Posts of የሕግ ቤት
" የተሰረቀ ዕቃ በቅናሽ ዋጋ መግዛት ወይም ይዞ መገኘት እንደ ወንጀሉ ክብደት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ያስቀጣል " - የሕግ ባለሙያ አንዳንድ ሰዎች የተሰረቁ ስልኮች፣ ላፕቶፖችና ሌሎች ዕቃዎች በርካሽ ዋጋ የሚሸጡባቸውን ቦታዎች በማፈላለግ ሲገዙ ይስተዋላል። አንዳንዶች ምንጫቸውን ሳያውቁ ያገለገሉ ዕቃዎችን በርካሽ ስላገኟቸው ብቻ ከሰዎች ላይ ይገዛሉ ፤ ሌሎች ደግሞ እቃውን በትንሽ ብር ገዝተው አትርፈው ይሸጣሉ። ታዲያ አንድ ሰው " ዕቃው በቅናሽ ዋጋ ስለቀረበልኝ በቅን ልቦና ነው የገዛሁት ፤ የተሰረቀ መሆኑን አላውቅም ነበር " ቢል ከሕግ ተጠያቂነት ያመልጥ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያና ጠበቃ የሆኑትን አቶ ጥጋቡ ደሳለኝን አነጋግሯል። የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት ምንድነው ? በአነስተኛ ዋጋ ስለተገኘ ብቻ የተሰረቀ ዕቃ የሚገዙና አትርፈው የሚሸጡ አካላት፣ በቅን ልቦናም ይሁን ሳያውቁ ቢገዙ ከሕግ ተጠያቂነት ነጻ እንደማይሆኑ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ገልጸዋል። በሕግ ፊት " የተሰረቀ መሆኑን አላውቅም ነበር " የሚል ምክንያት ተቀባይነት እንደሌለውም አስረድተዋል። " የተሰረቀ ዕቃ የዋጋ ቅናሽ ስላለውና ደረሰኝ ስለሌለው መግዛት፣ በሕጉ መሠረት የተሰረቀ ዕቃ በመግዛት እና ደረሰኝ የሌለው ዕቃ ይዞ በመገኘት እንደ ነገሩ ክብደት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ያስቀጣል። ከተጠያቂነት ነጻ መሆን የሚቻለው ከሕጋዊ ነጋዴ በስሙ የተቆረጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ሲቻል ብቻ ነው " - አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ የአንድ ግብይት ሕጋዊነት የሚረጋገጠው በደረሰኝ ብቻ መሆኑን ያነሱት ባለሙያው፤ ሻጩ ለሰጠው ዕቃ ወይም አገልግሎት ደረሰኝ የመስጠት፣ ገዢውም የከፈለበትን ደረሰኝ የመቀበል ግዴታ እንዳለበት ተናግረዋል። ግብይቱ በደረሰኝ እስካልተረጋገጠ ድረስ የትኛውም ግብይት የወንጀል ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል አሳስበዋል። የኦንላይን (ማኅበራዊ ሚዲያ) ግብይቶች ተጠያቂነት አለባቸው ? ከሰው ላይ የተሰረቁ ወይም በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኙ (የወንጀል ፍሬ የሆኑ) ዕቃዎችን ሰዎች ትክክለኛ መስሏቸው በቴሌግራም ቻናሎች፣ በፌስቡክ ገጾች እና በሌሎች የበይነመረብ አማራጮች ተታልለው ቢገዙና በኋላ የተሰረቀ ዕቃ መሆኑ ቢታወቅ፣ የወንጀል ተጠያቂነቱ በቀጥታ የሚያርፈው ዕቃውን ባሻሻጡት የኦንላይን ገጽ ባለቤቶች ወይም አንቀሳቃሾች (ኦፕሬተሮች) ላይ መሆኑን ጠበቃው ገልጸዋል። አክለውም በማኅበራዊ ሚዲያ " ዕቃ እናሻሽጣለን፣ ሻጭና ገዢ እናገናኛለን፣ የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን " የሚሉ አካላት በቀጥታ በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል። እነዚህ አካላት ዕቃውን ከማስተዋወቃቸው በፊት ዕቃው በሕጋዊ መንገድ የተገኘና የወንጀል ፍሬ አለመሆኑን፣ እንዲሁም ከትክክለኛ አቅራቢ ተገዝቶ ለትርፍ የቀረበ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው። ዕቃው በፖሊስ ቢወሰድ ገዢው ምን መብት አለው ? አንድ ገዢ በቅን ልቦና ያገለገለ ዕቃ ገዝቶ የተሰረቀ መሆኑ ተደርሶበት በፖሊስ ከተወሰደበት፣ ዕቃውን ለመግዛት ያወጣውን ገንዘብ ከካሳ ጋር በፍርድ ቤት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት እንዳለው አቶ ጥጋቡ ጠቁመዋል። ሆኖም የፍትሕ ሂደቱ እስከ 6 ወር ወይም ከዚያ በላይ ሊወስድ ስለሚችል፣ ዜጎች ገና ከጅምሩ በደረሰኝ በመገበያየት ራሳቸውን ከእንግልትና ከኪሳራ መጠበቅ እንደሚገባቸው መክረዋል። የተሰረቀ ዕቃ በስጦታ መልክ መቀበል የሚያመጣው ችግርስ ? " የተሰረቀ ዕቃ መሆኑን ሳያውቁ በስጦታ መቀበል ከሕግ ተጠያቂነት ያድናል ወይ ? " ለሚለው ጥያቄም የሕግ ባለሙያው የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡ የተሰረቀ ዕቃን በስጦታ የተቀበለ ሰው በሕግ ሲጠየቅ፤ " ዕቃው የተሰጠኝ በማኅበረሰቡ የመሰጣጣት ባህልና ልማድ መሠረት በስጦታ ነው፤ ቀደም ሲል በእኔ እጅ አልነበረም፤ እከሌ የሚባል ሰው ነው የሰጠኝ " ብሎ በሰው ምስክር ማረጋገጥ ከቻለ ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ ይሆናል። በሰነድ እንኳ ባይሆን በሰው ምስክር ማረጋገጥ ካልቻለ ግን፣ የተሰረቀ ዕቃን ለማሸሽ፣ ለመሸሸግ፣ ለመደበቅ፣ ለመሰወር ወይም አትርፎ ለመሸጥ የተደረገ ሙከራ ነው ተብሎ በወንጀል ይጠየቃል። በሕግ አግባብ ስጦታ መቀበል የሚቻለው ስጦታ ሰጪው ንብረቱ የራሱ ስለመሆኑ በውልና ማስረጃ መሥሪያ ቤት ሲያረጋግጥ ብቻ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው፤ በማኅበረሰቡ ዘንድ በተለመደው መንገድ ብቻ ዝም ብሎ ስጦታ መቀበል ከሕግ ተጠያቂነት እንደማያድን አስገንዝበዋል። በመጨረሻም ማኅበረሰቡ ለሚፈጽማቸው ማናቸውም ግብይቶች ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠትና መቀበልን ባህሉ ሊያደርግ እንደሚገባ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሳስበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in Telegramባለፉት አምስት አመታት ከ20 ሺህ በላይ ፍቺ ተመዝግቧል ከአዲስ አበባ ህዝብ ምዝገባ እና መኖሪያ ፈቃድ ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፉት አምስት ዓመታት ከ20 ሺህ በላይ ፍቺ ተመዝግቧል ተብሏል። ከዚህም ውስጥ ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑት ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ የተመዘገቡ መሆናቸው አሳሳቢነቱን ያሳያል። በአዲስ አበባ ከተማ እየጨመረ የመጣውን የፍቺ ቁጥር ለመቀነስ እና ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነቶችን ለመገንባት