Account

Posts of ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት

newest first

#1851Link preview
Views796+46%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#1850Photo
Views645+19%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#1849Link preview
Views552+2%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#1848Text

Forwarded from ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት

🌿🌷🌷🌷🌷🌿 ክፍል ፪ 🌿🌷🌷🌷🌷🌿 🌿ቅድስቲቱ ገዳም የመግባት ፍላጎቷ እየጨመረ መጣ። ከዚያም ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆርዮስ ተገለጸላት። ስለእርሱ ሰምታ አታውቅም ነበረ። እርሱም ራሱን ካስተዋቃት በኋላ ወደ ገዳሙ ወሰዳት። ከወሰዳትም በኋላ ገዳሙን ሁሉ አስጎበኛት። በኋላ ወደ ቤቷ በደቂቃ መለሳት ገዳሙ ርቀት ነበረዉ። የወሰዳትም በሕልም ሳይሆን በውን በፈረሱ ነዉ፡፡ 🌿 እመቤታችን ለእናትየዋ ተገልጻላት ያኔ ስትወልጂ የኛ ነች ብየሽ አልነበረ አሁንም ወደገዳም ውሰጃት አለቻት። (ምክንያቱም አባቷ አትሄጂም ብሎ ስለከለከላት)፡፡ ገዳምም ገብታ የገዳም ኑሮ ጀመረች በዚያ ገዳም እማሆይ አፍሮዚና የምትባል ኢትዮጵያዊት ቅድስት መናኝ ነበረች። እርሷም እንዳየቻት "ኢንቲ አልደብራ ረይሳ ደብራ አቡ ሰይፈን" አሏት። ትርጓሜውም አንቺ የደብረ አቡሰይፈን ገዳም እመምኔት (አለቃ) ትሆኛለሽ ማለት ነው። (ግብፆች ቅዱስ መርቆሬዎስን አቡሰይፈን ብለዉ ይጠሩታል አቡሰይፈን ማለት የሁለት ሰይፎች አባት ማለት ነዉ፡፡) 🌿የበጎ ነገር ጠላት የሆነዉ ሰይጣን ቅድስቲቱን ይፈትናት ነበር። እርሷም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታባረዉ ነበር። እመቤታችንም በየጊዜዉ ትጎበኛት ነበር፡፡ 💠የተተነበየላት ነገር ደረሰ እመምኔት እንድትሆን በቅዱስ ቄርሎስ ስድስተኛ ተመረጠች። እርሱም ፕትርክና ከመሾሙ በፊት አንድ ጊዜ አግኝቷት እመምኔት እንደ ምትሆን ነግሯት ነበር፡፡ ከዚያም ቅድስት ታማቭ ኢሪኒ እኔ እመምኔት መሆን አልፈልግም አለች። በግድ ጎትተዉ ወደ ጳጳሱ ወስደዋት ተባርካ አስኬማ ለብሳ እመምኔት ሆነች። 💠እመምኔት ከሆነች በኋላ በግል ፀባዩዋ ላይ የታየ ለውጥ አልነበረም። እንደድሮ ትህትናዋን ለብሳ እናቶችን ታገለግል ነበር። የቅዱስ ፓኩሚየስን ( ጳጉሚስ) የገዳማዊ ኑሮ ሥርዓት እንደገና በስራ ላይ እንዲውል ያደረገች ቅድስት ናት፡፡ 💠ካለችበት ቦታ ወደ ፈለገችው ቦታ ልክ እንደቀደሙት ቅዱሳን ወዲያውኑ ሰከንድ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትደርስ ነበር። ገነት እና የተሰወሩ የቅዱሳን ያሉበትን ቦታ በየጊዜው ትጎበኝ ነበር። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ድንግል እናቱ እና ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሌሎች ብዙ ቅዱሳን ጋር መጥተው ያረጓጓት ነበር።የሰዎችን ችግር ማንም ሳይነግራት አውቃ እስከነመፍትሄው ነግራ ታጽናናቸው ነበር። በሽተኞችን ትፈውስ ነበር። ያዘነውን ታረጋጋ ነበር። ገዳሙን ከነበረበት ችግር አላቃ ወደ ትልቅ ገነትነት ለውጣዋለች ። እናም ብዙ ልጆችን(መነኮሳያት) አፍርታ እነርሱም እንደእርሷ የበቁ ለመሆን ችለዋል፡፡መሞት አይቀርምና ገዳሙን በደንብ ካስተዳደረች በኋላ በክብር አርፋለች፡፡ 🙏ጸሎትና በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በታላቋ ቅድስት ጻድቅ ታማቭ ኢሪኒ ጸሎት ይማረን።🙏 Credit : ከወንድሜ ዲያቆን ሚካኤል fb page @hiwotemenekosat

Open in Telegram
Views412−24%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#1847Text

