እውነተኛው ኃይል ያለው የት ነው?" አንድ ወጣት ወደ ጥበብ መምህሩ ዘንድ ሄዶ ሕይወቱ በጭንቀትና በውድቀቶች የተሞላ መሆኑን፣ ችግሮችም ሁልጊዜ እንደሚያሸንፉት በአቤቱታ ተናገረ። መምህሩም ምንም አልተናገረም፤ ይልቅስ ወጣቱን ወደ ማብሰያው ወስዶ ሦስት የተለያዩ ማሰሮዎችን በውሃ ሞላና በእሳት ላይ አደረጋቸው። ውሃው መፍላት ሲጀምር አንደኛዋ ላይ ድንች፣ ሁለተኛዋ ላይ እንቁላል፣ ሦስተኛዋ ላይ ደግሞ የቡና ፍሬዎችን ከተታቸው። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መምህሩ ማሰሮዎቹን አወጣና ወጣቱን ጠየቀው፦ "በውሃው ውስጥ የገባውን ድንች፣ እንቁላል እና የቡና ፍሬ ምን እንደሆኑ እያየህ ነው? ሁሉም የገቡት በአንድ ዓይነት ፈታኝ ሁኔታ (በሚፈላ ውሃ) ውስጥ ነው፤ ነገር ግን እያንዳንዳቸው ምላሽ የሰጡት በተለያየ መንገድ ነው። ጠንካራው ድንች ለስልሶ ወጣ፤ በቀላሉ የሚሰበረው እንቁላል ውስጡ ደረቀ፤ የቡና ፍሬው ግን ውሃውን ቀይሮ ውብ መዓዛ ፈጠረ።" ኦሾ ይህንን ታሪክ ሲያብራራው፦ "በሕይወትህ ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታዎች (የሚፈላ ውሃ) ሲገጥሙህ ችግሩን ለመውቀስ አትቸኩል። ችግሩ እንደ ድንች ወይም እንቁላል እንዲለውጥህ አትፍቀድ፤ እንደ ቡና ፍሬ ሁኔታውን ቀይረህ በውስጥህ ያለውን ውበትና ኃይል አፍልቆ ማውጣት የሚችለው አንተ ራስህ ብቻ ነህ። ውጫዊው ዓለም ሁኔታዎችን ብቻ ነው የሚፈጥረው፤ ምላሹ ግን ሙሉ በሙሉ በአንተ እጅ ነው።" — ኦሾ @enlighten_ethiopia
Open in TelegramPosts of የስብዕና ልህቀት
"Trauma and Addiction" በመንገድ ላይ ወይም በቤተሰብህ ውስጥ በአደገኛ ዕፅ፣ በአልኮል፣ በቁማር ወይም በብልግና ምስሎች ሱስ የተተበተበን ሰው ስትመለከት፣ ማኅበረሰቡ በንቀትና በምሬት፣ ይህ ሰው ለምን ራሱን መግዛት ያቅተዋል? ለምን ይህን አጥፊ ሱስ አያቆምም? ብሎ በቁጣ ይጠይቃል። ነገር ግን መላው ዓለም ለዘመናት እየጠየቀ ያለው ጥያቄ ገና ከመነሻው ፍጹም የተሳሳተ ቢሆንስ? በዘመናችን የሱስ ሕክምናን መሠረት ያናወጡት ታዋቂው የሕክምና ዶክተርና ደራሲ Dr Gabor Mate መላውን ዓለም በአንድ አረፍተ ነገር አስደነገጡ፣ ሱስ ለምን ተፈጠረ ብላችሁ አትጠይቁ፣ ህመሙ ከየት መጣ ብላችሁ ጠይቁ። Don't ask why the addiction ask why the pain። ሱስ በራሱ ዋናው በሽታ አይደለም፣ ይልቁንም በልጅነት ዕድሜ ውስጥ በነፍስ ጥልቀት ላይ የተተከለን ያልተፈታ የስሜት ቁስል Trauma ለማደንዘዝ የሚደረግ አሳዛኝ የሰው ልጅ መፍጨርጨር ነው። ይህ የሰውን ልጅ ስቃይ እርቃኑን ያስቀረ ታላቅ የሕክምና ትንግርት ያልተፈታ የስሜት ቁስል እና ሱስ Trauma and Addiction ይባላል። Dr Gabor Mate በካናዳ Vancouver ከተማ ውስጥ፣ በሰሜን አሜሪካ እጅግ አስከፊና ከባድ የዕፅ ሱሰኞች በሚኖሩበት ሰፈር Downtown Eastside ለ12 ዓመታት በሐኪምነት ሲያገለግሉ ያገኟቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ታካሚዎች አንድ አስደንጋጭ የጋራ ታሪክ ነበራቸው። አንዳቸውም ቢሆኑ ያለምንም ከባድ የልጅነት በደል፣ ስነ ልቦናዊ ስብራትና የቤተሰብ ጥቃት ሱሰኛ የሆኑ አልነበሩም። The Anesthetic for the Wounded የተጎዱ ሰዎች ማደንዘዣ። ሱስ እንደ ጊዜያዊ መፍትሔ Dr Gabor Mate ሱስን ሲተረጉሙ፣ አንድ ሰው ጊዜያዊ እፎይታ ወይም ደስታ የሚያገኝበት፣ ነገር ግን የረጅም ጊዜ ጥፋት እያስከተለበት ሊተወው የማይችለው ማንኛውም ተግባር ነው። ይላሉ። አንድን ሱሰኛ ዕፁ ምን ሰጠህ? ብለህ ብትጠይቀው የሚሰጥህ መልስ፣ ውስጣዊ ሰላም ሰጠኝ፣ ከአእምሮዬ ጩኸት አሳረፈኝ፣ የብቸኝነት ህመሜን አደነዘዘልኝ፣ በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የመኖር ስሜት እንዲሰማኝ አደረገኝ። የሚል ነው። ስለዚህ ሱስ ችግር ብቻ አይደለም፣ ለሰውየው ሊሸከመው ያልቻለውን ጥልቅ ውስጣዊ ስቃይ ለማስታገስ ያገኘው የመጨረሻው የህልውና መፍትሔ ነበር። ችግሩ ያ የወሰደው ማደንዘዣ ውሎ አድሮ ይበልጥ ገዳይ አውሬ ሆኖ መመለሱ ነው። The Stunted Brain Circuitry የተሰበረው አንጎል ልደት። ፍቅር እንደ ባዮሎጂካል ፍላጎት ብዙ ሰዎች ሱስ በዘረመል Genetics የሚወረስ በሽታ ነው ብለው ያስባሉ። Dr Gabor Mate ግን በነርቭ ሳይንስ ጥናቶች ይህንን አፈ ታሪክ ያፈርሱታል። በአንጎላችን ውስጥ የደስታ፣ የመረጋጋትና የእርካታ ኬሚካሎችን Endorphins and Dopamine የሚቆጣጠሩት የነርቭ መስመሮች፣ በሕፃንነት ዕድሜያችን