Account
ፍኖተ-አበው

ፍኖተ-አበው

የቤተክርስቲያናችንን⛪ 📚 ትምህርት፣ 🎶 ዝማሬ፣ 📝 ኪነ-ጥበባት  የምናገኝበት  ቻናል ነው።👇👇👇 አንተን ማገልገል መባረክ ነው ምርጫ ነው ዕጣ ነው ክብር ነው እድል ነው

Username
@fenote_abew
Subscribers3,291
Avg views per post, 7d114−38.9% vs prev 7d
ERR3.47%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 9, 2026403
Nov 12, 2026362
Nov 13, 2026244
Nov 14, 2026192
Nov 15, 2026163
Nov 16, 2026243
Nov 20, 2026196
Nov 22, 2026150
Nov 24, 2026130
Nov 26, 202683

Most viewed this month

  1. የመጨረሻ ክፍል ክፍል 3⃣ #አንድ_ሰው_ወደ_አገልግሎት_ሲመጣ_በአገልግሎት_ሕይወት_ችግር_እንዳይገጥመው _ምን_ማድረግ_ይጠበቅበታል; ✅እለት እለት መንፈሳዊ መፅሐፍትን የሚመረምርና ራሱንም በእግዚአብሔር ቃል ሊፈትን /ሊፈልግ/ ይገባዋል 1ኛ ቆሮ 10.12 ✅በአልግሎት ዘመኑ ሰዎችን መመልከት የለበትም 1ኛ ቆሮ 3.1-9 ✅ስለሚያገለግለው አገልግሎት ምን ጊዜም ከመፀለይ ወደ ኋላ ሊል አይገባም /ከአገልግሎት በፊትና ከአገልግሎት በኋላ ሊፀልይ ያስፈልጋል/ ✅ለተገልጋዮች መሰናክል እንዳይሆን በተቻለ መጠን በምግባርና በሃይማኖት ከማይመስሉት ሰዎች ሕብረት እንዳይኖረው ሊጠነቀቅ ይገባዋል 2ኛ ቆሮ 6.14 ✅ ከሊቃውንት እግር ስር ተቀምጦ ሊማር፣ የተማረውንም ሊያስተምር ይጠበቅበታል ሉቃ 10.38-42 ✅ ከመንፈሳዊ ወንድሞች ጋር በአገልግሎት ዙሪያ መወያየት፣ ችግሮች ካሉ በጋራ በመቅረፍ መመላለስ ይጠበቅበታል፡፡ #ቤተክርስቲያን_ከሰ_ት/_ቤት_ምን_ትጠቀማለች ❇️ሰ/ት/ቤት ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ተተኪ ትውልድን በማበርከት ❇️በድቁና፣ በቅስና፣ በምንኩስናና በጵጵስና ቤተክስቲያንን የሚመሩ ትውልዶችን በማበርከት ❇️በቤተክርስቲያን ላይ የሚሰነዘሩ ጥያቄዎችን /በምንፍቅና/ የሚመክት የቤተ ክርስቲያን    አለኝታ የሚሆኑ ትውልዶችን በማበርከት ❇️ለሀገርና ለወገን የሚጠቅሙ ፍሬዎችን በማፍራት የቤተክርስቲያን ድምፅ በሀገር ደረጃ      ከፍ ብሎ እንዲሰማ የሚያደርጉ ትውልዶችን በማበርከት ❇️የቤተክርስቲያን ማዕዘንና ውበት በመሆን የቤተክርስቲያን ልጆችን፣ ቅርሶችንና ሀብቶችን     ከጠላት በመጠበቅ የሚተጋ ትውልድ ሰ/ት/ቤት ከተመሰረተችበት እለት ጀምሮ እስካሁን በማበርከት ላይ ትገኛለች፡፡ ❇️ሰንበት ትምህርት ቤት የምታበረክተው ጥቅም እጅግ ከሆኑ አንፃር ለመግለፅ ቃላትና  ጊዜያት ያጥራሉ እግዚአብሔር ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ከክፉ ሁሉ እንዲጠብቅ መፀለይ ግን የሁላችንም ሃላፊነትና ግዴታ ነው፡፡ #ማጠቃለያ ዛሬ ዓለማችን ወጣቱን ትውልድ የምታጠምድባቸው ከእግዚአብሔር ቤት የምታስኮበልልባቸው መንገዶች እጅግ አየበዙና እየረቀቁ በየጊዜውም መልካቸውን እየለዋወጡ በመምጣት ላይ ናቸው፡፡ እነዚህን ተቋቁሞ እስከ መጨረሻው ለመጓዝ ደግሞ በቤተክርስቲያን ጥላ ስር በሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች መጠለል ጊዜ የማይሰጠውና ቸል የማይባል ነገር ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ሕዝ 22.30 በፈረሰው በኩል የሚቆም እንዲል ትዕግስት፣ ፅናት፣ ጠንካራ የሆነን ውሳኔ ማሳለፍ ከእያንዳንዲ ወጣተ ትውልድ ይጠበቃል፡፡ ዛሬ መናፍቃ እጅግ ባልተጠበቀ ፍጥነት የዓለምን አብዛኛውን ክፍል ባጥለቀለቁበትና የምንፈቅና መረዛቸውን ብዙዎችን እየወጋ ከመንገድ እያወጣ ከእውነት እያራቀ ይገኛል፡፡ እኛ ግን ዛሬም ቀሰቃሽ እየፈለግን ባንበት ተኝተናል ግነ ለምን?; ብዙ የmiያሳስቡን የሥግና የነፍስ ጥያዎች እንዳሉን እውን ነው ግን ስለጊዜው ሳይሆን ስለዘለዓለሙ ሕይወት ልንጨነቅ ይገባል፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በዚህ ወቅት ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ከፊታቸው ከባድ የቤት ሥራ ተደቅኖባቸዋል ምዕመናኑን /ከሕፃን እስከ አዋቂ/ ከዓለም /ከምንፍቅና/ መርዝ የመጠበቅና በቤተክርስቲያን ላይ እየተቃጠ ያለውን የጥፋት ዘመቻ የማስወገድ ፈታኝ ወቅት ጋር ፊት  ለፊት ቆመዋል ይህን አስተውሎ አፋጣኝ የሆነ መፍትሔ መፈለግ የግድና የግድ አስፈላጊ ነው ለዚህም በእግዚአብሔር ኃይል ለመንነሳትና አምላክን ከፊት አስቀድመን ልንወጣ ይገባል “ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው” ወስብሐት ለእግዚአብሔር #share @Fenote_Abew #share @Fenote_Abew #share @Fenote_Abew ©senbet_timhertbet