Forwarded from ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።✝ 🌿🌷🌷🌷🌷🌿 ክፍል ፩ 🌿🌷🌷🌷🌷🌿 🌼በጥቅምት 21 ታላቋ ቅድስት ጻድቅ ተዓምር አድራጊዋ ሁለተኛዋ ቅዱስ ፓኩሚዮስ (ጳኩሚስ) የዋህ እና ርህርት የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ መርቆሪዎስ የሴቶች ገዳም እመምኔት እና የሰማዕቱ ወዳጅ የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቅድስት ታማቭ ኢሪኒ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው። 🌸ይህች ቅድስት የተወለደችዉ በግብፅ አገር ልዩ ስሙ ጊርጋ በተባለ ስፍራ ነዉ፡፡ የልደተት ስሟ ፋውዚያ ይባላል፡፡ ይህች ቅድስት እንደ ሌላዉ ቅዱሳን በሰላም አልተወለደችም ማለትም እናቷ ከመጠን በላይ ነበር የታመመችዉ (እርሷን በምትወልድበት ጊዜ) በዚያ በጭንቅ ሰዓት አባቷ እና አያቷ ይፀልዮ ነበር። አባቷ አምላክን ለወለደች ለክብርት እመቤታችን አያቷ ደግሞ ለሰማዕታት አለቃ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲያማልዷቸዉ አጥቀብዉ ይጸልዮ ነበር። 🌻 ከዚያም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትላ መጥታ ለእናትዋ ተገለጸችላት ቅዱስ ጊዮርጊስንም 'ጀርባዋን ዳስሰዉ' አለችዉ። እርሱም እጅ ነስቶ ጀርባዋን ዳሰሰዉ በሰላምም ተገላገለች። እመቤታችንም ህጻኗኗን ታቅፋ 'ይህች ልጅ የእኛ ናት' ብላ ህጻኗኗን ባርካ ወደ ሰማይ አረገች፡፡ 🌸ከዚያም እያደገች በሄደች ቁጥር ለክርስቶስ ያላት ፍቅር እየጨመረ መጣ። ሳታውቀውም ወደ ገዳም ለመሔድ ትናፍቅ ጀመረ። እንደዚህ አይነት ፍላጎት የጀመራት ገና የ8 ዓመት ልጅ በነበረችበት ጊዜ ነዉ፡፡ 🌺የምትማረዉ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ነበረ በዚያም ደናግላን (ሴት መነኮሳየያት) ነበሩ። እንደ እድሜ ጓደኞቿ መጫወትን ትታ እነርሱን ታይ ነበረ። እንድ ቀን በትምህርት ቤታቸዉ በሚገኝ የደናግላኑ ጸሎት ቤት ሄደች። ከዚያም አንዷ የካቶሊክ ደናግል ስትጸልይ አገኘቻት። ጸለሎቷን እስክትጨርስ ቁጭ ብላ መጠባበቅ ጀመረች። 🌼ያቺ መነኩሲት ጸሎቷን ፈጽማ ወደ ተቀመጠችዉ ቅድስት ሄዳ ልጄ ምን ሆንሽ አለቻት። ቅድስቲቱም እኔ እንደእናንተ መነኩሴ መሆን እችላሁ? ብላ ጠየቀቻት። መነኩሲቷም አዎን ትችያለሽ አለቻት። በመቀጠልም በመጀመሪያ እኔ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ስለሆንኩ በራሴ ቤተክርስትያን ልቁረብና ከዚያም ልቀላቀላችሁ አለቻት። 💐መነኩሲቷም መነኩሴ መሆን ከፈለግሽ ትችያለሽ ግን መቁረብ የምትችይዉ በእኛ ቤተክርስትያን ነዉ። ምክንያቱም የእኛ እምነት ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይያልና አለቻት። ቅድስቲቱም ታዲያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማትን አላውቃቸውም አለቻት። መነኩሲቷም እኔ እገርሻለሁ ለምንኩስና የሚያስፈልጉትን ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ አስተምርሻለሁ ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖትሽን እንድትለቂ አልፈልግም አለቻት፡፡ 🌾መነኩሲቷም እንደነገረቻት በቤቷም ሆነ በቤክርስትያን ትጸልይ ነበረ። በተለይም ጠዋት ጠዋት ደስ የሚል የቤተክርስትያን ዕጣን ይሸታት ነበረ። ግን ይህ የሚሆነዉ ከቅዳሴ በፊት ነበረ፡፡ 🌼ይህ ነገር ያሳሰባት እናቷ ወደቤተክርስትያን ሄዳ ለካህኑ ነገረችዉ። እርሱም ልጅሽ የተባረች ናት ያ የዕጣን ሽታ ሥውራን ባህታውያን በሚጸልዩት ሰዓት የሚሸት ነዉ አላት፡፡ 🍀 ከጥቂት ጊዜያት በኋላ እናቷ ታመመች ህመሙም የሚያነቃንቅ አልነበረም። ይህንን የምታውቀዉ ቅድስቲቱ እናቷን አጽናንታ ወደ ቤተ-ክርስትያን ሄዳ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ሥዕል ፊት ቆማ መጸለይ ጀመረች። እመቤቴ ሆይ እባክሽ እናቴን ፈውሻት እኛ ልጆችሽ ነን አምንሻለሁ ብላ ጸለየች። 🌿በመቀጠልም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ለእናቷ ተገለጸቸላት እንዲህም አለቻት። ለምን ታለቅሻለሽ እናትየዋም ልጆቼ ህጻናት ናቸዉ እኔ ከሞትኩ እግዚአብሔር እንደሚፈልገዉ ላያድጉ ይችላሉ እባክሽን ከጌታ ፊት አማልጂኝ ታላቅ እህታቸዉ እስክታድግና ኀላፊነትን እስክትረከብ ድረስ አለቻት ። አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን መልሳ ከእኔ ጋር ነይ አለቻት። 🌿ከዚያም እናትየዋ ወዴት እኔ ለባለቤቴ ሳልናገር አልወጣም አለቻት። አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን መልሳ አንቺ በባልሽ ቦታ ብትሆኚ ከጌታ እናት ጋር ለመሔድ ደስ ይልሽ ነበረ ብላ ወደ ሰማይ ይዛት ሄደች። ከዚያም በመልካም መኝታ አስተኛቻት። 🌿 ከዚያም እመቤታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ጊዮርጊስ እስኪ እያት መርራት አለችዉ። እርሱም እናቴ እመቤቴ ሆይ እንደምታውቂዉ የእርሷ ጉዳይ አብቅቷል ድናለች አላት። ክብርት እመቤታችንም እኔ እንዳማልዳት ጠይቃኝ ነበረ እኔም ልመናዋን ተቀብዬ ለልጄ ለወዳጄ ነግሬዋለሁ አሁን ያለባትን ችግር ነቅለህ ጣልላት አለችዉ። ቅዱስ ጊዮርጊስም እናቴ ያንቺ እጅ ይዳሳትና ከዚያ አወጣወዋለሁ አላት። እመቤታችንም ዳሰሰቻት ቅዱስ ጊዮርጊስም አውጥቶ ለእናትየዋ ይህንን ይዘሽ ወደቤትሽ ሒጂ አላት፡፡ Credit : ከወንድሜ ዲያቆን ሚካኤል fb page @hiwotemenekosat

