Account

Posts of EthioTube

newest first

#11735Photo
Views450−71%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
5 h412
9 h450
  1. After 6 hours412
  2. Total to date450
#11732Photo
Views667−58%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11731Photo
Views1,300−17%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11730Photo
Views1,710+9%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11728Photo

ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአሜሪካን ጥብቅ መረጃዎች ለኢትዮጵያ አሳልፎ መስጠቱን አመነ ትውልደ ኢትዮጵያዊው አብርሃም ተክሉ ለማ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት የአሜሪካን ምስጢራዊ መረጃ ለኢትዮጵያ መንግሥት ለማስተላለፍ በማሴር ወንጀል በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ መሆኑን አመነ። የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሜሪላንድ የሚኖረው የ53 ዓመቱ አብርሃም ተክሉ ለማ፣ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2021 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ከፍተኛ ሚስጥራዊነት ያላቸውን የአሜሪካ መረጃዎች ለኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ለማስተላለፍ በተደረገ ሴራ ውስጥ መሳተፉን አምኗል። አብርሃም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳዳሪነት የነበረውን የይለፍ ፈቃድ በመጠቀም፣ ደህንነቱ ከተጠበቀ ተቋም ውስጥ ከፍተኛ ምስጢራዊ መረጃን ጨምሮ የብሔራዊ መከላከያ መረጃን በሕገወጥ መንገድ በማውጣት ለኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣኖች አስተላልፏል" ሲሉ አቅቤ ሕጉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም አብርሃም ላይ ስለቀረበው ክስ ምንም ያለው ነገር የለም።የፍትህ መስሪያ ቤት እንደገለጸው፣ በቀረቡ የግንኙነት ሰነዶች ውስጥ አብርሃም ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር በጦርነት ላይ በነበሩ ታጣቂ ቡድኖች ላይ እርምጃ እንዲወስዱ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ሲያበረታታ እንደነበር ያመለክታሉ። አብርሃም ታህሳስ 9/2014 ዓ.ም. ለአንድ ተባባሪው ባስተላለፈው መልዕክት "እነዚህን ሰዎች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ማጥፋት አለብን። አለበለዚያ በኢትዮጵያ መቼም ሰላም አይኖርም" ሲል መጻፉ በፍትህ ሚኒስቴር መግለጫ ላይ ተካትቷል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል። #Ethiopia #EthiopianAmerican #AbrahamTekluLemma

Open in Telegram
Views2,570+64%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11727Photo
Views1,750+11%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11725Photo

አንጋፋው ሪፖርተር ጋዜጣ ታገደ ሪፖርተር ጋዜጣ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታወቀ። በ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሴንተር ኃ.የተ.የግል ማህበር ስር በሚታተሙ ሪፖርተር አማርኛ፣ ዘ ሪፖርተር እግሊዝኛ እንዲሁም ኢትዮጵያን ሪፖርተር የዲጂታል ፕላትፎርም ላይ የሚሰራጩ ይዘቶች ላይ ከአንድ ዓመት በላይ በተደረገው የይዘት ክትትል ተደጋጋሚ የህግና የሙያ ስነ ምግባር ጥሰቶች በሚዲያው መፈጸሙ ተረጋግጧል ሲል ባለሥልጣኑ አስታውቋል። በሀገር ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አውድ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ያላቸውን ርዕሰ ጉዳዮች በማንሳት ከሚሰጣቸው አርዕስት/Headline/ ጀምሮ ማጮህ /Sensationalize/፣ በተለያዩ መድረኮችና ሪፖርቶች ላይ የሚገኙ ሀገራዊ መረጃዎችን አጠቃላይ አውዱን ተገንዝቦ መረጃን ከማድረስ ይልቅ በቁንጽል እይታ ላይ በመዘገብ በህብረተሰቡ ዘንድ ጥርጣሬና ብዥታን መፍጠር፣ የውጭ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝምና ዲፕሎማሲ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨት፣ የሀገር ገጽታን የሚያጠለሹ፣ የሀገርን ብሄራዊ ደህንነትን የሚጎዱ፣ የህዝቦችን አብሮነትና እሴት የሚሸረሽሩ መረጃዎች ማሰራጨት፣ ሚዛናዊነት የጎደለው አድሏዊ ዘገባዎችን ማሰራጨት፣ ከራስ ጥቅምና የግል ፍላጎት በመነሳት ባልተረጋገጠ መረጃ የተቋማትን ስምና ገጽታ ማጠልሸት የሚሉ ክሶች በጋዜጣው ላይ ቀርበዋል። በዚህ ምክንያት የህግና የሙያ ስነ ምግባር ግዴታዎችን ተሟልተዉ ተግባራዊ እስኪደረጉ ድረስ የምዝገባ ምስክር ወረቀቱ ከሰኞ ጥቅምት 23/2019 ዓ/ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከህትመትና ከስርጭት ሙሉ በሙሉ ታግዶ እንዲቆይ ተወስኗል ሲል በመግለጫው አስፍሯል። #Ethiopia #EthiopianReporter #EthiopianPress #PressFreedom

