Account

Posts of ግጥም ፍቅር ቅኔ

newest first

#11349Text

"ኢ-ፍትኃዊነት ፈጣሪን የመስደብ ያህል ታላቅ ኃጢአት ነው:: ምክንያቱም የተፈጥሮ ሕግ ምክንያታዊ ለሆኑ ፍጥረታት ይህንን ሥርዓት ሠርቷልና። ይኸውም እንደየባሕርያቸው እርስ በርስ ሊረዳዱ እንጂ ሊጎዳዱ አይደለም። ስለዚህም የተፈጥሮን ፈቃድ የሚተላለፍ ሰው አምላኩን ይሳደባል።" "ነገሮች እንዲሆኑ ወይም እንዳይሆኑ ከመጸለይ ይልቅ፣ ምንም ነገር ቢሆን እንዳትፈራ፣ እንዳትመኝ ወይም እንዳታዝን ለምን አትጸልይም? አምላክ ሰዎችን መርዳት የሚችል ከሆነ በዚህ መንገድ ሊረዳን አይችልምን? ምናልባት “እነዚህን ነገሮች አምላክ በእኔ ስልጣን - ስር አድርጓቸዋል” ትልም ይሆናል᎓᎓ ታዲያ በቁጥጥርህ ስር ያልሆነውን ነገር ለመለወጥ እንደ ባሪያ ወይም እንደ ለማኝ ከምትማጸን፣ በስልጣንህ ስር ያለውን በነጻነት መፈጸም አይሻልህምን?" “ይህ ነገር ሁሌም ይገርመኛል፦ ራሳችንን ከሌሎች ሰዎች ይልቅ አብልጠን እንደምንወድ የታወቀ ነው። ሆኖም ስለ ራሳችን ከምናስበው ይልቅ ሌሎች ስለ እኛ ስለሚያስቡት እንጨነቃለን። መልአከ ወይም ጠቢብ ሰው ተገልጦን በልብህ የምታስበውን አትደብቅ፤ ወዲያውኑ ጩኸሀ ተናገረው ቢለን፣ አንዲት ቀን እንኳ አንዘልቅም ነበር። ለራሳችን ካለን እወነታኝነት ይልቅ የሌሎች አስተያየት ያንን ያህል ይገዛናል።” “ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ ለራስህ እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ዛሬ የማገኛቸው ሰዎች ጣልቃ ገቦች፣ ምስጋና ቢሶች፣ ትዕቢተኞች፣ አታላዮች፣ ምቀኞችና ርሀራሄ የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲህ የሆኑት መልካሙን ከክፉው መለያት ስለማይችሉ ነው። እኔ ግን የመልካምን ነገር ውበትና የክፉንም ነገር አስቀያሚነት አይቻለሁ፤ ስለዚህ አንዳቸውም ሊጎዱኝ አይችሉም።” "እውነተኛ እድለኛነት ማለት፣ ውሸትን፣ ግብዝነትን፣  ትዕቢትን ሳያውቁና ሳይቀምሱ ከዚህ ዓለም መሰናበት ነበር፡፡ ነገር ግን “ቀጣዩ ምርጥ ዕድል” እነዚህን ክፉ ነገሮች ከተጠየፍክ በኋላ መሞት ነው:: ወይስ ከክፋት ጋር ለመተኛት ወስነሃል? ልምድህ እንኳ እንደ ቸነፈር በሽታ እንድትሸሸው  አላስተማረህምን? ምክንያቱም የአእምሮ ክፋት ከተበከለ አየር ከሚመጣ በሽታ ይልቅ እጅግ የከፋ ቸነፈር ነውና። የሥጋ በሽታ ሕይወትህን ብቻ ያጠፋል፤ ይህኛው ግን ሰውነትህንና ሰብአዊነትህን ይገድላል።" Marcus Aurelius 📖Meditation

Open in Telegram
Views139−66%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#11348Text

