ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለድርድር የራሱን ቅድመ ሁኔታ አስቀመጠ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እና ልምድ ባላቸው ተቋማት የሚመራና አፈጻጸሙም የሚከታተል ድርድር ከመንግሥት ጋር እንዲደረግ ጥያቄ ከቀረበለት ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። የንቅናቄው ቃል አቀባይ አስረስ ማረ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፓርላማ ያቀረቡት ጥሪ ትክክለኛ የሰላም ድርድር ሳይሆን ታጣቂዎችን የማባበልና "የእጅ ስጡ ጥሪ" በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። አፋብን የአማራ ሕዝብን የፖለቲካና የህልውና ጥያቄዎች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ የድርድር ስልቶችን በሰነድ አዘጋጅቶ የሦስተኛ ወገን አሸማጋይነትን እየጠበቀ መሆኑን አስታውቋል። በሌላ በኩል፣ የአፋብን እና የሰባት ታጣቂ ኃይሎች ጥምረት የሆነው "የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለኅልውና" መሪ ዘመነ ካሴ ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጓንግ ኮንግ ጋር መወያየታቸው ተገልጿል። በዚህ ውይይት ዘመነ ካሴ ሁለቱንም ተቋማት በመወከል፣ የተመድን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ በመንግሥት ላይ ተገቢውን የዲፕሎማሲ ጫና እንዲያሳድሩ መጠየቃቸውን ቃል አቀባዩ አብራርተዋል። የትብብሩን ወቅታዊ እንቅስቃሴ በተመለከተም ጥምረቱ በጋራ የፖለቲካ ፕሮግራም እየተመራ መሆኑን የገለጹት አስረስ ማረ፣ በትግራይ ክልል ዳግም በተቀሰቀሰው ግጭት የተፈጠሩ "ያልተጠበቁ ወታደራዊ ውጤቶችን" ለመቀልበስ የትብብሩ ኃይላት በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የጥምረቱ መሥራች አመራሮች በአካል እየተገናኙ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን እያስቀመጡ እንደሚገኙም አረጋግጠዋል። Via BBC
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 2 h | 212 |
| 5 h | 350 |
| 8 h | 448 |
- After 1 hour212
- After 6 hours350
- Total to date448