Posts of "ኡማ ቲቪ " Tv
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 331 |
| 3 h | 1,730 |
- After 1 hour331
- Total to date1,730
እንዴት ደስ የሚል ነገር እናንተዬ? رجال الفجر የተሰኘው ንቅናቄ ልቤን እንዴት እንዳሞቀው ልነግራችሁ አልችልም። መልካም ነገር መኮረጅ ብልህነት ነውና ብንኮርጀውስ? በየመስጅዱ ያላቹህ ወጣቶች አከባቢውን አጀንዳ በማድረግ እንቅስቃሴ ይደረግ ?
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 721 |
| 4 h | 1,850 |
- After 1 hour721
- Total to date1,850
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 2 h | 1,540 |
| 5 h | 2,340 |
- After 6 hours2,340
- Total to date2,340
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 4 h | 1,910 |
| 7 h | 2,530 |
- After 6 hours2,530
- Total to date2,530
በአልጄሪያ የተጀመረው የፈጅር ሰላት ቻሌንጅ ወደ ተለያዩ ሙስሊም ሀገራት በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። «የፈጅር ወንዶች» የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ቻሌንጅ ከተጀመረ 10 ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ በሙስሊም ሀገራት ሰፊ ተቀባይነትን አግኝቷል። ቻሌንጁ ዕድሜያቸው ከ8 ዓመት በላይ የሆኑ ሕፃናትን ለፈጅር ሰላት በመቀስቀስ ወደ መስጅድ ይዞ የመሄድ ሲሆን፣ መነሻውን በ6 ሕፃናት ቢያደርግም አሁን ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችና ሕፃናት ተቀላቅለውታል። የፈጅር ወንዶች ቻሌንጅ በሀገራችን ኢትዮጵያም ለመተግበር እንቅስቃሴ ተጀምሯል። የቻሌንጁ ተሳታፊዎች ወደ መስጊድ ሲሄዱና ሲመለሱ የተቀረጸ ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋራሉ።
Open in Telegramዛሬ በጣም ደስ ያለኝ ቀን ነው በቅርበት የማቀው አንድ ዛሂድ ኡስታዜ አለ በቃ ብዙ ነገር አብረን አሳልፈናል ። ታላቅ ወንድም ጭምር በሉት ብዙ ጊዜ ይመክረኛል አንዳንድ ጉዳዬች ላይ ከፊት ሁኖ አቅጣጫ ያሳየኛል ልጅ እያለሁ እሱን ለመሆን ከምመኛቸው ሰወች መሀል ነበር ። በህይወቴ ላይ ትልቅ አሻራ ትቶል 🤲 ወደ ጉዳዩ ስገባ ለረጂም ጊዜ አብረን የነየትነውን የኡምራ ጉዞ የአላህ ፍቃድ ሁኖ ኡስታዜ ቀድሞ ተጠርቶ ዛሬ ለሊት ወደ አላህ ቤት እንደሚሄድ አበሰረኝ ። አልሀምዱሊላህ የወንድም ሀጃ የራስ ሀጃ ነው እንኳንም ተሳካልህ ለአላህ የነገርከው ሁሉ ደግመህ ቤቱ ተጠርተሀልና አሳምረህ ለምን ይህንን የኡምራ ጉዞ ከመቼ ጀምሮ እየጠበከሰ እንደነበር ስለማቅ በማሳካቱ በጣም ደስ ብሎኛል አላህ የተሳካ የኡምራ ጉዞ ይሁንልህ ሀቢቢ 🤲 እናላቹህ በቃ የቅርብ ሰው የኡምራ እድል ተሳክቶለት ማየት የተለየ ስሜት አለው በተለይ ብዙ ችግሮችን ላየ ኡስታዝ 🤲 ተራው የኛ እንዲሆን በዱዓቹህ አንረሳሳ ኸልቁ ሁሉ እየተጎዘ ነው አላህ ይጥራን አቦ