ከወላጆቻችን ከምናገኘው ፍቅር፣ እቅፍ፣ ደህንነትና ስሜታዊ ትስስር ጋር አብረው ነው የሚገነቡት። አንድ ሕፃን በልጅነቱ ፍቅርና ደህንነት ሲያጣ፣ ሲተወው፣ ወይም በቤተሰብ ጥቃትና ጩኸት ውስጥ ሲያድግ፣ አንጎሉ በተፈጥሮ መንገድ ራሱን በራሱ የሚያረጋጋበት ባዮሎጂካዊ ሥርዓት ሳይገነባ ተሰባብሮ ይቀራል። ያ ልጅ አድጎ ትልቅ ሰው ሲሆን፣ በውስጡ ዘላለማዊ የባዶነትና የጭንቀት ገደል ይሰማዋል። ያንን ገደል ለመሙላት ደግሞ ውጫዊ ኬሚካሎችን አልኮልን፣ ዕፅን፣ ስልክን ወይም ዝሙትን እንደ ሰው ሰራሽ ማረጋጊያ ለመጠቀም ይገደዳል። The ACE Study The Shocking Numbers የACE ታሪካዊ ጥናት ይህ በዶክተሮች የግል ምልከታ ብቻ የተገኘ ድምዳሜ አይደለም፣ በሕክምና ታሪክ ውስጥ ትልቁ የልጅነት መጥፎ ገጠመኞች ጥናት The Adverse Childhood Experiences ACE Study በVincent Felitti እና Robert Anda የተባሉ ሳይንቲስቶች ከ17,000 በላይ ሰዎች ላይ ባደረጉት ጥናት ተረጋግጧል። ውጤቱ አስደንጋጭ ነበር። በልጅነቱ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ከባድ የስሜት፣ የአካል ወይም የፆታ ጥቃቶችን ያሳለፈ አንድ ወንድ ልጅ፣ ምንም ዓይነት ጥቃት ካላሳለፈ ሌላ ሰው ጋር ሲነጻጸር፣ በደም ሥር የሚወሰድ አደገኛ ዕፅ IV Drug የመጠቀም ዕድሉ በ4,600 በመቶ በ46 እጥፍ ይጨምራል። ሱስ በዘፈቀደ የሚከሰት የባሕሪ ጉድለት ሳይሆን፣ በልጅነት ዕድሜ የተዘራ የህመም መከር ነው። ማኅበረሰባችን ለሱሰኞች የሚሰጠው ምላሽ ማግለል፣ ማዋረድና እፍረት ማሸከም Shame and Stigma ነው። Dr Gabor Mate ግን፣ አንድን የተሰበረ ሰው በማዋረድና በማሰቃየት ራሱን እንዲያፈቅር ማድረግ ፈጽሞ አይቻልም። ይላሉ። አንድ ሱሰኛ ራሱን በጠላ ቁጥር፣ ያንን የጥላቻና የጥፋተኝነት ህመም ለማደንዘዝ እንደገና ወደ ሱሱ ይሮጣል። ይህ አስከፊ የእፍረት አዙሪት Shame Spiral ይባላል። ዛሬ ዓለም የሚያስፈልገው ሱሰኞችን ወደ እስር ቤት ማጎር ሳይሆን፣ የልጅነት ቁስላቸውን በፍቅርና በርኅራኄ የሚያክም የህክምና ሥርዓት Compassionate Inquiry መገንባት ነው። ፈውስ የሚጀምረው ፍርድና ንቀት በሚያቆሙበት ቅጽበት ብቻ ነው። በሕይወትህ ውስጥ ያለህን ማንኛውንም አጥፊ ሱስ፣ ስልክ ማብዛት፣ ፖርኖግራፊ፣ ከመጠን በላይ መብላት ወይም ራስን ማደንዘዝ፣ በቁጣና በራስ ጥላቻ ልታሸንፈው አትችልም። በድፍረት ወደ ውስጥህ ተመልከትና ያንን የሚያለቅሰውን የቆሰለ ውስጣዊ ልጅህን እቀፈው። ያሳለፍከው ህመም እውነተኛ ነበር፣ አሁን ግን ሰላም ነህ። በለው። በሌሎች ሰዎች ላይም የምታየውን ጥፋት ከመኮነንህ በፊት፣ ከበስተጀርባው ያለውን ያልተፈታ እንባና የልብ ስብራት ተመልከት። ምክንያቱም እውነተኛው ፈውስ የሚመነጨው ከቅጣት ሳይሆን፣ ከማይነጥፍ ሰብዓዊ ርኅራኄና ፍቅር ብቻ ነውና። ©️የአፅናፍ ሰማይ ዜማ @enlighten_ethiopia
Open in Telegram#ማንኛውም የመሥሪያ ቤት ሠራተኛ ሊኖረው የሚገባ ዋና Soft Skills፣ 1. Communication Skills / የመግባባት ችሎታ ሀሳብን፣ መረጃንና ጥያቄን በግልጽ፣ በአክብሮትና በተገቢው መንገድ ማስተላለፍ። ጥሩ መግባባት የተሳሳተ መረጃንና አላስፈላጊ አለመግባባትን ይቀንሳል። 2. Active Listening | በትኩረት የማዳመጥ ችሎታ ሌላው ሰው ሲናገር መልስ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመረዳት ማዳመጥ። ጥያቄ መጠየቅ፣ ማረጋገጥና የሌላውን ሀሳብ በትክክል መረዳት ይህን ችሎታ ያካትታል። 3. Emotional Intelligence | ስሜታዊ ብልህነት የራስን ስሜት ማወቅና መቆጣጠር፣ የሌሎችንም ስሜት መረዳት። በግፊት ወይም በግጭት ጊዜ በስሜት ከመመራት ይልቅ በጥበብ እንዲመልሱ ያግዛል። 4. Teamwork | የቡድን ሥራ “እኔ” ከሚለው ይልቅ “እኛ” ብሎ መሥራት። ከባልደረቦች ጋር መተባበር፣ መረጃ መካፈልና የጋራ ዓላማን ለማሳካት መሥራት። 5. Accountability | ተጠያቂነት ለራስ ሥራ፣ ውሳኔና ውጤት ኃላፊነት መውሰድ። ስህተት ሲፈጠር ጥፋቱን በሌሎች ላይ ከመጣል ይልቅ ስህተቱን መቀበልና መፍትሔ መፈለግ። 6. Time Management | የጊዜ አጠቃቀም ሥራዎችን በቅድሚያ መለየት፣ ቅድሚያ መስጠትና deadlinesን ማክበር። ጊዜን በትክክል የሚጠቀም ሠራተኛ ሥራውን በተደራጀ ሁኔታ ያከናውናል። 7. Problem-Solving | ችግር የመፍታት ችሎታ ችግር ሲፈጠር “ማን ጥፋተኛ ነው?” ከማለት በፊት “መፍትሔው ምንድነው?” ብሎ ማሰብ። ችግሩን መለየት፣ አማራጮችን ማየትና ተገቢውን መፍትሔ መምረጥ። 