Open in Telegram
Views421−23%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#1846Photo

Forwarded from ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

ማኅበረ ቅዱሳን በአርሲ  ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ሃይማኖታዊ ጥቃት ለደረሰባቸውና በድርቅ ለተጎዱ  ወገኖች የድጋፍ ማሰባሰብ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አሳወቀ። ጥቅምት ፲፬ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም በአርሲ  ዞን በተለያዩ ወረዳዎች  በደረሰው ሃይማኖታዊ ጥቃት ምክንያት ከ60 በላይ ክርስቲያኖች ሕይወታቸው ማለፉና  የአካል ጉዳት የደረሰባቸው  በተጨማሪም በርካቶች መፈናቀላቸው ይታወቃል፡፡  እንዲሁም  በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ፣ ጠለምት፣ በየዳና ጃና አሞራ፣ እንዲሁም በዋግኸምራ ዞን ሰሃላና አካባቢው ድርቅ መከሰቱ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም ማኅበረ ቅዱሳን ለተፈናቀሉና በተለያዩ የሕክምና ተቋማት ሕክምና እያገኙ ለሚገኙ እና በድርቅ ለተጎዱ  ወገኖቻችን የሚውል የድጋፍ ማሰባሰብ ሥራ አራተኛ ቀኑን ይዟል። በዚህ የሃይማኖታዊና ሰብአዊ ድጋፍ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር የሚኖሩ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን  የድጋፍ ጥሪውን ተቀብለው በንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ። ይህም በችግር ውስጥ ላሉ ወገኖቻችን ያለንን ፍቅር፣ አንድነትና የወንድማማችነት መንፈስ በተግባር የሚገልጽ ነው ተብሏል። ማኅበረ ቅዱሳን ለዚህ የድጋፍ ጥሪ ምላሽ በመስጠት በገንዘብ፣ በሐሳብ፣ በጸሎትና በተለያዩ የማስተባበር ሥራዎች አስተዋፅኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናውን እያቀረበ፣የወገኖቻችን ችግር የሁላችንም ችግር በመሆኑ ይህን የድጋፍ ተግባር በቀጣይነት በሰፊው አጠናክሮ ለማስቀጠል  በተለይም ማኅበራዊ ተቋማትና የሚዲያ አካላት ለመላው ዓለም ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ሰጥታችሁ እንድትሠሩ እና የሁሉም  ተሳትፎ በሰፊው  እንዲጠናከር ጥሪውን ያቀርባል። 🔷አለሁ እኔ ለወገኔ🔷 👇👇👇 https://t.me/ArsiSupport

Open in Telegram
Views474−13%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#1843Link preview