    Text
    Views403
    Forwards—
    Reactions1
    Comments—
  2. ++++ አገልግሎት  +++++                  ++++++++++++ አንዳንድ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ለማገልገል ምንም ቦታ እንደሌላቸው ዐቅም እንደሚያንሳቸው ይናገራሉ፡፡ በማኅሌት ቢገቡ ሊቃውንቱ፤ በቤተ መቅደስ ቢገቡ ካህናቱ ዲያቆናቱ ቆመው ያገኟቸዋል፡፡ እንደ ሊቃውንቱ አልተማሩ እንደ ካህናቱና ዲያቆናቱ አልተሾሙ፥ ስለዚህ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን ለማገልገል ለእነዚህ ሰዎች በቤተ መቅደስ ውስጥ ምንም ድርሻ አይገኝላቸውም? በእውነት የልብን መሻት ብቻ ይዞ መጥቶ ማገልገል የሚቻልበት ስፍራ ከእግዚአብሔር ቤት በቀር ሌላ የት ይገኛል? ሰዎች የሆኑ እንደሆነ የትምህርት ደረጃ፣ የጤንነት ሁኔታ፣ የአካል ብቃትና ሌሎችንም ለሥራው አስፈላጊ ናቸው ያሏቸውን ነገሮች እንድናሟላ ይጠይቁናል፡፡ በቤተ እግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም፡፡ ማንም ሰው አገልግሎ ጸጋውን እንዲሳተፍ ተፈቅዶለታል፡፡ ከዕውቀት ጣራ የደረሰው አባ አርሳንዮስ የተጓዘበትን የቅድስና መንገድ መሬት አርሶ፥ እርሻ አለስልሶ ዘር ዘርቶ ከመኖር በቀር ሌላ ዕውቀት የሌለው የዋህ ጳውሊ ተጉዞበታል፡፡ እግዚአብሔር የገዳማውያን አባት ያደረገው ከሊቃውንት አንዱን ዮሐንስ አፈ ወርቅን ወይም ነባቤ መለኮት ጎርጎርዮስን አይደለም፡፡ ምንም ትምህርት የሌለውን አባ እንጦንስን ነው እንጅ፡፡ በእውነት እኔ በምን ዐቅሜ ሳልማር፣ መጻሕፍትን ሳልመረምር፣ በሀብት ሳልከብር ላገለግል እችላለሁ ከሚል ሰው በላይ እግዚአብሔርን የሚንቅ ሰው ያለ ይመስላችኋል? ባለጠጎች ሲመጡ እግዚአብሔርን ባለጠጋ የሚያደርጉት ይመስልሃል? ዐዋቂዎች ሲመጡ እግዚአብሔር ችግር ኑሮበት በዕውቀታቸው የሚፈቱለት ይመስልሃል? ደራሲዎች ስለደረሱ፣ ጸሐፊዎች ስለጻፉ ቤተ መዛግብቱን በመጻሕፍት ሞልተው ቤተ መቅደሱን በእነሱ ጥረት በአማኝ ሙሉ የሚያደርጉለት ይመስልሃል? ይሄማ እንዴት ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ያለ መምህራን አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን የመሳሰሉ አማኞችን አግኝቶ የለምን? ያለ መጻሕፍት እንደ ዮሴፍ ያለ ፈሪሐ እግዚአብሔር ያለው ሰው ማግኘት ተችሎ የለምን? ማንም ሳያስረዳው ከበጎ ልቡናው መልካም መዓዛ ያለው መሥዋዕት ማቅረብ የቻለ ደጉ ሰው አቤልን ማን አሳመነለት? እግዚአብሔርን ማንም ሰው በገንዘቡ፣ በጉልበቱ፣ በዕውቀቱ ወይም በሌላ ችሎታው ሊያከብረው አይችልም፡፡ የማንም ሰው ዐቅም እግዚአብሔር ነው፡፡ ግድ የለህም ወንድሜ ላንተ የሚሆን የአገልግሎት በር ተከፍቶ እየጠበቀህ ነው፡፡ ድሀ ብትሆን ጴጥሮስም እንዳንተ ድሀ ነበረ፡፡ ባለጠጋም ብትሆን ማቴዎስም እንዳንተ ባለጠጋ ነበር፡፡ ያልተማርህም ብትሆን ከሐዋርያትም ብዙዎች ምንም የማያውቁ ገበሬዎች እንደ ነበሩ አስተውል፡፡ የሰላ ምላስ ካላቸው ሰዎች ይልቅ አፈ ትብ የሆንኸውን አንተን ሰባኪ ያደርግሀል፡፡ ያለ አንደበት ያሰብካል፡፡ ያለ እግር ያስኼዳል፡፡ ያለ መጽሐፍ ያስተምራል፡፡ ያለ ሰባኪ ያሳምናል፡፡ ካህናቱ የተውትን ቅዳሴ የቢታንያ ድንጋዮች አስቀጥለውታል፡፡ መዘምራኑ ያቋረጡትን ዝማሬ የቤተ ልሔም እረኞች አቅርበውታል፡፡ ካህናቱ መባውን እየተቀበሉ ቢበሉት ነገሥታቱ መባ ይዘው መጡ፡፡ እግዚአብሔር ከኛ ሚፈልገው “እኔ ለእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ” ብሎ መቅረብ የሚችል ሰው ነው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ በምትችለው ታገለግላለህ፤ ካንተ የሚጠበቀው ለማገልገል ዝግጁ ሆኖ መምጣት ነው፡፡ እንደ ማርያም መማር ባትችል እንደ ማርታ ታገለግላለህ፡፡ እንደ አብርሃም ያለህን አንድ ልጅህን መስጠት ባትችል ጌታ ስጦታዋን እንዳደነቀላት መበለት ያለህን ገንዘብ ትሰጣለህ፡፡ ማገልገል በብዙ መንገድ ነውና በምትችለው ታገለግላለህ፡፡ እግዚአብሔር  እንድናገለግል ይርዳን🙏 ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