8. Creative Thinking | ፈጠራዊ አስተሳሰብ አንድን ሥራ ሁልጊዜ በተመሳሳይ መንገድ ከማድረግ ይልቅ አዲስና የተሻለ መንገድ መፈለግ። አዲስ ሀሳብ ማመንጨትና ችግሮችን ከተለያየ አቅጣጫ ማየት። 9. Adaptability | ለለውጥ መላመድ አዲስ የሥራ ሥርዓት፣ ቴክኖሎጂ፣ ኃላፊነት ወይም የሥራ ሁኔታ ሲመጣ በተለዋዋጭነት መላመድ። ለውጥን እንደ ችግር ብቻ ሳይሆን እንደ የመማር እድልም ማየት። 10. Resilience | ችግርን የመቋቋም ችሎታ ጫና፣ ትችት፣ ውድቀት ወይም አስቸጋሪ የሥራ ሁኔታ ሲያጋጥም ተስፋ ሳይቆርጡ እንደገና ተነስቶ ሥራን መቀጠል። 11. Empathy | ሌሎችን መረዳት ራስን በሌላው ቦታ አስቀምጦ የሌላውን ሁኔታና ስሜት ለመረዳት መሞከር። ይህ ከባልደረቦች፣ ከደንበኞችና ከአስተዳደር ጋር ጤናማ ግንኙነት ለመፍጠር ይረዳል። 12. Conflict Management | ግጭትን የመቆጣጠር ችሎታ አለመግባባትን ወደ ግል ጥላቻ ከመቀየር ይልቅ ችግሩን በመለየት፣ በመወያየትና በፍትሃዊነት መፍታት። 13. Leadership | አመራር አመራር ማለት ሌሎችን ማዘዝ ብቻ አይደለም። በምሳሌ መምራት፣ ሌሎችን ማበረታታት፣ ኃላፊነት መውሰድና የጋራ ዓላማን ለማሳካት ሌሎችን ማነሳሳት ነው። 14. Critical Thinking | ትንተናዊ አስተሳሰብ የሚሰማውን ሁሉ ወዲያውኑ ከማመን ይልቅ ማስረጃን መመርመር፣ ምክንያቱን ማየት፣ መረጃን ማነፃፀርና በምክንያት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ መስጠት። 15. Growth Mindset | የእድገት አስተሳሰብ “አልችልም” ብሎ ከመቆም ይልቅ “በመማርና በልምምድ ማሻሻል እችላለሁ” የሚል አመለካከት መኖር። 16. Lifelong Learning | የዕድሜ ልክ ተማሪነት ከተመረቁ በኋላ መማር አያበቃም። አዲስ እውቀት፣ ቴክኖሎጂ፣ የሥራ ዘዴና ሙያዊ ችሎታ ያለማቋረጥ መማር። 17. Professionalism & Respect | ሙያዊነትና አክብሮት የሥራ ቦታን ደንብ ማክበር፣ ሰዎችን በክብር መያዝ፣ ቃልን መጠበቅ፣ በሥራ ላይ ታማኝና የተደራጀ መሆን። 18. Social Skills | ማህበራዊ ችሎታ ከተለያዩ ሰዎች ጋር በተገቢው መንገድ ግንኙነት መፍጠር፣ ራስን በሁኔታው መሠረት ማስተካከልና በቡድን ውስጥ አዎንታዊ ሚና መጫወት። 19. Self-Control & Patience | ራስን መቆጣጠርና ትዕግሥት በቁጣ፣ በግፊት ወይም በአለመግባባት ጊዜ ስሜትን መቆጣጠር። ከመናደድ ወይም በፍጥነት ከመመለስ ይልቅ ማሰብና ተገቢውን ምላሽ መስጠት። 20.Self-Awareness | ራስን ማወቅ የራስን ጥንካሬ፣ ድክመት፣ ስሜትና ባህሪ ማወቅ። ብቁ ሠራተኛ “ምን አውቃለሁ?” ብቻ ሳይሆን “የት ላይ መሻሻል አለብኝ?” ብሎም ይጠይቃል። "Hard Skills ሥራውን ያስተምሩሃል፤ Soft Skills ግን ሥራውን እንዴት እንደምትሠራ ያሳዩሃል!" #ምንጭ: OECD. Social and Emotional Skills for Better Lives: Findings from the OECD Survey on Social and Emotional Skills 2023. @enlighten_ethiopia
Open in Telegramየኒውሮሳይንስ ግኝት፦ ዘወተር ስፖርት መስራት መጥፎና አስጨናቂ ትዝታዎች የሚያመጡትን የሥነ-ልቦና ጫና ይቀንሳል! አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ለአካላዊ ጤንነት ብቻ ሳይሆን አእምሯችን ከአስጨናቂ አጋጣሚዎችና ከአሰቃቂ ትዝታዎች (Stressful Memories) እንዲያገግም ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ የሳይንስ ጥናቶች አረጋግጠዋል! ዘወትር እንቅስቃሴ ማድረግ አስቸጋሪ አጋጣሚዎችን ሙሉ በሙሉ አጥፍቶ ባይረሳውም፣ አእምሯችን ለነዚያ ትዝታዎች የሚሰጠውን አሉታዊ የስሜት ምላሽ (Emotional Impact) በመቀነስ የረጋ አእምሮ እንዲኖረን ይረዳል። 📌 የስፖርት እና የአእምሮ ጤንነት ዋና ዋና ሳይንሳዊ ጥቅሞች፦ 1. የአእምሮን ስሜታዊ ተፅዕኖ መቀነስ (Neuroplasticity) ፦ ስፖርት በምንሰራበት ወቅት በአእምሯችን ውስጥ የሚለቀቁት BDNF እና Endorphin የተባሉ ሆርሞኖች አእምሮአችን ከአስጨናቂ ትዝታዎች ጋር የሚኖረውን አሉታዊ ትስስር እንዲያላላ ያደርጋሉ። 2. የኮርቲሶል (Cortisol) መጠንን ማመጣጠን ፦ የጭንቀት ሆርሞን በመባል የሚታወቀውን ኮርቲሶል በመቀነስ፣ አእምሮአችን ስሜታዊ መረጋጋት (Emotional Regulation) እንዲያገኝ ያግዛል። 3. በቀላል እንቅስቃሴ የሚጀመር ትልቅ ለውጥ ፦ ጥቅሙን ለማግኘት የግድ ከባድ ስፖርት መስራት አይጠበቅብዎትም፤ የ10 እና 15 ደቂቃ ፈጣን እርምጃ ወይም ቀላል እንቅስቃሴ አእምሮን አዲስ ለማድረግ በቂ ነው። ስፖርት የሙያዊ የነርቭና የስነ-ልቦና ህክምናዎችን ሙሉ በሙሉ ባይተካም፣ ጭንቅላታችንን ለማረጋጋት እና የውስጥ ጥንካሬያችንን ለመገንባት እጅግ አስፈላጊ መሣሪያ ነው! @enlighten_ethiopia
