ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ የድል መግለጫ ሕዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም የአፋብን ቴክኖሎጅ እና ምህንድስና መምሪያ ከቴወድሮስ ዕዝ መረጃ እና ደህንነት መምሪያ እንዲሁም ከዕዙ 102ኛ ኮር 22 ኛ ክፍለ ጦር ጋር በመተባበር በአገዛዙ አየር ኃይል የባህርዳር ምድብ ላይ የተሳካ ወታደራዊ ጥቃት ፈፅሟል። ሕዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም ለህዳር 20 አጥቢያ ከሌሊቱ 9:36 ላይ በተፈፀመ ጥቃት በባሕርዳር አየር ኃይል ግቢ የነበረ:- ፩) አንድ Su-27 ተዋጊ ጀት፤ ፪) ለግዳጅ ዝግጁ የነበረች አንድ ባይራክታር አኪንቺ ድሮን፤ ፫) አንድ ተንቀሳቃሽ የድሮን መቆጣጠሪያ ( Moblile ground control system) ሙሉ በሙሉ ማውደም ተችሏል። ፬) አንድ የSu-27 ጀት ዋና ቴክኒሽያን ተገድሏል። ፭) የድሮን ቦንብ አጉራሽ የነበረ የአየር ኃይል ባልድረባ ተገድሏል፤ ፮) ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ የጠላት አየር ኃይል ባልደረቦች ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው በጥቃቱ የተደናገጡ በርካታ የአየር ኃይሉ ስታፍ አባላት የአየር ኃይል ግቢውን ለቀው ጠፍተዋል። በኦፕሬሽኑ የተደናገጠው የብልፅግና አገዛዝ በርካታ የመከላከያ ኮማንዶ፥ ፌደራል ፖሊስ፣የአየር ኃይል ስታፍ አባላትን እና አካባቢው የሚኖር ማህበረሰብ በጅምላ በማሰር ላይ ይገኛል። መቶ በመቶ በድርጅታችን ቴክኖሎጅ እና ምህንድና መምሪያ አቅም የተመረተው እና WSM የተሰኘው መሳሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሞከረበት በዚህ ኦፕሬሽን የተገኘው ወታደራዊ ድል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን ተጋድሎ አንድ ደረጃ ከፍ ያደረገ ነው። በተለይም የአረብ ኢምሬትን ጨምሮ የባዕዳን ሀገራት ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ አገልግሎት የሚሰጠው እና የአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈፀም እያገለገሉ ያሉ ዘመናዊ ድሮኖችን የሚያስተናግደው የባህርዳር አየር ምድብ ጣቢያ ላይ ኦፕሬሽኑ መከናወኑ በአገዛዙ እና በላኪወቹ አገራት አየር ኃይል አዛዦች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መሰል ወታደራዊ ዒላማወች ላይ ያተኮረ እና በቴክኖሎጅ የታገዘ ጥቃትን በመፈፀም የአገዛዙን ህዝብ እና ሀገር የማጥፋት አቅም በማሳጣት ላይ አተኩሮ የሚሰራ መሆኑን ያሳውቃል።
Open in TelegramPosts of ግዮን-ፕረስ (Gion press)
🔥ዝርዝር የዓውደ ውጊያ መረጃዎች🔥 ከትናንት ሌሊት ኅዳር 19 እስከ ዛሬ ኅዳር 20/2019 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የጥይት ድምፅ ሳይሰማ የከረመውን የጎንደር ከተማን ጉምቱ የብልጽግና ማፍያ ወንበዴ ✅ፈንጠርን ✅ስመ ክፉን ✅አንገረብን ✅ማረሚያ ቤትን ✅ደፈጫን ✅ሸዋ ዳቦን ያካለለ ቅልጥ ያለ የጨበጣ ውጊያ በክላሽ፣ በቦንብና በሳንጃ ጭምር ሲካሄድ ውሏል። በዚህ ውጊያ ✍️በርካታ የአገዛዙ ኃይል ቁስለ፣✍️ከ30 በላይ እስከ ወዲያኛው የተሸኘ፣ ✍️30 ጥቁር ክላሽ ከነካዝናው የተማረከ፣ ✍️31 የወገብ ትጥቅ የተማረከ፣ ✍️10 የእጅ ቦንብ የተማረከ ሲሆን ✍️የፈንጠሩ ምሽግ ✍️የደፈጫ ኪዳነ ምህረቱ ምሽግ ሙሉ በሙሉ ተሰብሮ የጠላት ኃይል ብትንትኑ ወጥቷል። ይህ አስደናቂ ውጊያ በአፋብን:- በላይ ዘለቀ ፫ኛ እዝ፣ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር፣ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አማካይነት የተፈጸመ ሲሆን:- 💯የፈንጠሩ ግንባር በአርበኛ ሞላ ከፌ ተመርቶ ሙሉ ምሽጎች ተሰብረው ከሙትና ቁስለኛ የተረፈው ኃይል ብትንትኑ ወጥቷል፤ 💯የደፈጫውና ስመ ክፉ ግንባር በአርበኛ ጋሻው ስመኝ የተመራ ሲሆን የደፈጫ ኪዳነምህረቱን የጣሊያን ኮንክሪት ምሽግ ድርምስምሱን አውጥተው የጠላትን ኃይል ፋታ ነስቶ እንዲበተን ተደርጓል፤ 💯የአንገረቡ ግንባር በአርበኛ ኃይሌ አየልኝ ተመርቶ አስደናቂ ጀብዱ ተፈጽሞ የጠላትን አከርካሪ መስበር ተችሏል፤ 💯የመጨረሻው ግንባር በአርበኛ የሻምበል ሙሉሰው እና በአርበኛ ወልዴ የተመራው የማረሚያ ቤትና ሸዋ ዳቦ ውስጠኛው ግንባር አኩሪ ጀብዱ ተፈጽሞበታል። በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ውስጥ እና ዙሪያዋ በተደረገው በዚህ ታሪካዊ ተጋድሎ ሕዝባችንንና ሠራዊታችንን የሚያኮራ ድል መቀዳጀት ተችሏል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! ትብብር ለኅልውና:- አፋብን፣ በላይ ዘለቀ ፫ኛ እዝ፣ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ሰሎሞን ደሴ
Open in Telegramህዝባዊነት፣ ሰብዓዊነት እና ዲፕሎማሲያዊ ኃላፊነት በአንድ ላይ! 🤝🌍 የፋኖ ህዝባዊነት ዋና መሠረቱ ከህዝብ መወለድ፣ ለህዝብ መቆም እና የህዝብን ሰብዓዊ ክብርና ደህንነት ማስቀደም ነው። እውነተኛ ህዝባዊነት የሚለካው የዜጎችን ሕይወት በመታደግና መሠረታዊ ፍላጎታቸውን በማሟላት ነው። በዚህ ረገድ፣ እንደ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ያሉ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ተቋማትን መንከባከብና ልዩ ጥበቃ ማድረግ የህዝባዊ ዓላማችን አንዱ አካል ነው። የእነዚህን ተቋማት ሰብዓዊ ሥራ ከህዝባችን እውነተኛ ፍላጎትና ከተቋማዊ ህጋዊነት ጋር ስናስተሳስረው፣ በአንድ በኩል የወገናችንን ችግር እንፈታለን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ህዝባዊ ትግሉ ለዓለም አቀፍ ህግጋትና ስምምነቶች ተገዢ መሆኑን በተግባር በማሳየት ዲፕሎማሲያዊ ተአማኒነትን እንገነባለን። ለህዝብ ማሰብ፣ ዓለም አቀፍ አጋሮችን መጠበቅና ተቋማዊ ህጋዊነትን ማስከበር የህዝባዊነት መገለጫና የሁላችንም ማህበረሰባዊ ግዴታ ነው! አፋብንጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ 204ኛ ወንዱ አስቻለው ደሴ ኮር!
Open in Telegramበምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ግራር ውሃ ቀበሌ በተካሄደ የተቀናጀ ኦፕሬሽን በጠላት ኃይል ላይ ከባድ ኪሳራ ደረሰ! ሕዳር 19/2019 ዓ.ም አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ፣ በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ግራር ውሃ ቀበሌ ሰፍሮ በነበረው ፀረ-አማራው የጠላት ኃይል ላይ የተሳካ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ተፈጽሟል ። ሕዳር 19/2019 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ለአንድ ሰዓት ያህል በቆየ በዚህ ድንቅ ኦፕሬሽን 305ኛ ጎቤ መልኬ ኮር 76ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ሬጅመንት እና 52ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ሬጅመንት በጋራና በተቀናጀ መልኩ ባደረሱት መብረቃዊ ጥቃት የአገዛዙ ኃይል ከንፖቹ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ወጭ የሆኑ ሲሆን፣ በጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ቁሳዊ ፣ሞራላዊና ሰባዊ ኪሳራ ደርሶበታል። በተናበበው በዚህ ወታደራዊ እርምጃ በርካታ የጠላት አባላት ሲደመሰሱ፣ የተለያዩ ወታደራዊ ትጥቆች፣ ተተኳሾችና ስንቆችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ፨በኦፕሬሽኑ የተገኙ ትጥቆችና ውጤቶች፦ ➛5 ብሬን (መትረየሶች)፤ ➛55 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፤ ➛7,450 የብሬን ጥይቶች፤ ➛6,035 የክላሽንኮቭ ጥይቶች፤ ➛80 የክላሽንኮቭ ካዝናዎች፤ ➛42 የወገብ ትጥቆች፤ ➛57 የእጅ ስልኮች፤ ➛10 የተማረኩ የሰላም አስከባሪ አባላት ጨምሮ በርካታ ባለማዕረግ የአገዛዙ ቅጥረኞች ተደምስሰዋል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
Open in Telegramአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ የጭና ቁጥር ፩ (5ኛ ሬጅመንት) ወደ ሬጅመንት አመራርነት ባደጉና በተጓደሉ አመራሮች የመተካካት ስራ ሰርቷል ! ሕዳር 17/2019 ዓ.ም አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ተኛ ዕዝ የ208ኛ ኮር ጭና ቁጥር ፩ የዕዝ፣ የኮሩ እና የክፍለ ጦሩ አመራሮች እንዲሁም አባላቱ በተገኙበት ግምገማና ውይይት በማድረግ ሕዳር 17/03/2019 ዓ.ም የአደረጃጀት መተካካት ስራ ተሰርቷል። ሻንበል አንድ 1. ዋና አዛዥ ----------አርበኛ አስናቀው ጥጋቡ 2. ምክትል አዛዥ ------አርበኛ አስናቀው እዘዘው 3.የሰው ሀይል አስተዳደር ------------አርበኛ አስተውል ተቀባ 4.ዘመቻ ----------------አርበኛ ባበይ ለምለሙ 5.ሎጀስቲክ ------------አርበኛ ሰሎሞን ገበየሁ ሻንበል ሁለት 1. ዋና አዛዥ ----------አርበኛ ጎሸ ታየ 2. ምክትል አዛዥ --------አርበኛ ወንድምሹ ፍቃዴ 3.የሰው ሀይል አስተዳደር -----------------አርበኛ እንዳልክ ጌትነት 4.ዘመቻ ------------------አርበኛ አክሊሉ ተፈሪ 5.ሎጀስቲክ ------------አርበኛ አበራ ደሴ ሻንበል ሶስት 1. ዋና አዛዥ ----------አርበኛ እርስቱ ቻሌ 2. ምክትል አዛዥ --------አርበኛ በሬ ጥጋቡ 3.የሰው ሀይል አስተዳደር -----------------አርበኛ ክብረት ተስፋ 4.ዘመቻ ------------------አርበኛ አለነ በሬ 5.ሎጀስቲክ ------------አርበኛ አወቀ አስመቼ ሁነው የተመደቡ ሲሆን ለተሰጣቸው ኃላፊነት ከአደራ ጋር ለመወጣት ታጋዩን እና ማህበረሰባቸውን በቅንነት ለማገልገል ቃል መሀላ ፈጽመዋል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ይረጋገጣል! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ የ208ኛ ኮር ወታደራዊ ቃል አቀባይ