Open in Telegram#ሱብሃን_አላህ ከሁለት ሳምንት በፊት ድሃና በዕዳ የተዘፈቀው ሰው፣ በአጭር ጊዜ ሀብታም ሆነ! በአላህ ላይ ያለንን እምነት የሚያጠናክር፣ ከችግር በኋላ መፍትሔ እንደሚመጣና አላህ ከማንጠብቀው አቅጣጫ ሲሳይን እንደሚሰጥ የሚያስታውስ #አስደናቂ_ታሪክ! በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ከጁመአ ሶላት በኋላ በአንድ መስጂድ ውስጥ የተነገረ ልብ የሚነካ ታሪክ ነው። ታሪኩን የተረከው አንድ የመስጂድ ኢማም ሲሆን፣ ከኢማምነቱ በተጨማሪ የአንድ ሃብታም ሸይኽ ሥራዎችን በአደራ ይከታተል ነበር። #ኢማሙ እንዲህ ይላሉ፦ ብዙውን ጊዜ በቢሮ የሥራ ጫና ምክንያት የዙህርን ሶላት በመስጂድ አልሰግድም ነበር። ግን በዚያ ቀን አላህ በመስጂድ እንድሰግድ አደረገኝ። ሶላት ከጨረስን በኋላ አንድ ሰው ወደ እኔ መጣ። ወደ 1,200 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ርቀት ተጉዞ የመጣ ሲሆን፣ ጉዳይ ለማስፈፅምለት ሸይኹ የሚያቀርበውን የእርዳታ ጥያቄ ይዞ ነበር። ሰውየው ከ200,000 እስከ 230,000 ሪያል የሚደርስ ዕዳ ነበረበት። ወሩ ሲያበቃም በዕዳው ምክንያት ወደ እስር ቤት እንዳይገባ ይፈራ ነበር። ቤተሰብና ልጆችም ነበሩት፤ ከእሱ እርዳታን ይጠብቁ ነበር። አብሽር ብዬ ምሳ እንዲበላ ወደ ቤቴ ወሰድኩት። ምሳ ከጨረስን በኋላም እንዲህ አልኩት፦ «ከዚህ ሸይኽ የበለጠ ሀብታምና ቸር ወደሆነ አካል ብመራህ ምን ትላለህ?» #ሰውየውም፦ «#ማን_ነው?» ብሎ ጠየቀኝ። እኔም፦ «#አላህ_ሱብሓነሁ_ወተዓላ ነው!» አልኩት። ከዚያም ከልቡ ወደ አላህ እንዲመለስ፣ አላህን እንዲያመሰግንና እንዲያወድስ፣ በሌሊት የመጨረሻው ሰአታት እንዲነሳ፣ አላህን እንዲለምን መከርኩት። እንዲሁም ሀብትን፣ ኃይልንና ክብርን ከአላህ እንዲጠይቅና ኢስቲግፋርን እንዲያበዛ ነገርኩት። እዚህ ላይ የሚያስደንቅ ነገር ተፈጠረ! ሰውየው ይዞት የመጣውን የእርዳታ ደብዳቤ አነሳና በኢማሙ ፊት #ቀደደው። ከዚያም በሙሉ እምነት፦ «#በአላህ_ላይ_ተመካን!» አለ። ከዚያም ወደ አሮጌ መኪናው ገብቶ ጉዞውን ጀመረ። ከሁለት ሳምንት በኋላ ግን ለኢማሙ በታላቅ ደስታ ላይ ሆኖ ደወለላቸው። #መልካም_ዜና_ልነግርህ_ነው፣ #አላህ_ሰጠኝ! #ታላቁ_ጌታ! #ካልጠበኩት_ቦታ_ረዘቀኝ» አለ። አንድ በመንደሩ የሚገኝ የእሱ መሬት ጉዳይ ለሽያጭ እንደቀረበ። በዚያም መሬት ላይ ወደ 3 ሚሊዮን ሪያል የሚገመት ፕሮጀክት ሊጀመር መሆኑን ነገረኝ። ከአንድ ወር በኋላም ወደ መስጂዱ ሶላት ለመስገድ ተመለሰ። ሁኔታው ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል፤ አዲስ መኪና ገዝቶ መጣ። መኪናውም አዲስነቱን የሚያሳዩ የወንበሮቹ መጠቅለያዎቹ ገና አልተነሱም ነበር #ሱብሃን_አላህ! የሰውን ሁኔታ ከአንድ ሁኔታ ወደ ሌላ የሚቀይር አላህ ምንኛ ታላቅ ነው! #وَمَن_يَتَوَكَّلْ_عَلَى_اللَّهِ_فَهُوَ_حَسْبُهُ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ ▼▼▼አንዳንድ ጊዜ ዱንያ ትጠብበናለች፤ ዕዳ ያስጨንቀናል፤ በፊታችን ያሉ በሮች ሁሉ የተዘጉ ይመስሉናል። ግን የአላህ በር ፈጽሞ አይዘጋም። እዝነቱ ከጭንቀታችን ሁሉ የሰፋ ነው፤ የእርሱ ግምጃ ቤትም ፈጽሞ አያልቅም። የሌሊቱን የመጨረሻ ጊዜያት አትዘናጉ። ይህ ዱዓ፣ ልመናናችን ይዘን ከጌታችን ጋር የምንገናኝበት ውድ ጊዜ ነው። ያ አላህ ! የተጨነቀውን ሁሉ ጭንቀቱን አስወግድለት። ዕዳ ያለበትን ዕዳ ክፈልለት። የተቸገረውን ከሰፊው ችሮታህ ለግሰው። ከእያንዳንዱ ችግር መውጫን፣ ከእያንዳንዱ ጭንቀትም ገላግለው። አሚን #ኢስቲግፋር #ዱዓ #የሌሊት_ሶላት #ተወኩል #የአላህ_እዝነት #ከጭንቀት_መገላገል