Open in Telegramበምክንያት ወይስ በስሜት? የስሜት ብስለት ! ለስኬታማ የመሪነት ህይወት ! በፍፁም ንጉሴ የዓለማችንን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሁኔታ በጥብቅ ስንታዘብ፣ ዓለማችን ከምንጊዜውም በላይ በከፍተኛ የአመራር ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ እንረዳለን።በምዕራቡ ዓለም፡ የአሜሪካን ተለዋዋጭና ውጥረት የሞላበት ፖለቲካዊ ምህዳር ስንመለከት፣ እንዲሁም የታላቋ ብሪታንያን የበሰለና የረጋ መሪ እጥረት ስንታዘብ የችግሩን ስፋት እንገነዘባለን። በአፍሪካና በእኛ ሀገር ደግሞ በየደረጃው የሚታየው የከፋ የአመራር ክፍተት፣ የህዝቦችን እንግልት ከመጨመሩም በላይ ዘላቂ ሰላምና እድገትን እንዳይረጋገጥ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል። ይህ ሁኔታ የሚያሳየን ነገር ቢኖር፣ ዓለማችን በጥበብ፣ በምክንያት፣ በራዕይ እና በብስለት የሚመሩ መሪዎችን ጽኑ ረሐብ ላይ እንዳለች ነው ። ይህንን የጎላ የአመራር ክፍተት በመመልከት፣ በአመራር (Leadership) ዘርፍ ላይ ጥልቅ የሆነ ትምህርት ለመቅሰም፣ ምርምር ለማድረግ እና ወደፊት በስራና በተግባር ሰፊ የአሻራ ለማሳረፍ ትልቅ አላማና ሀሳብ ሰንቄያለሁ። ለዛሬ ግን " የስሜት ብስለት " ወይም Emotional Intelligence “ ስለሚባለው ነገር ጥቂት ለማለት ወደድኩ :: ውጤታማ መሪነትን የሚወስነው ምንድን ነው? (IQ vs. EQ) ብዙዎቻችን ስኬታማ መሪ ለመሆን ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ፣ ረጅም የልምድ ዘመን ወይም የላቀ የቴክኒክ ክህሎት (IQ - Intelligence Quotient) ብቻ የሚያስፈልግ ይመስለናል። ነገር ግን በዘርፉ የተደረጉ በርካታ ሳይንሳዊ ጥናቶች ሙሉ በሙሉ ተቃራኒ የሆነ እውነታን ያሳያሉ። "ለአንድ መሪ ውጤታማነት 20% የሚሆነው ሚና የዕውቀትና የቴክኒክ አቅም (IQ) ሲሆን፣ 80% የሚሆነውን የስኬት ድርሻ የሚይዘው ግን የስሜት ብስለት ወይም ስሜትን የመረዳትና የመምራት አቅም (Emotional Intelligence / EQ) ነው።" በማንኛውም የሕይወት መስክ—በድርጅት አመራር፣ በቤተሰብ፣ በማህበራዊ ህይወትም ሆነ በግል ስራ—ሰው አስተዳዳሪና ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን ዋናው ቁልፍ የስሜት ብስለት ነው። የስሜት ብስለት የሚገነባው በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች (የውስጥ ጥንካሬ እና የውጫዊ ግንኙነት) ነው። መሪነት የሚጀምረው "ከውስጥ ወደ ውጭ" (From Inside Out) በመሆኑ፣ ለመሪነት መሰረት የሆነውን የመጀመሪያውን እና ዋናውን፦ ክፍል—የውስጥ ጥንካሬን (Intrapersonal Foundation)—በዝርዝር እንመልከት። የውስጥ ጥንካሬ (Intrapersonal Foundation)፡ ራስን የመምራት ጥበብ :- ሌሎችን ከመምራትህ በፊት በቅድሚያ ራስህን መምራት አለብህ። ራሱን ማስተዳደር ያልቻለ መሪ ሌሎችን፣ ድርጅትን ወይም ሀገርን በብቃት ሊመራ አይችልም። የውስጥ ጥንካሬ በራስህ ስሜት፣ ሀሳብና ባህሪ ላይ የምታደርገው ጥበብ የተሞላበት ቁጥጥር ሲሆን፣ በሁለት ዋና ዋና መሠረቶች ይከፈላል፡ 1. ራስን ማወቅ (Self-Awareness) ራሱን ማወቅ የማንኛውም ታላቅ መሪ መነሻና መሰረት ነው። ይህም ማለት ስሜትህ፣ ሀሳብህ፣ እሴቶችህ እና ድክመቶችህ በዙሪያህ ባሉ ሰዎችና በሚወሰኑ ውሳኔዎች ላይ የሚያደርሱትን ተፅዕኖ በግልጽ የመረዳት አቅም ሲሆን ራስን ማወቅ በሶስት አቅጣጫዎች ይገለጻል፡ ሀ. የስሜት ብስለት/ንቅናቄ (Emotional Awareness)፦ በተናደድክ፣ በተጨነቅክ፣ በተስፋ መቁረጥ ወይም ከመጠን በላይ በደስታ ስሜት ውስጥ ስትሆን ወዲያውኑ የያዘህን ስሜት ለይተህ የማወቅና የመረዳት አቅም ነው። ለ. ትክክለኛ የግል ግምገማ (Accurate Self-Assessment)፦ ጥንካሬህን አውቀህ የመጠቀም ያህል፣ ድክመቶችህንና የዕውቀት ወሰኖችህን ያለ ምንም ሽፋን በቅንነትና በትህትና የመቀበል ድፍረት ነው። ሐ. በራስ መተማመን (Self-Confidence)፦ በራስህ እሴቶች፣ አቅምና ውሳኔዎች ላይ የጸና እምነት ማሳደር ነው። ይህም ራስን ከሌሎች ጋር ካለማወዳደር እና ከውጫዊ ሙገሳ ይልቅ በውስጣዊ ማንነት ከመመራት ይመነጫል። 2.ራስን መግዛት (Self-Management) : ራስን ማወቅ የመጀመሪያው እርምጃ ሲሆን፣ ሁለተኛውና ወሳኙ ደግሞ ያወቅከውን ስሜት በአግባቡ መቆጣጠርና መምራት ነው። አስቸጋሪ፣ ፈታኝና ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ በድንገት ወይም በቂ ጊዜ ሳይወስዱ ስሜታዊ ምላሽ ከመስጠት (Reaction) ይልቅ፣ ረጋ ብሎ ምክንያታዊና ጥበብ የተሞላበት ውሳኔ የመስጠት (Response) ክህሎት ነው። ራስን መግዛት በሚከተሉት ሶስት አዕማድ ይገለጻል፡ ሀ. ስሜትን መቆጣጠር (Emotional Self-Control)፦ በከፍተኛ ውጥረት፣ ቁጣ፣ ቅሬታና ፈተና ጊዜ መረጋጋትን አለማጣት፣ ራስንና ንግግርን የመግዛት አቅም ነው። ለ. ተለዋዋጭነት/መላመድ (Adaptability)፦ ዓለምና ሁኔታዎች በፍጥነት ሲቀያየሩ፣ ላልታሰቡ ለውጦችና ተጋላጭ ሁኔታዎች በፍጥነት ተላምዶ መፍትሔ የመስጠት አቅም ነው። ሐ. ጽናትና አዎንታዊነት (Optimism & Resilience)፦ ትልልቅ እንቅፋቶች፣ ውድቀቶችና አጣብቂኞች ሲያጋጥሙ ተስፋ ሳትቆርጥ፣ ከመከራው ውስጥ እድሎችንና ትምህርቶችን አጥርቶ የማየት የውስጥ ጥንካሬ ነው። በአጠቃላይ የውስጥ ጥንካሬ ወይም / IntraPersonal foundation/ ለማንኛውም ስኬታማና ዘላቂ መሪነት የማይናወጥ የመሰረት ድንጋይ ነው። ራሱን የማያውቅና ፣ ስሜቱን መግዛት የማይችል መሪ—በቁጣ፣ በደስታ፣ በስሜታዊነት ወይም ከመጠን ባለፈ በራስ መተማመን (Arrogance) ውስጥ ሆኖ በሚወስናቸው ግብታዊ ውሳኔዎችና በሚናገራቸው አላስፈላጊ ንግግሮች — ለዓመታት የለፋበትን ተቀባይነት፣ ክብርና ህዝባዊ እምነት በሰከንዶች ውስጥ አየር ላይ ሊበትነው ይችላል። መሪ በምክንያት እንጂ በስሜት መመራት የለበትም !! ስለሆነም፣ ከውጭው ዓለም፣ ከሰዎችና ከቡድናችን ጋር ስኬታማ ግንኙነት ከመፍጠራችንና መሪ ከመሆናችን በፊት፣ በቅድሚያ የራሳችንን ስሜት የመረዳት፣ የመግዛትና ንግግራችንን የመመዘን የውስጥ ጥንካሬን ልንገነባ ይገባል። በየትኛውም የሕይወት ዘርፍ አሻራ የሚያሳርፍ ታላቅ መሪ ለመሆን፣ ጉዞው የሚጀምረው ራስን በብስለት ከማወቅና ስሜትን ከማስተዳደር ነው። @enlighten_ethiopia
Open in Telegramዓመታት ዝም ብለው መጥተው ብቻ አይሄዱም፣ከሕይወታችን ገጽ አንድ ክፍል ቀንሰው ነው የሚያልፉት። ህይወት ማለት ያለ ማንም ፈቃድ፣ ያለ ማንም ማሳሰቢያ እንደ መጽሐፍ ገጽ እየተገለጡ የሚያልፉ የዓመታት፣ የወራት፣ የሳምንታት ድምር ነው። ለእርስዎ ሥልጣን፣ ማዕረግ ወይ ክብር፣ ደንታ በሌላቸው በእነዚህ የጊዜ ምዕራፎች ላይ፣ልናዝ የምንችለው ትልቁ ነገር ሁሉ ነገር ለሚገዛለት ለዚያ ወሰን ለሌለው ፈቃድ ፣ትርጉም ያለው ነገር ማበርከት ብቻ ነው። አዲስ ዓመት ብለን በምንጠራው በዚህ አዲስ ምዕራፍ ህይወታችሁን በፍቅር፣ በደስታና በሰላም እንድትሞሉት እመኛለሁ። በዚህች ምድር ላይ ባለን አጭር ቆይታ፣ ትልቅ አሻራና በጎ ተፅዕኖን ለማሳረፍ እንትጋ ምክንያቱም ከዚህ ዘመን የምናተርፈው፣ በራሳችን ቁርጠኛ ፈቃድ የገነባነውን ብቻ ነውና! @enlighten_ethiopia
Open in Telegramጊዜ ስጡት! አንዳንድ ነገሮች በቀላሉ ጊዜን ይፈልጋሉ፡፡ 1. ለስኬት ጊዜ ስጡት — ስኬት ጊዜ ይፈልጋል ትልቅ ስኬት በአንድ ሌሊት አይመጣም። እውቀት፣ ችሎታ፣ ተሞክሮ፣ ትዕግሥትና ትጋት በጊዜ ይገነባሉ። ዛሬ ትንሽ የሚመስለው እርምጃ ነገ ትልቅ ውጤት ሊሆን ይችላል። 2. ለሰዎች ጊዜ ስጡት — እውነተኛ ባሕርያቸውን ያሳያሉ ሰዎችን በቃላቸው ብቻ አትፍረዱ። ጊዜ ስትሰጧቸው ባሕሪቸው በተግባራቸው መታየት ይጀምራል፡፡ ሰዎች በንግግር ብቃታቸው ሊያሳምኗችሁ ይችላሉ፤ ግን ጊዜ እውነታውን ያሳያል። 3. ለስሜታችሁ ጊዜ ስጡት — ይረጋጋል በንዴት፣ በፍርሃት፣ በብስጭት ወይም በከፍተኛ ደስታ ውስጥ ስትሆኑ ወዲያውኑ ውሳኔና እርምጃ አትውሰዱ። ስሜት በወቅቱ በጣም ኃይለኛ ሊሆንና ሃሳብን ሊያዛባ ይችላል፤ ጊዜ ሲያልፍ ግን ይረጋጋል፣ አስተሳሰባችሁም ይጠራል። 4. ለራሳችሁ ጊዜ ስጡት — እያደጋችሁ ትሄዳላችሁ በአንድ የሕይወት ውድቀት ወይም አለመሳካት ምክንያት ሙሉ ሕይወታችሁ እንደዚያ እንደሆነ አታስቡ። እየተማራችሁ፣ እየተለወጣችሁ፣ እየበሰላችሁ እና እያደጋችሁ ነው። 5. ለሁኔታዎች ጊዜ ስጧቸው — ቀስ በቀስ ግልጽ እየሆኑ ይሄዳሉ ዛሬ የማትረዱት ነገር ነገ ቀስ በቀስ ግልጽ ወደመሆን ይመጣል። ዛሬ እንደ ሽንፈት የምታዩት ነገር ከጊዜ በኋላ እንደ ትምህርት፣ እንደ እድገት፣ እንደ ብስለት እና እንደ አዲስ እድል ሆኖ ሊታያችሁ ይችላል። ዶ/ር እዮብ ማሞ