ንስር አሞራ እና አንተ ... አንቺ ... እኔ ...  🌏 ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ ... ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ... #የመጀመሪያው :-  ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ... #ሁለተኛው :-  አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ... #ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል። እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው። ♦ 1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ? ♦ 2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ? የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል። ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል። ፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል። ፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል። ፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር  ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡ ፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል። ፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። 🔖  ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡ 🔥 ወዳጄ ሆይ:- 🔥 ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል። ችግሬ ... ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡኡኡ አትበል ፣ ስንት ነገር መስራት የምትችልበትን አዕምሮ ለሃሜትና  "አሉ ... አለች" መሳሪያ በመጠቀም "የውሸት እየኖርክ - የእውነት አትሙት" ... በቃ! ...  ልክ እንደ ንስር አሞራ በህይወትህ አጋማሽ ላይ ምርጫ መቶልሃል ... 🍋 ፩ኛ. ችግሩን ታቅፎ መሞት ... ፪ኛ. ለችግሩ መስዋትነት ከፍሎ ማለፍ ... ••• ♦ አስተውል ... ♦••• ሁለተኛውን ከመረጥክ ልክ እንደ ንስሩ አምስት ዋጋዎችን መክፈል አለብህና ዝግጁ ሁን ... ፩ኛ. ራስህን ከነገሮች አርቀህ በፅሞና ሃሳብህን መግራት ጀምር ... እዚህ ጋር ከወዳጅም ከጠላትም መራቅ ፍቱን መድሃኒት ነው ... ንስር አሞራው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚወጣው ከሁሉም ንስሮች እርቆ ለህይወቱ ዋጋ ለመክፈል ነው ... ይህን አይነት መላ ምሁራኑ "የስኬት ሱባኤ" ይሉታል። ፪ኛ. አንገብጋቢ ችግርህን ለመፍታት ቁርጥ ያለ አቋም ይዘህ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋትነት መክፈል። ንስሩ አፉ ላይ ያለውን ምግብ ማምጫ መንቁሩን እንደሚያስወግደው ሁሉ። ፫ኛ. መስዋት የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ... ይህ ደግሞ ንስሩ መንቁሩ እስኪያድግለት ድረስ ምግብ ሳይበላ እንደሚኖረው ሁሉ አንተም ዋጋ የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትእግስት እና እምነት መጠበቅ። ፬ኛ. በትእግስት ጠብቀህ ያሰብከው ነገር ከመጣ በዋላ ህይወትህን ጠፍንገው የያዙህን ነገሮች መፍታት ... ልክ ንስሩ መንቁሩ እንዳደገለት የእግሩን ጥፍሮች በመንቁሩ እየወጋ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ። ፭ኛ. ሁሉን ካሳካህ በዋላ ወደ ህልምህ መብረር ... ይህ ማለት ንስሩ የእግሮቹን ጥፍር አስወግዶ እና አሮጌ ክንፎቹን አስወግዶ ከጠበቀ በዋላ አዲስ ክንፍ ፣ አዲስ መንቁር እና አዲስ ጥፍር ካበቀለ በዋላ እንደ አዲስ ጉልበታም ንስር ቀሪ ዘመኑን ይኖራል። ሲጠቃለል ... 🔖🔖🔖 አንተም ፣ አንቺም ፣ እኔም በዚህ ሁሉ መንገድ አልፈን ከባዱን ጊዜ ካለፍን በዋላ በአዲስ የህይወት መንቁር ፣ የተስፋ ጥፍር እና የስኬት ክንፍ ከፍ ብለን እንበር ዘንድ ..... ኑ ንስር አሞራን እንምሰል። ♥ " . . " " 😉      @hollypoem 👕👉 @hollypoem 👖      @hollypoem

Open in Telegram
Views181−56%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#11344Text
Views399−2%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#11343Text
Views427+4%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#11342Text
Views476+16%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#11341Text
Views607+49%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#11340Text