Open in Telegram📚 الدورة العلمية الأولى يسرنا الإعلان عن دورة شرح كتاب التبيان في آداب حملة القرآن للإمام النووي رحمه الله، ضمن مسار الآداب والأخلاق في المركز العلمي لتعليم الكتاب والسنة وتدريس علومهما، في مركز ابن مسعود الإسلامي بحي ١٨، أديس أبابا. 🎙️ الشارح: فضيلة الشيخ إلياس أحمد 🗓️ الأيام: من الأربعاء إلى الجمعة 🕘 الوقت: من الساعة التاسعة صباحًا حتى الحادية عشرة صباحًا، باستثناء يوم الجمعة، حيث يُعقد الدرس عقب صلاة العصر. نسأل الله أن يجعلها دورة نافعة مباركة، وأن يرزقنا وإياكم العلم النافع والعمل الصالح. ____ 🕌 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
Open in Telegram🚨 ይህ ዕድል እንዳያመልጥዎ! 🔥 በእያንዳንዱ ክፍል 10 ተማሪዎችብቻ! 📌 ቦታዎን ከሌሎች በፊት ያስይዙ! ⏳ ነገ አይበሉ፤ ዛሬውኑ ይወስኑ! 📩 ለመመዝገብ አሁኑኑ Inbox ያድርጉን! ━━━━━━━━━━━━━━━━ 🚀 አዲስ ክህሎት ይማሩ፤ አዲስ የወደፊት እድል ይፍጠሩ! MIT በተግባር ላይ ያተኮሩ ለትምህርት፣ ለሥራ፣ ለንግድ እና ለግል እድገት የሚያግዙ የሙያ ስልጠናዎችን ያቀርባል። 📚 የምንሰጣቸው ስልጠናዎች 1️⃣ Graphic Design (ግራፊክ ዲዛይን) 2️⃣ Front-End Web Development 3️⃣ Back-End Web Development 4️⃣ Cybersecurity & Artificial Intelligence (AI) 5️⃣ English Language (እንግሊዝኛ) 6️⃣ Arabic Language (አረብኛ) 7️⃣ Python & C++ Programming 8️⃣ Digital Marketing (ዲጂታል ማርኬቲንግ) 9️⃣ Video Editing (ቪዲዮ ኤዲቲንግ) ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 💻 የስልጠና አማራጮች ስልጠናዎቻችንን በሁለቱም Online (በኢንተርኔት) እና In-Person (በአካል) መከታተል ይችላሉ። ለእርስዎ የሚመችዎትን ይምረጡ! 💳 የመመዝገቢያ ክፍያ፦ 500 ብር ብቻ 📍 አድራሻ፦ ቤቴል፣ ሶልፋም ሞል፣ 2ኛ ፎቅ። 🔑 VIP CLASS ይገኛል! Phone: +25196746 0676 Telegram: @meridian_facilitator ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🚨 ይህ ዕድል እንዳያመልጥዎ! በእያንዳንዱ ክፍል 10 ተማሪዎች ብቻ! MERIDIAN INSTITUTE OF TECHNOLOGY (MIT)