Open in Telegramፋሲል የኔዓለም 🗣️ “በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው “ የአብይ አህመድ ንግግር፣ ፍሬ ፈርስኪ ሆኖ በመገኘቱ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበናል። ካድሬው ሁሉ ሠራዊቱ አስመራ ስለሚገባበት ቀን ለመስማማት ጏጉቶ ሲጠብቅ፣ አጅሬው እጥፍ ብሎ ወደ ልመናና ልምምጥ በመግባቱ፣ ብዙዎቹ በሀዘን እንደሚዋጡ ግን ሳንናገር አናልፍም።
Open in Telegramየአገዛዙን ተልዕኮ በመቀበል ለአማራ ህዝብ ከፍተኛ ጥላቻ ያለው ሚኒሻ፣ አድማ ብተና፣ ፖሊስ እና ዘር ፈጁ የብልፅግና አገዛዝ በዲማ ከተማ እያደረገ ያለው አድራጎት ሰይጣናዊነቱ ተግባር እየፈፀመ ይገኛል። በዲማ ከተማ ሰፍሮ የሚገኘው የጠላት ሀይል በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ማዳበሪያ፣ ግብርና፣ የከተማ ሊዝና መሰል የፋይናንስ ክፍያ ትፈፅማላቹህ በማለት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ዝርፊያ እየፈፀመበት ይገኛል። በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየሰራ የሚገኘው የጠላት ኃይል ከዲማ ከተማ ከፍተኛ ዝርፊያ ማግስት ጀምሮ ከሌሎች አጎራባች የጠላት ኃይል ጋር ጥምረት በመፍጠር በግብር፣ በማዳበሪያና መሰል ስበባ ስበብ ከፍተኛ የሆነ ዝርፊያና ውድመት በህዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ መጠነ ሰፊ ችግር እያደረሰ መሆኑን እና ሀገር አፍራሹ የብልፅግና አገዛዝ ዝርፊያን ህጋዊ ካርድ በማድረግ የሀገርን ጥፋት እንደ መልካም አጋጣሚ በመቆጠር ለብልፅግና አገዛዝ ሽፋን በመስጠት የሚያገለግሉ በኮሪደር ልማት፣ በግብር፣ በገጠሩ ማህበረሰብ፣ በቢቸና፣ የትመን፣ የዕድውሃ፣ መርገጭ ከተማ ኗሪዎችን፣ በባለሀብቶችን፣ ነጋዴዎች በአሽከርካሪዎችና በነጋዴዎች እንዲሁም ኗሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ዝርፊያ እየፈፀመ ይገኛል። በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ የሚገኘው ሀገር በማፍረስ፣ የሀገርን ሰላም በመንሳት፣ የሀይማኖት ተቋማትን በማውደም፣ ንፁሃንን በጅምላ በመግ*ደል የተጠናወተው ዘር ፈጁ የብልፅግና አገዛዝ በገና ፆም በእለተ እሮቡ ይባስ ብሎ በታሪካዊ ታላቁ ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰንበት ትምህርት ቤት በማርገጃው ላይ ከብት በማረድ በታሪካዊነቱ ቀደምትና ድንቅ ተብሎ የሚታወቀውን የቅዱሳን ምድር ታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ ቦታ እያረከሰ ይገኛል። መረጃው የአፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ነው!! ህዳር 17/2019 ዓ.ም
Open in Telegramሦስት ሀገራትን ወደ አንድ ሰፊ አውደ-ውጊያ የሚቀይር ጦርነት እየመጣ ነው። (በአፋን ኦሮሞ ከለጠፍኩት በ Nur T Abdo የተተረጎመ ) 1.ተሳታፊ ሀገራት እና ከጀርባ ያለው ድጋፍ... ሦስቱ ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ኤርትራ ናቸው። ግብፅ ከሱዳንና ከኤርትራ ጀርባ ስትሰለፍ፣ ኤምሬትስ እና እስራኤል ደግሞ ከኢትዮጵያ ጎን በመሆን በግራና ቀኝ ተሰልፈዋል። ቱርክ እና ሳዑዲ በሀሳብ ወደ ሱዳንና ኤርትራ ቢያዘነብሉም፣ ለግዜው ከቀጥተኛ ተሳትፎ ራሳቸውን እየቆጠቡ ይገኛሉ። ሦስቱ ሀገራት፣ በውስጣቸው የሚንቀሳቀሱ አማፂያን እና እነሱን ለመደገፍ ከጀርባ የተሰለፉ ኃይሎች ለዚህ ወሳኝ ጦርነት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል። 2. የጦር ግንባሮች እና የኃይሎች እንቅስቃሴ... • አራት የጦር ግንባሮች፦ በሦስቱ ሀገራት ድንበሮች መካከል በአራት ዋና ዋና የጦር ግንባሮች ላይ ዝግጅት እየተደረገ ነው። አራቱ ግንባሮችም፦ 1) ቡሬ-አሰብ፣ 2) ባድመ-ጾሮና፣ 3) መተማ-ፋሻጋ-ሁመራ እና 4) ኩምሩክ-አሶሳ ናቸው። • የአማጺ ኃይሎች... ሱዳን የሕወሓት ኃይሎችን በመጠቀም በምዕራብ በኩል ኢትዮጵያን ለመምታት ስትዘጋጅ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን (RSF) በመጠቀም በመተማ-ፋሻጋ ድንበር በኩል የሱዳንን ጦር ለመክበብ ባለፉት ሳምንታት በጎንደር በኩል ዝግጅት ስታደርግ ቆይታለች። ሁኔታዎችን የማመቻቸት ጥቃቶች...