    Text
    Views362
    Forwards—
    Reactions1
    Comments—
  3. Views244
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  4. #ኅዳር_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን #የቅዱስ_ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት ቅዳሴ ቤቱ፣ ከእስክንድርያ አገር የሆነ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ዘወለቃ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው፣ #አባ_ናህርው በሰማዕትነት አረፈ፣ #የአባ_ሚናስ_ዘተመይ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱሳን_ዘኖቢስ እና እናቱ #ቅድስት_ዘኖብያ እንዲሁም #ቅዱስ_ሐዲስ_መርቆሬዎስ እና ወንድሙ #ቅዱስ_ዮሐንስ በሰማዕትነት አረፉ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕት ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ። ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ። ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_እስክንድርያ በዚህች ቀን የእስክንድርያ አገር የሆነ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባቱ በእስክንድርያ አገር በንግድ ሥራ የሚኖር ነው ልጅም አልነበረውም የልዳዊው ቅዱስ ጊዮርጊስም ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት የበዓልዋ መታሰቢያ ኅዳር ሰባት በደረሰ ጊዜ ልጅን ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲማልድለት ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመነው ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህን ልጅ ሰጠው ስሙንም በታላቁ ሰማዕት ስም ጊዮርጊስ ብሎ ስም አወጣለት። የዚህም ልጅ እናቱ ለእስክንድርያ አስተዳዳሪ ለአርማንዮስ እኅቱ ናት ከዚህም በኋላ እናትና አባቱ አረፉ እርሱም ከእናቱ ወንድም ዘንድ ተቀመጠ ሃያ አምስት ዓመትም በሆነው ጊዜ በጎ ሥራ የሚሠራ ሆነ ድኆችን እጅግ ይረዳቸው ይወዳቸውም ነበረ የሚራራና የሚመጸውት ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን መገሥገሥንም ይወዳል። ለመኰንን አርማንዮስም አንዲት ብቻዋን ሴት ልጅ አለችው ቦታዎችንም በመጐብኘት ደስ ይላት ዘንድ ከባልንጀሮቿ ጋር ወጣች ወደ ደብረ ቊስቋምም ስትደርስ ጣዕም ባለው ድምጽ በመዘመር ሲያመሰግኑ የተሰበሰቡ መነኰሳትን አገኘቻቸው ምስጋናቸውና መዝሙራቸውም ወደ ልቡዋ ገብቶ ተቀረጸ። የአባቷ እኅት ልጅ የሆነ ጊዮርጊስንም መነኰሳቱ ስለሚዘምሩት ያስረዳት ዘንድ ጠየቀችው እርሱም ወደማይጠፋ ዕረፍትና ተድላ እንደሚያደርሳቸው ትርጓሜውንና ጥቅሙን ሊያስረዳትና ሊያስገነዝባት ጀመረ። ወደ አባቷም አርማንዮስ በተመለሰች ጊዜ በፊቱ ቁማ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነች አባቷም ሊሸነግላት ጀመረ ልጄ ሆይ ይህን አታድርጊ አላት ነገሩን ባልተቀበለች ጊዜ ራሷን በሰይፍ አስቆረጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች። ከዚህም በኋላ ልጅህን ያሳታት የእኅትህ ልጅ ጊዮርጊስ ነው ብለው ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ሰምቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ጭካኔውንም አይቶ ወደ ሀገረ እንጽና ሰደደው በዚያም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይተው ቅድስት ራሱን በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ። በዚያም ሳሙኤል የሚባል ዲያቆን ነበር የቅዱስ ጊዮርጊስንም ሥጋ አንሥቶ ወደ ሀገረ መኑፍ ወሰደው። የአርማንዮስም ሚስት በአወቀች ጊዜ መልእክተኞችን ልካ አስመጣችው ከልጅዋም ሥጋ ጋር በአንድነት በእስክንድርያ አገር አደረገችው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ዘወለቃ ዳግመኛም በዚህች ቀን አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘወለቃ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው። የትውልድ ሀገራቸው ወሎ ቦረና ጋስጫ ነው፡፡ አባታቸው ተንሥአ ክርስቶስ እናታቸው አርሴማ ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ለመምህር ሰጧቸው፡፡ መምህሩም ጸጋ እግዚአብሔር እንዳደረባቸው ዐውቀው ‹‹ብዙዎችን የምታድን ጻድቅ ትሆናለህ›› ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ የመጻሕፍትንም ትርጓሜ በሚገባ ካስተማሯቸው በኋላ ንፍታሌም ይባል የነበረውን ስማቸውን ለውጠው ገብረ እንድርያስ አሏቸው፡፡ ጻድቁ በአቡነ ዮሐንስ ከማ ገዳም ለረጅም ጊዜ በታላቅ ተጋድሎ አገልግለዋል፡፡ አባታችን ሙታንን በማስነሣትና ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን ሲያደርጉ ኖረዋል፡፡ ብዙ አባቶች ሱባኤ ይይዙበት በነበረው በሰኮሩ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት ሲያደርጉ ቅዱስ ዑራኤል በወርቅ ጽዋ ሰማያዊ ወይንና ኅብስት መግቧቸዋል፡፡ እመቤታችንም ሦስት ጽዋ ማየ ሕይወት ሰጥታቸው በእርሱ ብዙ ሕሙማንን ፈውሰውበታል፡፡ ጻድቁ በስማቸው የፈለቀው ጸበል እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ጸበሉ ውስጥ እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት ነጭ መቁጠሪያ ሆኖ ይወጣል፡፡ ይህም እስከዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል፡፡ ጸበሉ ውስጥ ማታ የነከሩትን እንጨት ጠዋት ላይ መቁጠሪያ ሆኖ ያገኙታል፡፡ እጅግ አስገራሚ ነው በእውነት! መቁጠሪያውም ለእንቅርትና ለልዩ ልዩ ሕመሞች መድኃኒት ነው፡፡ ነገር ግን ጸበሉ ያለበት አካባቢው በመርዛማና አደገኛ እባቦች የተሞላ ነው፡፡ ሆኖም ግን እባቦቹ የጻድቁ ግዝት ስላለባቸው በገዳሙ ውስጥ ብቻ ማንንም አይነኩም፡፡ ጸበሉ ደግሞ የሚገኘው ከገዳሙ የአንድ ሰዓት ተኩል መንገድ ርቀት ላይ ነው፡፡ አባታችን እግዚአብሔር ኃጥአንን እንድምርላቸው ጣቀት ወንዝ ከተባለው ቦታ በአንገታቸው ላይ በጣም ትልቅ ድንጋይ እየተሸከሙ ይጸልዩ ነበር፡፡ በዚህ ይጸልዩበት ከነበረው ወንዝ ውስጥ ነው በተዓምራት መቁጠሪያ የሚሠራው ጸበል የፈለቀላቸው፡፡ ደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ የሚገኘው አቡነ ገብረ እንድርያስ ገዳም ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም በእግር የ3 ሰዓት መንገድ ያስኬዳል፡፡ ጻድቁ አቡነ ገብረ እንድርያስ ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም ይመላለሱ የነበረው በትልቅ ድንጋይ ላይ እንደ ደመና ተጭነው ነበር፡፡ ጻድቁ በአየር ላይ ሲጓዙ ድንጋዩን እንደ ሠረገላ ዋርካውን እንደ ጥላ ይጠቀሙበት ነበረ፡፡ ያ እንደ ሠረገላ ሆኖ ያገለግላቸው የነበረው ትልቅ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ ታሪኩም በቅዱስ ገድላቸው ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አባ_ናህርው