Open in Telegramየመጀመሪያው ፓኪስታናዊ የጠፈር ተመራማሪ ከቻይና ጋር በመሆን ወደ ሕዋ ተጓዘ! • ሀሩን ሚዲያ | ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ል ቻይና ሦስት የጠፈር ተመራማሪዎችን የያዘውን የጠፈር መንኮራኩር ማምጠቋንና በዚህም የ40 ዓመቱ ፓኪስታናዊ የጦር አውሮፕላን አብራሪ ሙሐመድ ዚሻን ዓሊይ ወደ ሕዋ በመጓዝ የመጀመሪያው ፓኪስታናዊ የጠፈር ተመራማሪ መሆኑን አናዶሉ ዘግቧል። መንኮራኩሩ በሰሜን ምዕራብ ቻይና ከሚገኘው የጂዩኳን የሳተላይት ማምጠቂያ ማዕከል መነሳቱን የቻይና የጠፈር ኤጀንሲ ያስታወቀ ሲሆን፣ ሙሐመድ ዚሻን ዓሊይ የቻይናውን የቲያንጎንግ የጠፈር ጣቢያን የጎበኘ የመጀመሪያው የውጭ ሀገር ዜጋ መሆኑም ተመላክቷል። ፓኪስታናዊው የጠፈር ተመራማሪ ከቻይናዊው አዛዥ ታንግ ሆንግቦ እና ከበረራ መሐንዲሱ ው ዪ ጋር በመሆን በጠፈር ጣቢያው ውስጥ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደሚቆይና ቡድኑ ወደ 90 የሚጠጉ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ካከናወነ በኋላ ወደ ምድር እንደሚመለስ ተገልጿል።
Open in Telegramበሚቀጥሉት ቀናት ጋዛን ይመታል የተባለው ከባድ አውሎ ንፋስ በ1.7 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን ላይ ትልቅ ስጋት መደቀኑ ተገለጸ በመጪዎቹ ቀናት የጋዛ ሰርጥን ይመታል የተባለው ከባድ አውሎ ንፋስና ዝናብ በድንኳን ውስጥ የተጠለሉ ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃይ ፍልስጤማውያንን ሕይወት ለከፋ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል የጋዛ መንግሥት ሚዲያ ጽሕፈት ቤት አስጠንቅቋል። የጽሕፈት ቤቱ ዳይሬክተር እስማኤል አል-ታዋብታ የአደጋውን ክብደት በመጥቀስ፣ ቤተሰቦች ለዚህ ስጋት ሲጋለጡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዝምታን መርጧል ሲሉ ወቅሰዋል። በጦርነቱ ምክንያት መኖሪያ ቤቶችና መሠረተ ልማቶች በመውደማቸው፣ ብዙ ተፈናቃዮች ከዝናብና ከብርድ መከላከል በማይችሉ ያረጁ ድንኳኖች እንዲሁም ለመደርመስ በተቃረቡ ሕንፃዎች ውስጥ ለመኖር መገደዳቸው ተመላክቷል። የጋዛ ሲቪል መከላከያ ቃል አቀባይ ማህሙድ ባዛል በበኩላቸው፣ ከባዱ ዝናብ ድንኳኖችን በጎርፍ ሊያጥለቀልቅ እንደሚችልና ኃይለኛ ነፋስም ተጨማሪ ስጋት መፍጠሩን ገልጸዋል። የአየር ሙቀቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ በመምጣቱና ቤተሰቦች ድንኳኖቻቸውን የሚያሞቁበት ምንም ዓይነት መንገድ ባለመኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት በብርድ ምክንያት ሕይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። ባለፈው ጥቅምት 27 የተከሰተው አውሎ ንፋስ 70 ሺህ ድንኳኖችን በጎርፍ ማጥለቅለቁን ያስታወሱት ቃል አቀባዩ፣ ለሕፃናት፣ ለሕሙማንና ለአረጋውያን አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 24 h | 3,820 |
| 26 h | 3,930 |
- After 24 hours3,820
- Total to date3,930