Open in Telegramጸጥታ እና እርጋታ በአንድ ገጠራማ አካባቢ ማያ የሚባሉ በጣም የረቀቀ አዕምሮ ያላቸው ሽማግሌ አባት ይኖሩ ነበር። በአንድ ወቅት ይኖሩበት የነበረው አካባቢ በከባድ ድርቅ፣ ጎርፍ እና በብዙ ማህበራዊ ውጣ ውረዶች ይታወቅ ነበር። ነገር ግን ማያ ምን ጊዜም በጸጥታ እና በእርጋታ የተሞላ ሕይወት ይኖሩ ነበር። አንድ ቀን አንድ ወጣት በእጅጉ ተጨንቆ ወደ እሳቸው መጣና እንዲህ አላቸው "አባቴ አገራችን በችግር ተመታለች አየሩ ይከብዳል፣ ሰዎች ይለወጣሉ፣ ነገ የሚሆነውን አናውቅም። በዚህ ሁሉ አለመረጋጋት ውስጥ እንዴት እንዲህ ሊረጋጉ ቻሉ ? እኔስ እንዴት ተራጋግቼ ልኑር ? ልቤ በጭንቀት ተወጥሯል አላቸው፡፡ ማያ አጭር ፈገግታ አሳዩና ወጣቱን ይዘው ወደ ግዙፍ ተራራ እና ወደ አንድ የውሃ ወንዝ ወሰዱት። ከዚያም አንድ ከባድ ድንጋይ አንስተው ወንዙ ውስጥ ወረወሩት። ድንጋዩ ገብቶ ውሃው ተረጨ፣ ሞገዱም ተነሳ፤ ነገር ግን ተራራው ግን ምንም ሳይንቀሳቀስ ባለበት ጸንቶ ቆመ። ሽማግሌውም ወጣቱን እንዲህ አሉት፦ ልጄ ይህ ወንዝ መቀየር የማይችሉት ነገሮች ምሳሌ ነው። የሰውን ሐሳብ፣ የአየር ሁኔታውን፣ የጊዜን መለዋወጥ እና የውጭ ዓለምን ሁኔታዎችን መቆጣጠር አንችልም። እነሱ ልክ እንደ ወንዙ ሁልጊዜ ይፈሳሉ፣ ይለዋወጣሉ፣ አንዳንድ ጊዜም አውሎ ነፋስ ይሆናሉ። ይህ ተራራ ደግሞ የእኛ ውስጣዊ ልብ እና አዕምሮ ምሳሌ ነው። ውጭ የሚሆነውን ነገር ማቆም አንችልም ነገር ግን በውስጣችን ያለውን የሰውን ማንነት እና ጽናት መምረጥ እንችላለን። ማያ አክለውም “ሰዎች ብዙ ጊዜ ኃይላቸውን የሚያባክኑት የማይለወጡትን ነገሮች ለመለወጥ በመጣላት ነው። ሰንሰለቱን ለመስበር ትሞክራለህ እንጂ ሰንሰለቱ የታሰረብህን እጅ መቆጣጠር ትረሳለህ” ጥበብ ማለት ሊለወጡ የሚችሉትን ነገሮች የመለወጥ ኃይል የማይለወጡትን ደግሞ በጸጋ የመቀበል ልብ እና ሁለቱን መለየት የሚችል ማስተዋል መኖር ነው አሉት፡፡ ✍️ዮናስ @enlighten_ethiopia
Open in Telegram#የሰው_ልጅን_የሚለውጡ_ልማዶች !! 1. የአቶሚክ ልማዶች (Atomic Habits)፦ ትናንሽና ተከታታይነት ያላቸው ለውጦች በረጅም ጊዜ ውስጥ ትልቅ ውጤት ያመጣሉ። 2. በማንነት ላይ ያተኮረ ልማድ (Identity-Based Habits)፦ ልማድን ለመቀየር "ምን ማግኘት እፈልጋለሁ?" ከሚለው ይልቅ "ምን ዓይነት ሰው መሆን እፈልጋለሁ?" በሚለው ላይ ማተኮር። 3. አራቱ የባህሪ ለውጥ ህጎች (The Four Laws)፦ ማንኛውንም ልማድ ለመገንባት ግልጽ ማድረግ፣ ማራኪ ማድረግ፣ ቀላል ማድረግ እና አርኪ ማድረግ። 4. ልማድ መደራረብ (Habit Stacking)፦ አዲስ ልማድን ቀድሞ በነበረና በለመድነው ልማድ ላይ መጨመር። 5. አካባቢን ማስተካከል (Environment Design)፦ ለጥሩ ልማዶች ግልጽ የሆኑ ምልክቶችን በአካባቢያችን ማዘጋጀት 6. የሁለት ደቂቃው ህግ (The Two-Minute Rule)፦ ማንኛውንም አዲስ ልማድ ሲጀምሩ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ሊያልቅ በሚችል ቀላል ስራ መጀመር። 7. የማይመች ማድረግ (Make it Difficult)፦ መጥፎ ልማዶችን ለማቆም በመንገዳችን ላይ እንቅፋቶችን መፍጠር። አጫሽ ከሆንክ ለማጨስ በማይመች ቦታ መዋል። 8. ልማድን መከታተል (Habit Tracking)፦ የምናደርጋቸውን ስራዎች መዝግቦ መያዝ ስኬታማነታችንን እንድናውቅ ይረዳናል። 9. ወዲያውኑ የሚገኝ እርካታ (Instant Gratification)፦ አእምሯችን ለወደፊት ከሚገኝ ጥቅም ይልቅ አሁን ለሚያገኘው ደስታ ቅድሚያ ስለሚሰጥ፣ ለጥሩ ልማዶች አነስተኛ ሽልማቶችን ማዘጋጀት። 10. መሰላቸትን ማሸነፍ (Goldilocks Rule)፦ ልማዶች በጣም አስቸጋሪ ወይም በጣም ቀላል ሳይሆኑ፣ ተግዳሮት ያለባቸው ሲሆኑ ይቀጥላሉ። 📖 "Atomic Habits" ✍️ጄምስ ክሊር @enlighten_ethiopia
Open in Telegram🛑 #የዘገየ_ትክክለኛ_ውሳኔ... ራሱ ሌላ ስህተት ነው! (The Law of Timing) "አንድን ውሳኔ በትክክለኛው ጊዜ ካልወሰንከው፣ በኋላ ላይ መቶ በመቶ ትክክለኛ ቢሆን እንኳ ዋጋ የለውም፤ ምክንያቱም ጊዜው አልፏል።" ብዙ ሰው በሕይወቱ ስህተት ላለመሥራት በሚል ሰበብ አንድን ነገር ለማድረግ ለወራትና ለዓመታት ያስባል። "ሁሉንም ነገር አጥንቼና እርግጠኛ ሆኜ ነው የምወስነው" ይላል። እውነቱ ግን ይህንን ነው፦ "ፍጹም የሆነውን ቀን ለመጠበቅ ስትል የምታዘገየው እያንዳንዱ ትክክለኛ ውሳኔ፣ ዕድሉ ካለፈ በኋላ ምንም ዓይነት ውጤት ስለማያመጣ በራሱ ትልቅ ስህተት ነው።" ✅ ስኬት የሐሳብ ጥራት ብቻ አይደለም፤ የስሌትና የሰዓት (Timing) ጉዳይም ጭምር ነው። ልክ ከ3 ዓመት በፊት መጀመር የነበረብህን አንድ የዲጂታል ቢዝነስ ወይም ኢንቨስትመንት፣ ዛሬ ላይ ቆመህ "አሁን በሚገባ አጥንቼ ገባሁበት" ብትል እንኳ ያኔ ልታገኘው የምትችለውን ትልቅ የዕድገት ማዕበልና ጥቅም አታገኘውም። ውሳኔው ዛሬም ትክክል ሊሆን ይችላል ፤ ሰዓቱ ግን ስህተት ነው። በጦር ሜዳ ላይ ጥይት ካለቀ በኋላ የሚተኮስ እጅግ ምርጥ ኢላማ እንደማይጠቅመው ሁሉ፣ ዕድሎች ካለፉ በኋላ የሚወሰን "ትክክለኛ ውሳኔ" የቁጭት መሸፈኛ ጭምብል ብቻ ነው። ✅ ፍጽምና ወጥመድ ነው፦ ሁሉንም ነገር አውቄ እጀምራለሁ ስትል ጊዜው ይቀድምሃል። ፍጹም ዝግጁ ለመሆን አትጠብቅ ፤ ውሳኔህን ዛሬውኑ አውጅ። ✅ የፍጥነት ዋጋ ከፍ ያለ ነው፦ በዘመናዊው ዓለም ውስጥ ቀስ ብሎ በትክክል ከሚራመደው ይልቅ፣ ፍርሃቱን ተቋቁሞ በፍጥነት ወስኖ ስህተቱን በመንገድ ላይ የሚያርመው ቆራጥ ሰው ቀድሞ ግቡ ላይ ይደርሳል። ✅ ጊዜ ዕድልን ይበላል፦ ዛሬ ያመነታህበትና ወደኋላ ያልከው ዕድል፣ ነገ ሌላ ሰው ቀድሞህ ወስኖበት ታሪክ ሲሠራበት ማየትህ አይቀሬ ነው። ታላላቅ የዓለማችን መሪዎችና ባለሀብቶች በሙሉ መቶ በመቶ እርግጠኛ እስኪሆኑ የጠበቁ አይደሉም፤ የጊዜን ውድነት ተረድተው "አሁንኑ" በሚል ፍጥነት የወሰኑ ጀግኖች እንጂ። አንተስ? ዛሬም ውሳኔህን በማዘግየት ላይ ነህ? @enlighten_ethiopia
Open in Telegramየህይወት ህግ!! ህይወት በራሷ መንገድ የምትመራባቸው የየራሷ ህጎች አሏት። ከእነዚህም መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ሁለት ትላልቅ እና የማይለወጡ ወርቃማ ህጎች አሉ። የሚያስደንቀውና ደስ የሚለው ነገር ግን፣ ከእነዚህ ሁለት ህጎች መካከል የትኛውን መርጠን መጓዝ እንዳለብን ሙሉ ምርጫው ለራሳችን መሰጠቱ ነው! ይህም እኛ ምን ያህል እድለኞች መሆናችንን ያሳያል። እነዚህ ሁለት ወርቃማ ህጎች የሚከተሉት ናቸው፡- 1. "Pay now, play later" (በቅድሚያ መክፈል፣ በኋላ ላይ መጫወት/መደሰት) ይህ ህግ "ዛሬ ዋጋህን ክፈልና ነገ ትደሰታለህ" የሚል ትርጉም አለው። 👉ጥልቅ ሀሳብና ውጤቱ፡ ይህንን መንገድ የሚመርጡ ሰዎች ዛሬ ላይ ምቾታቸውን መስዋዕት ያደርጋሉ። ለህልማቸው ሌሊት ይተጋሉ፣ እውቀት ይገበያሉ፣ በዲሲፕሊን ራሳቸውን ይገነባሉ እንዲሁም ገንዘብና ጊዜያቸውን ባልረባ ነገር ላይ ከማባከን ይቆጠባሉ። የዚህ ምርጫ ውጤት ዘላቂ ስኬት፣ የውስጥ ሰላም እና በነጻነት የሚመራ ድንቅ ህይወት ነው። ዛሬ የዘሩትን መራራ የስራ ፍሬ ነገ በደስታ ያጭዱታል። 2. "Play now, pay later" (በቅድሚያ መጫወት/መደሰት፣ በኋላ ላይ መክፈል) ይህ ህግ ደግሞ "ዛሬ ተደሰትና ዋጋውን ነገ ትከፍላለህ" ማለት ነው። 👉ጥልቅ ሀሳብና ውጤቱ፡ ይህንን መንገድ የሚመርጡ ሰዎች የዛሬውን ጊዜያዊ ስሜት እና የቅፅበት መዝናናትን ብቻ ያስቀድማሉ። ለነገ እቅድ የላቸውም፤ ራሳቸውን ከማሳደግ ይልቅ ውጫዊ ገጽታና ጊዜያዊ ደስታ ላይ ያተኩራሉ። ነገር ግን የዚህ ምርጫ ውጤት ከባድ ነው። ጊዜው አልፎ እድሜው ሲገፋ፣ ትላንት ያልከፈሉት ዋጋ ዛሬ ላይ ተከማችቶ በትልቅ እዳ፣ በቁጭትና በችግር መልክ እንዲከፍሉ ያስገድዳቸዋል። ውድ ምርጫችን! ህይወት ፍትሃዊ ናት፤ ዋጋ ሳያስከፍሉ ስኬትን አትሰጥም። ልዩነቱ ዋጋውን የምንከፍልበት ጊዜ ላይ ብቻ ነው። ዛሬ በፈቃደኝነት በዲሲፕሊን መኖር ካልመረጥን፣ ነገ በግዴታ በቁጭት ዋጋ መክፈላችን የማይቀር ነው። ደግነቱ ግን ዛሬ እጃችን ላይ ትልቅ እድል አለ፤ የትኛውን ህግ እንደምንከተል የመወሰን ስልጣኑ ሙሉ በሙሉ የራሳችን ነው። @enlighten_ethiopia
Open in Telegram#እርምጃ_ውሰዱ_እንጂ !!! አንድ ሰው አጠገቡ ለነበሩ ሰዎች በጨዋታ መልክ እንዲህ ሲል ጥያቄን አቀረበ፡- “በአንድ መሬት ላይ በተጋደመ ትልቅ ግንድ ላይ ሶስት እንቁራሪቶች በመደዳ ቆመው ነበር፡፡ አንደኛዋ እንቁራሪት ቆመው ከነበረበት ግንድ ላይ ወደ መሬቱ ለመዝለል ወሰነች፡፡ ስንት እንቁራሪቶች ግንዱ ላይ ቀሩ?” ይህንን ጥያቄ የሰሙት በሙሉ መልሳቸው፣ “ሁለት” የሚል ነበር፡፡ ሰውየውም መልሳቸው ትክክል እንዳልሆነ ገለጸላቸው፡፡ “አንዷ እንቁራሪት የመዝለል ውሳኔ አደረገች እንጂ አልዘለለችም፡፡ ስለዚህ አሁንም የቀሩት ሶስት እንቁራሪቶች ናቸው” ነበር ማብራሪያው፡፡ “አያችሁ”፣ አለ በመቀጠልም፣ “ይህ የሚያመለክተው ውሳኔን ከተግባር ጋር የማምታታት ዝንባሌያችንን ነው፡፡ አንድ ውሳኔ ወደተግባር እስኪለወጥ ድረስ ከውሳኔው በፊት ከነበርንበት ሁኔታና ደረጃ ትንሽም እልፍ አያደርገንም”፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አንድን ነገር ለማድረግ ብዙ ካወጣን፣ ካወረድንና ከወሰንን በኋላ ልክ እንዳደረገ ሰው ኑሯችንን እንቀጥላለን፡፡ ውሳኔ ግን ያው ውሳኔ እንጂ ተግባር ማለት አይደለም፡፡ ለዚህ አይነቱ አደገኛ ልምምድ አጋልጠው ከሚሰጡ ሁኔታዎች መካከል . . . 