መልእክተ ቅዳሜ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ ያገኙትን ሽባ የነበረውን ተመጽዋች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፈወሱት። ብዙ አይሁድም "በመገረም" ግር ብለው ሲመጡ ጴጥሮስ፣ “እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል” አላቸው (ሐሥ 3፥19)። ትንግርቱ ዘወር እንዲሉ አደረጋቸው። ታላቁ ፈዋሽ በዚያ መቅደስ ብዙ ጊዜ ተመላልሷል፤ አሁን ደግሞ ተከታዮቹ። ስሙ ከብሮ ሥራው ስለ ጸና፣ ወደ እርሱ የሚመለሱትን በሰማይ ሆኖ ያድናል፤ ይቀድሳል፤ ይፈውሳልም።
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 5 h | 71 |
| 11 h | 137 |
- After 6 hours71
- Total to date137