) ነው። (ሊንክ፦ የሕጻናት አመጋገብ እስከ 6 ወር ዕድሜ) ሕጻናት 6 ወር ከሞላቸው በኋላ ግን የሚያስፈልጓቸውን ከጡት ወተት የሚያስፈልጓቸውን ንጥረ ነገሮች ሁሉ አያገኙም። የጡት ወተት በተለይ እስከ አንድ ዓመት ዕድሜ አንዱ ወሳኝ የምግባቸው አካል ሆኖ ቢቀጥልም፣ በ6 ወር ዕድሜ ተጨማሪ ምግብ መጀመር ይኖርባቸዋል። አንዳንድ ሕጻናት ገና 6 ወር ሳይሞላቸው ምግብ ለመጀመር ዝግጁ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ሆኖም የቱንም ያህል ቢቀድም ከ4 ወር በፊት ጠጣር ምግብ መጀመር የለባቸውም። ሕጻናት ጠጣር ምግብ ለመጀመር ዝግጁ ሲሆኑ በሚከተሉት ይታወቃል፦ 👉🏾 ራሳቸውን (ጭንቅላታቸውን) በራሳቸው መደገፍ ይችላሉ 👉🏾 የሕጻናት ወንበር ላይ ወይም በድጋፍ መቀመጥ ይችላሉ 👉🏾 ጉልህ የሆነ የክብደት ጭማሪ ያሳያሉ (ሲወለዱ ከነበረው እጥፍ ይመዝናሉ)፤ ቢያንስ 6 ኪሎ ይሆናሉ 👉🏾 ማንኪያ እንደጎረሱ አፋቸውን መግጠም ይችላሉ 👉🏾 የጎረሱትን ምግብ ወደ አፋቸው ውስጠኛ ክፍል መግፋት ይችላሉ ሕጻናት ምግብ ሲጀምሩ በምን ያህል መጠን እና በምን ዓይነት ምግብ ማስጀመር ይሻላል የሚለው ላይ እንመለሳለን። #አራስ #አራስ_ልጅ #ሕጻን #አመጋገብ #6_ወር #አንደኛ_ዓመት Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views165−39%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#447Photo

እርግዝና እና የፎሊክ አሲድ አወሳሰድ በእርግዝና ጊዜ ልጅሽ በጤና እንዲያድግ ፎሊክ አሲድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የፎሊክ አሲድ እንክብል መውሰድሽ በልጅሽ ላይ የነርቭ ቱቦ ችግር የመከሰት አደጋን ይቀንሳል። (ሊንክ፦ ፎሊክ አሲድ ምንድን ነው? ከምን ከምን ይገኛል?) (ሊንክ፦ ፎሊክ አሲድ ምን ይጠቅማል?) (ሊንክ፦ ፎሊክ አሲድ እና ስፒና ቢፊዳ) ፎሊክ አሲድ ምን ያህልና ከመቼ ጀምሮ መውሰድ አለብኝ? 👉🏾 ለማርገዝ ከመሞከርሽ በፊት (12 ሳምንት ድረስ ቀደም ብለሽ) ጀምሮ፣ አርግዘሽ 12 ሳምንት እስኪሆንሽ ድረስ ፎሊክ አሲድ መውሰድ አለብሽ። (እንደውም የመውለጃ ዕድሜ ላይ የደረሱ ሴቶች ሁሉ ፎሊክ አሲድ እንዲወስዱ ይመከራል) 👉🏾 በዚህ ጊዜ በየቀኑ አንድ 400 ማይክሮ ግራም የፎሊክ አሲድ እንክብል መውሰድ አለብሽ። 👉🏾 ፎሊክ አሲድ ያለ ሐኪም ማዘዣ ከመድሃኒት ቤት መግዛት ይቻላል። 👉🏾 ከፎሊክ አሲድ እንክብሎች በተጨማሪ ፎሌት የሚገኝባቸው እንደ አትክልት፣ ብርቱካን፣ አቮካዶ፣ ጥራጥሬ ያሉ ምግቦችን ተመገቢ። (ሊንክ፦ ፎሊክ አሲድ ከምን ከምን ይገኛል?) ፎሊክ አሲድ መውሰድ የሚያስከትለው አደጋ አለ? በአጠቃላይ የፎሊክ አሲድ በትክክለኛ መጠን መውሰዱ አደጋ አያስከትልም፤ ሰውነታችን ከሚያስፈልገው በላይ የሆነ ፎሊክ አሲድን በሽንት ያስወግዳል። ፎሊክ አሲድ የመውሰድ የጎንዮሽ ምልክቶችና አለርጂ አንዳንድ ሰዎች የሚከተሉት አነስተኛ የጎንዮሽ ምልክቶች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ፦ 👉🏾 የአፍ መምረር 👉🏾 ማቅለሽለሽ 👉🏾 የምግብ ፍላጎት ማጣት 👉🏾 ግራ የመጋባት ወይም የብስጭት ስሜት 👉🏾 የእንቅልፍ መዛባት ፎሊክ አሲድ መውሰድ ስትጀምሪ የሚከትሉት የአለርጂ ምልክቶች ከታዩብሽ ወደ ሐኪም መሄድ ይኖርብሻል፦ 👉🏾 ቆዳ ላይ ሽፍ ማለት 👉🏾 ማሳከክ 👉🏾 የቆዳ መቆጣት/መቅላት 👉🏾 ሲተነፍሱ መቸገር Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views175−35%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#446Photo
Views202−25%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#445Photo