ያ...ወጣት ከጉባኤው መሃል.. ከአዳራሹ ጥግ ከምዕመኑ ጀርባ አንድ ወጣት ይታያል ከራሱ ያደባ ነፍስ አልባ ገላ መንፈስ እየጠማው ከህዝቡ ነጠላ እግዚያር አልባ በድን ገላን ይዞ የሚፍጨረጨረው ከምዕመኑ ጋራ ስሜት ለመጋራት፣ በራሱ ዓለም ነው ወኔን የሚጭረው በድን ይዞ አካል ስጋ የእግዚያር ዓለም ለሱ መቼ ነጋ አ..ል..ነ..ጋ..ም። እዚያ ከመቅደሱ ስግዱ  ሲል ድንገት፣ ዲያቋኑ ተነስቶ ሁሉም ሰው ሲያለቅስ፣ ለነፍሱ ተደፍቶ የመንፈሱ ሙላት፣ በቅጡ ያልገባው እንዴት? ለምን? የሚል ለነፍስ የሚነባው አንድ ወጣት ይታያል፣ ከምዕመኑ ጀርባ ሃሳብ የሚንጠው፣ ከራሱ ያደባ። ትላንት የነበረው... ሁሉም እልል ሲል፣ ታሪኩን እያወሳ ትላንቱ የጠፋው፣ እራሱን የረሳ አምላኩን እንኳን ማወደሻ ሽርፍራፊ ትላንት፣ ታሪክ ማስታወሻ ከልቡ ከረጢት፣ ፈትቶ ሚበረብር አንድ ወጣት ይታያል ማነኝ በሚል ጭጋግ፣ ነፍሱ ምትሸበር። እዚያ ከመቅደሱ ቅዱስ መንፈስ መጥቶ ሲያርፍ በነፍስ አካል ሲርከፈከፍ ህዝቡ ሃሴት ሲጭር፣ ሰማይ ሲሄድ በመንፈሱ አንድ ወጣት ይታያል ብቻውን የቀረ፣ እዚያው ከመቅደሱ። እራሱን የታዘበ አካል ስጋው የለዘበ ማነኝ ያለ ገላ፣ ያዘነ ከነፍሱ መንፈሱን የገፋ፣ የቀረ ከራሱ ከመስኮቱ ታክኮ፣ መገኘቱን ያጣ አንድ ወጣት ይታያል መሄድ የሚቃጣ። ¶ መሽቶ ነግቶ፣ በሳምንቱ የሱ ስፍራ ከመስኮቱ አካል ስጋው እያነባ ሰውነቱ' ከሰው ጀርባ አንድ ወጣት ይታያል፣ እግዚያሩን ሚጠብቅ እስከ በደል ጉድፉ ሙት አካል ነኝ ያለ እስኪጎድል ሰልፉ " እስከመቼ ሲሉት እስካገኘው ያለ አንድ ጭፍርር ወጣት መስኮቱ ጋር አለ። እስከ መች? እስካገኘው By semere @hollypoem

Open in Telegram
Views578+41%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#11339Text
Views510+25%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#11337Text