ያለመ "ቁርስ ከደሚና ጋር" የተሰኘ አዲስ የፍቅር ግንኙነት ትምህርት፣ የሥልጠና እና የምክር አገልግሎት ኢኒሼቲቭ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል ። የትዳር አማካሪ ኢብሳ ደሚና "ሀገር የሚመሰረተው ቤት ውስጥ ነው፤ ቤተሰብ ከተረጋጋ ሀገር ይረጋጋል" በማለት የቤተሰብን ወሳኝ ሚና አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። አክለውም በትዳር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እና ትውልድን ለመታደግ መፍትሔው ከራሳችን መጀመር እንዳለበት አመልክተዋል። አዲስ ተጋቢዎችንና ጥንዶችን የሚያካትተው ይህ መርሃ ግብር፥ውጤታማ ግንኙነት፣ ስሜታዊ ግንዛቤ እና ግጭትን በአግባቡ መፍታት ላይ የሚያተኩር የአንድ ቀን ስልጠና በመስጠት ከ1 ሺህ በላይ ሰዎችን ለመድረስ አቅዷል። ችግሮች ከመባባሳቸው በፊት መፍትሄ ለመስጠት ያለመው ይህ መርሃ ግብር ጤናማ ቤተሰቦችን ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል። ሊዲያ ደሳለኝ ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም
Open in Telegramየዳኞች አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ደኅንነት ጉዳይ በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ውስጥ አሳሳቢ ነው ተባለ። ⚫ በባለፈው አመት ወደ አራት ዳኞች በስራ ላይ እያሉ ሞተዋል፣ አንድ ሴት ዳኛ ተገድላለች! በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ውስጥ ብዙ ጊዜ ትኩረት የማይሰጠው፣ ነገር ግን የፍትሕን ጥራት እና የዳኞችን ሕይወት በቀጥታ እየተፈታተነ ነው የተባለው የዳኞች አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ደህንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተመላከተ። ጉዳዩ የተነሳው የፌዴራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት "የዳኝነት ደህንነት ፅንሰ ሀሳብ፤ ዓለም አቀፍ የሕግ ማዕቀፍ እና የሌሎች ሀገራት ልምድና ተሞክሮ" በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ጥናታዊ ሲምፖዚየም ላይ ነው። በሲምፖዚየሙ ላይ የተገኙ የሕግ ባለሙያዎች፣ የፍርድ ቤት ዳኞች እና ምሁራን እንዳሉት፣ ዳኞች በየዕለቱ ከሚከመሩባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ መዝገቦች እና ከባድ የሥራ ጫናዎች ባሻገር፤ ከባለጉዳዮች፣ ከሚዲያ፣ ከህዝብ እና ከተቋማት ከሚመጡ ጫናዎች እንዲሁም ከክልሎች ልዩ የደህንነት ስጋቶች ጋር እየታገሉ ይገኛሉ። ይህ የከፋ ጫና ዳኞች ከሥራ ብዛትና ከጤና እክል የተነሳ በሥራ ገበታቸው ላይ እስከ መውደቅ እና ሕይወታቸው እስከ ማለፍ መድረሱ ተገልጿል። የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካርያስ ሰርኮላ፤ ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ ዙሪያ ችሎት ላይ እያለች በጥይት