ፎሊክ አሲድ እና ስፒና ቢፊዳ ስፒና ቢፊዳ ምንድን ነው? (ሊንክ፦ እርግዝና እና ፎሊክ አሲድ - ፎሊክ አሲድ ምንድን ነው? ከምን ከምን ይገኛል?) (ሊንክ፦ እርግዝና እና ፎሊክ አሲድ - ፎሊክ አሲድ ምን ይጠቅማል?) ስፒና ቢፊዳ ሕጻናት የጀርባ አጥንታቸው (ሰረሰርን የሚይዘው) እና ሰረሰራቸው በሚገባ ሳያድግ ሲቀር የሚከሰት ከውልደት ጀምሮ የሚያጋጥም ችግር ነው። ስፒና ቢፊዳን የሚያስከተለው መነሻ ምን እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ባይታወቅም፣ ከዘረ መል ውርስ (ለምሳሌ የቤተሰብ የነርቭ ቱቦ አለመዳበር የኋላ ታሪክ) እና አካባቢያዊ ነገሮች (ለምሳሌ የፎሌት እጥረት) ድምር ውጤት ጋር ይያያዛል። የስፒና ቢፊዳ ምልክቶች ምንድን ናቸው? የስፒና ቢፊዳ ዓይነቶች፣ ምልክቶች እና ደረጃው ከሰው ሰው ይለያያል። እንዲያም ሆኖ፣ በአጠቃላይ የስፒና ቢፊዳ ምልክቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ፦ 👉🏾 የታችኛው የሰውነት ክፍል እግርን ጨምሮ የሚከሰት ሽባነት (paralysis) እና ተያይዞ ለመራመድ መቸገር ወይም አለመቻል 👉🏾 ሽንትን/ሰገራን መቆጣጠር አለመቻል 👉🏾 የጀርባ አጥንት ቅርጽ መዛባት እና የ S ቅርጽ መያዝ 👉🏾 ሲተነፍሱ፣ ሲውጡ፣ ዓይኖችን ሲያንቀሳቅሱ መቸገር 👉🏾 አንድን ነገር ለመማር/ለመልመድ መቸገር ስፒና ቢፊዳ ኖሯቸው የሚወለዱ ሕጻናት በአብዛኛው “ሃይድሮ ሴፋለስ” (hydrocephalus) የተባለ (ጥሬ የላቲን ትርጉሙ “አንጎል ውስጥ ያለ ውሃ” ማለት የሆነ) ሁኔታ ይኖራቸዋል። ይህ ሁኔታ ፈሳሽ ከአንጎል እንዳይወጣ በመዝጋት የሕጻናቱ የጭንቅላት መጠን ከተገቢው በላይ እየጨመረ እንዲሄድ ያደርጋል። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲከሰት በቀዶ ሕክምና ፈሳሽ ከአንጎል ወጥቶ የሚፈስበት ቱቦ በመሥራት ማስተካከያ ይደረጋል። አብዛኛውን ጊዜ የእርግዝና 18ኛ ሳምንት አካባቢ በሚደረግ የአልትራሳውንድ ምርመራ ስፒና ቢፊዳ መኖር አለመኖሩ መጣራት ይችላል። ፎሊክ አሲድ መውሰዱ አንዱ ወሳኝ የሆነበት ምክንያት ስፒና ቢፊዳ የመከሰት ዕድሉን ለመቀነስ ነው። ገና ለማርገዝ ስታስቢ ጀምሮ ፎሊክ አሲድ መውሰድሽ፣ እንዲሁም ፎሌት የሚገኝባቸው ምግቦች መመገብሽ ስፒና ቢፊዳን ይከላከላል። ምን ያህል ፎሊክ አሲድ መውሰድ ያስፈልጋል፤ እንዲሁም የጎንዮሽ ጉዳት ይኖረው ይሆን ወይ የሚለው ላይ እንመለሳለን። #እርግዝና #መጸነስ #ጤና #ፎሊክ_አሲድ #ፎሌት #ቫይታሚን #ስፒና_ቢፊዳ Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views223−18%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#444Photo

ልጆችን ማድነቅ እና በቂ ትኩረት መስጠት በራስ የመተማመን ስሜታቸውን ይገነባል፤ ለራሳቸው የሚሰጡት ዋጋ ከፍ እንዲልም ያደርጋል። ልጆችን በማድነቅ ስለራሳቸው ቀና የሆነ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ማስለመጃ አንድ ሁነኛ መንገድ ነው። እንዲሁም ጥሩ ነገሮችን ማድረግ እንዲቀጥሉ ማበረታቻም ነው። ልጆቻችንን ስናደንቅ ጥሩ ነገር ሲያከናውኑ ለራሳቸው እውቅና እንዲሰጡ እንዲሁም በራሳቸው ማንነት እንዲኮሩ ማስለመድ ነው። ልጆችን በየዕድሜያቸው ለሚያደርጓቸው ልዩ ልዩ ነገሮች ልናደንቃቸው እንችላለን። ሕጻናትን ያልናቸውን ነገር ስላደረጉ፣ መጫወቻቸውን ወይም የያዙትን ነገር ለሌላ ልጅ ስላጋሩ ወዘተ ልናደንቃቸው እንችላለን። ዕድሜያቸው ከፍ ሲል ራሳቸውን ችለው ስለሚያደርጓቸው ነገሮች ልናደንቃቸው እንችላለን። በአስራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ልጆችን ትምህርታቸውን በአግባቡ ስለያዙ እና የቤት ሥራቸውን ያለ እኛ ማሳሰቢያ ስለሠሩ ልናደንቃቸው እንችላለን። #ሕጻን #ልጅ #እድገት #አስተዳደግ #ወላጅነት #አድናቆት #ማድነቅ #በራስ_መተማመን Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views220−19%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#443Photo