Open in Telegram
Views1,710+9%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11722Photo
Views1,490−5%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11721Photo

“የሕዝብ መናቅ፣ የሕዝብ አለመከበር፣ የሕዝቡ ፍትሕ ማጣት፣ ባመናቸው ሰዎች መካዱ በጣም ያሳስበኛል” ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል በራሱ የዩቲዩብ ቻና የኮሜዲ ሥራዎችን እያቀረበ የሚገኘው ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ጉዳዮች እንደሚያሳስቡት ገልጿል። "ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማንሳት የአንድ ኪነጥበብ ውስጥ ያለ ሰው ኃላፊነት ነው ብዬ አምናለሁ የሚለው ምናለ፣ በሥራዎቹ ያሳስቡኛል የሚላቸውን ጉዳዮች እንደሚያነሳ፣ በሳቅ የተዋዛ መልዕክት እንደሚያስተላልፍ ተናግሯል። ሳተየር ዘውግ ያለው የኮሜዲ ሥራው በሀገሪቱ የሚከናወኑ ጉዳዮችን እያነሳ ሳቅ እንደሚፈጥር ገልጿል። ኮሜዲያን ምናለ በነበረው ቃለ መጠይቅ "እንደ ዜጋም ሆነ እንደ አንድ ኪነጥበብ ውስጥ እንዳለ ሰው ፖለቲካው ውስጥ ባሉ ሰዎች የሕዝብ መናቅ በጣም ያሳስበኛል፤ የሕዝብ አለመከበር፣ የሕዝቡ ፍትሕ ማጣት ያሳስበኛል ብሏል። አክሎም ሕዝቡ “ባመናቸው ሰዎች መካዱ በጣም ያሳስበኛል፤ ማንነት ተኮር ጥቃቶች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ መቆሚያ ያጡ ጦርነቶች እነዚህ ሁሉ የሚደረጉ ነገሮች ሁሉ በጣም ያሳስበኛል" በማለት ስሜቱን አጋርቷል። "እንደ አንድ ግለሰብ [ለሚያሳስቡኝ ጉዳዮች] መፍትሔ ብሰጠው ደስ ይለኛል። ብችል እነዚህን ነገሮች ማቆም መከልከል ብችል ደስ ይለኛል። ያንን ነገር ለማድረግ ግን አቅሙ የለኝም። አቅሜ ምንድን ነው? በጉዳዩ ላይ ማውራት ወይ ማፌዝ ነው። እንደ ሳታየር ኮሜዲ ፊት ላይ ሳቅ መፍጠር አእምሮ ላይ ደግሞ መልዕክት ማስቀመጥ ነው ሃሳቤ” ሲል የኮሜዲ ሥራውን ዓላማ አስረድቷል። ለተመልካች በሚያቀርባቸው የኮሜዲ ሥራዎች ሳቢያ "የሆኑ ነገሮች ሊመጡ እንደሚችሉ እረዳለሁ ወደፊት የሆኑ ችግር ሊያመጡብኝ እንደሚችሉ ይገባኛል" ሲል ስጋቱን አጋርቷል #Ethiopia #MinaleYaregal

Open in Telegram
Views1,330−15%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11720Photo