ኩርት ቮነጉት የጦርነትን አሰቃቂነት እና የሰው ልጅ ዕብደትን በህይወቱ ተሞክሮ ልክ እንዳልሆነ አይቶ የሚያሳይ ደራሲ ነው፡፡ ኩርት ቮነጉት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጀርመን ድሬስደን ከተማ የቦምብ ድብደባ ውስጥ ተይዞ ከሞት የተረፈ ሰው ነው። ይህ ገጠመኙ ጦርነት የጀግንነት ማሳያ ሳይሆን ንጹሐንን የሚጨፈጭፍ፣ ሰብአዊነትን የሚያጠፋ እና ትርጉም የለሽ አረመናዊ ድርጊት መሆኑን ይናገራል፡፡ ኩርት ቮነጉት በሞራል እና በፖለቲካ መካከል ስላለው  ግጭት "ማዘር ናይት" ብሎ በሰየመው ድረሰቱ  በጦርነት ጊዜ መንግሥታት ሕዝቦችን ለራሳቸው ዓላማ ሲሉ "ጥሩ" እና "ክፉ" ብለው ይከፋፍሏቸዋል ይለናል። ነገር ግን በግለሰብ ደረጃ "ለሀገር ብዬ ነው" "ተላላኪ ነበርኩ" ወይም "የትዕዛዝ ግዴታ ነው" ተብሎ የሚሰራው ክፉ ነገር የሰውን ህሊና እና እውነተኛ ማንነት ለዘላለም እንደሚበክለው ለማሳየት ይሞክራል። ኩርት ቮነጉት "እኛ የምንመስለው የምንመስልበትን ነገር ነን" ይለናል፡፡ ይህም ማለት በውስጣችን ጥሩ ሐሳብ አለን ብንልም በውጭ ላይ የምንፈጽመው ተግባር ጥላቻን መስበክ፣ መከራን ማባባስ ይሆናል፡፡ ይህም በሂደት የእኛ እውነተኛ ማንነት ይሆናል ስለዚህ ድርጊታችን ከሐሳባችን ጋር ሊጣጣም ይገባል እያለ አበክሮ ይሞግተናል። ኩርት ቮነጉት በጦርነትና በግጭት ጊዜ "እኛ ፍጹም ጻድቃን ነን፣ እነሱ ደግሞ ፍጹም ክፉዎች ናቸው" የሚለው አመለካከት የሐሰት ትርክት መሆኑን እና ሁለቱም ወገን የሰውን ልጅ ሕይወት እንደሚያጠፉ ያሳያል። እንደ "ማዘር ናይት" ታሪክ ሁሉ ዛሬም በኢትዮጵያ ውስጥ በፖለቲካ እና በቡድን ስም ተነስተው ጥላቻን የሚሰብኩ ሕዝብን እርስ በእርስ የሚያጣሉ አካላት አሉ። ኋላ ላይ "ለዓላማ ብዬ ነው" ወይም "በትዕዛዝ ስር ስለነበርኩ ነው" "ተላላኪ ነበርኩ"  የሚሉ ማስተባበያዎች ቢቀርቡም በምድር ላይ የጠፋው ንጹህ ሕይወት እና የተበላሸው ማህበራዊ ትስስር ግን ሊመለስ አይችልም። ስለዚህ ማይክ በያዝን ወቅትም ሆነ አደበታችንን በከፈተን ጊዜ ሁሉ "ምን እየፈጠርን እና ምን እያስተላለፍን ነው?"