እርግዝና እና ፎሊክ አሲድ ፎሊክ አሲድ ምን ይጠቅማል? (ሊንክ፦ እርግዝና እና ፎሊክ አሲድ - ፎሊክ አሲድ ምንድን ነው? ከምን ከምን ይገኛል?) ፎሊክ አሲድ ለሁሉም ሰው የአካል እድገት እና መዳበር አስፈላጊ ቢሆንም፣ ለነፍሰ ጡር እናቶች ደግሞ ይበልጥ ወሳኝ ነው። 👉🏾 ሰውነትሽ የልጅሽን ዘረ መል (DNA) ለመሥራት የሚጠቀመው ፎሊክ አሲድን ነው። 👉🏾 እንዲሁም የልጅሽ የነርቭ ሥርዓት እና የነርቭ ቱቦ በአግባቡ እንዲዳብር ፎሊክ አሲድ ያስፈልጋል። የነርቭ ቱቦ (neural tube) በጽንስ ጊዜ ቀድመው ከሚዳብሩ የአካል ክፍሎች አንዱ ሲሆን፣ ቆየት ብሎ አንጎል እና ሰረሰር እንዲሁም እነዚህን ክፍሎች የሚከቡ አጥንቶች የሚሆን ነው። የነርቭ ቱቦ የሚዳብረው በእርግዝና ከ4 እስከ 6 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው። የነርቭ ቱቦ ላይ የሚኖር እንከን ልዩ ልዩ የአካል ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፤ እነዚህም ሽንት እና ሰገራ መቆጣጠር አለመቻል (ካደጉ በኋላም)፣ እንዲሁም የእግር ሽባነት ያካትታሉ። አንዳንዴ መዘዙ የከፋ ሲሆን ደግሞ “ስፒና ቢፊዳ” (spina bifida) የሚባለውን የነርቭ ቱቦ ችግር ሊፈጠር ይችላል። የስፒና ቢፊዳ ምንነት እና የፎሊክ አሲድ ተጨማሪ ነጥቦች ላይ እንመለሳለን። #እርግዝና #መጸነስ #ጤና #ፎሊክ_አሲድ #ፎሌት #ቫይታሚን Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views237−12%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#442Photo

የሕጻናት የወሊድ ክብደትን የሚወስኑ ነገሮች (ሊንክ፦ የሕጻናት የመጀመሪያ ዓመት የሰውነት ክብደት) አዲስ የሚወለዱ ሕጻናት ክብደት በሚከተሉት ነገሮች ሊወሰን ይችላል፦ 👉🏾 የዘረ መል ውርስ የወላጆች የሰውነት ክብደት የሚወለዱት ሕጻናት ክብደት ጋር ተያያዥነት ሊኖረው ይችላል። 👉🏾 የእርግዝና ጊዜ ርዝመት ከሚጠበቀው መውለጃ ቀን ቀድመው የሚወለዱ ሕጻናት በአብዛኛው ክብደታቸው አነስ ይላል፤ ቆይተው የሚወለዱት ደግሞ ይጨምራል። 👉🏾 የእርግዝና ጊዜ አመጋገብ በእርግዝና ጊዜ ጤናማ አመጋገብን መከተል ልጅሽ በማኅጸን ውስጥ ሳለች እና ከዚያም በኋላ ጤናማ እድገት እንዲኖራት ያግዛል። 👉🏾 የእርግዝና ጊዜ የኑሮ ዘዬ ሲጋራ ማጤስ፣ አልኮል መጠጣትና የመሳሰሉ ነገሮች ሌሎች ብዙ ችግሮች ከማስከተል ሌላ ሕጻናት ቀጭጨው እንዲወለዱ ያደርጋሉ። 👉🏾 የሕጻናት ጾታ በትንሹም ቢሆን ወንዶች ከሴቶች ሕጻናት ከፍ ያለ ክብደት ኖሯቸው ይወለዳሉ። 👉🏾 እናት በእርግዝና ጊዜ የነበራት ጤና ይዞታ እንደ ስኳር ሕመም፣ የልብ ሕመም፣ የደም ግፊት፣ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት የመሳሰሉ የእናቲቱ ሁኔታዎች የሚወለደው ሕጻን ክብደት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። 👉🏾 በአንድ ጊዜ የተጸነሱ ሕጻናት ቁጥር መንታ ወይም ከዚያ በላይ የተረገዙ ከሆነ ማኅጸን ውስጥ ቦታ ስለሚጋሩ ክብደታቸው የቀነሰ ይሆናል። 👉🏾 የውልደት ቅደም ተከተል የበኩር ልጆች ቀጥለው ከሚወለዱ ልጆች በአብዛኛው ክብደታቸው ያነሰ ይሆናል። 👉🏾 የሕጻኑ ጤና ሕጻናት ሲወለዱ ያሉበት የጤና ይዞታ (ከጽንስ ጊዜ ጀምሮ ያለ የጤና እክል ካለ) ክብደታቸው ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። #አራስ #አራስ_ልጅ #ሕጻን #እድገት #ክብደት Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views291+7%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#441Photo

