Account

Posts of Hule Addis Media ( HAM)

newest first

#40111Photo
Views2970%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#40110Photo

የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል ! ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብርየዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። 1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%) 2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%) በልዩ ድጋፍ የሚታይ የተማሪ ምድብ 1. ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) 2. ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) 3. በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውር ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%) 4. በተፈጥሮ ወይም በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) ሆኗል።

Open in Telegram
Views733+147%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#40108Text

ለፈተና ትቀመጣላችሁ ተብሏል! በቀድሞው ዲፕሎማ ወይም ከ12+2 ወይም ከ10+3 የተመረቁና ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ ኖሯቸው ነገር ግን የደረጃ ስድስት የብቃት ማዕቀፍ ሳይኖራቸው በመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው የተመረቁ ተማሪዎችን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ የሚያስችል መመሪያ ሊዘጋጅ ነው፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ ባደረገው የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫና የአቻ ግመታ መመሪያ ማሻሻያ ላይ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የተመረቁና የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፉ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ እንዲሁም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ የሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም የሦስተኛ ዲግሪ የያዙ ተማሪዎች ሚኒስትሩ በሚያወጣው የትምህርት ደረጃ ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው እንደሚሆነም አስፍሯል፡፡ ይህ ማሻሻያ መመሪያ የትምህርት ማስረጃ ሰነድ ማረጋገጫ ሂደቶችን በአስፈላጊነቱ አገልግሎት ለመስጠትና ለማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ የተዘጋጀ መሆኑንም ተገልጿል፡፡ የማሻሻያ መመሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ማንኛውም የመንግስትና የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎች ላይ የሚተገበር ነው፡፡ እንዲሁም በዲግሪ መግቢያ መስፈርት የተቀመጠውን የደረጃ ስድስት የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሳይወስዱ ዲግሪ ተምረው የተመረቁትን፤ ወይም በዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የደረጃ ስድስት የብቃት ማረጋገጫ ፈተና የወሰዱትን ተመራቂዎች የሚያጠቃልል ነው፡፡

Open in Telegram
Views1,190+301%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—
#40107Text

በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% መደረጉ ተገለጠ ከ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤት ኪራይ ገበያ ላይ የሚታየውን ያልተገባ አሰራር በዘላቂነት ለመግታትና የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል ያለመ አዲስ መመሪያ ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ዓመታዊ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ብቻ ሆኖ እንዲገደብ መወሰኑን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። * ቀደም ሲል በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት፣ የአከራይና ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የቤቶች አስተዳደር ፅሕፈት ቤቶች በይፋ መተግበር ጀምሯል። * ቢሮው እንዳመለከተው፤ ይህ የዋጋ ማስተካከያ የተደረገው በዘፈቀደ ሳይሆን፣ የሕዝቡን እውነተኛ የመክፈል አቅምና ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት ከተካሄደ በኋላ ነው። * አዲሱ አሰራር በአንድ በኩል አከራዮች ፍትሐዊና ተመጣጣኝ ገቢ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ተከራዮች ካልተገባ የዋጋ ጭማሪና ከማኅበራዊ ቀውስ ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ያግዛል። "የአከራይ-ተከራይ ግንኙነትን በሕግ ማዕቀፍ በመምራት የጋራ ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን!" ይህ ርምጃ በከተማዋ እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና በከፍተኛ ደረጃ የመቀነስ፣ የጎላ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ፋይዳዎች እንዳሉት ተገልጿል። ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የጭማሪው ማሳያ ምሳሌዎች (በ11.5% ስሌት መሠረት)፦ አዲሱ አዋጅ በሚፈቅደው ከፍተኛው የ11.5% የኪራይ ጭማሪ ጣሪያ መሠረት የወደፊቱ ክፍያ በሚከተለው መልኩ ይተመናል፦ 1. በአሁኑ ወቅት የቤት ኪራይ 15,000 ብር ለሚከፍሉ ተከራዮች ፦ ህጋዊው የጭማሪ መጠን 1,725 ብር ብቻ ስለሚሆን አዲሱ ጠቅላላ የቤት ኪራይ 16,725 ብር ይሆናል ማለት ነው። 2. በአሁኑ ወቅት የቤት ኪራይ 10,000 ለሚከፍሉ ተከራዮች ህጋዊው የጭማሪ መጠን 1,150 ብር ብቻ ስለሚሆን አዲሱ ጠቅላላ የቤት ኪራይ 11,150 ብር ይሆናል ማለት ነው። 3. በአሁኑ ወቅት የቤት ኪራይ 20,000 ብር ለሚከፍሉ ተከራዮች ህጋዊው የጭማሪ መጠን 2,300 ብር ብቻ ስለሚሆን አዲሱ ጠቅላላ የቤት ኪራይ 22,300 ብር ይሆናል። 4. በአሁኑ ወቅት የቤት ኪራይ 5,000 ብር ለሚከፍሉ ተከራዮች ህጋዊው የጭማሪ መጠን 575 ብር ብቻ በመሆኑ፣ አዲሱ አጠቃላይ ክፍያቸው ከ 5,575 ብር ይሆናል::