የተገደለችውን ሴት ዳኛ ጨምሮ፣ በርካታ ዳኞች በሥራ ጫናና በጤና እክል ምክንያት በሥራ ገበታቸው ላይ እያረፉ መሆኑን አንስተዋል። ዳኞች የሚያጋጥማቸውን ከፍተኛ የአእምሮ ውጥረት ለመቋቋምና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ጤናቸውን የሚመረምሩበት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበትና ውጥረትን የሚቀንሱበት ሥርዓት ሊኖር እንደሚገባ አሳስበዋል። በሲምፖዚየሙ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት የጉማ የሕግ ቢሮ መስራችና ማኔጂንግ ፓርትነር አቶ ዳሳ ቡልቻ በበኩላቸው፣ የዳኝነት ሥራ የአእምሮ ሥራ ብቻ ተደርጎ እንደሚወሰድ ነገር ግን በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የጉልበት ሥራ እየመሰለ መምጣቱን ገልጸዋል። አቶ ዳሳ አያይዘውም፣ ሕገ-መንግሥቱ ዳኛን ከሥራ በቀላሉ ማንሳት እንደማይቻልና የሚነሳው በጤና ምክንያት ሥራ መስራት ካለፈ ብቻ መሆኑን በመጥቀስ "በእኛ ሀገር ከሥራ ላለመባረር ሲሉ ዳኞች ዝም ብለው ከራሳቸው ጋር ብቻ ይታገላሉ፤ ብዙ ዳኞች ከጓደኞቻቸው ጋር እንኳን ሳይቀር ስለ አእምሮ ጤናቸው አያወሩም" ሲሉ የሁኔታውን አሳሳቢነት አስረድተዋል። ዳኞች ከማኅበራዊ ሕይወታቸው ተገልጸው መኖራቸው ከቤተሰብና ከሥራ ባልደረቦች ጋር ያላቸውን ትስስር ማላላቱንም አንስተው፥ እንደ አውስትራሊያ፣ ካናዳ እና ኬንያ ያሉ ሀገራት በዳኞቻቸው ላይ የደህንነት ስጋቶች ሲጨምሩ የአእምሮ ጤና ፕሮግራሞችን በመቅረጽ መፍትሔ መስጠታቸውን ጠቅሰዋል። በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ዳኛ የሆኑት ቀነአ ቂጠታ በበኩላቸው፣ ዳኞች በየዕለቱ በችሎት የሚሰሟቸው፥ በትዳር መቃወስ፣ ፆታዊ ጥቃት፣ የስደተኞች ስቃይ እና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ያሉ አስፈሪ ታሪኮች በዳኛው ስሜት ላይ ከባድ የሥነ-ልቦና ጠባሳ እና ስብራት እንደሚያሳርፉ ገልጸዋል። የዳኞች ደህንነት አለመጠበቅ ስሜታቸውን ብቻ ሳይሆን የማስረጃ ምዘና አቅማቸውን እና ሕግ የመተርጎም ችሎታቸውን እንደሚያዳክም አብራርተዋል። ዳኞች በማኅበረሰቡ ተጽዕኖ የተነሳ አእምሯዊና ሥነ-ልቦናዊ ስብራታቸውን ደብቀው በዝምታ እንደሚሰቃዩም ጠቁመዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ጌታሁን አለማየሁ በበኩላቸው፣ የሀገር ደኅንነት በአካላዊ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን በዳኞች ማኅበራዊ ዋስትና ላይ ጭምር የሚቆም መሆኑን ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ "የዳኝነት ፖሊሲ" አለመኖሩና ለዳኞች ቤተሰቦች ጭምር ጥበቃ አለመደረጉ ቀውሱን እንዳባባሰው ገልጸው፣ ፍርድ ቤቶች ብቻቸውን ይህንን ቀውስ መግታት ስለማይችሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ከፍተኛ የፖሊሲ አውጭ አካላት ጣልቃ ገብተው መፍትሔ ሊበጁለት እንደገባ አሳስበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም @TikvahethMagazine