እርግዝና እና ፎሊክ አሲድ እርግዝና ገና ሲታሰብ ጀምሮ አንዱ መወሰድ ያለበት ወሳኝ ንጥረ ነገር ፎሊክ አሲድ ነው። ፎሊክ አሲድ እና ሌሎች ወሳኝ ንጥረ ነገሮችን ጽንስ ከመፈጠሩ በፊትም ሆነ በእርግዝና ጊዜ መውሰድ እጅጉን አስፈላጊ ነው። የፎሊክ አሲድ እንክብሎች ለመጸነስ እየሞከሩ ላሉ ሴቶችም ሆነ ለነፍሰ ጡሮች እንዲወስዱ የሚመከር ነው። ፎሊክ አሲድ ምንድን ነው? ፎሊክ አሲድ “ፎሌት” የሚባለው ቫይታሚን ቢ 9 ሰው ሠራሽ ምርት ነው። ፎሌት ወይም ቫይታሚን ቢ 9 በተፈጥሮ የሚከተሉት ምግቦች ውስጥ ይገኛል፦ 👉🏾 አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልት (ጎመን፣ ጥቅል ጎመን፣ ቆስጣ የመሳሰሉ) 👉🏾 ብርቱካን፣ መንደሪን እና ሎሚ 👉🏾 ጥራጥሬ 👉🏾 ለውዝ ከእርግዝና ጊዜ ውጪ ላሉት ጊዜያት ከምግብ የሚገኘው ፎሌት በአብዛኛው በቂ ነው። ሆኖም ፎሌት ምግብ ሲበስል በቀላሉ ሊጠፋ ይችላል። ለማርገዝ እየሞከሩ ላሉ ሴቶች እና ለነፍሰ ጡሮች በተጨማሪ ፎሊክ አሲድ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ፎሊክ አሲድ ስላለው ጠቀሜታ እና ሳይወሰድ ሲቀር ሊከተል ስለሚችለው ችግር እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እንመለሳለን። #እርግዝና #መጸነስ #ጤና #ፎሊክ_አሲድ #ፎሌት #ቫይታሚን Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views281+4%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#440Photo

የሕጻናት የመጀመሪያ ዓመት የሰውነት ክብደት በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት የመጀመሪያ ዓመት የሕጻናት አማካይ ክብደት በሠንጠረዥ የቀረበው ነው። ልጆች ከዚህ የበለጠ ወይም ያነሰ ክብደት ኖራቸው ማለት ቀጣዩ ሕይወታቸውን ሁሉ አነስተኛ ወይም ከፍተኛ ክብደት ይኖራቸዋል ማለት አይደለም፤ ወይም አንዳች የእድገት ችግር እንዳለባቸው የሚያመለክትም አይደለም። ይህ አማካይ የክብደት ሠንጠረዥ የሚጠቅመው ድንገት ሕጻናት ካሉበት አማካይ ክብደት በጣም ከቀነሱ ለመከታተል እንዲያመች ነው፤ ከዚያ ደግሞ ከፍ ወዳለ ክብደት ከሄዱ እድገታቸው በፍጥነት እንድቀጠለ የሚያመላክት ነው። በውልደት ጊዜ፦ 👉🏾 ከመደበኛ ያነሰ የሚባለው ከ1.5 እስከ 2.5 ኪ.ግ ሲመዝኑ ሲሆን፣ 👉🏾 ከመደበኛ በጣም ያነሰ የሚባለው ደግሞ ከ1.5 ኪ.ግ ያነሰ ክብደት ሲኖራቸው ነው። ክብደታቸው በዚህ መጠን የሆኑ ሕጻናት የሰውነታቸው ክብደት እስኪስተካከል ልዩ የሕክምና እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል። “የሕጻናት የወሊድ ክብደትን የሚወስኑ ነገሮች” የሚለው ላይ እንመለሳለን። #አራስ #አራስ_ልጅ #ሕጻን #እድገት #ክብደት Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views283+5%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#439Photo

እርግዝና እና የጽንስ እንቅስቃሴ ምን ሲሆን ሊያሳስበኝ ይገባል? የጽንስ እንቅስቃሴ ከ18 - 20 ሳምንት እርግዝና ጊዜ አንሥቶ ለእናት የሚሰማና እስከ ወሊድ ጊዜ የማያቆም ነው። (ሊንክ፦ እርግዝና እና የጽንስ እንቅስቃሴ) የጽንስ እንቅስቃሴ መቀነስ ሲያጋጥም፣ አሳሳቢነቱና የሚያስፈልገው ክትትል እንደ እርግዝናሽ ደረጃ ይወሰናል። 👉🏾 ከ24 ሳምንት በፊት ለሆነው እርግዝና፦ በአብዛኛው የጽንስ እንቅስቃሴ ከ18 - 20 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ስለሚሰማ፣ 24 ሳምንት ሆኖሽ ጽንሱ ሲንቀሳቀስ ተሰምቶች የማያውቅ ከሆነ፣ ወደ ሕክምና መሄድ ይኖርብሻል። ሐኪም የልጅሽን የልብ ምት ከማዳመጥ ጀምሮ፣ እንደ አስፈላጊነቱ የአልትራሳውንድ ምርመራ ሊያዝ ይችላል። 👉🏾 ከ24 እስከ 28 ሳምንት ለሆነው እርግዝና፦ በዚህ ጊዜ ውስጥም የጽንሱ እንቅስቃሴ ካልተሰማሽ ወይም በጣም ከቀነሰ፣ ወደ ሕክምና መሄድ ይኖርብሻል። በዚህ ጊዜም ሐኪም የልጅሽን የልብ ምት ያዳምጣል፣ እንደ አስፈላጊነቱ የአልትራሳውንድ ምርመራ ያዛል፤ የደም ግፊትሽ ይለካል፣ ሽንትሽ ውስጥ ፕሮቲን ይገኝ እንደሁ ምርመራ ይደረጋል። 👉🏾 28 ሳምንት ላለፈው እርግዝና፦ ከ28 ሳምንት በኋላ የጽንስ እንቅስቃሴ መቀነስ ወይ መቆም ካጋጠመ ሳይውል ሳያድር ወደ ሕክምና መሄድ ያስፈልጋል። በዚህ ጊዜም ከላይ የተገለጹት ምርመራዎች ይበልጥ ጊዜ ተወስዶ ይደረጋሉ። የጽንስ እንቅስቃሴ አንዴ ሊጨምር አንዴ ሊቀንስ ስለሚችል በአብዛኛውን ምርመራው ሁሉ ነገር ሰላም እና ጤና እንደሆነ ለማረጋገጥ የሚደረግ ቢሆንም፣ “ሰላም ነው” ብሎ ቸል ከማለት ምረምራውን አድርጎ ማረፉ በእጅጉ የተሻለ ነው። #እርግዝና #ጽንስ #ጤና #እንቅስቃሴ #አሳሳቢ Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views316+17%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#438Photo
Views310+14%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#437Photo

