ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ያደረጉት የሁለትዮሽ ውይይቶች፣ 👉 ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸው በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ያለውን ትብብር ማሳደግ፣ በኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ማበረታታትና ኖርዌይ ኢትዮጵያ ለምትረከበው የCOP32 ፕሬዝዳንትነት የምታደርገውን ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ መክረዋል። የሁለትዮሽ ትብብርን ጨምሮ በወቅታዊ፣ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሃሳብ ልውውጥ የተደረገበት ሲሆን፣ ይህም በተግባራዊ የትብብር መስኮች ወደፊት ለመራመድና አጋርነታችንን ይበልጥ ለማጠናከር ያለንን የጋራ ፍላጎት ያንጸባረቀ ነው። 👉 ከፊንላንድ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ከዚህ በፊት በG20 ጉባኤ ወቅት ባካሄድነው የሁለትዮሽ ስብሰባችን ወቅት የተደረጉ ውይይቶችን ተግባራዊነት የተመለከተ ውይይት አድርገዋል። በዋና ዋና ዓለም አቀፍ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች፣ በቀጣናዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች እና በጋራ ፍላጎቶችን በውይይታችን የተመለከትን ሲሆን፤ ይህም ፊንላንድ ኢትዮጵያ የምትረከበውን የCOP32 ፕሬዝዳንትነት ድጋፍ ጨምሮ፣ የጋራ መግባባት የተደረሰባቸውን ዘርፎች ቀጣይነት ባለው ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት የሰጠንበት ነው። 👉 ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ፤ በአቪዬሽን ትብብርና የኢትዮጵያን የCOP32 ፕሬዝዳንትነት ለመደገፍ በሚደረገው አጋርነት ላይ መክረዋል። የጋራ ፍላጎቶችን መሠረት በማድረግ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ይበልጥ ለማስፋት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የወል ጉዳዮች ወደ ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር የሚያስችል ፍሬያማ ምክክር አድርገናል። #ClimateSummit #COP31 #COP32 #ClimateFinance #ClimateAction #Ethiopia #ActOnClimate #turkey #EthiopiaNorwayRelations
Open in TelegramPosts of Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
የወርሀ መስከረም እና ጥቅምት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት፤ የሽግግር እና የዲፕሎማሲ ወር! ✅ ዲፕሎማሲና የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረኮች ተሳትፎ አድርገዋል። በሩሲያ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በንግድ፣ ጤና እና ኃይል ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር አካሂደዋል። በ3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ ላይም ዘመናዊ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ከሩሲያ ጋር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ከቀድሞ ስምምነቶች አንጻርም ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን አሥራ ሁለት Su-35 ተዋጊ ጄቶችና አራት የS-400 የአየር መከላከያ ባትሪዎችን ተረክባለች። በመጨረሻም መደመር መጽሐፍ የሩሲያኛ ዕትም በሞስኮ በይፋ መመረቁ የሀገሪቱ የፖለቲካና የአስተዳደር ፍልስፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተደራሽነት ይበልጥ ያሰፋ ሆኗል። የመደመር መንግሥት ምሥረታን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳና የናይጄሪያውን ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማን በይፋዊ የሥራ ጉብኝት ተቀብለዋል። ከሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንም ጃይሻንካር፣ ከእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁና ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ስትራቴጂካዊ ትብብሮችን ለማጠናከር የሚያስችሉ ውጤታማ ውይይቶችን አድርገዋል። ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከርም በኬንያው የማሹጃ( የጀግኖች) ቀን አከባበር ላይ ተገኝተዋል። በባሕርዳር ከተማ በተካሄደው 12ተኛው የጣና ከፍተኛ የደህንነት ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ ከኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ኪቱሬ ኪንዲኪና ከሞዛምቢኩ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቻፖ ጋር ተወያይተዋል። በፎረሙ የመክፈቻ ንግግራቸውም አፍሪካውያን ሀገራት ውስጣዊ አቅማቸውን እንዲገነቡና በዓለም አቀፍ ሥርዓት አወንታዊ ዐሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል። ✅ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ፣ ጉብኝት እና ምረቃ ጥቅምት ወር በሀገራዊ የኢንዱስትሪ፣ የመሠረተ ልማት እና የግብርና አቅም ግንባታ ረገድ ትልቅ እመርታ የታየበት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በዓመት 600 ቶን የማጣራት አቅም ያለውን ብሔራዊ የከበሩ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መርቀዋል። በተጨማሪም ለሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የኢትዮጵያ ሚትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን እና የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንን ጎብኝተዋል። በክልሎችና በከተሞችም የልማት እንቅስቃሴዎች ተፋጥነዋል። በጎንደር 185 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ የመያዝ አቅም ያለውና ከ17 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚያለማው የመገጭ መስኖ ግድብ ተመርቋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በቆይታቸው የፋሲል ግቢንና የ«መሶብ›› ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል። በአዲስ አበባ ደግሞ 351 ሄክታር መሬት ያረፈውና 10 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የቀጨኔ አምባሳደር ጊዮን ኢሬቻ ባምቢስ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ተመርቋል። በተያያዘም የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ በሀገር ውስጥ ከነዳጅ ወደ የተፈጥሮ ጋዝ (CNG) የተቀየሩ የመጀመሪያዎቹ 26 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች በይፋ ሥራ ጀምረዋል፤ ይህም የትራንስፖርት ወጪን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስና የሕዝብ የጉዞ ታሪፍን በግማሽ የሚያቀል ነው። ✅ ማኅበራዊ ጉዳዮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመላው ኢትዮጵያውያን የኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ በዓሉ ሰላምን፣ የገዳ ሥርዓትን የሥልጣኔ መሠረቶችና የጋራ ብልጽግናን የሚያጎላ መሆኑን ገልጸዋል። “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!'” በሚል መሪ ቃል በተከበረው 19ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ላይም ሰንደቅ ዓላማው የሉዓላዊነታችን መገለጫ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። አያይዘውም የዓድዋን ታሪካዊ ቅርስ በማስታወስ ዜጎች ለሀገራዊ አንድነት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። በመጨረሻም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከኢቢሲ ጋር በትግርኛ ቋንቋ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ✅ የአስተዳደር ጉዳዮች ይህ ወር በታሪካችን ውስጥ ታላቅ ምዕራፍ የተመዘገበበት ነው፤ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መሠረት አዲሱ የመደመር መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ተመስርቷል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ _ አሕመድ የካቢኔ አባላትን ሹመት በማጽደቅና የመንግሥት ኃላፊነት የላቀ ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን በማጉላት ለሁለተኛው የሥራ ዘመናቸው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀውን የምክክር አጀንዳ ለፌደራልና ለክልል አካላት በይፋ አስረክበዋል። ይህን ታላቅ ሀገራዊ ስትራቴጂ ከግብ ለማድረስና ሁለንተናዊ ዝግጁነትን ለማጎልበት ከፍተኛ የመንግሥት አመራር አካላት በአካል ብቃት፣ በሥነ-ምግባር እና በዲሲፕሊን የሚያንጽ የወታደራዊ ሳይንስ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
Open in Telegram