Open in Telegram
Views958+223%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#40106Photo
Views802+170%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#40105Text

ዜና፦ ቮዳኮም በሳፋሪኮም ውስጥ ያለውን የአብላጫ ድርሻ ግዥ ማጠናቀቁን ገለጸ፤ በኢትዮጵያ ያለውን የማደግ ፍላጎትም ጠቅሷል ​በደቡብ አፍሪካ መሥሪያ ቤቱን ያደረገው ቮዳኮም ግሩፕ  በሳፋሪኮም ኃ/የተ/የግል ማኅበር ውስጥ የነበረውን ድርሻ በ20% በማሳደግ፣ ጠቅላላ የባለቤትነት ድርሻውን ወደ 55% አካባቢ ማድረሱንና በኬንያ እና በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሰውን የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ የአብላጫ ባለቤትነት መብት መረከቡን አስታውቋል። ​ኩባንያው ሰኔ 23 ቀን  ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሰኔ 19 ቀን የኬንያ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረውን ዕገዳ ማንሳቱንና የቀሩት ቅድመ ሁኔታዎች በሙሉ መሟላታቸውን ተከትሎ ግብይቱ በይፋ መጠናቀቁን ገልጿል። ​እንደ ኩባንያው ገለጻ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በታኅሣሥ 2018 ዓ.ም  ይፋ የተደረገው ይህ የ2.1 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት፤ ከኬንያ መንግሥት የ15% ድርሻን እንዲሁም ከቮዳፎን ግሩፕ የ5% ድርሻን በአንድ አክሲዮን በ34 የኬንያ ሺሊንግ መግዛትን ያጠቃልላል። የኬንያ መንግሥት በናይሮቢ የአክሲዮን ገበያ ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን የሳፋሪኮምን 20% ድርሻ ይዞ ይቀጥላል። ​ቮዳኮም ይህ ግዥ የሳፋሪኮምን የፋይናንስ ውጤቶች በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS) መሠረት እንደ ተባባሪ ኩባንያ ከመቁጠር ይልቅ፣ በቀጥታ ከራሱ የሒሳብ መግለጫዎች ጋር አጠቃሎ ለማሳየት እንደሚያስችለው ገልጿል። ​ኩባንያው ይህ ግዥ በምሥራቅ አፍሪካ ያለውን ተደራሽነት እንደሚያጠናክርለት የገለጸ ሲሆን፣ በተለይም ሳፋሪኮም ወደ ሀገሪቱ የቴሌኮም ዘርፍ ከገባ ጀምሮ ወደ 14 ሚሊዮን ገደማ ደንበኞችን ያፈራባትን ኢትዮጵያን እንደ ዋና የማደጊያ ገበያ ጠቅሷታል። ​የቮዳኮም ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሻሚል ጁሱብ ግብይቱ “በኬንያ እና በኢትዮጵያ የዲጂታል እና የፋይናንስ አካታችነትን በሰፊው ለማሳደግ አዳዲስ ዕድሎችን ይከፍታል” ያሉ ሲሆን፣ ኩባንያው ሥራውን እያሰፋ ሲሄድ ከሁለቱም ሀገራት መንግሥታት ጋር አብሮ ለመሥራት እንደሚፈልግ አክለዋል። ​

Open in Telegram
Views667+125%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#40104Text