እርግዝና እና የጽንስ እንቅስቃሴ የጽንስ እንቅስቃሴ አብዛኛውን ጊዜ ለነፍሰ ጡር እናቶች መጀመሪያ የሚሰማቸው ከ18 እስከ 20 ሳምንት ባለው የእርግዝና ጊዜ ነው። ሆኖም የመጀመሪያ እርግዝና ላይ እስከ 20 ሳምንት ድረስ ምንም እንቅስቃሴ ላይሰማሽ/ላይታወቅሽ ይችላል። እርግዝናሽ የመጀመሪያሽ ካልሆነ አንዳንዴ 16 ሳምንት ሲሆንሽ ጀምሮ እንቅስቃሴው ሊሰማሽ ይችላል። በእርግዝና ጊዜ እናቶች ልጃቸው እጁን እና እግሩን ሲያወናጭፍ ወይም ሲገለባበጥ ይሰማቸዋል። ልጅሽ እያደገ ሲመጣ፣ የሚሰማሽ እንቅስቃሴ ብዛትም ዓይነትም እየተቀያየረ ይሄዳል። አብዛኛውን ጊዜ እንቅስቃሴው የሚጨምረው ከሰዓት በኋላ እና ምሽት ላይ ነው። ቀንም ሆነ ሌሊት ልጅሽ በአብዛኛው ከ20 እስከ 40 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ያህል (ረዘመ ቢባል በአብዛኛው ከ90 ደቂቃ ያልረዘመ ጊዜ) ይተኛል። ልጅሽ በሚተኛባቸው በእነዚህ ሰዓታት እንቅስቃሴው ላይሰማሽ ይችላል። ከ32 ሳምንት በኋላ የልጅሽ እንቅስቃሴ ብዛት የመቀነስ አዝማሚያ ያሳያል፤ ከዚያ መልሶ በመጠኑ ይጨምራል። ያም ሆኖ የሚሰማሽ የእንቅስቃሴ ዓይነት መውለጃሽ እየተቃረበ ሲመጣ እየተቀየረ መሄዱ አይቀርም። አብዛኛውን ጊዜ በተለይ በሥራ ተወጥረሽ ከሆነ ሁሉም እንቅስቃሴ ላይሰማሽ ይችላል። አስፈላጊው ነጥብ ምጥ እስኪጀምርሽ ወይም ልትወልጂ እስከደረስሽበት ሰዓት ድረስ የልጅሽ እንቅስቃሴ ሊሰማሽ ይገባል። (ልጅሽ በምጥ ሰዓትም እንቅስቃሴ አያቆምም።) ከጽንስ እንቅስቃሴ ጋር ተጨማሪ ነጥቦች ላይ እንመለሳለን። #እርግዝና #ጽንስ #ጤና #እንቅስቃሴ Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views310+14%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#436Photo

ወላጅነት እና ራስን መንከባከብ ለልጆቻችን የተሻልን እናት፣ የተሻልን አባት መሆን የምንችለው ራሳችንን "ስንረሳ" አለመሆኑን ማሰብ አለብን። ወላጆች ለልጆቻቸው ሊያደርጉ የሚችሉት አንዱ ትልቁ ነገር ራሳቸውን መንከባከብ ነው። ወላጆች የራሳቸውን ጤና (አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ ወዘተ) ቸል ካሉ፦ 👉🏾 የራሳቸው ጤና ችግር ላይ ሊወድቅ ይችላል 👉🏾 ስሜታዊ "መገንፈል" (ድንገተኛ ቁጣ ወይም ለቅሶ እና የመሳሰሉ) ሊያጋጥማቸው ይችላል (ይህም ልጆች ላይ አሉታዊ የሥነ ልቦና ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው) 👉🏾 ልጆቻቸው ራስን ስለመንከባከብ ትክክለኛ አቋም እንዳይዙ እንቅፋት ይሆናል እንደ ወላጅ ራስን ለመጠበቅ/ለመንከባከብ ቢያንስ የሚከተሉትን ማድረግ ይመከራል፦ 👉🏾 በተቻለ መጠን በቂ እንቅልፍ ማግኘት 👉🏾 የተስተካከለ እና ጤናማ አመጋገብ 👉🏾 በየቀኑ የአእምሮ ወይም የአካል ጤናን ለመጠበቅ አንድ ነገር ማድረግ (በእግር መንሸራሸር፣ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ስፖርት መሥራት፣ መጽሐፍ ማንበብ የመሳሰሉ) 👉🏾 ከራስ (እና ከትዳር አጋር) ጋር የጥሞና ጊዜ መውሰድ #ወላጅነት #ጤና #እንክብካቤ #ሥነልቦና Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views320+18%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#435Photo