    Text
    Views243
    Forwards—
    Reactions2
    Comments—

Latest posts

#8818Text

‎፭.ጾመ ፊልጶስ፡-ሐዋርያው ፊልጶስ በአፍራካ አውራጃዎች በመዘዋወር ወንጌልን እየሰበከና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ፣ ያመኑትን እያጸና፣ ያላመኑትን እየመለሰ ቆይቶ በሰማዕትነት ዐረፈ። ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ቢሹ አጡት፤ ተሰውሮባቸው ነበርና። እግዚአብሔር እንዲገልጥላቸው ሱባኤ ይዘው በጾም በጸሎት ቢለምኑት በሦስተኛው ቀን ተገልጦላቸዋል። እነሱም በክብር አሳረፉት። ጾሙን ግን እስከ ጌታ ልደት ቀን ድረስ ጹመውታል። በዚህም ምክንያት ጾመ ፊልጶስ እየተባለ ይጠራል። ‎፮. ጾመ ማርያም፡-እመ አምላክ፣ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ወልደ እግዚአቤሔርን እንደምትወልደው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቢያበሥራት ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ፀንሼ፣ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ›› በማለት በትሕትና ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጹማ ነበርና ጾመ ማርያም ተብሏል። ‎እንግዲህ ከላይ ያየናቸው ቀደምት ቅዱሳን በዚህ ጾም ተጠቅመውበታል። እኛም አምላካችን ምሕረት ይሰጠን ዘንድ እንዲሁም ከቅዱሳኑም በረከት እናገኝ ዘንድ ልንጾመው ግድ ነው። ‌‎ ✝️ውድ ኦርቶዶክሳውያን ስንጾም እነዚህን ነገሮች ልብ ማለት ይገባል። ‎ሀ. በእምነት ሁነን መጾም፦ እግዚአብሔር ይሰማኛል፤ ዋጋ አገኝበታለሁ ብለን እያመንን መሆኑን ማስተዋል ይገባል። ‎ለ. በፍቅር መጾም፦ ከወንድሞችና ከእኅቶች ጋር በመስማማትና በአጠቃላይ ክፋት በማይታሰብበት ልቡና ሆኖ መጾም ያስፈልጋል። ‎ሐ. ንስሓን፣ ጸሎትን፣ ምጽዋትን፣ ይቅርታን ገንዘብ በማድረግ መጾምን አለብን። ‎መ. ከክፉ ነገር ሕዋሳቶቻችንን ዐቅበን (ጠብቀን) መጾም፦ ዐይን፣ ጆሮ፣ እጅ፣ እግር፣ አፍ ይጹም ብሎ እንደነገረን ቅዱስ ያሬድ እኛም ከክፉ ሁሉ ተከልክለን እንዲህ ባለው አኳኋን ከጾምን ቸሩ አምላካችን ምሕረቱን ይልክልናል። ‎በመጨረሻም ስንጾም በመከራ ውስጥ ስላሉት ወገኖቻችን እያሰብን እንዲሁም ሁሉም ነገር መልካም የሚሆነው ሀገር ሰላም ሲሆን ነውና ለሀገራችን ሰላምን፣ ለሕዝቦቿም ፍቅር፣ አንድነትን እያሰብን አምላካችንን እንለምነው። የራሔልን ዕንባ የተቀበለ አምላካችን ጾማችንን ይቀበልልን፤ አሜን።    ወስብሐት  ለእግዚአብሔር! 🔷ለበለጠ መረጃ @Fenote_Abew