ባለፉት ሳምንታት ለትልቁ ጦርነት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የታቀዱ ወሳኝ የአየር ጥቃቶችና እና የምድር ውግያዎች በሁሉም አቅጣጫ ተፈፅሟል። የአየር ጥቃቶቹ እና ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን የማስለቀቅና የመያዝ እርምጃዎች የዝግጅቱ አካል ናቸው። የኤርትራ የሥልጣን ዕቅድ...ኢትዮጵያ እና አጋሮቿ ከኢሳይያስ ውድቀት በኋላ ኤርትራ እንዴት ትረጋጋለች በሚለው ጉዳይ ላይ ውይይትና ዝግጅት ከጀመሩ ቆይተዋል። ሻዕቢያም ምናልባት ኢሳይያስ ቢገደል ወይም አስመራ ብትያዝ ሥርዓቱን ሳይፈርስ እንዲቀጥል የሚያስችል ዕቅድ ማውጣቷ ይነገራል። በተለይም የሥልጣን ክፍተት (power vacuum) ወይም ለሥልጣን በሚደረግ ሽኩቻ (power struggle) ተፈጥሮ ሥርዓቱ እንዳይፈርስ መደረግ ስላለበት ጉዳይ (succession plan) ላይ ከቅርብ ሰዎቻቸው ጋር ተወያይተው አቅጣጫ አስቀምጠዋል ይባላል። የቀድሞው የኢራን መሪ አያቶላህ ኾሜኒ እሳቸውና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ሊገደሉ እንደሚችሉ በመገመት አስቀድመው የተተኪ አመራር ዕቅድ ማስቀመጣቸው ለኢሳይያስና ለቡድናቸው ትምህርት የወሰደች ይመስላል። የቀጥታ ጦርነት ዕድል እና የግብፅ ሚና... በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል በቀጥታ መደበኛ ጦርነት የመካሄድ ዕድሉ ጠባብ ነው። ሁለቱም ወገኖች የሌላውን አማጺ ከመጠቀም እና ከድሮን ጥቃት ባለፈ የምድር ጦራቸውን በቀጥታ ማጋጨት አይፈልጉም። ግብፅ የሱዳንን የአየር ክልል ለመከላከል በአውሮፕላኖች እና በፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤሎች ድጋፍ ታደርጋለች፤ ነገር ግን እግረኛ ጦር የማስገባት ዕድሏ ጠባብ ነው። ኤርትራ የኢትዮጵያን የአየር ኃይል የበላይነት እንድትቋቋም ግብፅ ቀጥተኛ ያልሆነ ድጋፍ ታደርጋለች። አብራሪዎቿ የራሳቸውን አውሮፕላኖች ሳይሆን የሱዳንን እንዲጠቀሙ በማድረግ፣ እንዲሁም ዜጎቿን እና ቅጥረኛ ባለሙያዎችን (mercenaries) ድሮን እንዲያበሩ ለኢሳይያስ በማቅረብ ድጋፍ እንዲያደርጉ አዘጋጅታለች። 3. የዲፕሎማሲ ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ • ሦስቱ ሀገራት ጦርነቱ ሲጀመር የዲፕሎማሲ ድጋፍ ለማግኘት እርስ በርስ መወነጃጀሉን አጠናክረው ቀጥለዋል። ሱዳን በበኩሏ ከኢትዮጵያ የሚነሳ ድሮን ለስድስት ወራት እያጠቃኝ ነው በማለት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ክስ አስገብታለች። ኢትዮጵያ ደግሞ ሱዳን የሕወሓትን እና ሌሎች አማጺያንን በመሬቷ ላይ በማስፈር ታስጠቃኛለች ስትል ትወነጅላለች። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የሱዳን ኃይሎች እንዲታረቁ ትናንት ያወጡት መግለጫ፣ የሰላም ጥሪ ሳይሆን ለጄኔራል ቡርሃን የተሰጠ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው። ኢትዮጵያ የኤርትራ መንግሥት አማጺያንን ከሀገሯ እንድታስወጣና በባሕር በር ጉዳይ ላይ ውይይት እንድትጀምር ጠይቃለች። የትኛውም ወገን ለቀረበበት ቅሬታ የእርቅና የሰላም በር የሚከፍት ምላሽ አልሰጠም፤ እንደውም በተቃራኒው ውጥረቱን አጠናክረው ቀጥለዋል። የሶማሊያ እና የኳርቴት (Quartet) ሁኔታ... በሌላ በኩል ደግሞ ኳርቴት የሚባለው የአራት ሀገራት ጥምረት ከጥቂት ቀናት በፊት ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። የዚህ ጥምረት አባል የነበረችው ሶማሊያ በሰሞኑ ስብሰባ ላይ አልተሳተፈችም። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በውስጥ ቀውስ እና በኤምሬትስ ጫና ምክንያት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ስለገባ፣ በዚህ ስብሰባ በመሳተፍ ኢትዮጵያን ይበልጥ ማስቆጣት የፈለጉ አይመስልም። ይህ ደግሞ የጥምረቱን ሞራል ሰብሮታል። 