Open in TelegramForwarded from አለ ሕግ
በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ውስጥ ግብይት እንዴት እንደሚከናወን፣ ስርዓቶቹና ሂደቶቹስ ምንድናቸው? የሚሉትን ቁልፍ ሀሳቦች በዛሬው የኢንቨስትመንት ትምህርት ክፍላችን የምንዳስሰው ይሆናል። በዚህ የትምህርት ክፍል፤ በገበያው ላይ የግብይት ዑደት (Trading Cycle) ክንውኖችን እና ዋና ዋና ደረጃዎችን በዝርዝር የምናይ ሲሆን፤ የግዢ እና የሽያጭ ትዕዛዞች በስርዓቱ ውስጥ እንዴት እንደሚዛመዱ፣ የግብይት አገናኝ አባላትን (Trading Members) ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም ግብይት ስፈጸም (Trade Execution) እና በኋላ ባሉት ሂደቶች (Post-trade Settlement and Clearing) መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ እንመለከታለን። Read More Source: Ethiopian Securities Exchange Telegram #Ethiopianbusinessdaily https://t.me/AleHig 🙏 https://t.me/AleHig ✍️ https://t.me/AleHig ✅
Open in Telegram🚨 ውድ ግብር ከፋዮቻችን በአዲሱ የፌደራል የታክስ አስተዳደር ማሻሻያ አዋጅ (ቁጥር 1434/2018) መሠረት ከደረሰኝ አጠቃቀም እና ከድርጅት አመራሮች ተጠያቂነት ጋር የንግድ ማህበረሰቡ ሊያውቋቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦ 📌 የደረሰኝ ጥፋትና የቅጣት መጠኖች (አንቀጽ 125 እና 137) · ❌ ደረሰኝ አለመስጠት፦ በእያንዳንዱ ያልተሰጠ ደረሰኝ 100,000 ብር አስተዳደራዊ ቅጣት ይጣላል (ይህ ቅጣት በባለሥልጣኑ ሊነሳ አይችልም)። · ❌ የጋራ ዋጋ ማሳነስ ወይም መቀየር፦ 100,000 ብር መቀጫ + ከ5 እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ያስቀጣል። · ⚖️ የወንጀል ክስ መመስረት፦ በአንድ የግብር ዘመን ውስጥ 2 ጊዜ አስተዳደራዊ ቅጣት ከተቀጡ በኋላ ተመሳሳይ ጥፋት ከተደገመ ቀጥታ ወደ ወንጀል ክስ ያመራል። ⚠️ የስራ አስኪያጆችና የፋይናንስ ኃላፊዎች ግልጽ ተጠያቂነት (አንቀጽ 149) በድርጅት ውስጥ ለሚፈጸም የታክስ ወንጀል፣ ወንጀሉ በተፈጸመበት ወቅት የነበረ ሥራ አስኪያጅ ወይም የፋይናንስ ኃላፊ በግል በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል! ከተጠያቂነት ነፃ መሆን የሚቻለው፦ 1. ድርጊቱ ከእሱ እውቅና ውጪ መፈጸሙን፣ 2. የወንጀሉን መፈጸም ያልፈቀደ ወይም ያልተባበረ መሆኑን፣ ወይም 3. ወንጀሉ እንዳይፈጸም ውጤታማ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋቱን ማስረዳት ሲችል ብቻ ነው። 💡 መፍትሔ፦ ድርጅትዎ ያልተጠበቀ ከባድ የገንዘብና የእስራት ቅጣት እንዳይገጥመው የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓትዎን (Internal Control) ያጠናክሩ፤ የደረሰኝ አሰጣጥዎን በጥብቅ ይከታተሉ! 📲 መረጃው ለሌሎች የንግድ አጋሮችዎ እንዲደርስ ሼር (Share) ያድርጉ!