Open in Telegram
Views144−29%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#8817Photo

ጾመ  ነቢያት ‎ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም ‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውን ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ድረስ ይጾማል። እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን ሲል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ ከንጽሕተ ንጹሓን፣ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም መወለዱን፣ ወደ ግብጽ መሰደዱን፣ በዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርተ ወንጌልን ማስታማሩን፣ በመጨረሻም በሞቱ ሞትን ማጥፋቱን፣ ትንሣኤውንና ዕርገቱን ሁሉ አስቀድመው የተነሡ ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ትንቢት በተናገሩት መሠረት ተፈጽሟል፡፡ ነቢያቱም ትንቢታቸው እንዲፈጸም ‹‹አንሥእ ኀይለከ ፈኑ እዴከ፤ኃይልህን አንሳ እጅህንም ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው መምጫውን በጊዜ እየለኩ ሲጠባበቁ ኑረዋል። ትንቢቱም ጊዜው ሲደርስ ተፈጽሟል፡፡ እኛም ከዚህ በመነሣት ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሠረት ልንጾም ይገባናል፡፡ ✝️ጾሙ የሚጠራባቸው ስያሜዎች ‎፩.ጾመ ነቢያት ፡- ይህ ጾም ከላይ ለመግለጥ እንደሞከርነው ሁሉ ነቢያት የእግዚአብሔርን ሰው መሆንና ዓለሙን የሚያድነበትን ጊዜ እየተጠባበቁ የጾሙት በመሆኑ ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም) ተብሏል። ፪. ጾመ አዳም ፡- ‎ለአዳም የተነገረው የድኅነት ተስፋ ስለመፈጸሙ የተሰጠው ስያሜ ነው። ‌‎፫. ጾመ ስብከት፡- ‎ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት በመሆኑ ጾመ ስብከትም እየተባለ ይጠራል። ‎፬. ጾመ ሐዋርያት፡-‎ሐዋርያት በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እንፈታለን፤ በዓለ ልደትንም ይህን ጾም ጾመን እንፍታ ብለው ሲጾሙት ስለነበር ጾመ ሐዋርያት ይባላል።

Open in Telegram
Views116−43%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#8816Text