የሚያንማር የዘር ማጥፋት ውሳኔ ለእስራኤል የጋዛ ክስ ከፍተኛ የሕግ አንድምታ እንዳለው ተገለጸ! • ሀሩን ሚዲያ | ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ል ዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ሚያንማር በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሟን በማረጋገጥ የሰጠው ውሳኔ፣ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ በጋዛ ጉዳይ ባቀረበችው የዘር ማጥፋት ክስ ላይ ከፍተኛ የሕግ አንድምታ እንደሚኖረው የምዕራብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሜላኒ ኦብራየን በዩኒቨርሲቲው በወጣ ትንታኔ አመላክተዋል። በሚያንማር ክስ ላይ ፍርድ ቤቱ «የዘር ማጥፋት ዓላማን» ለማረጋገጥ የባለሥልጣናትን የጥላቻ ንግግርና የወታደራዊ ኃይሎችን የተግባር ሂደት በማስረጃነት መውሰዱን ፕሮፌሰሯ ገልጸዋል። ሚያንማር ዘመቻውን «የሽብርተኝነት መከላከል» በሚል ብታቀርብም፣ ፍርድ ቤቱ ሲቪሎችን መግደል፣ ሕፃናትን ማጥቃትና መንደሮችን ማውደም ሕጋዊ ወታደራዊ ተግባር አለመሆኑን በመወሰን ከፀረ-ሽብር ዘመቻ ጎን ለጎን የዘር ማጥፋት ዓላማ ሊኖር እንደሚችል ማረጋገጡ ተመላክቷል። በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በሚያንማር ከ2,000 በታች የሆኑ ሕፃናት መገደላቸውን የዘር ማጥፋት ዓላማ መገለጫ አድርጎ መውሰዱን የጠቀሱት ኦብራየን፣ በጋዛ ወደ 22,000 የሚጠጉ ሕፃናት መገደላቸውን መረጃ እንደሚያሳይ በመጥቀስ ይህ ሁኔታ በእስራኤል ላይ የቀረበውን ክስ በእጅጉ እንደሚያጠናክር አስታውቀዋል። 📅 ጁማደል ሳኒ 14 ቀን 1448 ዓ.ሂ © ሀሩን ሚዲያ
Open in Telegramየወደፊት ስኬትዎን ዛሬ ይጀምሩ! MERIDIAN INSTITUTE OF TECHNOLOGY (MIT) ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ! በባለሙያ አሰልጣኞች ተፈላጊ የሥራ ገበያ ክህሎቶችን ይማሩ! በአንድ ክላስ 10 ተማሪዎች ብቻ! 📚 የምንሰጣቸው ስልጠናዎች፦ 1️⃣ Web Development HTML, CSS, JavaScript, PHP በመጠቀም ዘመናዊ ድረ-ገጾችን መገንባት ይማሩ። 2️⃣ Programming Python, Java እና C++ በመማር የፕሮግራሚንግ ክህሎትዎን ያሳድጉ። 3️⃣ Graphics Design ሎጎ፣ ብራንዲንግ፣ ፎቶ ኤዲቲንግ እና ዲጂታል ዲዛይን ይማሩ። 4️⃣ Digital Marketing ማህበራዊ ሚዲያ፣ የይዘት ፈጠራ፣ SEO እና የዲጂታል ማርኬቲንግ ስልቶችን ይማሩ። 5️⃣ Cyber Security & AI የዲጂታል ደህንነት፣ የመረጃ ጥበቃ፣ የሳይበር ጥቃት መከላከል እና AI አጠቃቀም ይማሩ። 6️⃣ English & Arabic Language የሰዋሰው፣ የቃላት እና የንግግር ክህሎትዎን ያሳድጉ። ለምን MERIDIAN INSTITUTE OF TECHNOLOGY? ✅ በአንድ ክላስ 10 ተማሪዎች ብቻ! ✅ በአካል እና በኦንላይን ✅ በተግባር ላይ ያተኮረ ስልጠና ✅ ጥራት ያለው ትምህርት 🔑 VIP CLASS ይገኛል! አድራሻ : ቤቴል፣ ሶልፋም ሞል፣ 2ኛ ፎቅ - አዲስ አበባ Phone: 096 746 0676 Telegram: @meridian_facilitator 🚀 እድልዎን በእውቀትና በክህሎት ይፍጠሩ! MERIDIAN INSTITUTE OF TECHNOLOGY Learn Today. Lead Tomorrow.