4. ስትራቴጂ እና የኃይል ሚዛን • የኢትዮጵያ እና የአጋሮቿ ስትራቴጂ የተቀናጀ፣ ፈጣን እና ከፍተኛ ኃይል(overwhelming force) በመጠቀም ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ነው። የሱዳን፣ የኤርትራ እና ከእነሱ ጎን የተሰለፉት ኃይሎች እቅድ ደግሞ ኢትዮጵያን በሁሉም ድንበሮች እና በውስጥ በማዋጋት ጦርነቱን ማራዘምና ኢትዮጵያን ማዳከም ነው። • የስነ-ልቦና ጦርነት እና የውስጥ ሁከት... በግንባር ከሚካሄደው መደበኛ ጦርነት በተጨማሪ የተለያዩ ጥቃቶች እና ሁከቶች እንደሚኖሩ ይገመታል። በትግራይ ጦርነት መጀመሪያ ሰሞን እንዳየነው አይነት በኢትዮጵያ ከተሞች ላይ ያነጣጠሩ የድሮን ጥቃቶች ሊኖሩ ይችላሉ። የእነዚህ ጥቃቶች ዓላማ ከወታደራዊ ግብ ይልቅ ሕዝቡን በማስደንገጥ የስነ-ልቦና ቀውስ መፍጠር ነው። ይህንኑ ዓላማ ከግብ ለማድረስ የተለያዩ መልክ ያላቸው የሽብር ጥቃቶችም ሊፈጸሙ እንደሚችሉ ይጠበቃል። በተጨማሪም በብሔር፣ በሃይማኖት እና በጎሳዎች መካከል ግጭት በመቀስቀስ የኢትዮጵያን መንግሥት በውስጥ በማመስ የጦርነቱን ጊዜ ለማራዘም ሥራ ላይ ሊውል የሚችሉ ተጠባቂ ስልቶች ናቸው። • በአሁኑ ወቅት በኃይል ሚዛን (በዘመናዊ መሣሪያ፣ በወታደር ብዛት፣ በመረጃ/ደህንነት፣ በሞራል እና በዲፕሎማሲ) ኢትዮጵያ እና አጋሮቿ የበላይነት አላቸው። ይህንን የኃይል ሚዛን በተቀናጀ እና ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ ከተጠቀሙበት ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ የማጠናቀቅ ዓላማቸውን ማሳካት ይችላል። ነገር ግን መጓተት፣ መወላወል እና ሰሞኑን በትግራይ ጦርነት የታየውን ዓይነት ቅንጅት ይዘው ካልተጓዙ፣ ሌላኛው ወገን ጦርነቱን ለማራዘም ያለው ተስፋ ዕድል ያገኛል። 5. መጨረሻውና ቀጣይ ዕጣ ፈንታ -ዝግጅት እየተደረገበት ያለው ይህ ጦርነት እንደታቀደው ከተካሄደ፤ በአጭሩ የሚቋጭም ሆነ የተራዘመ ጦርነት፣ የአፍሪካ ቀንድ ታላቅ ለውጥ ለማስተናገድ ትገደዳለች። - በዚህ ጦርነት ውስጥ ከሚሳተፉ የመንግሥት እና የአማጺ መሪዎች መካከል፣ በጦርነቱ ማግስት በሕይወትም ሆነ በሥልጣን ቆይተው የማይሻገሩ ሊኖሩ ይችላሉ። -የቀጣናው ሀገራት ድንበሮች አሁን ባሉበት ሁኔታ ላይቀጥሉ ይችላሉ። - የምናውቃቸው ነባር ሀገራት ሲፈርሱ፣ አዳዲስ ሀገራት ደግሞ ሲወለዱ ልናይ እንችላለን። - የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት በቀጣናችን እያደረጉት ያለው ፉክክርም በአንዱ ወገን የበላይነት ሊቋጭ ይችላል።
Open in Telegramበአማራ ክልል ወረታ ከተማ በተፈጸመ የወጣቶች አፈሳ፣ ልጆቻቸው በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተጭነው ሲወሰዱ ለማስጣል ከተሽከርካሪው ጋር እየተሯሯጡ ያለቀሱት አባትና እናቶች ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የብዙዎችን ልብ ሰብሯል። ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም. በወረታ ከተማ መፈጸሙ የተገለጸውን ይህንን አፈሳ የሚያሳየውና በቲክቶክ መድረክ ላይ በስፋት እየተዘዋወረ የሚገኘው ተንቀሳቃሽ ምስል፣ በርካታ ወጣቶች በአንደኛ ደረጃ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተጭነው በመስኮት እጃቸውን እያውለበለቡ ሲወሰዱ ያሳያል። #አውቶቡሱ መንቀሳቀስ ሲጀምርም ጋቢ የለበሱና በትር የያዙ አንድ አባት ልጃቸውን ለማስጣል ከመኪናው ጋር በኃይል ሲሮጡ፣ እንዲሁም ሕፃን ልጅ በጀርባቸው ያዘሉ እናትን ጨምሮ ሌሎች እናቶች ራሳቸውን ይዘው በምሬት እያለቀሱ አውቶቡሱን ተከትለው ሲሯሯጡ በምስሉ ላይ ይታያል። ምስሉ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መሰራጨቱን ተከትሎ በርካታ ዜጎች የወላጆቹን ዕምባና መከራ በመመልከት ጥልቅ ሐዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ ከተሞች የሚፈጸመው የወጣቶች አፈሳ ዳግም መበራከቱን ወጣቶችና ነዋሪዎች በስፋት እየተናገሩ ሲሆን፣ ድርጊቱ በወጣቶች ሕይወትና በወላጆች ሥነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫናና ስጋት እየፈጠረ መሆኑ ተመልክቷል።
Open in Telegramሰበር ዜና የትብብር ለህልውና ፕሬዘደንት አርበኛ ዘመነ ካሴ ከሱዳን ፕሬዘዳንት አልቡርሃን ጋር በመገናኘት የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮችን በማንሳት ተወያይተዋል ።
Open in Telegram*በዳጋምቤላ ተወላጁ ጋቶች በባሕር ዳር ከተነዛው የሀሰት ፀረ አምሓራ ክስ በኋላ በጋምቤላ እየደረሰ ያለው የአምሓሮች እልቂት‼️* በባሕር ዳር "የዘረኝነት ስድብ ደረሰብኝ" ብሎ የሀሰት ክስ ያቀረበው ጋቶች ጉዳይ ብዙዎችን ሲያናድድ፣ በሌላ በኩል በጋምቤላና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አዋሳኝ አካባቢ የአማራ ተወላጆች እየተፈጁ ነው። ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም. በኮይ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ስፍራ በአማራ ተወላጆች ላይ በተፈጸመ ማንነት ተኮር ጥቃት ከ25 እስከ 30 የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች እና የዓይን እማኞች ገልጸዋል። ምንጮቹ እንደሚሉት፦ - ጥቃቱን የፈጸሙት በአካባቢው የተደራጁ ታጣቂዎች ናቸው - ጥቃቱ በሚፈጸምበት ወቅት በአካባቢው የነበሩ የክልል እና የፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች ጣልቃ ገብተው ለማስቆም ፈቃደኛ አልነበሩም፣ "አልታዘዝንም" ብለዋል - በኮይ ቀበሌ የሚገኘው የአማራ ማህበረሰብ ራሱን ለመከላከል ተዋግቶ ታጣቂዎቹን ከአካባቢው አስወጥቷል - ነገር ግን በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሁንም አስተማማኝ አይደለም ጋቶች በተባለ ቀሳጢ በባሕር ዳር የሀሰት የዘረኝነት ክስ ስም ማጥፋት በአምሓራ ህዝብ ላይ ከተሰራ በኋላ በጋምቤላ ንጹሃን አምሓሮች መግደል አገርሽቷል። _ይህ መረጃ ከአካባቢው ምንጮች እና የዓይን እማኞች የተገኘ ነው። ሕዳር 15/2019 ዓ.ም
Open in Telegramየአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ፫ኛ ዕዝ እና የ208ኛ ራስ አሞራው ውብነህ ኮር አመራሮች ከጭና ክፍለጦርና አመራሮችና ሰራዊት ጋር ውይይት አደረጉ። በዛሬው እለት ማለትም ቀን 15/3/2019 ✔️ጎ/ ጠ/ግ/በ/ዘ ፫ኛ ዕዝ አርበኛ አስምሮ ፍቃዴ ✔️ጎ/ጠ/ግ/በ/ዘ ፫ኛ ዕዝ መ/ር ንጉስ አዱኛ ✔️ጎ/ጠ/ግ/በ/ዘ ፫ኛ ዕዝ አርበኛ ዳንኤል አስረስ ✔️የ208ኛ ኮር ዋና አዛዥ አርበኛ ወርቁ ሙሉ ✔️የ208ኛ ኮር ሃ/አ/መ/ሃላፊ አርበኛ በውቀት አላቸው ✔️የ208ኛ ኮር መረጃና ደህንነት መምሪያ ሀላፊ ------- ✔️የ208ኛ ኮር ህዝብ አስተዳደር አርበኛ ፍቅሩ የማታው ✔️የ208ኛ ኮር ሎጀስቲክ መምሪያ ሀላፊ አርበኛ በሬ አወቀ ✔️የ208ኛ ኮር ልዩ ኦፕሬሽን መምሪያ ሀላፊ መቶ አለቃ ባምላኩ ጌታቸው ✔️የ208ኛ ኮር ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሳሙኤል አበራ ✔️የጭና ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ተራለው ተቀባ እንዲሁም የጭና ቁጥር ፩ ክፍለጦር አመራሮችና ሁሉም የጭና ክፍለጦር ሰራዊት በተገኙበት አንድነትን የማፅናት እና አደረጃጀት በተመለከተ እና የክፍለጦሮችን ወቅታዊ አቋም በመገምገምና የውስጥ ታሀድሶ በማፅናት እንዲሁም የቀጣይ የስራን መመሪያ በመስጠት ለቀጣይ ግዳጅ ዝግጁ መሆኑን ከፍ ባለ ሞራል አፅድቁ ተነስቷል ። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!! አርበኛ ሳሙኤል አበራ የ208ኛ ራስ አሞራው ውብነህ ኮር ወታደራዊ ቃል አቀባይ ህዳር 15/03/2019 ዓ.ም
Open in Telegramመዘዞን ከተማን ለማስለቀቅ የሞከረው የጠላት ሠራዊት፡ በ501ኛ ኮር 72ኛ ክፍለ ጦር ተገርፎ መመለሱ ተገለፀ!! ኅዳር፡ 15/2019 ዓ.ም መነሻውን ከጣርማበር፣ ከደብረሲና እና ከሰላድንጋይ አድርጎ ወደ መዘዞ የተንቀሳቀሰው የፀረ-ሕዝቡ አገዛዝ ሠራዊት፡ በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ 501ኛ ኮር 72ኛ ክ/ጦር ተመትቶ ወደ መጣበት መመለሱን የኮሩ ቃል አቀባይ አስታወቀ። በርካታ የመካናይዝድ ኃይል አሰልፎ በሁለት አቅጣጫ ማለትም፡ በጣርማበርና በሰላድንጋይ በኩል ወደ መዘዞ ከተማ ለዘረፋና ጭፍጨፋ በቀን 14/03/2019 ዓ.ም ጥዋቱ 1:00 ሰአት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ሲጋጋጥ የዋለው የጠላት ኃይል በአይበገሬዋ 72ኛ ክፍለ ጦር በመልሶ ማጥቃት ሲገረፍ መዋሉ ታውቋል። የፀረ-ሕዝቡ ስርዓት አገልጋይ የሆነው ሠራዊት በተደጋጋሚ የመካናይዝድ ኃይል በመጠቀም መንዝና ግሼ አውራጃን ለመቆጣጠር ሲጋጋጥ የከረመው ጠላት፡ ዛሬም በከፍተኛ ወኔ ከሦስት ከተማዎች በመካናይዝድ የታገዘ በርካታ እግረኛ ኃይልን ይዞ መዘዞን ለመቆጣጠር የሞከረው ከታላቅ ሽንፈት ጋር ከሽፎበታል። ዛሬም ከትላቱ ያልተማረው ይሕ አረመኔ አገዛዝ ዛሬም እደትላቱ ከባድ ኪሳራ ያስተናገደው ጠላት፡ በርካታ የሠራዊት አባላት ማስጨረሱ ተረጋግጧል። በዚሕ አውደ ውጊያ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ እግረኛ የሠራዊት አባላት መሞታቸውና መቁሰላቸው ሲታወቅ፡ ሙትና ቁስለኞችን በኦራል መኪና ማመላለሱ ሲገለፅ ያቀደውን ሳያሳካ ወደ መጣበት መመለሱ ተሠምቷል። " ክብር ለትግሉ ሠማዕታት! " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
