Forwarded from ፈዋኢድ
የጋራ ጠላትን መመከት በጣም ጥሩ ነው፤ ይህ ግን ሙኻለፋ እየታየ ዝም ይባላል ማለት አይደለም፤ በተለይም ከሥርህ ያሉ ወጣቶችን የሚያስበላ ሲሆን። በድምፃችን ይሰማ ዘመን አህባሾችን የጋራ ጠላት ናቸው በሚል ብዙ ዝምታን መርጦ፣ በአብዮቱ ሽፋን ስንቱን ሰለፊ ወጣት ኢኽዋን ወሰደው! ከታሪክ መማሩ መልካም ነው፤ ታሪክ ራሱን ሊደግም ይችላል። የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦ ምእመን ከአንድ ጉድጓድ ሁለት ጊዜ አይነደፍም። لولا الله ثم الأستاذ سادات والأستاذ ابن منور وغيرهما من الأفاضل لكان كثير من الشباب السلفي في صف الإخوان . በሑነይን ዘመቻ اجعل لنا ذات أنواط كما لهم ذات أنواط በተባለ ጊዜ ውዱ ነቢያችን صلى الله عليه وسلم ኢንካር አድርገዋል، بأبي هو وأمي. [لقد كان لكم في رسول الله أسوة حسنة] ሸይኹል ኢስላም رحمه الله ታታር ሙስሊሙን ኡማ ሲያጠቁ በጋራ መከላከላቸው ሙንከርን ኢንካር ከማድረግ ወደ ኋላ አላደረጋቸውም (الاستغاثة والرد على البكري، ص 413). በዘመናችንም ሸይኽ ጀሚሉ አር'ረሕማንም በአፍጋን ምድር አህለሱናዎችን በሙኻሊፋች ሳያስበሉ፣ ከሶቪየት ሕብረት ጋር እስከ ጥግ ይታገሉ ነበር፤ ከሙኻለፋዋችም ያስጠነቅቁ ነበር። رحمك الله أيها المجاهد السلفي الأبي. በዚህም የምጠቁመው ሙኻለፋን ኢንካር ሲያደርጉ ወዲያውኑ መለወጡ ወይም በሚመከረው ሰው ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩ መስፈርት አይደለም፤ መቀየሩ ከዓላማዎቹ አንዱ ቢሆንም። አንድ ሸይኽ ስለ ፈርዱል ኪፋያ ካወሩ በኋላ እንዲህ ይላሉ፦ كأمر معروف ونهي منكر \* وإن يظن النهي لم يؤثر የንግግራቸው ጭብጥ ሀሳብ ፦ (በጎን ነገር ማዘዝና ከክፉ ነገር መከልከል የሚደነገጉት፣ የተከለከለው ሰው ከክልከላው ተጽዕኖ እንደማይደርስበት በአብዛኛው ቢገመትም ጭምር ነው።) ይህ ግን የሸሪዓው ትልቁ መርህ የጥቅምና የጉዳት ሚዛንን ሙሉ በሙሉ መተው ማለት አይደለም። ካፒታልህ የሆኑትን ይዘህ የጋራ ጠላት መክት ነው በአጭሩ። والسلام.
Open in Telegram