Forwarded from ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት

​#ዝክረ_አበው_መነኮሳት ታላቁ ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ''''''''''''''''''''''''''' ''''''''''''''''''''''''''' ይህች ቀን ታላቁ ብርሃን እና ቅዱስ መነኮስ ዮሐንስ አጭሩ ያረፈባት ናት። በላዕላይ ግብጽ የቤጻ ሰው ነበር፥ አንድ ወንድምም ነበረው። ወላጆቹ ጻድቃን እና እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥በእምነት እና በጎ ስራ ባለጸጎች ነበሩ። 8 ዓመት ሲሆነው ልቡን ከዚህ አለም ምኞት እና ክብር መለሰ፤ የምንኩስናን ሕይወትም ይሻ ነበር። የእግዚአብሔር ጸጋ ወደ አስቄጥስ በረሃ እንዲሄድ አነሳሳው፤ በዚያም ወደ ተፈተነ እና ቅዱስ ወደ ሆነው ወደ አባ ጴምዋ(ባይሞይ) ወደ ሚባል የአል-ብህናሳ ሰው መጣ። ዮሐንስ አብሮት ይኖር ዘንድ አባ ጴምዋን ጠየቀው። ቅዱሱም ሲፈትነው እንዲህ አለ፦"ልጄ ከኛ ጋር መቆየት አትችልም፥ ይህ ከባድ በረሃ ነውና፥ በውስጡም የሚኖሩት በእጃቸው ከሚሰሩት ነው የሚመገቡት፥ ብዙ አጽዋማትንም ይጾማሉ፥ ጸሎትም እንዲሁ፣ መሬት ላይ መተኛት እና ይህን የመሰለውን ብዙ ትሕርምት ይፈጽማሉ። ሂድ እና ወደ አለም ተመልሰህ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር" አባ ዮሐንስም እንዲህ አለው፦"እባክህን ስለ እግዚአብሔር ስትል አትመልሰኝ፥ እኔ የመጣሁት በትዕዛዝህ እና ጸሎትህ ስር ለመሆን ነውና። ከተቀበልከኝ እግዚአብሔር ልብህን በኔ ደስ እንደሚያሰኘው አምናለሁ።" አባ ጴምዋ ምንም ነገር ቢሆን በፍጥነት ያለማድረግ ልምድ ነበረው፥ ስለዚህ ወጣት ሰው ጉዳይ እንዲገልጥለት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየ። የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት እንዲህ አለው፦"ምርጥ ዕቃ ይሆናልና ተቀበለው።" አባ ጴምዋ ወደ ራሱ አምጥቶት የራሱን ጸጉር ላጨው። የመነኮሳትን ቀሚስ ዘርግቶ ለሦስት ቀናት እና ሌሊቶች ጸለየበት። ቀሚሱንም ሲያለብሰው መልአኩ የመስቀል ምልክት አድርጎ ሲያማትብበት ተመለከተ። ቅዱስ ዮሐንስ የምንኩስና ሕይወቱን በታላቅ ትሕርምት እና ታላላቅ ስራዎች ጀመረ። ከዕለታት አንድ ቀን አባ ጴምዋ ሊፈትነው ወደደ፥ ስለዚህም እንዲህ እያለው ከበዓቱ አስወጣው፦"ካንተ ጋር መኖር አልችልም" ዮሐንስ ለ 7ቀናት በውጭ ኖረ። በየለቱም አባ ጼምዋ እየወጣ በዘምባባ ቅርንጫፍ ይመታው ነበር፥ ዮሐንስም "በድያለሁ" እያለ በፊቱ ይሰግድ ነበር። በሰባተኛው ቀን ወደ ቤተክርስቲያን ሊሄድ ወጣ፥ 7 መላዕክትም 7 አክሊላትን በአባ ዮሐንስ ራስ ላይ ሲያደርጉ ተመለከተ። ከዚያች ቀን ጀምሮ በክብር እና ፍርሃት ይይዘው ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን አባ ጴምዋ ደረቅ እንጨት አምጥቶ "ይህን እንጨት ውሰድ፥ ተክለህም ውሃ፣ አጠጣው" ብሎ አዘዘው። ቅዱስ ዮሐንስም ታዞ ከረጅም ርቀት(25ኪ.ሜ በላይ) ተጉዞ በቀን ሁለት ጊዜ ውሃ ያጠጣው ጀመር።ከሦስት ዓመታት በኃላ እንጨቱ ለምልሞ ፍሬ አፍርቷል።አባ ጴምዋ ከዚያ ፍሬ ጥቂት ወስዶ ለአረጋውያን መነኮሳት ሰጣቸው፥ እንዲህ እያለ፦"ውሰዱ ከመታዘዝ ፍሬ ብሉ" ይህ ዛፍ ዛሬም ድረስ በገዳሙ ይገኛል። አባ ጴምዋ ለ12 ዓመታት ታሞ ተኛ፥ አባ ዮሐንስም ያገለግለው ነበር፥ ከአገልግሎቱ አንድም ቀን አጉድሎ አስታጉሎ አያውቅም ነበር። አባ ጴምዋ በብዙ የተፈተነ እና የደረቀ እንጨት እስኪመስል ድረስ ህመም ሰውነቱን ያደቀቀው ልምድ ያለው አረጋዊ ነበር፥ ይህም የተመረጠ መስዋዕት እንዲሆን ነው። አባ ጴምዋ ከዚህ አለም ለማረፍ ሲቃረብ አረጋዊ መነኮሳትን ሰበሰበ እና የአባ ዮሐንስን እጅ ይዞ እንዲህ እያላቸው ሰጣቸው፦"እርሱ ሰው ሳይሆን መልአክ ነውና ውሰዱት፥ አኑሩትም።" ዮሐንስም እንጨት በተከለበት ቦታ እንዲቆይ አዘዘው። ከዚህን በኃላ የአባ ዮሐንስ ታላቅ ወንድም ወደ ገዳሙ መጣ፥ ከርሱም ጋር መነኮሰ። ክቡር መነኮስም ሆነ። ፓትርያርኩ አባ ቴዎፍሎስ አባ ዮሐንስን በገዳሙ መጋቢ እና አበምኔት አድርጎ እየሾመ ሳለ እጁን በራሱ ላይ ሲጭን እዚያ በነበሩት ሁሉ የተሰማ ድምጽ ከሰማይ መጣ እንዲህም የሚል፦"አግዚዮስ አግዚዮስ አግዚዮስ"(ይደሉ ወይም ይገባል ለማለት ነው)። ይህ ቅዱስ መስዋዕት ባቀረበ ጊዜ ማን ሊቀበለው የተገባ እና ማን ያልተገባ እንደሆነ ያውቅ ነበር። አባ ቴዎፍሎስ በእስክንድርያ ለሠለስቱ ደቂቅ ቤተክርስቲያን ሰራ፥ ስጋቸውንም አምጥቶ በውስጡ ሊያኖረው ወደደ። አባ ዮሐንስን ጠርቶት ወደ ባቢሎን ሄዶ ቅዱሱን ስጋቸውን ይዞ እንዲመጣ ጠየቀው። ከብዙ ጽናት በኃላ አባ ዮሐንስ ይህን ተልዕኮ ለመሄድ ተስማማ። ከፓትርያርኩ ሲወጣ ደመና መጥቶ ወደ ባቢሎን ነጠቀው። ወደ ከተማዋ ገብቶ በውስጧ ሃውልቶቿን፣ ወንዞቿን እና ቤተመንግስቶቿን ተመለከተ፥ የቅዱሳኑንም ስጋ አገኘ። ከቦታቸው ሊያንቀሳቅሳቸው በጀመረ ጊዜ ከቅዱስ ስጋቸው እንዲህ የሚል ድምጽ መጣ፦"እስከ ሙታን ትንሳኤ(ዳግም ምጽአት) ድረስ ይህን ቦታ እንዳንለቅ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ቢሆንም ስለ አባ ቴዎፍሎስ ፍቅር እና ስላንተም ድካም ስንል በቤተክርስቲያን ውስጥ እንገለጣለን፣ ምልክት ይሰጣችኃል፦ ለአባ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው ሁሉንም ሰው በቤተክርስቲያን እንዲሰበሰብ እና በማብራዎቹ ዘይት እንዲጨምር ነገር ግን እንዳያበራቸው ንገረው ስንገለጥ መብራቶቹ ይበራሉ።" አባ ዮሐንስ ወጥቶ ወደ እስክንድርያ ተመለሰ፥ ቅዱሳኑ ያሉትንም ለፓትርያርኩ ነገረው። ፓትርያርኩ እና ህዝቡ ሁሉ በቤተክርስቲያን ተሰብስበው ሳለ ድንገት መብራቶቹ በሩ፥ ሁሉም እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ከዕለታት በአንዱ ቀን አንድ መነኩሴ ወደ አባ ዮሐንስ በዓት መጣ፥ መላዕክት ክንፋቸውን በላዩ እያርገበገቡ ተኝቶ አገኘው። በኃላ ላይ በርበሮች ገዳሙን አጠቁት፥ አባ ዮሐንስም ሸሸ። ለምን እንደሸሸ ሲጠየቅ ሞትን ፈርቶ ሳይሆን እርሱን የሚገድለው በርበራዊ ሲዖል እንዳይገባ አዝኖ መሆኑን ተናገረ። ምንም እንኳ በአምልኮ ባይመስለውም በሰውነቱ ግን ወንድሙ ስለሆነ ነው። ከዚህን በኃላ በቀይ ባሕር። ወደ ሚገኘው ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ሄደ። በዚያም በአንዲት መንደር አቅራቢያ ተቀመጠ፥ እግዚአብሔር የሚያገለግለውን ምዕመን ላከለት። እግዚአብሔር እረፍት ሊሰጠው እና ሊያሳርፈው በወደደ ጊዜ ዕረፍቱን እንዲነግሩት እና እንዲያጽናኑት የርሱን ሁለት ጻድቃን አባ መቃርዮስን እና አባ እንጦንስን ላከለት። በእሁድ ዋዜማ ታሞ ተኛ፥ ረድዑንም የሆነ ነገር ከመንደሩ እንዲያመጣለት ላከው። መላዕክት እና የቅዱሳን ማህበር ቅድስት ነፍሱን ተቀብለው እሰክ ሰማያት አደረሷት። በዚያች ሰዓት አገልጋዩ ተመልሶ መጣ፥ የቅዱሱም ነፍስ በቅዱሳን ማህበር ተከባ፥ መላዕክቱም በነርሱ ፊት እየዘመሩ ተመለከተ። ከማህበሩም ሁሉ ፊት አንድ እንደ ፀሐይ የሚያበራ እና የሚዘምር አንድ ነበር። በዚህ ግሩም ነገር አገልጋዩ አደነቀ። አንድ መልአክ መጥቶም የእያንዳንዱን ቅዱስ ስም ነገረው። አገልጋዩም ከሁሉም ፊት ለፊት ያለውና እንደ ፀሐይ የሚያበራው ማን እንደሆነ ጠየቀው። የእግዚአብሔር መልአክም መልሶ እንዲህ አለው፦"ይህ የመነኮሳት አባት አባ እንጦንስ ነው።"አገልጋዩ ወደ በዓቱ ሲገባ ቅዱሱ ተንበርክኮ ነፍሱን እንደሰጠ አየ። ረድዑ በስጋው ላይ አለቀሰ፥ እንባውን አፈሰሰ፣ ፈጥኖም ተነስቶ የሆነወን ለመንደሩ ሰዎች ነገረ። ወደ አባ ዮሐንስ ስጋ መጥተው በታላቅ ክብር ተሸከሙት፥ ወደ መንደሩ ሲያመጡት ብዙ ድንቆች እና ተአምራት በስጋው ተፈጸመ። ጸሎቱ እና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፥ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። አሜን። @hiwotemenekosat