ህወሓት ጀነራል ጆን መዲድ “ክህደት መጽመዋል” አለ የቀድሞው የፌደራል መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንን እና የትግራይ ኃይሎች ደቡባዊ ግንባር አዛዥ የሆኑት ሜጀር ጄነራል ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ (ጆን መዲድ) ለኢትዮጵያ መንግሥት “እጅ መስጠታቸው” ከተሰማ በኋላ ህወሓት ጄነራሉን “በከሃዲነት” ፈርጇል። ጄነራል ጆን መዲድ በትግራይ መንግሥት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም ኃላፊነታቸውን በሚገባ አለመወጣታቸውን ህወሓት በመግለጫው አሳውቋል። በዚህ ሳቢያ ከማዕከላዊ ኮማንድ ተነጥለው እንዲቆዩ መደረጉንም መግለጫው ይጠቅሳል። በዚህ ቆይታቸው ጄነራሉ “ከጠላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ተቀላቅለዋል” ሲል ህወሓት ገልጿል። ሜጀር ጄነራል ዮሐንስ በተያዙበት ጊዜ የደኅንነት ጠባቂዎቻቸው፣ የኮሎኔል ማዕረግ ያላቸው ሰባት አዛዦች እና ሌሎች በርካታ መኮንኖች ከእርሳቸው ጋር እንደነበሩ ቢቢሲ ዘግቧል። "ጆን መዲድ" በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት ሜጀር ጄነራል ዮሐንስ፣ በትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ መዋቅር ውስጥ ከሚገኙ ከፍተኛ የጦር አመራሮች መካከል አንዱ ነበሩ። #Ethiopia #Tigray #TPLF #GeneralYohannis #JohnMedid

Open in Telegram
Views2,100+34%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11719Photo

በአርሲ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 60 ደረሰ - የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በኦሮሚያ ክልል አርሲ በሚገኙ ወረዳዎች በተለያየ ቀን በደረሰው ጥቃት 60 ምዕመን መገደላቸውን በመግለጽ ጥቃቱን “በጽኑ እንደሚያወግዝ” አስታውቋል። በሸርካ ወረዳ 46 እና በመርቲ ወረዳ 14 ምዕመናን “ግፍ በተሞላበት ጭካኔ” መገደላቸውን አረጋጧል። የ 20 ምዕመናን መኖሪያ ቤት ሙሉ ለሙሉ እንደወደመ እና 20 ሰዎች ደግሞ በጥቃቱ ተጎድተው ሕክምና ላይ መሆናቸው ተመላክቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ ፤ በአርሲ አገረ ስብከት እና በሌሎችም አካባቢዎች “ኦርቶዶክሳውያን ንጹኃን ልጆቻችን ላይ የሚፈጸመው እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ተከታታይነት ባለው ሁኔታ፣ ያለማቋረጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ” መጥቷል ብሏል። “በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን በሕይወት የመኖርና በነጻነት የማምለክ መብትን እንዲያስከብሩልን” ሲል ጠይቋል። ድርጊቱን የፈጸሙትን “ወንጀለኞች ለሕግ በማቅረብ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ እንዲህ ዓይነቱ አረመኔያዊ ተግባር ከእንግዲህ በኋላ እንዳይደገም አስፈላጊውን የሕግ ከለላ” እንዲሰጥ ሲኖዶሱ አሳስቧል። የኦሮሚያ ክልል በበኩሉ በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ “ጽምዶ” በሚል ጥምረት የፈጠሩ ኃይሎች እንደፈጸሙት ገልጿል። #Ethiopia #EOTC #Arsi #Oromia #EthiopianOrthodox

Open in Telegram
Views1,920+22%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11718Photo

በምሥራቅ አርሲ ዞን በርካታ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መገደላቸው ተገለጸ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሸርካ ወረዳ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ላይ “ከፍተኛ ጥቃት መድረሱን” ቤተክርስቲያኗ አስታውቃለች። በአካባቢው እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ተባብሶ በመቀጠሉ እስካሁን ድረስ የደረሰው የሞት አደጋ በውል መታወቅ እንዳልቻለ ቢገለጸም የሟቾች ቁጥር ከ 40 በላይ እንደሆነ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገው ትላንት ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ከማለዳ ጀምሮ በወረዳው በሚገኙት ጠሬታ፣ ቢርቦና ጮሌ እና ሶሌ ዲገሉ በተባሉ ቀበሌዎች ከፍተኛ ጥቃትና ግድያ ተፈጽሟል። ጥቃቱ ድንገተኛ ብቻ ሳይሆን ስልታዊ በሆነ መልኩ በኦርቶዶክሳውያን እና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል ሲልም አመልክቷል። የምሥራቅ አርሲ ዞን ሸርካ ወረዳ ከ2016 ዓ.ም. ጀምሮ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሲፈጸሙ እንደቆዩ ዘገባው አስታውሷል። #Ethiopia #EOTC #EthiopianOrthodox #Arsi #Oromia