Open in Telegramተሰናባቹ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ያለ አዲሱ መንግሥት ይሁንታ በኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት እንዳይፈጽሙ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው በእስራኤል አዲስ መንግሥት እንዲመሠርቱ ኃላፊነት የተሰጣቸው ጋዲ አይዘንኮት፣ በአሁኑ ወቅት አዲስ መንግሥት ከመቋቋሙ በፊት ወታደራዊ እርምጃ የሚያስፈልገው ቀጥተኛና አፋጣኝ የኢራን ስጋት አለመኖሩን አስታውቀዋል። የእስራኤል ፓርላማ (ክኔሴት) የውጭ ጉዳይና መከላከያ ኮሚቴ አዲሱ ሰብሳቢ አቪግዶር ሊበርማን በበኩላቸው፣ ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በራሳቸው ውሳኔ በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈጸም ትዕዛዝ ቢሰጡ "በግልጽ ሕገ-ወጥ ትዕዛዝ" እንደሚሆንና ተቀባይነት እንደሌለው አስጠንቅቀዋል። አይዘንኮት ከኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲ ጋር የጥምር መንግሥት ለመመሥረት የሚደረገው ድርድር የሀገሪቱን ዲሞክራሲ በመጠበቅና ብሔራዊ የምርመራ ኮሚሽን በማቋቋም መርህ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጸዋል። ድርድሩ ሳይሳካ ከቀረ ግን የአይዘንኮት 'ያሻር' ፓርቲ እስከ ታኅሣሥ 6 ባለው ጊዜ ውስጥ 19 መቀመጫዎች ባሏቸው የአረብ ፓርቲዎች (ጆይንት ሊስት እና ዩናይትድ አረብ ሊስት) የውጭ ድጋፍ የሚታገዝ የአናሳዎች መንግሥት ለማቋቋም መታቀዱ ተመላክቷል። በጋዛ በፈጸሙት የጦር ወንጀልና በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ምክንያት ከ2024 ጀምሮ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) የእስር ማዘዣ የወጣባቸውና በሙስና ክስ ላይ የሚገኙት ኔታንያሁ በበኩላቸው፣ "ስጋቶችን አሳንሰው የሚያዩ አካላት ለፖለቲካዊ ዓላማ የሚያደርጉት ነው" በማለት በቀጣናው ወታደራዊ ውጥረቱ እንዲቀጥል ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ ምላሽ ሰጥተዋል።
Open in Telegramከሰው ልጅ አዕምሮ የሚበልጥ ሱፐር ኢንተለጀንስ እየመጣ መሆኑን የሜታ ዋና የኤአይ ኃላፊ አስታወቁ የሜታ ዋና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኃላፊ አሌክሳንደር ዋንግ፣ የሰው ልጅን የማሰብ አቅም የሚበልጥ ሱፐር ኢንተለጀንስ (Superintelligence) እየመጣ መሆኑን በመግለጽ፣ የሰው ልጅ ይህንን ቴክኖሎጂ እንዴት እንደሚቆጣጠረው የሚወሰንበት ቀጣዩ አንድ ዓመት እጅግ ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል። የ29 ዓመቱ የቴክኖሎጂ መሪ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ቴክኖሎጂው በሳይንሳዊ ምርምር፣ በችግር አፈታትና በቴክኖሎጂ ዕድገት ዘርፎች በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ የሰው ልጅ አዕምሮዎች በላይ መሥራት የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሱንና በቀጣዩ ዓመት የሚወሰዱ እርምጃዎች የዓለምን የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንደሚወስኑ አመልክተዋል። ይህ የዋንግ ማስጠንቀቂያ የተሰማው አንድ የ'አንትሮፒክ' ተመራማሪ የኩባንያውን 'ክላውድ' የተሰኘ የኤአይ ሞዴል በመጠቀም ለ167 ዓመታት ሳይፈታ የቆየውን ውስብስብ የሂሳብ ቀመር ማረጋገጥ መቻሉን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው። ይህንን ክስተት "የታላቅ ለውጥ መጀመሪያ" ሲሉ የገለጹት ዋንግ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት በቅርቡ ራሱን በራሱ እያሻሻለ ከሰው ልጅ ቁጥጥር ውጭ የመውጣት አቅም እንደሚኖረውና በሥነ-ሕይወት፣ በጦር መሣሪያዎችና በኢኮኖሚ ዘርፎች የሚደረጉ ምርምሮችን የሰው ልጅ ሊከተለው ከሚችለው ፍጥነት በላይ ሊያፋጥን እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል። የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሱፐር ኢንተለጀንስ የማይቀር ክስተት እንደሆነ በማሰብ ብቻ መዘናጋት እንደሌለባቸው ያሳሰቡት የሜታ ኃላፊው፣ የሰው ልጆች በቴክኖሎጂው ላይ ያላቸውን ቁጥጥርና የበላይነት የሚያረጋግጡ ተጨባጭና የተለዩ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። የ'ስኬል ኤአይ' መሥራች የነበሩት አሌክሳንደር ዋንግ በ2025 ሜታ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ኢንቨስት ካደረገ በኋላ የኩባንያውን የሱፐር ኢንተለጀንስ ላብራቶሪ እንዲመሩ የተሾሙ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት እንደ ሜታ፣ ኦፕንኤአይ፣ ጎግል እና አንትሮፒክ ያሉ ግዙፍ ተቋማት ይህንኑ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ላይ ይገኛሉ።
Open in Telegram🌙 ማታ ሱቁን ሲዘጉ… ደብተር አያገላብጡም። በእጅ አይደምሩም። "ዱቤ የወሰደው ማን ነበር?" ብለው አይጨነቁም። ስልክዎን ብቻ ይከፍታሉ 📱 💰 የዛሬ ሽያጭ — ወዲያው ይታያል 📈 የዛሬ ትርፍ — በትክክል ይሰላል 📦 ሊያልቅ የደረሰ ዕቃ — አስቀድሞ ያስታውስዎታል 👥 ዱቤ ያለበት ደንበኛ — በስም ይታያል ይሄ ህልም አይደለም 😌 Easy Business Solution ለሱቅ፣ ለጅምላ ንግድ፣ ለዕቁብ በአማርኛ የሚሰራ ሲስተም ይሰራልዎታል። ንግድዎን በግምት ሳይሆን በእውነተኛ መረጃ ይምሩ። 🎯 ለማንኛውም ዓይነት ንግድ፤ እንደ ፍላጎትዎ ተዘጋጅቶ ይሰራል። 📞 አሁኑኑ ይደውሉ: 0948943490 📲 Telegram: @easybusinesssolutionn 📢 የEasy Business Solution Telegram ቻናልን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/easybusinesssolution ✨ ኢዚ ቢዝነስ ሶሉሽን “ንግድዎን በእጅዎ ያድርጉ!” 🚀
Open in Telegram