Open in Telegram
Views570+5%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#1841Link preview

Forwarded from ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት

​#ዝክረ_አበው_ባሕታውን #ዝክረ_አበው_መነኮሳት አባ አጋቶን ዘዓምድ ∞∞ ∞ ∞∞ በዚህች ቀን አባ አጋቶን ዘዓምድ አረፈ። ቴኒስ የምትባል ከተማ ሰው ነበር። የአባቱ ስም ማትራ፥ የእናቱ ስም ማርያም ነበር። ጻድቃን እና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ነበሩ። ለድሀ እና ችጋረኛ ምጽዋትን እና ትሩፋትን ማድረግ ይወዱ ነበር። የምንኩስና ሀሳብ ዘውትር በአዕምሮው ይመላለስ ነበር። 35 ዓመት በሆነው ጊዜ ካህን ሆኖ ተሾመ፥ ራሱን በማትጋት ዘውትር ቤተክርስቲያንን ያገለግል ነበር። ከዚህ ዓለም የሚለይበትን ምቹ ሁኔታ እና ወደ በረሃ የሚሄድበትን ጊዜ እንዲያቀርብለት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ዘውትር በቀን እና ማታ ይጠይቀው ነበር። ጌታችንም ጥያቄውን መለሰለት፥ከከተማው ወጥቶ ወደ ተርኖት(ማርዮት) ከተማ መጣ፥ ከዚያን የእግዚአብሔር መልአክ በመነኩሴ አምሳል ተገልጦለት አብሮት በአስቄጥስ ወደ አባ መቃርዮስ ገዳም ሄዱ። ወደ ብጹአን አባቶች አባ አብርሃም እና አባ ገዋርጋ መጥቶ ደቀ መዝሙራቸው ሆነ፥ ከነርሱም ጋር ለሦስት ዓመታት ኖረ። ከዚህን በኃላ ወደ መሰዊያው ወስደውት አበምኔቱ አባ ዮሐንስ ባለበት የምንኩስና ልብሱ ላይ ለሦስት ቀናት ጸለዩበት። ከዚህን በኃላ ቅዱሱን አስኬማ አለበሱት። ከዚያች ሰዓት ጀምሮ በማያቋርጥ ጾም እና ጸሎት ራሱን አስገዛ፥ ታላቅ ተጋድሎንም ተጋደለ። አጥንቱ ከስጋው እስኪጣበቅ ድረስ መሬት ላይ ይተኛ ነበር። ዘውትር የአባ ስምዖን ዘዓምድን ገድል ያነብ ነበር፥ የብሕትውና ሕይወትን መምራትን ያስብ ነበር። ስለዚህ ጉዳይ ከቅዱሳን አባቶች ጋር ተማክሮ ፈቀዱለት። ጸሎት ካደረጉለት በኃላ ሄደ፥ ሳካ ወደ ምትባል ከተማ አቅራቢያ መጥቶ በዚያ በትንሸዬ ቤተክርስቲያን ውስጥ መኖር ጀመረ።ምዕመናን ለርሱ የሚሆን ቦታ በዓምድ(ምሰሶ) ላይ ሰሩለት፥ በርሱም ላይ ወጥቶ በጽናት ለ15 ዓመታት የትሕርምት ሕይወትን መራ። በርሱ ዘመንም መንቻካ(ግትር) የሆነ አጋንንት ያለበት ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ብዙ ሰዎችን አስቶ ነበር። በቤተክርስቲያን መሃል ይቀመጥ ነበር፥ ሰዎችም ሊሰሙት በዙሪያው ይሰበሰባሉ፥ የዛፍ ቅርንጫፎችን ይይዙ ነበር። አባ አጋቶን በአጋንንት የተያዘውን ሰው አስጠርቶ በላዩ ላይ ከጸለየ በኃላ ብዙዎችን ሲያስት የነበረውን አጋንንት አስወጣው። በተመሳሳይ ቅዱስ ሚናስ አነጋገረኝ የምትል ሴት የከተማዋን ሰዎች በቅዱስ ሚናስ ስም ጉድጓድ እንዲቆፍሩ እና በዚያ ጉድጓድ ውሃ ለተጠመቀ ሁሉ ፈውስ ይሁን ብላ አዘዘቻቸው። ቅዱስ አጋቶን ርኩሱን መንፈስ ከርሷ ላይ እስኪያወጣ በሴቲቱ ላይ ጸለየ፥ የከተማውንም ሰዎች የቆፈሩትን ጉድጓድ እንዲደፍኑት አዘዘ። በዚህ ቅዱስ ሰው አባ አጋቶን እግዚአብሔር ብዙ ተአምራትን አደረገ። ብዙዎች ሕመምተኞችን ፈወሰ፥ ርኩሳን መናፍስትንም አስወጣ። አጋንንት በመላዕክት አምሳል ተገልጠውለት ጣፋጭ ዝማሬን እየዘመሩ እና እየባረኩት በማስመሰል ሊያስቱት ሞክረዋል፥ ነገር ግን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክህሎት ደባቸውን አውቆ በመስቀል ምልክት አማተበባቸው፥ ተሸንፈውም ሸሹ። እግዚአብሔር ከዚህ አለም ድካም ሊያሳርፈው በወደደ ጊዜ ለአጭር ጊዜ ከታመመ በኃላ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ አሳልፎ ሰጠ። በስብከቱ እና በትምህርቱ ሲጠቀሙ የነበሩ ሰዎች በዙሪያው ተሰብስበው አምርረው አለቀሱ። ይህ ቅዱስ አባት ለ100 ዓመታት ኖረ። 40 ዓመታትን በአለም(በክህነት)፣ 10 ዓመታት በበረሃ እና 50 ዓመታት በብሕትውና በዚያ ዓምድ ላይ ኖረ። ጸሎቱ እና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፥ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። @hiwotemenekosat .