Open in Telegram
Views2,010+28%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11717Photo

ሱዳን የትግራይ ተዋጊ ኃይሎችን ድሮን ማስታጠቋን አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ በቀድሞ ጦርነት ወቅት “ግብጽ 500 መቶ ሺህ ዶላር ሰጥታናለች” የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ተዋጊ ኃይሎች ከሱዳን የተላከ ድሮን ታጥቀው እንደነበር ገልጸዋል። ሆኖም የድሮን አጠቃቀሙን “በደንብ ስላልተለማመዱ ብዙ[ድሮን] እንደታሸገ ነው የተያዘው” ብለዋል። አቶ ጌታቸው አክለውም በፕሪቶሪያ ስምምነት በተቋጨው ጦርነት ወቅት አባል የነበሩበት ህወሓት ከግብጽ የ 5 00 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ጠይቆ እንደነበር ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ይህ ገንዘብ ብዙ በመሆኑ 500 ሺህ ዶላር ተሰጥቶናል ብለዋል። አቶ ጌታቸው፤ በአሁን ወቅት መከላከያ ሰራዊት ከኤርትራ ድንበር በአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ “አዲ ፍታው” የተባለች ቦታ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ በሚገኙ አካባቢዎች ግጭት ቢፈጠር “የኤርትራ ምሽግ የመሰበር እድሉ ሰፊ ነው። ምሽጉ ከተሰበረ በኋላ አስመራ ለመግባት የሚወስድ በጣም አጭር ጊዜ ነው” ብለዋል። #Ethiopia #GetachewReda #Tigray #Sudan #TPLF

Open in Telegram
Views1,850+18%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#11716Photo

ባለቤቱንና የአንድ ዓመት ሕፃን ልጁን በ25 ጥይቶች የገደለው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ ​በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ፍኖተ ሰላም ከተማ ባለቤቱንና የአንድ ዓመት ሕፃን ልጁን በጥይት በመግደል የተከሰሰ ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ። ​የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር አለህኝ አለባቸው እንደገለጹት፤ ወንጀሉ የተፈጸመው ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 ልዩ ስሙ ሰፈር 3 በተባለ አካባቢ ነው። ተከሳሹ ይናገር ደመላሽ ሁነኛው፣ "በውሃ ቅዳ" እና "ልብስ እጠቢ" በሚል ጉዳይ በተፈጠረ አለመግባባት ተነሥቶ በእጁ በነበረ ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ 25 ጥይቶችን በመተኮስ ባለቤቱንና በእቅፏ የነበረውን የአንድ ዓመት ሕፃን ልጃቸውን በግፍ ገድሏል። ግለሰቡ ከዚህ አሰቃቂ ድርጊቱ በፊትም በባለቤቱ ላይ ተደጋጋሚ ድብደባና ጥቃት ያደርስ እንደነበር በምርመራ መረጋገጡን ኃላፊው አክለው አብራርተዋል። ​ወንጀሉ ከተፈጸመ በኋላ ፖሊስ ተከሳሹን ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር በማዋል፣ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አደራጅቶ መዝገቡን ለዞኑ ፍትህ መምሪያ ማስተላለፉን ምክትል ኮማንደር አለህኝ ጠቁመዋል። የፍትህ መምሪያው ዐቃቤ ሕግም የምርመራ መዝገቡን ከመረመረ በኋላ፣ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 539(1)(ሀ) መሠረት በከባድ ሰው ግድያ ወንጀል ሁለት ክሶችን በመመሥረት ጉዳዩን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። በችሎት ሂደትም ተከሳሹ የተከሰሰበትን ድርጊት ቢክድም፣ ዐቃቤ ሕግ ባቀረባቸው ማስረጃዎች ወንጀሉን መፈጸሙ በማያወላዳ ሁኔታ በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ አሳልፎበታል።

Open in Telegram
Views1,780+13%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—