ጾመ ነቢያት ህዳር ፲፭(15) ይጀመራል(ይገባል) በዘመነ ብሉይ ነቢያት እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን፤ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ለአዳም የገባለትን ቃል ይፈጽም ዘንድ  ትንቢት በመናገር ለሕዝቡ የምሥራችን ቃል ያበሥሩ ነበር፡፡ አምላካችን ከድንግል ተወልዶ ከእናቱ ጋር ወደ ግብፅ ምድር እንደሚሰደድ፣ በባሕረ ዮርዳኖስ እንደሚጠመቅ፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል መከራና ስቃይ እንደሚቀበል፣ እንደሚሰቀል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ እንደሚያርግና ዳግም ለፍርድ እንደሚመጣ  በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀድመው ትንቢት ተናግረዋል፡፡ ነቢያቱም የትንቢቱን መፈጸም በተስፋ ይጠብቁ፣ በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ይማጸኑ ነበር፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ‹‹ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች›› በማለትም እንደተናገረ ትንቢት ኢሳይያስ ላይ ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ (ኢሳ. ፯፥፲፬ እንዲሁም ነቢዩ ሚክያስም በቤተ ልሔም እንደሚወለድ እንዲህ በማለት ገልጿል፤ ‹‹ አንቺም የኤፍራታ ምድር ቤተልሔም ሆይ! አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ነገር ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል፡፡›› ሚክ ፭፥፪ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በኋላም ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብፅ ሀገር እንደሚሰደድ እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት አናግሯል፡፡ ‹‹እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ እየበረረ ወደ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅም የእጆቻቸው ሥራዎች በፊቱ ይዋረዳሉ፤ የግብፃውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል›› እንዲል፡፡ (ኢሳ.፲፱፥፩) ነቢዩ ዳዊትም ‹‹ባሕር አየች፥ ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደኋላው ተመለሰ፡፡ ተራሮች እንደ ኮርማዎች፥ ኮረብቶችም እንደ በጎች ጠቦቶች ዘለሉ፡፡ አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንተም ዮርዳኖስ ወደ ኋላህ የተመለስህ ምን ሁናችሁ ነው?› ብሎ እንደተናገረው ምሥጢረ ጥምቀቱ ይፈጸም ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ፍቃዱ ሆነ፡፡ ጌታችን ኢየሱስም የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን ለመቀደስ፣ የአዳምን ልጆች የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ በዮርዳኖስ ወንዝ እንደሚጠመቅ ቀድሞ ተነገረ፡፡ (መዝ. ፻፲፫፥፫) ጌታችንም ከተጠመቀና ለትምህርተ ወንጌል በሚገለጥበት በ፴ ዓመቱ ለብዙዎች ትምህርተ ወንጌልን እንደሚሰብክ እና በጨለማ ውስጥ ላሉት ሕዝብም ሁሉ ብርሃን እንደሚወጣላቸውም  የተስፋ ቃል ለሰው ልጅ ሁሉ ተነግሯል፡፡ ይህንንም ነቢዩ ኢሳይያስ ሲገልጽ ፤ ‹‹በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላና በጨለማ ሀገርም ለነበሩ ብርሃን ወጣላቸው›› ብሏል፡፡ (ኢሳ.፱፥፪) ነቢዩም ጌታችን ስለ እኛ መከራ እንደሚ ቀበል ‹‹ እርሱ ግን ስለ ኃጢአታችን ቈሰለ፤ ስለ በደላችንም ታመመ፤ የሰላማችንም ተግሣጽ በርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተ ፈወስን››  በማለት አስቀድሞ እንደተናገረ በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቧል፡፡ ከዚህ ሁሉ መከራና ስቃይ በኋላም ጌታችን ኢየሱስ ሞትንም ድል አድርጎ እንደሚነሣ ‹‹እኔ ተኛሁ፤ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም አንሥቶኛልና ተነሣሁ›› በማለት እንዲሁም ተነሥቶ እንደሚዐርግ ‹‹እግዚአብሔር በእልልታ÷ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዐረገ›› በማለት ነቢዩ ዳዊት ትንቢት ተናግbል፡፡ (ኢሳ. ፶፫፥፭፣መዝ.  ፫፥፭፣ መዝ. ፵፮፥፭) ይህ ይፈጸም ዘንድ ነቢያቱ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ሆኖ ዓለምን የሚያድንበትን ዘመነ ሥጋዌ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መሆን ተፈጽሟል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ታሳቢ በማድረግ በዘመነ ማቴዎስ፣ ማርቆስና ሉቃስ፤ ከኅዳር ፲፭ አስከ ታኅሣሥ ፳፱፤  በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ እስከ ታኅሣሥ  ፳፰ ጾም ታውጃለች፡፡ ✅ነቢያት የጾሙት ይህ ጾም በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፤ ሁሉን ነገር በምክንያት የሚያደርገው አምላካችን እግዚአብሔር ለአዳም ድኅነት ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው የገባለት ቃል እንዲፈጸም ትንቢት በተነገረው መሠረት ነቢያት ቢጾሙት እና ‹‹የነቢያት ጾም (ጾም ነቢያት)›› ተብሎ ቢጠራም በመሰቀሉ የተቀበለለት መከራ ሁሉ የአዳምን እዳ ይከፍልለት ዘንድ ነውና ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡ ✝ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመሆኑም ‹‹የስብከት ጾም (ጾመ ስብከት)›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመሆኑ ደግሞ ‹‹የልደት ጾም(ጾመ ልደት)›  በመባል ይታወቃል፡፡ ✝ይህ ጾም ‹‹የፊልጶስ ጾም (ጾመ ፊልጶስ)››  ተብሎ ይጠራል፤ የዚህም ምክንያት ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ሁሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባኤ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው ፈጣሪያቸውን በመማጸናቸው እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መለሰላቸው፤ ሥጋውንም (አስከሬኑን) በክብር ቀብረውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ ጾመዋል፤ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹የፊልጶስ ጾም (ጾመ ፊልጶስ) እየተባለ ይጠራል፡፡ በነቢያት ጾም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛም በዚህ ዘመን ከገባንበት ችግርና መከራ አምላካችን እግዚአብሔር ከፈተና እንዲያወጣን በጾም በጸሎት እንማጸን፤ ቸርነትንና ምሕረትንም እንለምን፡፡ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ሁላችንም በዚህ የነቢያት ጾም ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡ ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።   ወስበሐት_ለእግዚአብሔር    ወለወላዲቱ_ድንግል ወለመስቀሉ_ክቡር አሜን ፫💓🕊 እርሱ ይርዳን🙏

Open in Telegram
Views163−20%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#8810Text