Open in Telegram
Views1,530+181%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#1840Text

Forwarded from የተዋሕዶ ልጅ

ከአሮጌው ዘመን ጋር "አሮጌውን ሰው አስወግዱ" (ኤፌ 4፥22) ዘመን መለወጫ ብዙ ነገሮችን የምንልውጥበት ወቅት ነው። የቤታችንንም እቃዎች ፣ አልባሳትን ሌሎችም ሌሎችም እንለውጣለን። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ እውነተኛውን ቤት የእግዚአብሔርም ቤት/መቅደስ ስለሆነው ሰዉነታችን ግን ችላ እንላለን። “፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።” (1ኛቆሮ3፥17 ) "አቤቱ እኛ ስጋውያን የምንሆን የስጋን ነገር እናስባለን በስጋም መንገድ እንሔዳለን " (ኀዳፌ ነፍስ) ዘመንም ሲለወጥ የስጋን ነገር እናቅዳለን። እግዚአብሔርም ዘመንን እንደ ስጦታ ሲሰጠን ለምን እንደሆነ እንዘነጋዋለን። እርሱ " በልባችሁ መታደስ ተለወጡ '' (ሮሜ 12፥2) ብሎ ዘመንን ሲለውጥ እኛ ግን የቤቶታችንን እቃዎች ብቻ እንለውጣለን። "አዲሱን ሰዉ ልበሱ '' (ኤፌ 4፡24 ) ብሎ በአዲስ ዘመን ቅዱስ ልብስ ሲሰጠን እኛ ደግሞ እርሱን ችላ ብለን የስጋን ልብስ እንለብሳለን። እኛ ሁሌ የስጋን ነገር ስለምናስቀድም አይሞላልንም። የነፍስ ነገር ግን ብናስቀድም የስጋን ነገር ያሟላልን ዘንድ የታመነ ነው። “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።” (ማቴ 6፥33 ) እግዚአብሔር የተሻለውን የነፍስን ነገር ያስቀድማል። ለዛም ነው በወንጌል የስጋ ደዌያቸውን ብቻ አስበው ወደ እርሱ የመጡትን እርሱ ግን አስቀድሞ የነፍስን መድኃኒት ይሰጣቸዋል ። ከዛም ቀጥሎ የስጋን መድኃኒት ይሰጣቸዋል። "እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፦ አንተ ልጅ፥ አይዞህ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።እነሆም፥ ከጻፎቹ አንዳንዱ በልባቸው፦ ይህስ ይሳደባል አሉ።ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ፦ ተነሣና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል?ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፥ በዚያን ጊዜ ሽባውን፦ ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው።ተነሥቶም ወደ ቤቱ ሄደ። '' (ማቴ 9፥2-7 ) ዘመንም ሲለወጥ የስጋን ነገር እንለውጥ ዘንድ ብቻ ሳይሆን አስቀድመን የነፍስን ነገር እንለውጥ ዘንድ ነው እግዚአብሔር የንስሐ ጊዜ የሚሰጠን። "በልባችሁ መታደስ ተለወጡ " (ሮሜ 12፥2) ብሎ አሮጌውን ልባችንን አስወግደን የክርስቶስም ልብ ወደ መያዝ እናድግ ዘንድ አዲስ ዘመን ሲሰጠን እኛም እንጠቀምበት ። '' እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን '' (1ቆሮ 2፥16) ። ከአሮጌው ዘመንም ጋር ''አሮጌውንም ሰዉ አስወግዱ " ( ኤፌ4፥22) ብሎ አዲስ ዘመን ስለሰጠን እኛም '' ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥።” (ኤፌ4፥12-13) ክርስቶስን ወደ መምሰል እንደግ። እግዚአብሔርም የንስሐ ጊዜ ስለሰጠን ደስ ይበለን። “በጌታ ደስ ይበላችሁ፤።” “በጌታ ደስ ይበላችሁ።” “በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።”ፊልጵስዩስ 4፥4

Open in Telegram
Views1,680+209%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#1838Link preview