ብሎ መጠየቅ የጊዜው ጥያቄ ነው። በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ባሳለፈቻቸው ግጭቶችና ጦርነቶች ያየነው እውነት ቮነጉት ከድሬስደን ውድቀት ጋር ካስተማረው ትምህርት ጋር አንድ ነው። በጦርነት ውስጥ አሸናፊ የሚባል ወገን የለም፡፡ ሁለቱም ወገን የሚያጡት ወጣቶቻቸውን፣ ሰብአዊነታቸውን እና ሀገራዊ ሀብታቸውን ነው። ስለሆነም ዛሬም ቆም ብለን ብናስብ፡፡ ለሕይወት እና ለአብሮነት መስጠት ያለብን ዋጋ ብንሰጥ በየቀኑ የሚሞተውን ህይወት መታደግ እንችላለን፡፡ ቮነጉት በድረስቱ እንዳለው  ሰው በምድር ላይ የሚቆየው እጅግ ለአጭር ጊዜ ነው። ይህችን አጭር ዕድሜ በጎጥ፣ በዘር እና በጥላቻ ከማጥፋት ይልቅ እርስ በእርስ በመተሳሰብ፤ ተፈጥሮን በመውደደ ና በመዋደድ የተሰጠንን የሕይወት ስጦታ በምስጋና ማሳለፍ እንዳለብን ይነግረናል፡፡ ቮነጉት በ"ካትስ ክሬድል" ስራው ላይ  እንዲህ እያለ ይቃትታል "እግዚአብሔርም ብቸኛ ሆኖ ተሰማው። እግዚአብሔር ጭቃ ፈጠረ። ስለዚህ ለአንዳንድ ጭቃዎች እንዲህ አላቸው፦ "ተነስታችሁ ተቀመጡ!" እግዚአብሔርም "የፈጠርኳቸውን ሁሉ ተመልከቱ፤ ኮረብታዎቹን፣ ባሕሩን፣ ሰማዩን፣ ከዋክብቱን" አለ። እኔም ተነሥቼ እንድዞር እና እንድመለከት ከተደረጉት ጭቃዎች መካከል አንዱ ነበርኩ። ዕድለኛ ነኝ፡፡ ዕድለኛ ጭቃ! እኔ ጭቃው ተነሥቼ ተቀመጥኩ፡፡ እግዚአብሔርም ምንኛ ድንቅ ሥራ እንደሠራ ተመለከትኩ። በጣም አሪፍ ሥራ ነው እግዚአብሔር! ከአንተ በቀር ማንም ይህንን ሊያደርገው አይችልም ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሆይ! እኔማ ከቶውንም አልችለውም ነበር። ከአንተ አንጻር ስታይ እኔ ከቶውንም ዋጋ የሌለኝ ሆኖ ይሰማኛል። እኔ ትንሽ መሆኔን ረሳሁ ብዬ የምፅናናበት ብቸኛ መንገድ ተነሥተው እንዲቀመጡ እና ዓለምን እንዲመለከቱ ዕድል ያልገጠማቸውን ያን ሁሉ ጭቃ ሳስብ ብቻ ነው። እኔ ብዙ አገኘሁ፡፡ አብዛኛው ጭቃ ግን ይህ እድል አልሆነለትም። ለዚህ ታላቅ ክብርም አመሰግናለሁ! አሁን ጭቃው እንደገና  ይተኛል። ጭቃው ሊኖሩት የሚችሉ ምን ያህል አስደናቂ ትዝታዎች ናቸው! የገጠሙኝ ሌሎች አስደናቂ ተነስተው የተቀመጡ ጭቃዎች (ሰዎች) ምንኛ ድንቅ ነበሩ! ያየሁትን ሁሉ ወደድኩት!" ይለናል፡፡ በየቀኑ የሰውን ልጅ የሞት ዜና መስማት ያማል ፡፡ በጋራ ለመዳን በጋራ መቆም አለብን፡፡ለየብቻው እና በየተራ የሚያለቅስ ህዝብ አይሻገርም!! ፀሀፊ - ዮናስ ዘውዴ @hollypoem