‎እንኳን ለሰማይ ሠራዊት አለቃ፣ ለቅዱሳን መላእክት መሪ፣ ለእግዚአብሔር ባለሟልና ለሰው ልጆች ታላቅ ረዳት ለሆነው ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ የመታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ‎ ‎በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሥርዓትና የታሪክ ማኅደር መሠረት ኅዳር 12 ቀን (እንዲሁም በየወሩ 12ኛ ቀንና ሌላው በታላቁ ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ሰኔ 12) አበው ሊቃውንትና አእላፋት ምዕመናን የዚህን ታላቅ መልአክ ሰማያዊ ክብር፣ በሰማይና በምድር የፈጸመውን ድንቅ ተአምራት እና የመንፈሳዊ ድል አድራጊነት ሥልጣኑን በማሰብ በታላቅ ምስጋና፣ በዝማሬና በክብር የሚያከብሩት እጅግ ታላቅ ዓመታዊ የበዓል ዕለት ነው። ‎ ‎ቅዱስ ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ “መኑ ከመ አምላክ” ማለት ሲሆን፣ ትርጉሙም “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው። ይህንንም ስም ያገኘው በመጀመሪያው የፍጥረት ዕለት ሳጥናኤል በትዕቢት ተነሳስቶ “እኔ ፈጣሪ ነኝ” ባለ ጊዜ፣ መላእክት በተደናገጡበት ሰዓት ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ ቅናት ተነሥቶ “ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ” (ፈጣሪያችንን እስክናገኝ ድረስ በያለንበት እንጽና) በማለት መላእክትን በእምነት አጽንቶ ዲያብሎስንና ሠራዊቱን ከሰማይ ድል ነሥቶ ወደ ጥልቁ በመጣሉ ነው። ‎ ‎በኅዳር 12 ቀን በልዩ ሁኔታ የሚከበረውም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ታዝዞ ለነቢዩ ለኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ በተመዘዘ ሰይፍ ተገልጦለት የእስራኤልን ሕዝብ የመራበትና የጠላቶቻቸውን ቅጥር ያፈረሰበት፣ እንዲሁም የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተቀድሶ በውስጡ ታላላቅ ተአምራት የተደረጉበት ዕለት ስለሆነ ነው። ‎ ‎በተጨማሪም በብሉይና በሐዲስ ኪዳን እስራኤልን በምድረ በዳ በደመና ዓምድና በእሳት ዓምድ የመራ፣ ነቢዩ ዳንኤልን ከአናብስት አፍ የጠበቀ፣ በመጨረሻውም ዘመን የሙታንን አፅም የሚሰበስብና ስለ ቅዱሳን የሚማልድ የምሕረት መልአክ ነው። ‎ ‎እግዚአብሔር አምላክ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ታላቅና ድንቅ ቃል ኪዳን የሰጠ ሲሆን፣ ስሙን ጠርተው የሚማጸኑትን፣ ዓመታዊና ወርሃዊ መታሰቢያውን በፍቅር የሚያከብሩትን፣ በስሙ ለነዳያን የሚመጸውቱትንና በምልጃው የሚታመኑትን ሁሉ ከክፉ መንፈስ፣ ከደዌና ከጠላት ወጥመድ እንደሚጠብቅ ቃል ገብቷል። ‎ ‎የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል ለእኛ ለክርስቲያኖች ታላቅና ጥልቅ መንፈሳዊ አስተምህሮን ይዞልናል። የመጀመሪያው ትምህርት በትዕቢት ፈንታ በትሕትናና በእምነት ጸንቶ መቆም ነው። ቅዱስ ሚካኤል የዲያብሎስን የትዕቢት ሐሳብ ተቃውሞ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት በመመስከር የሰማይ ሠራዊት አለቃ ሆኖ ተሹሟል። ይህም እኛም በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ከትዕቢትና ከኩራት ርቀን ለእግዚአብሔር ክብር በትሕትና በመገዛት ታማኝ አገልጋዮች መሆን እንዳለብን ያስተምረናል። ‎ ‎ሁለተኛው ትምህርት ደግሞ በመከራና በፈተና ጊዜ በእግዚአብሔር ረድኤትና በቅዱሳን መላእክት ጥበቃ መታመን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” እንደሚል፣ እኛም በሕይወታችን የሚገጥሙንን መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ ውጊያዎች በጸሎትና በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ማሸነፍ እንዳለብን ያሳስበናል። ‎ ‎እግዚአብሔር አምላክ ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል በሰጠው ታላቅ ቃል ኪዳን መሠረት፣ ስሙን ጠርተው የሚማጸኑትን፣ ዓመታዊና ወርሃዊ መታሰቢያውን በፍቅር የሚያከብሩትን፣ በስሙ ለነዳያን የሚመጸውቱትንና በምልጃው የሚታመኑትን ሁሉ ከክፉ መንፈስ፣ ከደዌ፣ ከድንገተኛ አደጋና ከልዩ ልዩ መከራ ይሰውራቸዋል፤ በቤታቸውም የመንፈስ ቅዱስን በረከት፣ የልቦናን ሰላም፣ ረድኤትና አምላካዊ ጥበቃን ያበዛል። ‎ ‎በዚህ በረከትና ረድኤት በሞላበት ታላቅ ዓመታዊ የመታሰቢያ ዕለት፣ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት፣ ጸሎትና ሰማያዊ ጥበቃ ከሁላችን ጋር እንዲሆን እንመኛለን። ‎ ‎ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ፍጹም ሰላምን፣ አንድነትንና የድል መንፈስ እንዲያማልድልን፣ በልቦናችን ውስጥ እውነተኛውን የእምነትና የጽናት መንገድ አምላካችን እንዲያበራልን እንጸልያለን። የቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ በረከትና ረድኤት በቤታችን ላይ ይደር፤ መልካም የበዓል ቀን ይሁንልን! ‎ ‎©zewdu_kassie ‎#ቅዱስ_ሚካኤል #ሊቀ_መላእክት #ሚካኤል #ኅዳር12 #ዓመታዊ_ክብረ_በዓል #መኑ_ከመ_አምላክ #ተዋሕዶ #ኦርቶዶክስ #ኢትዮጵያ #የቅዱሳን_በረከት #ቅድስና #ጸሎት #በረከት #ምልጃ #ሰላም_ለኢትዮጵያ @Fenote_Abew

Open in Telegram
Views196−3%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8809Text