Open in Telegramየሬማ ከተማ የዘመናት የመጠጥ ውሃ አንገብጋቢ ጥያቄ በጀግናው የአማራ ፋኖ አስተባባሪነት ዕልባት ማግኘቱ ተገለፀ!! ኅዳር 14/2019 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ ሚዳ ሬማ ወረዳ የሬማ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች የዘመናት አንገብጋቢ ጥያቄ የነበረው ከፍተኛ የመጠጥ ውሀ ችግር በቀጠናው በሚገኙ የህዝብ ልጅ በሆነው በአማራ ፋኖ አስተባባሪነት መፈታቱን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ 505ኛ ኮር ቃል አቀባይ አሳወቀ። በመርሀቤቴ አውራጃ ውስጥ የምትገኘው ሬማ ከተማ በውሀ የተከበበች ደሴት ሆና ሳለ ለዘመናት ያክል ከፍተኛ የመጠጥ ውሀ ችግር ገጥሟት የነበረ ቢሆንም ጀግናው የህዝብ ልጅ ፋኖ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ወረዳውን ከተቆጣጠረ በኃላ በከተማዋ ለዘመናት ተከስቶ የነበረውን አንገብጋቢ የመጠጥ ውሀ ችግር የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር በከፍተኛ መጠኑ ዓመታዊ ፍሰት የሚታወቀውን የጃራን ወንዝ ወደ ከተማዋ በማስገባት ያለምንም መቆራረጥ ከኅዳር 12/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ህዳር 24/2019 ዓ.ም ለተከታታይ 48 ሰዓታት ስኬታማ የሙከራ ስርጭት በማድረግ ለሬማ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ የውሀ መጠጥ አገልግሎት መስጠቱን በታላቅ ኩራት አብስሯል። በዚሕ ልዩ እና ታሪካዊ የሬማ ከተማ የመጠጥ ውሀ ምርቃት ላይ ከሁለቱ የአፋብን ዕዞች ማለትም የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ እና የወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በአካል ተገኝተው ምርቃቱን አብስረዋል። የዘመናት ጥያቄ የሆነው የሬማ ከተማ የመጠጥ ውሀ ምርቃት ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ እና የወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች፣የሬማ ከተማ የሃይማኖት አባቶች፣ የከተማዋ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ፕሮጀክቱ ተመርቋል። በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት በየደረጃው የተገኙት አካላት፡ ለሬማ ከተማና አካባቢው ማህበረሰብ "የእንኳን ደስ አላችሁ!" መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ የአማራ ፋኖ እያደረገ ካለው የትጥቅ ትግል ጎን ለጎን የሬማ ከተማ የዘመናት የመጠጥ ውሀ ጥያቄን ለመፍታት ደጉ የሬማ እና አካባቢው ማህበረሰብና ባለሙያዎችን በማስተባበር "ከህዝባችን፣ለህዝባችን" በሚል መሪ ቃል በከፍተኛ መጠኑ ዓመታዊ ፍሰት የሚታወቀውን የጃራን ውሀ ወደ ከተማዋ በማስገባት ያለምንም መቆራረጥ የተሟላ አገልግሎት ለነዋሪዎቿ እየሰጠ መደረጉን አመስግነዋል። " ክብር ለትግሉ ሠማዕታት! " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
Open in Telegramከአፋብን አባት አርበኞች ም/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ ሕዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም ውድ የአማራ ህዝብና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!!! የአማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ከመጀመሩ በፊት የጠላትን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አሰላለፍ በልኩ ቀድሞ ከተረዱ አንጋፋ ታጋዮች መካከል አርበኛው መሳፍንት ተስፉ አንዱና ግንባር ቀደም ተጠቃሽ እንደነበር ድርጅታችን አፋብን ያምናል። በመሆኑም ከብዙ ድርጅቶች ምሥረታ እስከ አፋብን ድረስ ባለው ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ትግል የአባትነት ሚናውን በማክበር በመሸማገልና በማሸማገል ሂደት ውስጥ ከፊት በማስቀደም አክብሮት ስንሰጠው ቆይተናል። የድርጅታችን አፋብን ምሥረታንም አስመልክቶ አርበኛ መሳፍንት ተስፉን የአባት አርበኞች ምክር ቤት ሰብሳቢ በማድረግ ትልቅ ክብርና ኃላፊነት የሰጠነው ላበረከተው አስተዋጽኦና ለወደፊትም የአባትነት ፍቅር እንዳይለየን ካለን ተስፋ የተነሳ መሆኑ አጠያያቂ ባይሆንም ካለፉት ጥቂት ወራት በፊት ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ከአፋብን እውቅና ውጪ በሆነ መልኩ መግለጫዎች ማውጣቱን ተከትሎ በድርጅታችን መመሪያና መርህ መሠረት ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው መቆየቱና የአባት አርበኞች ም/ቤት ሰብሳቢ ሆኖ በሚሰራበት ጊዜያትም አንድም ቀን የምክር ቤቱን አመራርና አባላት ለስብሰባ ጠርቶ ሳያወያይና ተገቢውን የስራ ሀላፊነት ሳይፈፅም ቀርቶ በድርጅታችን አፋብን እና በም/ቤቱ መመሪያ መሠረት በተወሰደው አፋጣኝ እርምጃ ኮማንደር አረጋ አለባቸውን በጊዜያዊ ሰብሳቢነት በመሾም የም/ቤቱን ስራ ማስቀጠል መቻሉ የሚታወቅ ነው። እስካሁን ከተፈፀሙትና በመፈፀም ላይ ካሉት የብልፅግናው ሰውበላ ስርዓት ስፍር ቁጥር የሌለው ወንጀሎች መካከል ከ180 በላይ ቤተ ክርስቲያናት፣ ከ15 በላይ ገዳማት፣ መስጊዶችና ልዩልዩ የሀይማኖት ስፍራዎች፣ ት/ቤቶችና የተለያዩ ተቋማትን ማቃጠልና ማውደም እንዲሁም በየዕለቱ በማንነታቸውና በሃይማኖታቸው ምክንያት መንግሥታዊ በሆነ የጅምላ ግድያና ጭፍጨፋ እየተፈጸመባቸው የሚገኙ አባቶች፣ እናቶችና ሕፃናት ባሉበት ወቅት በማናቸውም ምክንያት ቢሆን እንኳን ከአፋብን ተቃራኒ ሆኖ መቆም አጥፊዎችን እንደመደገፍና የአማራና መላው የኢትዮጵያ ህዝብን እንደመካድ ይቆጠራል። የአማራ ሕዝብ ከ50 ዓመታት በላይ የፈጀበትን ድርጅት የማዋለድ ሂደት እውን ለማድረግ ከፍተኛ ትንቅንቅ በሚደረግበት ወቅት አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ወደ ኋላ ለመመለስ ጥረት ሲያደርግ ይታያል። አፋብን ከተመሠረተ በጥቂት ወራት ውስጥ ከአማራዊ አንድነት አልፎ ኢትዮጵያዊነትን መዳረሻ በማድረግ ከ7 በላይ ድርጅቶችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ "ትብብር ለሕልውና" በሚል ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ክስተት በሆነ፣ የጠላትን ቅስም በሰበረና የኢትዮጵያን ሕዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ትስስር በከፍተኛ ደረጃ በማነቃቃት ከጥላቻ ወደ ፍቅር ጎዳና በመምራት በከፍተኛ የድል ግስጋሴ ላይ ባለበት ወቅት የጠላት አጋር በሚመስል መልኩ የተሰበሰበውን ለመበተን፣ የተቀጠለውን ለመቁረጥ፣ አንድነቱን ለማፍረስና ድርጅት አልባ ለማድረግ መርህ አልባ የሚዲያ አጠቃቀም ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወቅ ሀቅ ነው። በመሆኑም ምንም እንኳን ድርጅታዊ ተልዕኮን መሠረት በማድረግ የድርጅቱ አመራሮች ከአርበኛ መሳፍንት ተስፉ ጋር ሰፊ ውይይት ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የሰራውን ተደጋጋሚ ስህተት ተረድቶ ማስተካከያ ከማድረግ ይልቅ በዚያው የስህተት መንገድ በመቀጠል በእጅ አዙር ለጠላት መጠቀሚያ የሚሆን እንዲሁም የሕዝብንና የድርጅቱን ዓላማ የሚጎዳ ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል። በመሆኑም አርበኛ መሳፍንት ተስፉ በተለያዩ ጊዜያት እየሰጠ ያለው መግለጫ የአፋብን ድርጅትን፣ የአባት አርበኞች ም/ቤትን እና አጠቃላይ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግልን የማይወክል እንደሆነ እናሳውቃለን። የአርበኛ መሳፍንት መግለጫ አንድነታቸውን በአፋብን ስር አፅንተው የሚታገሉ ዕዞችንም የሚከፋፍል በመሆኑ የአፋብን አባት አርበኞች ም/ቤት ለመላው የአማራ ህዝብ፣ ለመገናኛ ብዙኃን እና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚከተሉትን ነጥቦች በአጽንኦት እናሳስባለን፦ ለመላው የአማራ ህዝብ:- ድርጅታችን አፋብን የአማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ከመምራት ባለፈ በ"ትብብር ለሕልውና" ማዕቀፍ ከ7 በላይ ድርጅቶችን በማሰባሰብ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አንድነት ለማረጋገጥ በከፍተኛ የድል ግስጋሴ ላይ ይገኛል። በመሆኑም በዚህ ወሳኝ የትግል ምዕራፍ ላይ የሚሰጡ ማናቸውም መግለጫዎችና የሚተላለፉ መረጃዎች የሕዝቡን አንድነት የሚያጠናክሩና ኃላፊነት የሚሰማቸው ሊሆኑ እንደሚገባ በመገንዘብ ከአፋብን እውቅና ውጪ በግለሰብ ደረጃ በሚሰጡ መግለጫዎች ሳትደናገሩ የህልውና ትግሉን እንድታስቀጥሉ እናሳስባለን። ለመገናኛ ብዙኃን (ሚዲያዎች)፦ በአሁኑ ወቅት በግለሰቦች ወይም በተናጠል የሚወጡ መግለጫዎች የአማራን ሕዝብ የትግል አንድነት የሚሸረሽሩ፣ ዕዞችን የሚከፋፍሉና ሕዝቡን ለዳግም እርስ በርስ ግጭት የሚዳርጉ ቅስቀሳዎችን ያዘሉ በመሆናቸው ሚዲያዎች የሙያ ሥነ-ምግባርን በመጠበቅ ከድርጅታችን አፋብን ሕጋዊና መደበኛ መዋቅር ውጭ የሚሰራጩ መርህ አልባ መረጃዎችን ከማስተጋባት እንድትቆጠቡ እናሳስባለን። ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፦ አፋብን የሕዝቡን ሕልውና የማስከበርና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ አጠናክሮ ቀጥሏል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም የትግሉን ትክክለኛ ገጽታና የሕዝቡን የጋራ ፍላጎት በመረዳት በተናጠል ወይም በግል ፍላጎት ተነሳስተው በሚሰጡ የተሳሳቱ መግለጫዎች ሳትደናገሩ ከሕዝቡ እውነተኛ የሕልውና ትግል ጎን በአንድነት እንድትቆሙ እናሳስባለን። ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!! ድል ለፋኖ!!! ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ድል ለትብብሩ ኃይላት!!! የአፋብን አባት አርበኞች ም/ቤት ህዳር 14/2019ዓ.ም
Open in Telegram