የዱባይ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ለመግባት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተገለጠ ​በአቡ ዳቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደገለጸው፣ የዱባይ ንግድ ምክር ቤት አባል የሆኑ ኩባንያዎች፣ ሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ የወሰነችውን ውሳኔ ተከትሎ “ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ እና የባንክ ዘርፍ ለመግባት ዝግጅት” ጀምረዋል። ​በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች  የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር፣ ከዱባይ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሐመድ አሊ ራሺድ ሉታህ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል። ኤምባሲው እንደገለጸው፣ ውይይቱ ከዱባይ የሚመጣውን ኢንቨስትመንት ለማመቻቸት ቀደም ሲል ከተደረጉ ስብሰባዎች ቀጣይነት ያለው ሲሆን፣ በቅርቡ በአዲስ አበባ የተካሄደውን የ“ዱባይ-ኢትዮጵያ ቢዝነስ ኮኔክት” መድረክን ውጤት የተመለከተ ነው። ​ሉታህ በ36 አባላት የተዋቀረ የንግድ ልዑካን ቡድንን በመምራት በቅርቡ በአዲስ አበባ ስላደረጉት ጉብኝት አንስተው፤ ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በተግባር መመልከቱን ኤምባሲው ጠቅሷል። ​እሳቸውም ማሻሻያዎቹ “ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ አየር” መፍጠራቸውንና ይህም በዱባይ በሚገኙ ባለሀብቶች ዘንድ “ከፍተኛ መነቃቃትን” መፍጠሩን ገልጸዋል። ​ይህንን ተከትሎም በምክር ቤቱ ስር ያሉ “ትላልቅ ኩባንያዎች” በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውን እና በቅርቡ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ወደተደረገው የኢትዮጵያ “የፋይናንስ እና የባንክ ዘርፍ” በይፋ ለመግባት “ከፍተኛ ዝግጅት መጀመራቸውን” አስታውቀዋል። ​ኤምባሲው አክሎም፣ አምባሳደር ጀማል የዱባይ ንግድ ምክር ቤት በአዲስ አበባ ጉብኝቱ ወቅት ላመቻቸው የንግድ ለንግድ  ትስስር ምስጋና ማቅረባቸውን የገለጸ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በፋይናንስ፣ በግብርና፣ በታዳሽ ኃይል እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ዕድሎችን ለሚፈልጉ የዱባይ ኩባንያዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

Open in Telegram
Views470+58%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#40103Photo

ስደተኞችን የተቃወመው የደቡብ አፍሪካውያን ሠላማዊ የተባለሠልፍ በተለያዩ አካባቢዎች እየተጀመረ ነው። የደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙኃን ከማለዳው ጀምሮ ስደተኞችን በተቃወመው የደቡብ አፍሪካውያን አስፈሪ የተቃውሞ ሠልፍ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሽፋኖችን በመስጠት ተጠምደዋል። በተለይም በጠዋቱ የዘገባ ሠዓታቸውየደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅቶ የተቃውሞ ሠልፉ ወደመጥፎ ክስተት እንዳይቀየር እየሰራ ስለመሆኑ በተለያዩ ከተማዎች ያሉ ሁኔታዎችን በማሳየት በስፋት ሲዘግቡተስተውለዋል። ከደቂቃዎች በፊት እየተሰሙ ያሉ መረጃዎች የማርች ኤንድ ማርች ንቅናቄ የሚመራው የተቃውሞ ሠልፍ በደርባን ኢተክዊኒ እና ምስራቅ ኬፕታውን አካባቢ ተጀምሯል። አፍሪካን ሬኔሳንስ ቴሌቪዥን ባገኘው መረጃ ሠልፉ በስፋት እንደሚከናወን ከተነገረባቸው ከተሞች አንዷበሆነችው ፕሪቶሪያ ፤ በተለይም የስደተኛ ሱቆች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል ተዘግተዋል።እንዲሁም በአካባቢው ያሉ የፀጥታ ኃይሎች በተጠንቀቅ ቆመው እየታዩ ነው። (Arts TV)

Open in Telegram
Views497+67%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#40102Text

ቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የ‘ጄሲአይ’ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱ ተነገረ ቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ ከጆይንት ኮሚሽን ኢንተርናሽናል (ጄሲአይ) የላቀ የሕክምና አገልግሎት ጥራትና የሕሙማን ደህንነት ማረጋገጫ ዕውቅና በማግኘት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሆስፒታል ሆኗል። ይህ በሀገሪቱ የጤናው ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ ተብሎ የተጠቀሰው ስኬት የተሰማው ሆስፒታሉ የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት ባከበረበት ወቅት ነው። የጄሲአይ ዕውቅና በዓለም አቀፍ ደረጃ በጤና ተቋማት የጥራት ቁጥጥርና የሕሙማን ደህንነት ጥበቃ ረገድ እጅግ ከፍተኛውና ተደራሽ ለመሆን አስቸጋሪው መመዘኛ እንደሆነ ይታወቃል። አንድ የሕክምና ተቋም ይህንን ዕውቅና ለማግኘት የክሊኒካዊ እንክብካቤ ደረጃን፣ የኢንፌክሽን መከላከያና መቆጣጠሪያ ስልቶችን፣ የመድኃኒት አያያዝን፣ የተቋማዊ አመራር ብቃትንና አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸምን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥብቅ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅበታል። ይህንን ስኬትና የሆስፒታሉን አንደኛ ዓመት በዓል አስመልክቶ በተዘጋጀው ሥነ-ሥርዓት ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል። በወቅቱ ንግግር ያደረጉት ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የተገኘው ዕውቅና ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ትልቅ ኩራት መሆኑን ገልጸው፣ ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና የሕሙማንን ደህንነት የሚያረጋግጡ የሕክምና ተቋማትን መገንባትና ማስተዳደር እንደምትችል ማረጋገጫ ነው ብለዋል። አክለውም መንግሥት የሀገሪቱን የሕክምና አገልግሎት ደረጃ ከፍ ለሚያደርጉና በጥራት ላይ ለሚሰሩ የግል የጤና ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍና ማበረታቻ ማድረጉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የሆስፒታሉ አመራሮች በበኩላቸው፣ ይህንን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ለማግኘት በሕክምና ሥርዓቱ፣ በመሰረተ ልማት እና በባለሙያዎች ልማት ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ መፈሰሱን ገልጸዋል። ስኬቱ የተገኘውም ከመላው የሕክምናና የአስተዳደር ሰራተኞች የተቀናጀ ጥረትና ለላቀ አገልግሎት ከነበራቸው ቁርጠኝነት በመነጨ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ይህ ዕውቅና ቤተስዳ ሆስፒታልን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተገዢነታቸውን ካረጋገጡ ጥቂት ተቋማት ተርታ የሚያሰልፈው ሲሆን፣ በሀገሪቱ የመንግሥትም ሆነ የግል የጤና ተቋማት የሕክምና ጥራትንና የአሠራር ሥርዓትን እንዲያሻሽሉ ምሳሌ እንደሚሆን የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል። ስኬቱ የኅብረተሰቡን በሀገር ውስጥ ሕክምና ላይ ያለውን እምነት ከማሳደጉም በላይ፣ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና በሕክምናው ዘርፍ ያላትን ስም እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል።

Open in Telegram
Views605+104%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#40098Photo

ማዕከላዊ ባንኩ ለአራተኛው ሩብ ዓመት 200 ሚሊዮን ዶላር ሊያቀርብ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  የ2018 በጀት ዓመት የመጨረሻ ሩብ ዓመት የውጭ ምንዛሬ ጨረታ መርሃ-ግብርን ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ለዚሁ ተግባር 200 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መመደቡን አስታውቋል። ይህ የተመደበው በጀት በሙሉ በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል መሆኑን ባንኩ ገልጿል። ​የማዕከላዊ ባንኩ መግለጫ እንዳመለከተው፣ ይህ አዲስ የአቅርቦት ስትራቴጂ በበጀት ዓመቱ መጠናቀቂያ ላይ የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ለማረጋጋት ታሳቢ ያደረገ ነው። ​ባንኩ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ይፋ ካደረገው 520 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦት አንጻር፣ በሦስተኛው ሩብ ዓመት የነበረው አሰራር በእያንዳንዱ ጨረታ 70 ሚሊዮን ዶላር በስድስት ክፍለ-ጊዜዎች መከፋፈሉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ አሁን ባለው የሰኔ ወር ዕቅድ መሠረት፣ አጠቃላይ 200 ሚሊዮኑ ዶላር በሁለት ዋና ዋና ጨረታዎች ተከፋፍሎ ይቀርባል፤ ይህም በእያንዳንዱ የጨረታ መስኮት 100 ሚሊዮን ዶላር እንዲኖር ያደርጋል ተብሏል።