#ኅዳር_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን #የቅዱስ_ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት ቅዳሴ ቤቱ፣ ከእስክንድርያ አገር የሆነ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ዘወለቃ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው፣ #አባ_ናህርው በሰማዕትነት አረፈ፣ #የአባ_ሚናስ_ዘተመይ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱሳን_ዘኖቢስ እና እናቱ #ቅድስት_ዘኖብያ እንዲሁም #ቅዱስ_ሐዲስ_መርቆሬዎስ እና ወንድሙ #ቅዱስ_ዮሐንስ በሰማዕትነት አረፉ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕት ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ። ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ። ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_እስክንድርያ በዚህች ቀን የእስክንድርያ አገር የሆነ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባቱ በእስክንድርያ አገር በንግድ ሥራ የሚኖር ነው ልጅም አልነበረውም የልዳዊው ቅዱስ ጊዮርጊስም ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት የበዓልዋ መታሰቢያ ኅዳር ሰባት በደረሰ ጊዜ ልጅን ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲማልድለት ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመነው ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህን ልጅ ሰጠው ስሙንም በታላቁ ሰማዕት ስም ጊዮርጊስ ብሎ ስም አወጣለት። የዚህም ልጅ እናቱ ለእስክንድርያ አስተዳዳሪ ለአርማንዮስ እኅቱ ናት ከዚህም በኋላ እናትና አባቱ አረፉ እርሱም ከእናቱ ወንድም ዘንድ ተቀመጠ ሃያ አምስት ዓመትም በሆነው ጊዜ በጎ ሥራ የሚሠራ ሆነ ድኆችን እጅግ ይረዳቸው ይወዳቸውም ነበረ የሚራራና የሚመጸውት ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን መገሥገሥንም ይወዳል። ለመኰንን አርማንዮስም አንዲት ብቻዋን ሴት ልጅ አለችው ቦታዎችንም በመጐብኘት ደስ ይላት ዘንድ ከባልንጀሮቿ ጋር ወጣች ወደ ደብረ ቊስቋምም ስትደርስ ጣዕም ባለው ድምጽ በመዘመር ሲያመሰግኑ የተሰበሰቡ መነኰሳትን አገኘቻቸው ምስጋናቸውና መዝሙራቸውም ወደ ልቡዋ ገብቶ ተቀረጸ። የአባቷ እኅት ልጅ የሆነ ጊዮርጊስንም መነኰሳቱ ስለሚዘምሩት ያስረዳት ዘንድ ጠየቀችው እርሱም ወደማይጠፋ ዕረፍትና ተድላ እንደሚያደርሳቸው ትርጓሜውንና ጥቅሙን ሊያስረዳትና ሊያስገነዝባት ጀመረ። ወደ አባቷም አርማንዮስ በተመለሰች ጊዜ በፊቱ ቁማ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነች አባቷም ሊሸነግላት ጀመረ ልጄ ሆይ ይህን አታድርጊ አላት ነገሩን ባልተቀበለች ጊዜ ራሷን በሰይፍ አስቆረጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች። ከዚህም በኋላ ልጅህን ያሳታት የእኅትህ ልጅ ጊዮርጊስ ነው ብለው ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ሰምቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ጭካኔውንም አይቶ ወደ ሀገረ እንጽና ሰደደው በዚያም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይተው ቅድስት ራሱን በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ። በዚያም ሳሙኤል የሚባል ዲያቆን ነበር የቅዱስ ጊዮርጊስንም ሥጋ አንሥቶ ወደ ሀገረ መኑፍ ወሰደው። የአርማንዮስም ሚስት በአወቀች ጊዜ መልእክተኞችን ልካ አስመጣችው ከልጅዋም ሥጋ ጋር በአንድነት በእስክንድርያ አገር አደረገችው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ዘወለቃ ዳግመኛም በዚህች ቀን አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘወለቃ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው። የትውልድ ሀገራቸው ወሎ ቦረና ጋስጫ ነው፡፡ አባታቸው ተንሥአ ክርስቶስ እናታቸው አርሴማ ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ለመምህር ሰጧቸው፡፡ መምህሩም ጸጋ እግዚአብሔር እንዳደረባቸው ዐውቀው ‹‹ብዙዎችን የምታድን ጻድቅ ትሆናለህ›› ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ የመጻሕፍትንም ትርጓሜ በሚገባ ካስተማሯቸው በኋላ ንፍታሌም ይባል የነበረውን ስማቸውን ለውጠው ገብረ እንድርያስ አሏቸው፡፡ ጻድቁ በአቡነ ዮሐንስ ከማ ገዳም ለረጅም ጊዜ በታላቅ ተጋድሎ አገልግለዋል፡፡ አባታችን ሙታንን በማስነሣትና ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን ሲያደርጉ ኖረዋል፡፡ ብዙ አባቶች ሱባኤ ይይዙበት በነበረው በሰኮሩ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት ሲያደርጉ ቅዱስ ዑራኤል በወርቅ ጽዋ ሰማያዊ ወይንና ኅብስት መግቧቸዋል፡፡ እመቤታችንም ሦስት ጽዋ ማየ ሕይወት ሰጥታቸው በእርሱ ብዙ ሕሙማንን ፈውሰውበታል፡፡ ጻድቁ በስማቸው የፈለቀው ጸበል እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ጸበሉ ውስጥ እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት ነጭ መቁጠሪያ ሆኖ ይወጣል፡፡ ይህም እስከዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል፡፡ ጸበሉ ውስጥ ማታ የነከሩትን እንጨት ጠዋት ላይ መቁጠሪያ ሆኖ ያገኙታል፡፡ እጅግ አስገራሚ ነው በእውነት! መቁጠሪያውም ለእንቅርትና ለልዩ ልዩ ሕመሞች መድኃኒት ነው፡፡ ነገር ግን ጸበሉ ያለበት አካባቢው በመርዛማና አደገኛ እባቦች የተሞላ ነው፡፡ ሆኖም ግን እባቦቹ የጻድቁ ግዝት ስላለባቸው በገዳሙ ውስጥ ብቻ ማንንም አይነኩም፡፡ ጸበሉ ደግሞ የሚገኘው ከገዳሙ የአንድ ሰዓት ተኩል መንገድ ርቀት ላይ ነው፡፡ አባታችን እግዚአብሔር ኃጥአንን እንድምርላቸው ጣቀት ወንዝ ከተባለው ቦታ በአንገታቸው ላይ በጣም ትልቅ ድንጋይ እየተሸከሙ ይጸልዩ ነበር፡፡ በዚህ ይጸልዩበት ከነበረው ወንዝ ውስጥ ነው በተዓምራት መቁጠሪያ የሚሠራው ጸበል የፈለቀላቸው፡፡ ደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ የሚገኘው አቡነ ገብረ እንድርያስ ገዳም ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም በእግር የ3 ሰዓት መንገድ ያስኬዳል፡፡ ጻድቁ አቡነ ገብረ እንድርያስ ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም ይመላለሱ የነበረው በትልቅ ድንጋይ ላይ እንደ ደመና ተጭነው ነበር፡፡ ጻድቁ በአየር ላይ ሲጓዙ ድንጋዩን እንደ ሠረገላ ዋርካውን እንደ ጥላ ይጠቀሙበት ነበረ፡፡ ያ እንደ ሠረገላ ሆኖ ያገለግላቸው የነበረው ትልቅ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ ታሪኩም በቅዱስ ገድላቸው ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አባ_ናህርው

Open in Telegram
Views243+20%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#8808Photo
Views163−20%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#8797Photo
Views183−10%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—

All posts