እርግዝና እና ትኩሳት በእርግዝና ጊዜ ፈጽሞ ቸል ሊባሉ ከማይገቡ ነገሮች አንዱ ትኩሳት ነው። ከ24 ሰዓት በላይ የቆየ መለስተኛ የሚባል ትኩሳት እንኳን ቢሆን የኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ስለሚችል እርግዝና ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል። በጊዜው ያልታከመ ኢንፌክሽን ያለጊዜ የመውለድ አንዱ የተለመደ ምክንያት ነው። በተለይ በመጀመሪያው 3 ወር ትኩሳት ጽንሱ ላይ ችግር ሊያስከትል ይችላል። ሐኪም ጋር መሄድ ያለብኝ ምን ሲሆን ነው? 👉🏾 ትኩሳት እያለሽ ከምን እንደመጣ ርግጡን ካላወቅሽ (ለምሳሌ አብሮ ጉንፋን ይዞሽ ካልሆነ) 👉🏾 ትኩሳትሽ ከጉንፋን ጋር የተያያዘ ሆኖም ከ24 ሰዓት በላይ ሳይበርድ ከቆየ ብርድ ብርድ የሚል ስሜት ከተሰማሽ 👉🏾 ከትኩሳቱ ጋር ሰውነትሽ ውስጥ ያለው ፈሳሽ መጠን ማነስ ምልክት ከታየብሽ (ማለትም ከፍተኛ የውሃ ጥም፣ የሽንት ቢጫ መሆን፣ ወይም የሽንት መጠን መቀነስ) 👉🏾 ትኩሳት ኖሮሽ ከብልት የሚወጣ ፈሳሽ መጠን መጨመር ካጋጠመሽ፣ ወይም ፈሳሹ ደስ የማይል ጠረን ከኖረው 👉🏾 የስኳር ሕመም ወይም አስም ኖሮብሽ ትኩሳት ከኖረሽ 👉🏾 ከትኩሳቱ ጋር ተያይዞ የጽንሱ እንቅስቃሴ መቀነሱ ከተሰማሽ ሐኪም ጋር መሄድ ይኖርብሻል። (ሊንክ፦ አሳሳቢ የእርግዝና ጊዜ ምልክቶች) #ትኩሳት #እርግዝና #ጤና #አሳሳቢ Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views336+24%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#434Photo

አዲስ ልጅ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ትዳር ውስጥ የሚፈጠር ውጥረትን እንዴት እንቀንስ? ከአዲስ ልጅ መምጣት ጋር ተያይዞ ትዳር ውስጥ ውጥረት ሊፈጠር ይችላል፤ አብዛኞቹ ጥንዶችም ከወትሮው በተለየ ወይም በበለጠ በመካከላቸው ጠብ ሊፈጠር ይችላል። ይህ ይሁን እንጂ ይህ ጊዜ ትዳራችሁ ላይ የሚፈጥረውን ውጥረት ተቋቁማችሁ ማለፍ ከቻላችሁ፣ ከዚያ በኋላ በጋብቻችሁ የሚሰማችሁ ደስታ/እርካታ ልጅ ከመውለዳችሁ በፊት ከነበረው የበለጠ እንደሚሆን ጥናቶች ያሳያሉ። (ሊንክ፦ የአዲስ ልጅ መምጣት የባልና ሚስት ጠብን ያባብሳል?) ለዚህም የሚከተትሉትን ሦስት ነገሮች (ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ) ማድረግ ይመከራል፦ 1👉🏾 የሌላውን ስሜት እውቅና መስጠት እና መረዳት (ልክ ነው/አይደለም ማለትን ትቶ “እንዲህ እንደተሰማሽ/እንደተሰማህ ገብቶኛል” ማለት) 2👉🏾 በግልጽ በመነጋገር ኃላፊነቶችን (የቤት ውስጥ ሥራን ጨምሮ) መካፈል/ተጋግዞ መወጣት 3👉🏾 የዘመድ/ወዳጅ/ጎረቤት ወዘተ ድጋፍን እንደ አስፈላጊነቱ መጠየቅ በመካከላችሁ ያለው ውጥረት የከፋ በሚመስልበት ጊዜ ሁሉ፣ ጠላት ሳይሆን አጋር እንደሆናችሁ በማሰብ በጋራ ትዳርን ማለምለም ይቻላል። #ወላጅነት #ጥንዶች #ግንኙነት #ትዳር #ጋብቻ Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views361+33%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#433Photo

የእርግዝና ጊዜ መርሳትን/ዝንጉነትን መቋቋሚያ ዘዴዎች በእርግዝና ጊዜ አነስተኛ የመርሳት ችግር ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው፤ አብዛኛውን ጊዜም የዕለት ተዕለት ተግባርን የማያደናቅፍና በቀላሉ ተጽዕኖውን መግታት የሚቻል ነው። (ሊንክ፦ እርግዝና እና የመርሳት ነገር) (ሊንክ፦ እርግዝና እና የመርሳት ነገር - ምልክቶቹ፣ ጅማሬው፣ አሳሳቢነቱ) ምንም እንኳ የአእምሮ አቅም ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ባይኖርም፣ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም የሚከተሉትን ዘዴዎች መጠቀም ትችያለሽ፦ 👉🏾 የየእለት ማስታወሻ/አጀንዳ መያዝ ስልክሽ ላይ ያለ የቀን መቁጠሪያ/ካላንደር መተግበሪያን በመጠቀም ወይም አነስተኛ ማስታወሻ በመያዝ “ብረሳቸው” ብለሽ የሚያሳስቡሽን ነገሮች መመዝገብ ትችያለሽ። 👉🏾 አስፈላጊ ነገሮችን ቋሚ ቦታ መስጠት ብዙ ጊዜ የምጠቀሚባቸውን ነገሮች (ለምሳሌ ቁልፍ) ሁልጊዜ በአንድ ቦታ አስቀምጪ። 👉🏾 ማስታወሻ “አላርም” እና የመሳሰሉ ዘዴዎችን መጠቀም 👉🏾 በቂ እንቅልፍ መተኛት በቂ እንቅልፍ ማግኘት ትውስታሽ የተሻለ እንዲሆን እና አእምሮሽ ንቁ እንዲሆን ያግዛል። 👉🏾 እገዛ መጠየቅ እንደ አስፈላጊነቱ ባለቤትሽን፣ ሌሎች የቤተሰብ አባላትን አሊያም ወዳጅ ዘመድን በአንዳንድ የእለት ተእለት ተግባሮች እንዲያግዙሽ ጠይቂያቸው። ይህ መሆኑ ውጥረት ስለሚንቀንስልሽ የማስታወስ አቅምሽ የተሻለ እንዲሆን ያግዛል። 👉🏾 በአንድ ጊዜ አንድ ነገር ብቻ አድርጊ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገሮችን ታደርጊ ከነበር፣ እንዲያ ማድረግሽን ትተሽ ቅድሚያ የሚገባቸውን ነገሮችን ቀድመሽ ፈጽሚ። አቅምሽን ወሳኝ ለሆኑ ነገሮች ብቻ “ቆጥበሽ” ተጠቀሚ። #እርግዝና #መርሳት #መዘንጋት #ዝንጉነት Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views358+32%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#432Photo

የአዲስ ልጅ መምጣት የባልና ሚስት ጠብን ያባብሳል? ጥናቶች እንደሚጠቁሙት፣ በአማካይ ከሦስት ጥንዶች ሁለቱ አዲስ ልጅ የተወለደ ሰሞን ትዳራቸው በጠብ ወጀብ ይጎበኛል። ብዙ ጥንዶች ልጅ ከተወለደ ወዲህ በትዳራቸው የሚሰማቸው ደስታ ይቀንሳል ይላሉ። ያም ሆኖ በትዳር አጋሮች መካከል ያለው ቁርኝት ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርሰው ልጆች በአስራዎቹ እድሜዎች ውስጥ ሲገቡ እንደሆነ፣ መልሶ የሚያገግመውም ልጆች ጊዜያቸው ደርሶ ከቤት ሲወጡ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ። አዲስ ልጅ ከመወለዱ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር የትዳር ውጥረት “እኛ ላይ ብቻ የወረደ ዕዳ ነው” ብሎ የሚያሳስብ ጉዳይ የለም - ብዙዎችን ያጋጥማል። በእናትና አባት መካከል የሚፈጠር ውጥረት ወይም ጠብ (ነገሩ ከፍቶ ፍቺ ከመጣም) የልጃችሁን የአእምሮ እድገት የሚጎዳ ሁኔታን ይፈጥራል። የሚከተሉት ነገሮች ካሉ ደግሞ ውጥረቱ የተባባሰ ሊሆን ይችላል፦ 👉🏾 የእናት/አባት ወላጆች የተፋቱ ከሆኑ ወይም ወላጆች ብዙ ሲጣሉ እያዩ ያደጉ ከሆነ 👉🏾 ተጋብታችሁ ብዙ ሳትቆዩ (አብሮ በመኖር ትውውቃችሁ ሥር ሳይሰድ) ከወለዳችሁ 👉🏾 ከመውለዳችሁ በፊት ያላችሁ ተግባቦት ብዙ አሉታዊ ገጽታዎች ካሉትና ስትጋጩ በአግባቡ ሳትፈቱ ታልፉ ከነበረ 👉🏾 ከሁለት አንዳችሁ መውለድ አትፈልጉ ከነበረና ልባችሁ ሙሉ በሙሉ ሳይፈቅድ የቀጠላችሁበት ከሆነ ሆኖም - የምስራች! ይህ ጊዜ ትዳራችሁ ላይ የሚፈጥረውን ውጥረት ተቋቁማችሁ ማለፍ ከቻላችሁ፣ ከዚያ በኋላ በጋብቻችሁ የሚሰማችሁ ደስታ/እርካታ ልጅ ከመውለዳችሁ በፊት ከነበረው የበለጠ እንደሚሆን ጥናቶች ያሳያሉ። (በዚህ ነጥብ ላይ እንመለሳለን) #ወላጅነት #ጥንዶች #ግንኙነት #ትዳር #ጋብቻ Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views354+31%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#431Photo