Open in TelegramForwarded from አለ ሕግ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ቀን ሊከበር ነው! ⚖️💎 በሺዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ጠበቆች አምረው፣ ደምቀው እና ተውበው በሚታዩበት ልዩ ቀን‼️ ሁሉንም የፌዴራል ጠበቆች በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስበው ታላቅ "የጠበቆች ቀን" (Lawyers' Day) በቅርብ ቀናት ውስጥ በደማቅ ሁኔታ ሊካሄድ መሆኑን በዝግጅት ኮሚቴው ይፋ ሆነ! ✔️💎 ጠበቆች በሀገር ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በፍትህ ማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የሚጫወቱት ሚና የማይተካ በመሆኑ፤ የሙያዊ ህብረት እና አወንታዊ ተፎካካሪነትን ማሳደግ፣ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በጋራ መፍትሔ መስጠት እና የሙያ ትስስራቸውን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ የጠበቆች ቀን ተዘጋጅቷል‼️ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ታሪካዊ መርሃ-ግብር የሙያውን ክብር ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ፣ በፌዴራል ጠበቆች ማህበር አዘጋጅነት ሁሉም ጠበቆች የሚታደሙበት የማይረሳ ምሽት ይሆናል! 🍷ይህ ደማቅ ፕሮግራም ምን ምን ያካተተ ነው?⁉️ 🍽 የራት ግብዣ (Gala Dinner) 🎶 የተለያዩ ማራኪ የመዝናኛ ፕሮግራሞች 🤝 የኔትወርኪንግና የእርስ በእርስ ትውውቅ መድረክ 📺 የሀገር ውስጥና የውጭ ትልልቅ ሚዲያዎች ሽፋን ⚖️ የፍትሃዊነትና የጠበቆችን ማህበራዊ ሚና ማጎልበቻ ውይይቶች ቀን እና ቦታው በጥቂት ቀናት ልዩነት ይፋ ይደረጋል!💡 #የኢትዮጵያፌዴራልጠበቆች #የጠበቆችቀን #FirstLawyersDay #EthiopianLawyers #Networking #GalaDinner #LegalExcellence
Open in Telegram#ለመረጃ: ለአትክልት እና ፍራፍሬ ማቀናበር እና ማቆየት የሥራ ዘርፍ የሚያስፈልጉ የካፒታል ዕቃዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው እንዲገቡ የገንዘብ ሚኒስቴር የማሻሻያ ደብዳቤ አውጥቷል! መመሪያ ቁጥር 1064/2017 የኢንቨስትመንት ማበረታቻን ለማስፈጸም የወጣውን መመሪያ ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች ተቀምጧል!
Open in TelegramForwarded from አለ ሕግ
📌 ያለ ሕግ ሰላም ይኖራል? አንዳንዶች "ሕግ ነፃነቴን ይገድባል" ይላሉ፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ቦታ እውነተኛ ሰላም ሊኖር አይችልም! ሕግ የሌለበት ሰላም: ጊዜያዊ ወይም በኃይለኞች ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የውሸት እፎይታ ነው። ሕግና ፍትሕ ሲኖሩ: የሁሉም ሰው መብት ይከበራል፤ የሕግ የበላይነት ባለበት ቦታ ደግሞ ዘላቂ ሰላም ይነግሣል። ሕግ ሰላምን የሚጠብቅ አጥር እንጂ ነፃነትን የሚያስር እሰር አይደለም። ያለ ሕግ አስከባሪና ያለ ሕግ የበላይነት ዘላቂ ሰላምን ማሰብ አይቻልም! 💬 እርስዎ ምን ያሰባሉ? ሰላም ከሕግ ይመነጫል ወይስ ሕግ ከሰላም? አስተያየትዎን በኮመንት ያጋሩን! 👇 🌍 Different voices. Different views. One shared humanity. #ሕግ #ሰላም #የሕግበላይነት #ፍትሕ #PeaceAndLaw #RuleOfLaw #Justice #Ileadpeace #PeaceStartsWithMe #YouthForPeace #PeacefulCommunities #AyreseTechShow #DignityForLife #GNRC #Arigatou
