Posts of ካሊድ አቅሉ
ስለረሳሽዉም ስለረሳሁትም (ካሊድ አቅሉ) ——————- ይቅር ብያለዉ ይቅርም በይኝ አልድንም ነገር እንዳታስታሚኝ ደጅ እንዳልጠና ብዙ ሄደሻል ትዳር ከሚባል ግቢ ደርሰሻል ! ግን ግን የኔ ዉድ ….. እኔን ሚመስል ሰዉ ድንገት ካየሽ በህይወት እድሜ ድንገት በአመሻሽ ፤ በበጎ ነገር ሂጂ በምልሰት ድቅን አይበል ያለፈ ስህተት ፈገግ እንበል እንዉጣ ከአለም አይረሳም ያሉት ስለረሳሽዉም ስለረሳሁትም!
Open in Telegramእስኪ እይዋት ሸጋ ነገር ናት ገብታቹ ታደሙአት ወዶቼ 👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻 https://vt.tiktok.com/ZSph7vvEh/
Open in Telegram“በሀይሉ ገብረመድህን የሚላት አንድ አባባል አለች ‘ከብሩህ አንጎል ደብዛዛ ማስታወሻ ይሻላል።’ የሚለዉ ነገር አለዉ እዉነት ይመስለኛል ብሩህ አንጎል አንድ ቀን ይረሳል ደብዛዛ ማስታወሻ ግን የያዘዉን ይዞ ይቀመጣል ስለዚህ ወጣቶች ይሄንን ሚያስዉሉ ደስ ይለኛል ።” ——————————— ገጣሚ ደራሲና ተርጓሚ ነብይ መኮንን እንደነገረን ፣ በሀይሉ ገብረመድህን ጨዋታ አዋቂ የስታቲክስ ባለሙያ ነዉ የነብይ የረጅም ጊዜ ወዳጅ ።
Open in Telegram“ የስነ ፅሁፍ ቤተሰቦች ሁልጊዜ አዕምሮዋቸዉ ክፍት እንዲሆን እመክራለዉ። አዲስ ነገር ሳታዉቁ አትተኙ። ሁልጊዜ …አንድ አንድ አዲስ ነገር ምን ሰርቻለዉ ምን አዉቂያለዉ ብላቹ አስቡ እንደዛ ከተኛቹ ሚቀጥለዉ ቀን አንድ የእናንተን ያህል ሰዉ ጨምራቹ ነዉ ምታድጉት። እሱ important ይመስለኛል ።” ———————————— ገጣሚ ጋዜጠኛ እና ተርጓሚዉ ጋሽ ነብይ መኮንን ‘ ካሳ podcast’ ላይ እንደተናገረዉ።
Open in Telegramእንደምን አላቹ ወዶቼ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር የሆነዉ ወዳጄ ፕሮፌሰር አንተነህ ሰይፉ በድምፅ እና ቅንብር የተሳተፈበት አጠር ያለች ስራችንን ቲክ ቶክ መንደር ጎራ ብላቹ ታደሙልን 👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻 https://vt.tiktok.com/ZSgptMNpD/
Open in Telegramእንኳንስ ሊበላ ( ካሊድ አቅሉ) እንብላ ባትይኝ እንዳልበላ ፈርተሽ በመንገብገብ መሀል ስሪቱን እረሳሽ ! የሚበላ ማዕድ ለሆድ የሚጋብዝ የቅኖች ሙያ ነዉ የሌለበት መርዝ እንጂማ በቅናት ተበስሎ ተንኮል ያቀረበዉ ፣ እንኳንስ ሊበላ ሲያዩት አይደለ እድሜን ሚያሳጥረዉ ።
Open in Telegramጥቅምት ወር የተወለደዉን ሰአሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ በትንሹም ቢሆን እንዲህ አዉስተነዋለዉ ገብታቹ ታደሙ 👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻 https://vt.tiktok.com/ZSg4hQgw9/
Open in Telegram- “ምንም ነገርን ቀስ ብሎ መጀመር እና ቀስ ብሎ መጨመር በጣም አስፈላጊ ነገር ነዉ። “ ዶክተር ዳዊት ወንድማገኘ (የአለመኖር እና አለማወቅ ደራሲ)
Open in TelegramForwarded from ካሊድ አቅሉ
“ ቁስሎች በቁስል ይጠፋሉ እንዴ ቂም በቂም ይጠፋል እንዴ ያነሰን ፍቅር ነዉ ። እኔም ያነሰኝ ፍቅር ነበር ጥቂት ሰዉ መሆን ነዉ ያነሰን ወንዝ አይደለም ። ለተከፋይ የምናረግፈዉ አንድ የእንባ ጠብታ ነዉ እሱም ዉድ አይደለም ሁሉ በየሀይማኖቱ ይመርቃል ብዙ የተማርኩ ባልሆንም አይቻለዉ ። ቁጭ ብዪ ቂጤ እስኪያብጥ ሰዉ ሲያሴር ሲተበትብ ሲያፈቅር አይቻለዉ ሰምቻለዉ ። በብዛት ካሉ ጥሩ መስመሮች ለምን እግሮቻችን ሞላጫላጫዉን ጎዳና እንደሚመርጡ አላዉቅም የአይምሮ ብስለት ነዉ እንዳልል ናና ከረሜላ ለልጆቻችን እንኳን አልሰራንም።” ግራጫ ቃጭሎች (አዳም ረታ)
Open in Telegram