ክቡር አምባሳደር ፍፁም አረጋ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ክቡር አምባሳደር ፍፁም አረጋ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የሆኑትን ቸን ሃይን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ትብብርን ይበልጥ ለማጠናከር ከተቋማችን በሚጠበቁ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በወቅቱም የቻይና ኤምባሲ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በቋንቋ ልዩነት የሚያጋጥም አለመግባባትን ለመቀነስ የሚያስችል ዲጂታል መተርጎሚያዎችን፣ ፕሪንተሮችንና ዲጂታል ስክሪኖችን በድጋፍ መልክ ያበረከተ ሲሆን፣ ዋና ዳይሬክተሩም ምስጋና አቅርበዋል።
አምባሳደር ሃይ የስልጠና እድሎችንና የአቅም ግንበታ ድጋፎችን ለማመቻቸት ቃል የገቡ ሲሆን፣ ከቻይናውያን ጋር በተያያዘ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት መደበኛ የግኑኝነት መድረክ በማዘጋጀት በትብብር ለመስራት ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም ሰው የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ......
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
X: https://x.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/