Open in Telegramታካሚዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት ጭምር ያስከተሉ የህክምና ስህተት አቤቱታዎች መቅረባቸውንና የሚቀርቡ አቤቱታዎች እየጨመሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ገለጸ። የባለስልጣኑ የህግ፣ የጤና ባለሙያዎችና ሥነምግባር ክትትል ዳይሬክር አቶ መትከል ገብረመድህን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ከሆነ፣ ከህክምና ስህተት ጋር በተያያዘ 42 አቤቱታዎች ቀርበዋል። የቀረቡት አቤቱታዎች ምን የተመለከቱ ናቸው? በእነዚህ አቤቱታዎች በህክምና ስህተት የሞቱ፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን የሚመለከቱ አሉ? በሚል ላቀረብነው ጥያቄ ዳይሬክተሩ፣ "አዎን። እሱማ አለ። የአካል ጉዳትም አለ፤ ሞትም አለ" ብለዋል። "ግን እንደዚህ አይነት ነገሮች ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ሚዲያ ላይ ሲወጣ ባለሙያዎች ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ቀላል አይደለም" ብለው፣ የሟችና ጉዳተኞችን ቁጥር ከመግለጽ ተቆጥበዋል። የህክምና ስህተት ተፈጸመ በሚል የሚያቀረቡ አቤቱታ እየጨመረ ወይስ እየቀነሰ ነው? መንስኤው ምንድን ነው? ስንላቸው፣ "በተለያዩ መንገዶች በደንብ እየሰራን ስለሆነ ህብረተሰቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግንዛቤው እየዳበረ መጥቷል። ግንዛቤ እየዳበረ በመምጣቱ የሚቀርበው የቅሬታ መጠንም ከፍ እያለ መጥቷል" ብለዋል። "የቅሬታ መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው" ያሉን ሲሆን፣ "ይህ ማለት የህክምና ስህተት ጨምሮ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፤ ያ በጥናት ነው የሚረጋገጠው" ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። የሚቀርቡ አቤቱታዎች ሲጨምሩ በጤና ባለሙያዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ የመጨመር እድሉ ሰፊ መሆኑንም ገልጸዋል። አቶ መትከል 42 አቤቱታዎች መቅረባቸውን ተከትሎ፣ "31 የሚሆኑ ጤና ባለሙያዎችን ተጠያቂ አድርገናል። በማጣራት ሂደት ብዙ ባለሙያዎች ናቸው የሚሳተፉት፤ ከበርካታ ባለሙያዎች መካከል ነው 31 ባለሙያዎችን ተጠያቂ ያደረግነው" ሲሉ ነግረውናል። ዘንድሮ 42 ሰዎች ካቀረቧቸው አቤቱታዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ምን እንደሆኑ ስንጠይቃቸው፥ የሞት፣ የአካል ጉዳት አቤቱታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። - በጨቅላ ህፃናት፣ - በነፍሰጡሮች፣ - በጥርስ ህክምና - በዓይን ህክምና - በውስጥ ደዌ በሽታዎች - በወሊድ እና ከወሊድ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች መሆኑንም አስረድተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ፥ ጤና ባለሙያዎች የህክምና ስህተት ለመፈጸሙ ምክንያት የሚሉት ምንድን ነው? ሲል የጠየቃቸው አቶ መትከል፣ "የተለያዩ ምክንያቶች ሊያቀርቡ ይችላሉ። የሚያቀርቡት ምክንያት ግን ትክክለኛ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የህክምና ግብዓት እጥረት፣ የጤና ባለሙያዎች፣ "ትኩረት አለመስጠት"፣ "የሙያ ማነስ"፣ "የእውቀት እና ክህሎት ማነስ" ሊኖር እንደሚችል ዳይሬክተሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ባለስልጣኑ፣ "ከ42 አቤቱታዎች ውስጥ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ጥፋተኛ የተባሉትን፦ - 3 ሚድዋይፈሪ፣ - 9 ዶክተሮች፣ - 14 ነርሶች፣ - 3 ጤና መኮንን፣ - 1 አንስቴቲስት፣ - 1 የድንገተኛ ቀዶ ጥገና ባለሙያ በድምሩ 31 ጤና ባለሙያዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተወስኖባቸዋል" ሲል አስታውቋል። 30 ባለሙያዎች ከአንድ ወር እስከ አንድ ዓመት ከሁለት ወር የሚደርስ የሙያ ፈቃድ እገዳ እንደተጣለባቸው፣ አንድ ባለሙያ ላይ ደግሞ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ ገልጿል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in Telegram