Forwarded from ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት

​#ዝክረ_አበው_መነኮሳት ቅዱስ አባ ቢሳሪዮን ታላቁ °°°°°°°°°°°°°    °°°°°°°°°°°° በዚህች ቀን ታላቁ ተሓራሚ አባት አባ ቢሳሪዮን አረፈ። የተወለደው በምስር(ግብጽ) ከሀብታም ክርስቲያን ወላጆች ነው። ባደገ ጊዜ የምንኩስናን ሕይወት ይናፍቅ ነበርና ወደ አባ እንጦንስ ሄደ፥ በርሱም ስር ለተወሰነ ጊዜ ቆየ። ከዚያን ወደ አባ መቃርዮስ ሄደ፥ በርሱም ስር ለተወሰነ ጊዜ ቆየ። ከዚህን በኃላ በበረሃ ውስጥ ዞረ፥ ጣሪያ ባለው ስፍራ አርፎ አያውቅም ነበር። ከዚህ አለም በፍጹም አንዳች ነገር አልነበረውም፥ ከአንዲት ሸካራ የቁርበት ልብሱ በቀር። ወንጌል ተሸክሞ የመነኮሳትን በዓት እያነባ የመዞር ልምድ ነበረው። የሚያለቅስበትን ምክንያት ሲጠየቁት እንዲህ ብሎ ይመልስላቸዋል፦ "ሀብቴ ሁሉ ተሰርቋል፥ ከሞትም አምልጫለሁ። ቤተሰቦቼም ከክብር ወደ ወርደት ወድቀዋል"። ቃላቱ የሚገልጹት በመጀመሪያው አባት አዳም የቀደመውን ትዕዛዝ መጣስ ምክንያት የመጣውን የሰውን ልጅ ስላገኘው ውድቀት ነበር። ምን ለማለት እንደፈለገ ያልገባቸው እንዲህ ብለው ያጽናኑት ነበር፦" እግዚአብሔር የተሰረቀብህን ነገር ይመልስልህ"። አባቶች ብዙ ተአምራቱን እና ስራዎቹን መዝግበውልናል። ከነርሱም አንዳንዶቹ፦ × በአንድ ወቅት ከሁለት ደቀመዛሙርቱ ዮሐንስና ዱላስ ጋር በቀይ ባሕር ዳር እየተጓዙ ሳለ ውሃ ተጠሙ። ቅዱስ ቢሳሪዮን ጥቂትቱን ጨዋማ ውሃ ወስዶ ሲጸለይበት ጣፋጭ ሆነ፥ ከርሱም ጠጡ። × በሌላ ጊዜ ደግሞ በእርኩስ መንፈስ ተይዞ ያበደ ሰው አረጋውያኑ ይጸልዩለት ዘንድ ወደ አስቄጥስ አመጡ። አባ ቢሳሪዮን ውዳሴ ከንቱን እንደሚጠላ አረጋውያኑ ስለሚያውቁ ለታመመው ሰው እንዲጸልይለት አልጠየቁትም፥ ነገር ግን ሰውዬውን ቤተክርስቲያን ውስጥ ቅዱስ ቢሳሪዮን ዘውትር በሚቆምባት ስፍራ አስቀመጡት። ቅዱስ ቢሳሪዎን ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ ሰውዬውን በዚያ አንቀላፍቶ አገኘው፥ ሲቀሰቅሰው ሰውዬው በሙሉ ጤንነት ተፈውሶ አዕምሮው ተመለሰለት። እግዚአብሔር በእጆቹ ብዙ ተአምራት ፈጸመ። በሰላምም አረፈ። ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን። አሜን። @hiwotemenekosat

Open in Telegram
Views1,640+202%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—
#1835Photo

¤ አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ    ፦ አባታቸው - ዲላሶር    ፦ እናታቸው - እምነጽዮን    ፦ ትውልዳቸው - ኢየሩሳሌም - ሳሬራ ሲሆን ፨ የካቲት 28 ፡ (29 ከወርኃዊ በዓላቸው ጋር) - ጽንሰታቸው፤ ፨ ኅዳር 28 ፡ (ሌሊት ለ29 አጥቢያ ልደታቸው/ የተወለዱበት) ፨ ሐምሌ 29 ፡ ከ500 ዘመን የምድር ኑሮ በኋላ ማረፋቸው (ዕረፍታቸው) ይከበራል። ፨ አባታችን በ 5 ዓመታቸው ከቤት ወጥተው በዛው በእሥራኤል " ባመዋ " በሚባል ተራራ ተለይተው በመውጣት የተባሕትዎ የብቸኝነት ሕይወታቸውን ጀምረዋል። ፨ ብጹእ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት "ልጄ ሆይ ገረምከኝ" ብለው ያደነቋቸው አባት ናቸው። ፨ ሥርዐተ ምንኩስናቸውን በደብረ ሊባኖስ ተቀብለዋል።      "ሰላም ለከ ዮሐንስ አቡነ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ እንተ ወሀበነ ለነ፤ ኪያከ አበ ወጸወነ፤ ኃይለ ጸሎትከ ከመ ያድኅነነ፤ እመሥገርቱ ለሰይጣን ፀርነ።" ⁴¹.ዮሐንስ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን። የጸሎትህ ኃይል ከጠላታችን ከሰይጣን ወጥመድ ታድነን ዘንድ አንተን አባትና መጠጊያ አድርጎ ለእኛ የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን።            (ተረፈ መልክአ ዮሐንስ) @Hiwotemenekosat

Open in Telegram
Views2,230+310%vs avg
Forwards—
Reactions20
Comments—