Account

Posts of ልብወለድ Ethio_Fiction

newest first

#9497Photo
Views2,230−32%vs avg
Forwards—
Reactions41
Comments—
#9491Text

'የታክሲ የለኝም እባክህ ልጄን ይዘሃት ሂድ....😥; «እባክህ ልጄን ይዘህልኝ ትሄዳለህ? እኔ የታክሲ ገንዘብ የለኝም... እቀፋት ንፁህ ናት!» ዛሬ ጠዋት ታክሲ ውስጥ ሙሉ ተሳፋሪውን በእንባ ያራጨ፣ እስከ አሁን ድረስ ውስጤን እያደማው ያለ ልብ ሰባሪ ክስተት... ጠዋት ወደ ስራ ለመሄድ ታክሲ ተሰልፌ ገባሁ። በመስኮት በኩል ሳስተውል አንዲት እናት በጣም ቆንጆ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም የለበሰች ትንሽ ልጇን እጅ ይዛ ቆማለች። ታክሲው ሊሞላ ጥቂት ሰው ብቻ ነው የቀረው፤ «ይቺ እናት ለምን አትገባም? ልጇ አረፈደች እኮ...» እያልኩ በልቤ ሳስብ... እናትየው ድንገት ወደ መጀመሪያው ወንበር ተጠግታ መስኮቱን አንኳኳች። የፊት ወንበር ላይ የተቀመጠው ሰውዬ መስኮቱን ሲከፍተው በለዘበ፣ በሀፍረትና በጭንቀት በተሰበረ ድምፅ እንዲህ አለችው፦ «ወንድሜ... እባክህ ልጄን ይዘህልኝ ትሄዳለህ? እኔ የታክሲ ገንዘብ የለኝም... እቀፋት ንፁህ ናት!» ይሄን ስትል የታክሲው ድባብ ድንገት ፀጥ አለ፤ ልቤ ተንሰፈሰፈ! «እቀፋት ንፁህ ናት» የሚለው ቃሏ እንደ ጦር ልቤ ውስጥ ተሰካብኝ። ድህነት እንዲህ ያሳንሳል? የገዛ ልጇን ሰው እንዲሸከምላት ስትለምን እንኳ «ንፁህ ናት» ብላ ይቅርታ እንድትጠይቅ ያስገድዳል? የፊት ወንበር የተቀመጠው ጨዋ ሰው ያለምንም ማመንታት «ኧረ በደስታ እህቴ! ምንም ችግር የለውም፤ ችግር አይንካሽ አምጪያት» ብሎ ልጅቷን በክብር ተቀብሎ አቀፋት። ረዳቱም «የትምህርት ቤቱን በር አውቀዋለሁ እዛው አወርዳታለሁ አትጨነቂ» አለ። እናት ግን ልቧ አልቻለም... የልቧ ጭንቀት እረፍት ነሳትና ዐይኖቿ በእንባ ተሞልተው «እባክህ ስልክህን ጻፍልኝ?» አለችው፤ የእናት አንጀት አይደል! ስልኩን ተቀበለች። ድህነት አይኑ ይጥፋ ወላሂ! ይሄን ያየው ተሳፋሪ በሙሉ ልቡ ተነካ። ሁሉም ኪሱን ፈትሾ ለነገዋ፣ ለቀጣዩ ቀኗ የታክሲ የሚሆናትን ብር አዋጥቶ ሰጣት። ታክሲው ተነስቶ መንቀሳቀስ ሲጀምር... ያቺ ምስኪን እናት ታክሲው እይታዋ እስኪሰወር ድረስ እዛው ቆማ፣ በልጇ ላይ ያፈጠጠውን የፍቅርና የጭንቀት ዐይኗን ሳትነቅል እያየችን ቀረች። እናት ማለት ይቺ ናት... ለልጇ ትምህርት ስትል ክብሯን ጥላ የምትለምን፣ ራሷ በባዶ እግሯ ቆማ ልጇን ወደ ከፍታ የምትሸኝ! ፈጣሪ ለደጉ ተሳፋሪም፣ ለምስኪኗ እናትም ይድረስላቸው። (መረጃው የአሃዱ ሚዲያ ነው/Afi Natilus)

Open in Telegram
Views3,650+12%vs avg
Forwards—
Reactions47
Comments—
#9227Text
Views13,900+325%vs avg
Forwards—
Reactions47
Comments—
#9176Text
Views20,400+524%vs avg
Forwards—
Reactions19
Comments—