እርግዝና እና የመርሳት ነገር - ምልክቶቹ፣ ጅማሬው፣ አሳሳቢነቱ (ሊንክ፦ እርግዝና እና የመርሳት ነገር) ምልክቶቹ ምንድን ናቸው? 👉🏾 የቅርብ ጊዜ ነገሮችን መዘንጋት 👉🏾 የቆዩ ትውስታዎችን “እንዲህ ነው” ብሎ ለማስታወስ መቸገር 👉🏾 አትኩሮትን ለመሰብሰብ መቸገር 👉🏾 አንድን ነገር ልብ ብሎ ለመስማት ወይም ለመከታተል መቸገር (የሃሳብ ጭልጥ ብሎ መሄድ) 👉🏾 ከጊዜና ቦታ ጋር ተያይዞ የግራ መጋባት ስሜት (ሰዓት ሳያውቁት ሲሄድ/ሲዘገይ ወይም ልብ ሳይሉ አንድ ቦታ መድረስ የመሳሰለ) 👉🏾 እንደ ቀድሞው ለማንበብ መቸገር 👉🏾 ቃላትንና ስሞችን ለማስታወስ መቸገር መቼ ይጀምራል? የእርግዝና ጊዜ ዝንጉነት መቼ እንደሚጀምር እቅጩን የሚጠቁም ጥናት ባይኖርም፣ ከነፍሰ ጡር እናቶች የተሰበሰቡ መረጃዎች የሚጠቁሙት ከሁሉም የሚከፋው በሦስተኛው 3 ወር ጊዜ (ከ6 እስከ 9 ወር) እንደሆነ ነው። ሆኖም አንዳንዴ ገና ከእርግዝና የመጀመሪያ ሰሞን ሊጀምር ይችላል። ምን ሲሆን ሊያሳስበኝ ይገባል? ምንም እንኳ በእርግዝና ጊዜ መጠነኛ ዝንጉነት የተለመደ ቢሆንም፣ አትኩሮትሽን ለመሰብሰብ እጅግ ከተቸገርሽ፣ ወይም ከቀኑ አብዛኛውን ጊዜ በመደበት ካሳለፍሽ፣ ወይም ሌላ ጊዜ ደስታ ይሰጡሽ የነበሩ ነገሮች ሁሉ ካስጠሉሽ ምናልባት ከእርግዝና ጋር የተያያዘ ጠንከር ያለ የመደበት ስሜት ውስጥ ልትሆኚ ትችያለሽ። ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከደረሰ፣ ሐኪም ማማከር ይኖርብሻል። (በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ዝንጉነትን እንዴት እንያዘው/ተጽዕኖውን እንቀንስ የሚለው ላይ እንመለሳለን) #እርግዝና #መርሳት #መዘንጋት #ዝንጉነት Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views372+37%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#430Photo

የልጆች አንጎል እድገት - 5 ነጥቦች 1👉🏾 የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ለአንጎል እድገት ወሳኝ ናቸው የአንጎል ሴሎች (ኒውሮኖች) አብዛኞቹ ትስስሮች ተያይዘው የሚጠናቀቁት እስከ 10 ዓመት እድሜ ነው። 2👉🏾 ነገሮችን "መደጋገም" ለአንጎል እድገት ይበጃል ነገሮችን መደጋገም ለሕጻናት አእምሮ መዳበር ጠቃሚ ነው። የሕጻናት መዝሙሮች ተደጋጋሚ ነገሮችን በውስጣቸው የሚይዙበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው። ይህ በርግጥ ተደጋጋሚ ልማዶችንም ያካትታል። አእምሮን ከማዳበር በተጨማሪ፣ ሕጻናት ዘላቂ የሆኑ ልምዶችን የማዳበር አቅም እንዲኖራቸው ያግዛል። 3👉🏾 የአካል እንቅስቃሴ ለአንጎል እድገት ጠቃሚ ነው ንቁ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ ለንቁ አእምሮም ጠቃሚ ነው። (በነገራችን ላይ ይህ ለሕጻናት ብቻ ሳይሆን ለአዋቂም እንዲሁ ነው።) 4👉🏾 ጭንቀት/ውጥረት የመማር አቅምን ይቀንሳል ውጥረት/ጭንቀት በሚፈጥር ክስተት ውስጥ ስናልፍ "ኮርቲሶል" የተባለ ሆርሞን ይመነጫል፤ ይህም ለመማር እና ለማስታወስ የሚጠቅምን የአንጎል ክፍል ይጎዳል። ልጆችን ሊገጥማቸው ከሚችል ውጥረት ሁሉ ለመጠበቅ የሕይወት ክህሎት እንዳያድዳብሩ እንቅፋት ስለሚሆን ጥሩ ባይሆንም፣ ከእናትና አባት ጋር የጠበቀ ግንኙነት ሲኖራቸው ስለራሳቸው ጥሩ እንዲሰማቸው እና የጭንቀት/ውጥረት ስሜታቸው እንዲቀንስ ያደርጋል። 5👉🏾 ሙዚቃ ለአእምሮ እድገት ጠቃሚ ነው ለሕጻናት መዘመር፣ አብሮ ሙዚቃ መስማት፣ እንዲሁም ሙዚቃ መጫወት ስለ ቦታ አቀማመጥ መረዳትን ለመጨመር፣ እንዲሁም የሂሳብ ችሎታን ለማዳበር ያግዛል። #ልጅ #ሕጻን #አራስ #አራስ_ልጅ #አስተዳደግ #እድገት #አንጎል #አእምሮ Telegram፦ t.me/LeLijeInc Facebook፦ facebook.com/LeLijeInc Instagram፦ instagram.com/LeLijeInc Tiktok፦ tiktok.com/@LeLijeInc LinkedIn፦ linkedin.com/company/LeLijeInc 🌐 LeLije.com #ለልጄ © LeLije Inc

Open in Telegram
Views393+45%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—