Open in Telegram
Views478+17%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#11335Link preview

​​​በፊልሙ «300» ውስጥ እንደ አስፈሪና ኃያል ንጉሥ የተቀረጸውን ሰው ታውቃታላቹ መቸም.. ስሙ ዘርክሲስ 1 ይባላል። ከ2,400 ዓመታት በፊት ከዓለም ታላላቅ ኢምፓየሮች አንዱን ይመራ ነበር። ግሪክን ለማሸነፍ ታላቅ ወረራ አደረገ፤ ግን ታሪኩ በድል ብቻ አልተጠናቀቀም። ​ዘርክሲስ 1 በግምት 518 ዓ.ዓ. አካባቢ ተወለደ። አባቱ ታላቁ ዳርዮስ 1 ሲሆን፣ እናቱ አቶሳ ነበረች። አቶሳ የታላቁ ቂሮስ ልጅ ነበረች። ይህም ዘርክሲስን ከፋርስ የንጉሣዊ ቤተሰብ ሁለት ኃያላን መሪዎች ታሪክ ጋር ያገናኘዋል። ​ስለ ትክክለኛው የልጅነት ሕይወቱ ብዙ ዝርዝር መረጃ የለንም። ነገር ግን በንጉሣዊ ቤተሰብ ውስጥ አድጎ የኢምፓየሩን ሥልጣንና ኃላፊነት የሚያውቅበት አካባቢ እንደነበረ መረዳት ይቻላል። ​486 ዓ.ዓ. አካባቢ አባቱ ዳርዮስ 1 ከሞተ በኋላ ዘርክሲስ የፋርስ ንጉሥ ሆነ። በዚያን ዘመን የፋርስ ኢምፓየር ከሰሜን አፍሪካና ከእስያ እስከ ሌሎች ሰፊ ክልሎች የተዘረጋ ኃያል መንግሥት ነበር። ​ነገር ግን ዙፋኑን ሲይዝ በኢምፓየሩ ውስጥ ችግሮች ነበሩ። በግብፅ የተነሳውን አመፅ አስተናገደ፤ በባቢሎንም የተነሱ ተቃውሞዎችን ለመቆጣጠር ሞከረ። እነዚህ ክስተቶች ንጉሡ ከመጀመሪያው ጀምሮ የገጠሙትን ፈተናዎች ያሳያሉ። ​ዘርክሲስ ከአባቱ ዳርዮስ ዘመን ጀምሮ የቆየውን ከግሪክ ከተሞች ጋር ያለውን ግጭት ቀጠለ። በ480 ዓ.ዓ. በግሪክ ላይ ታላቅ ወታደራዊ ዘመቻ አደረገ። ​የወረራው ዓላማ የግሪክን ተቃውሞ ማሸነፍና የፋርስን ቁጥጥር ማስፋት ነበር። ሠራዊቱ በየብስና በባሕር ተንቀሳቀሰ። የጥንታዊው ዓለም አስደናቂ ወታደራዊ ዘመቻዎች አንዱ ሆነ። ​በቴርሞፒላይ በሚባል ጠባብ መተላለፊያ ላይ የፋርስ ሠራዊት ከግሪክ ኃይሎች ጋር ተጋጠመ። በዚህ ጦርነት የስፓርታው ንጉሥ ሊዮኒዳስና ተዋጊዎቹ በታሪክ ታወቁ። ​የግሪክ ተከላካዮች ከፍተኛ ተቃውሞ ቢያሳዩም የፋርስ ሠራዊት በመጨረሻ መተላለፊያውን አለፈ። የሊዮኒዳስና የስፓርታውያን ታሪክ በኋላ በተለያዩ መጻሕፍትና ፊልሞች ውስጥ ተወዳጅ ሆነ። ​የፋርስ ሠራዊት ወደ ግሪክ ውስጥ ገብቶ አቴንስን ያዘ፤ የከተማዋም ክፍሎች ተቃጠሉ። በዚህ ወቅት ዘርክሲስ የግሪክን ተቃውሞ እንደሚያሸንፍ የሚያስመስል ወታደራዊ ጥቅም አግኝቶ ነበር። ​ግን ከተማ መያዝ ማለት ጦርነቱን ማሸነፍ አይደለም። የግሪክ ኃይሎች ጦርነቱን ለመቀጠል ተዘጋጁ፤ የዘርክሲስም ታላቅ ዘመቻ ወደ ወሳኝ ደረጃ ገባ። ​480 ዓ.ዓ. በሳላሚስ ደሴት አቅራቢያ የፋርስና የግሪክ መርከቦች ተጋጠሙ። የግሪክ ኃይሎች ጠባቡን የባሕር መንገድ በመጠቀም በፋርስ መርከቦች ላይ ወሳኝ ድል አገኙ። ​ይህ ድል የዘርክሲስን የወረራ ዕቅድ ከባድ ፈተና ውስጥ ከተተው። ንጉሡ ወደ ፋርስ ተመለሰ፤ ነገር ግን የሠራዊቱ ክፍል በግሪክ ቀረ። ​በ479 ዓ.ዓ. በፕላታያ የፋርስ የየብስ ሠራዊትም ተሸነፈ። ይህ የግሪክን ወረራ ለማስፋት የነበረውን የዘርክሲስ ዕቅድ በእጅጉ አዳከመው። ​ዘርክሲስ በጦርነት ብቻ አልታወቀም። በፋርስ ዋና ከተማዎች ውስጥ የንጉሣዊ ሕንፃዎችንና የሥነ ሕንፃ ሥራዎችን አስቀጠለ። በፐርሴፖሊስ የአባቱን የግንባታ ሥራዎች አስፋፋ፣ እንዲሁም የንጉሣዊ ሥልጣኑን የሚያሳዩ ሕንፃዎችን አስገነባ። ​እነዚህ ሕንፃዎች የፋርስ ኢምፓየር ሀብትን፣ የንጉሣዊ ሥልጣኑንና የዘመኑን የሥነ ሕንፃ ብቃት የሚያሳዩ ምልክቶች ሆነው ቀሩ። ​ዘርክሲስ 1 እስከ 465 ዓ.ዓ. ድረስ ገዛ። በዚያ ዓመት በቤተ መንግሥት ውስጥ በተፈጠረ ሴራ ተገደለ። በግድያው ውስጥ የቤተ መንግሥቱ ኃላፊዎች እንደተሳተፉ የጥንት ምንጮች ይናገራሉ፤ የክስተቱ ዝርዝሮች ግን ሙሉ በሙሉ አንድ አይደሉም። ​ከሞቱ በኋላ ልጁ አርታክሰርክሲስ 1 ዙፋኑን ያዘ። ዘርክሲስ የፋርስን ሰፊ ኢምፓየር ቢመራም፣ በግሪክ ላይ ያደረገው ወረራ በመጨረሻ ወሳኝ ድሎችን ማምጣት አልቻለም። ​የ2006ቱ 300 ፊልም ዘርክሲስን በጣም የተለየ መልክ ያሳያል። ይህ የፊልም ጥበባዊ ትርጓሜ ነው፤ የታሪክ ሰነድ ወይም የንጉሡ ትክክለኛ ምስል አይደለም። የዘርክሲስ ቁመትና መልክ በፊልሙ እንደታየው እንደነበር የሚያረጋግጥ ታሪካዊ ማስረጃ የለም። ​ዘርክሲስ 1 የኃያል ኢምፓየር ንጉሥ፣ ታላቅ ወረራ ያደረገ መሪና በታሪክ ውስጥ የተወሳ ሰው ነበር። ታሪኩ ግን አንድ ትልቅ ትምህርት ይሰጠናል፤ ታላቅ ሠራዊትና ሰፊ ኢምፓየር መኖር ሁሉንም ጦርነቶች ለማሸነፍ ዋስትና አይሆንም። " @hollypoem

Open in Telegram
Views497+22%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#11334Text
Views489+20%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#11333Text
Views557+36%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11331Text

ጠቃሚ ምክሮች❗ እስከመጨረሻው አንብቡት👇 📌በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል። 📌ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። 📌የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም፣ ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ። 📌ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ፣ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው፣ በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። 📌 ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ። 📌የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ። ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። 📌ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ። 📌የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። 📌ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ። ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ። 📌ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ። ላለው አትሩጥ ፣ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። 📌ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ፣በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር። 📌ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ። ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው። 📌እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ። 📌ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ። :በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ። 📌የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ። 📌ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! :መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው። 📌ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል። 📌ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። 📌እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው። 📌ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ። 📌ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። 📌ሠዎች  የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ። ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ። 📌የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው። 📌ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ። :📌ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።: ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ። 📌እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ። 📌ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤ ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ። " @hollypoem

Open in Telegram
Views743+82%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#11330Text
Views600+47%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—