Open in Telegram
Views827+178%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#40097Text

በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች በ500,000 እና 400,000 ብር ዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ። መንሱር ጀማል የተባለው ተከሳሽ ግን አቃቢ ህግ መቃወሚያ ስላቀረበበት ዛሬ ከሰዓት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ከድርጅቱ ጋር በተያያዘ በ1.9 ቢሊዮን ብር የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ታዋቂ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች፣ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ፈቅዷል። ባለፈው ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከ5 ተከሳሽ መንሱር ጀማል ውጭ ባሉ ተጠርጣሪዎች ከሀገር እንዳይወጡ እና ከፍ ያለ ዋስትና አስይዘው የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከውጭ ሆነው ጉዳያቸውን ቢከታተሉ እንደማይቃወም አስረድቶ እንደነበር ይታወሳል። ዛሬ በዋለው ዝግ ችሎት ተርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ተከብሮላቸው፣ ከእስር ተፈትተው በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። በዚህ መሠረት ከአንድ እስከ አራት ያሉ ተከሳሾች ማለትም ሰራዊት ፍቅሬ፣ ሰለሞን ቦጋለ፣ ይገረም ደጀኔና ዳንኤል ተገኝ በ500 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ሲፈቀድላቸው። ስድስተኛና ሰባተኛ ተከሳሽ አብርሀም ግዛውና ካሊድ ናስር በ400 ሺህ ብር እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ጠበቃ አበባው አበበ ነግረውናል። አምስተኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማል በተመለከተ አቃቢ ህግ ባቀረበው መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ 8 ሰዓት ቀጠሮ መሰጠቱን ጠበቃ አበባው አበበ ተናግረዋል፡፡ ሁሉም ተከሳሾች ከሃገር እንዳይወጡ እገዳም ተጥሎባቸዋል ተብሏል። (ገዛ ጌታሁን - ሸገር ኤፍኤም)

Open in Telegram
Views1,010+240%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#40096Text
Views892+200%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#40095Photo
Views884+198%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#40094Text

" ለሚፈጠረው ችግር ሁሉ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ስልጣን በጉልበት በመያዝ ላይ ያለው ኃይል መሆኑ እገልፃለሁ " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ባለፈው ማክሰኞ ሚያዝያ 27/2018 ዓ.ም 'ነባር ምክር ቤትና መንግስት መልሻለሁ ' ያለውና ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)ን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ የሰየመው ህወሓት ዛሬ በደብረፅዮን (ዶ/ር) መሪነት በክልሉ የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የመጀመሪያውን የካቢኔ ስብሰባ ማካሄዱን አስታውቋል። በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)  መሪነት የተከናወነው የካቢኔ ስብሰባ በክልሉ የዜና ማሰራጫዎች መነገሩ ተከትሎ በሰዓታት ልዩነት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) በፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ አጭር መልስ ሰጥቷል። የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ምን አሉ ? " በቅርብ ቀናት የተፈጠረው ሁኔታ ተከትሎ ሊመጣ የሚችለው ጉዳት ለማስቀረት ፤ ችግሩን በጋራ ውይይትና መግባባት ለመፍታት የቀረበውን ጥሪ ወደ ጎን በመተው 'የተመረጥኩኝ ነኝ ' የሚል አካል ዛሬ ሚያዝያ 30/2018 ዓ/ም የፀጥታ አካላት ጥበቃ ተሰጥቶት በጊዚያዊ አስተዳደሩ የመሰብሰብያ አዳራሽ የካቢኔ ስብሰባ ጀምሯል። ይህ ተግባር ቀጣይ አደገኛ መንገድ የተጀመረበት ቀን ስለሆነ በዚሁ ምክንያት ለሚከተለው አደጋ ሁሉ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ስልጣን በጉልበት በመያዝ ላይ ያለ ኃይል መሆኑ እገልፃለሁ " ብለዋል። በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) መሪነት የተከናወነው የካቢኔ ስብሰባ በዜና ማሰራጫዎች መዘገቡን ተከትሎ ዛሬ አርብ ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ለሁለተኛ ጊዜ የውግያ ጀት አውሮፕላን በመቐለ ከተማ ሰማይ ላይ መታየቱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ገልጿል። #ቲክቫህ

Open in Telegram
Views621+109%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#40093Photo
Views521+75%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#40092Photo
Views450+52%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—