Posts of Esdros S.C
የወላጅ ኮሚቴ በበጎ ፍቃደኛ ወላጆች በ1.26 ሚሊየን ብር ወጪ ያሰራውን መጫወቻ ሜዳ አሰረከበ ************* ************** ************ የአቡነ ጎርጎሪዮስ ሰንሻይን ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የወላጅ ኮሚቴ በጎ ፍቃደኛ ወላጆችን በማስተባበር ያሰራውን ግምቱ 1.26 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ስፋቱ 800 ካሬ ሜትር አራት በአንድ ( እግር ኳስ፣እጅ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ እና መረብ ኳስ) የሆነ የተማሪዎች የስፓርት ሜዳ በማሠራት ለቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ አስረከበ፡፡ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም በተደረገ የርክክብ ሥነ ሥርዓት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የሥራ ኃላፊዎች፣ የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ አመራር እና የወላጅ ኮሚቴዎች በተገኙበት ለሜዳው ሥራ በገንዘብ፣ በጉልበት እና በሐሳብ (በዕወቀት) አስተዋፅኦ ላበረከቱ መምህራን እና ወላጆች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111575954/0973-60-00-10 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ::
Open in Telegramበአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በመሪ 2ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ት/ቤት ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ ************* ************** ************ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በመሪ 2ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በወላጅ ኮሚቴ ሙሉ ድጋፍ ሁለንተናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ‘’Mind Set’’ በሚል ርእሰ ጉዳይ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ወጣት ማእከል አዳራሽ በተካሄደው መርሐ ግብር ከፍተኛ የሥነ ልቦና ባለሙያ እና አማካሪ ሽመልስ ገበየሁ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማይንድ ሴት ስልጠና ተሰጠ። በዚሁ መርሐ ግብር የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር ጣሳቸው ጫኔ የስልጠናውን መዘጋጀት በተመለከተ የወላጅ ኮሚቴ ከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ጋራ በመተባበር በርካታ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ እና ተማሪዎች በስልጠናው ባገኙት ትምህርት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የወላጅ ኮሚቴ ከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ጋራ በመነጋገር በርካታ የመማር ማስተማር ሥራውን በማገዝና በማመቻቸት ጭምር ሰፊ ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ እና ወደፊትም አብሮ ለመሥራት እና ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን ከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111575954/0973-60-00-10 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ::
Open in Telegramጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደ የውይይት መርሐገብር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አቬሽን ዩኒቨርስቲ ለአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች የምስጋና እና የዕውቅና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡ የአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በአየር መንገዱ አቬሽን አካዳሚ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ማለፋቸውን ተከትሎ አየር መንገዱ ለአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች ይህንን እውቅና እና ምስጋና ማቅረቡን ከውይይቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111575954/0973-60-00-10 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ::
Open in Telegramየኢትዮጵያ አየር መንገድ አቬሽን ዩኒቨርስቲ ከአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ውይይት ተደረገ ************* ************** ************ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቬሽን ዩኒቨርስቲ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በኢትዮጵያ አቬሽን ዩኒቨርስቲ በመግቢያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን ተከትሎ በቀጣይ አብሮ ለመስራት የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል፡፡
Open in Telegramበአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ባሕር ዳር 2ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ በባሕር ዳር ከተማ ተሸለመ ************* ************** ************ በባሕር ዳር በተካሄደ የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና ወስደው በውጤታቸው 540 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት በተዘጋጀ የዕውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር ከግል ትምህርት ቤቶች መካከል ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ እና ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ በማሳለፍ ባሕር ዳር ቀበሌ 16 2ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን፣ ከ90 ፐርሰንት በላይ ያሳለፉ ትምህርት ቤቶችንና በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎች ላሳለፉ ዞንና ከተማ አስተዳደሮች ዕውቅና እና ሽልማት አበርክቷል። ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ በተካሄደ የሽልማት መርሐ ግብር ውጤታቸው ከ540 በላይ የሆኑት ተማሪ አብርሃም አዲሱ 541፣ ተማሪ ህሊና ውበት 550.25፣ ተማሪ በእምነት መቆየት 551.41 እና ተማሪ ጽዮን እሱባለው 554.84 ውጤት በማምጣት እያንዳንዳቸው የ35,000 ብር ሽልማት እና ሰርተፍኬት፤ በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ባሕር ዳር ቀበሌ 16 2ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ዋንጫ ፣ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር ሲበረከትለት ለርእሰ መምህሩ የሰርተፍኬት ሽልማት ከክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ከዶክተር ሁሴን አብዱ እጅ ተበርክቶላቸዋል፡፡ በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የባሕር ዳር ቀበሌ 16 2ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ት/ቤት በ2018 ዓም ያስፈተናቸውን 80 ተማሪዎች 100% ማሳለፉ ይታወቃል፡፡
Open in Telegramበአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአዋሬ 1ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ት/ቤት ለወላጆች ስልጠና ተሰጠ ************* ************** ************ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ዋነኛ ትኩረት ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ በሆነው የወላጆችን ሁለንተናዊ ሰብእና ግንባታ እና በመማር ማስተማሩ ላይ ያተኮረ መርሐ ግብር ተካሄደ፡ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ በተካሄደው መርሐ ግብር ከፍተኛ የሥነ ልቦና ባለሙያ እና አማካሪ ሽመልስ ገበየሁ “የልጆች አስተዳደግ እና አያያዝ” ላይ ሙያቸውን እና ልምዳቸውን መሠረት በማድረግ ጥልቅ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ በዚሁ መርሐ ግብር የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር ደረጀ በቀለ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱን የመማር ማስተማር የትኩረት አቅጣጫን በማስመልከት የመነሻ ሀሳብ በማቅረብ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ወላጆችም በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ሁለንተናዊ ድጋፍ እና አጋርነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ፡፡ በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአዋሬ 1ኛ እና መካከለኛ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በ2007 ዓ.ም ተመስርቶ የመማር ማስተማር ሥራውን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በ2018 የትምህርት ዘመን በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100% በማሳለፍ ከወረዳ እና ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ጽ/ ቤት ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111575954/0973-60-00-10 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ::
Open in Telegramለሁለት ቀናት በተካሄደው ስልጠና የሕክምና እና የሥነ ልቦና ባለሙያ በሆኑት በዶ/ር እንግዳ ግርማ ‘’School Partnership and Communication Skill’’ በሚል ርእስ ፣የኤስድሮስ የዳሬክተሮች ቦርድ አባል እና የትምህርት ባለሙያ በሆኑት በዶ/ር ቴዎድሮስ ሀብቴ ‘’Instructional Leadership’’፣ የኤስድሮስ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ በአቶ ታምሩ ለጋ ‘’Decision Making and Delegation’’ እና በኤስድሮስ የዳሬክተሮች ቦርድ ም/ሰብሳቢ አምባሳደር ዓለም ፀሐይ መሠረት አማካኝነት ‘’ Planning, KPIS and Accountability ‘‘ በሚሉ ርእሶች ተግባራዊ ስልጠና ተካሄዷል፡፡ ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111575954/0973-60-00-10 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com. በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ::
Open in Telegram