1. ፍርሃት አንድን ነገር ገና ሳንጀምረው፣ “ባይሳካስ” የሚል ፍርሃት የሚያጠቃን ከሆነ፣ ሁኔታው ቢሳካ የምናገኘውን ጥቅም ሳይሆን ባይሳካ የሚደርስብንን ጉዳት፣ ሃፍረትና የመሳሰሉት ነገሮች ነው የምናሰላስለው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ያሰብነውን ነገር ከመጀመር ይገታናል፡፡ መፍትሄው፡- ጥንቃቄ በተሞላው እና ትርፍና ኪሳራን ባመዛዘነ መልኩ ፍርሃትን መጋፈጥ ነው፡፡ 2. ለነገ አስተላላፊነት ለነገ የማስተላለፍ ልማድ አንዳንድ ጊዜ ከፍርሃት ጋር ቢገናኝም ሌሎች ምክንያቶች ግን አሉት፡፡ ለምሳሌ፣ ለመጀመር ባሰብነው ነገር ላይ በቂ ክህሎት እንደሌለን ማሰብና በራስ አለመተማመን፣ የዲሲፕሊን ችግር፣ የሰዎችን ሃሳብ እየሰሙ ሃሳብን መለዋወጥ፣ በወቅቱ ስሜትና “ሙድ” ተጽእኖ ስር መውደቅ እና የመሳሰሉት፡፡ መፍትሄው፡- አንድን ነገር እንድናስተላለፍ የሚያደርግን ችግራችን ምን እንደሆነ መለየትና በማንበብ፣ በመሰልጠንና በመሳሰሉት መንገዶች መቅረፍ፡፡ 3. ዓላማ ቢስነት አንድ ለመጀመር ወይም ለማድረግ የምንፈልገው ነገር በመጨረሻ ከአንድ ማከናወን ከምንፈልገው ዋና ዓላማ ጋር የተነካካ ካልሆነ በውስጣችን ግለትና ጉጉት ስለሚጎድለን እርምጃን የመውሰድ አቅም አይኖረንም፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ዋነኛው የመነቃቃት (Motivation) ምንጭ የሕይወት ዓላማ ማወቅ ስለሆነ ነው፡፡ መፍትሄው፡- የምናደርጋቸውን ነገሮች በሙሉ ከዋናው የሕይወታችን ዓላማ ጋር ወይም ከአንድ ወሳኝ ግብ ጋር መያያዙን እርግጠኛ መሆን፡፡ ዶ/ር እዮብ ማሞ @enlighten_ethiopia
Open in Telegramራስህን በፀፀት አለንጋ መግረፍህን አቁም። እናንተ "ጸጸት" የምትሉት ነገር አእምሯችሁ ራሱን ቅዱስ ለማድረግ የሚጠቀምበት ሌላኛው የውሸት ጭንብል ነው። "ያኔ ያንን ባላደረግኩት፣ ያንን ስህተት ባልሰራሁት፣ ያንን ሰው ባላስቀየምኩት" እያልክ ትላንት በሞተው ታሪክ ላይ ዛሬህን ትገብራለህ። ያ የአእምሮህ ጨዋታ እንጂ ንቃት አይደለም። ትላንትናን መለወጥ አትችልም፤ ነገር ግን በትላንትናው መቃብር ላይ ቁጭ ብለህ ስታለቅስ፣ አሁን በአጠገብህ እያለፈች ያለችውን ህይወት በገዛ እጅህ ትገድላታለህ። አንድ እውነተኛ ገጠመኝ ልንገራችሁ። አንድ ቀን በህይወቱ በሰራው አንድ ትልቅ ስህተት ምክንያት ለዓመታት ራሱን ሲወቅስ የኖረ፣ ፊቱ ላይ ታላቅ ስቃይ የሚታይበት ሰው ወደ እኔ መጣ። "ከዓመታት በፊት አንድ የቅርብ ጓደኛዬን ከዳሁት። ከዚያ ቀን ጀምሮ ውስጤ ሰላም አጣ። በየቀኑ ራሴን እረግማለሁ። እባክህ ይህንን የውስጤን የጸጸት እሳት እንዴት ላጥፋው?" አለኝ እኔም ትኩር ብዬ አየሁትና ፈገግ አልኩ። "ችግርህ እኮ ያኔ የሰራኸው ስህተት አይደለም፤ ችግርህ ያ የሞተው 'አንተ' ዛሬም በህይወት ያለ መስሎ መታየትህ ላይ ነው። ያኔ ያንን ስህተት የሰራኸው በዚያን ጊዜ በነበረህ የንቃት ደረጃ (Awareness) ልክ ነበረ። ዛሬ ላይ ቆመህ ትላንትናን ስትወቅስ ግን ራስህን እንደ እግዚአብሔር ፍጹም አድርገህ እያሰብክ ነው። ይህ ደግሞ ያንተ 'እኔነት' (Ego) እንጂ መጸጸት አይደለም" አልኩት። ያለፈው ነገር አልፏል፤ ድንጋይ ሆኗል። ድንጋዩን በትከሻህ ላይ ተሸክመህ ብትዞር የሚደክመው ያንተ ትከሻ እንጂ ድንጋዩ አይቀልጥም። የትላንትናውን አስክሬን የመሸከም ውጫዊ እብደታችሁን አቁሙ። ልክ እንደ መኸር ዛፍ ሁኑ። የደረቁ ቅጠሎች ከዛፉ ላይ ሲረግፉ፣ ዛፉ ስለወደቁት ቅጠሎች አያለቅስም፣ አይቆጭም። ቅጠሎቹ መውደቃቸው ተፈጥሮአዊ ነው። ዛፉ ግን ወደ አዲሱ የጸደይ ወቅት ያያል፣ አዳዲስ ቅጠሎችንና አበባዎችን ያበቅላል። ህይወት ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አትፈስም። ያለፈውን ስህተትህን እንደ ትልቅ የትምህርት ቤት መጽሐፍ ተመልከተው እንጂ እንደ ሰንሰለት አታድርገው። ከእሱ ተማር፣ ወደ ህልውናው ዝምታ ተመለስ፣ ከዚያም እራስህን ይቅር በል። አሁን በዚህች ቅጽበት አዲስ ነህ። ከአሮጌው ታሪክህ ነጻ ስትሆን፣ ያኔ እውነተኛውን መለኮታዊ ብርሃንና ውስጣዊ ሰላም ታገኛለህ። ራስህን ፍታው! "ትላንትና የታተመ መጽሐፍ ነው፣ ገጹን ማስተካከል አትችልም። አሁን ግን ንጹህ ነጭ ወረቀት በእጅህ ላይ አለ። በትላንትናው ቀለም የዛሬውን ወረቀት አታቆሽሸው፤ አሁንህን አዲስ አድርገህ ጻፈው።" — ኦሾ @enlighten_ethiopia
Open in Telegram“የሕይወታችን ጥራት የሚወሰነው በውሳኔዎቻችን ጥራት ነው” ይባላል! በጊዜ ሂደት ደጋግመን የምናደርጋቸው ምርጫዎች፤ ግንኙነታችንን፣ ጤናችንን፣ ፋይናንሳችንን (የኢኮኖሚ ደህንነታችንን) እና በመጨረሻም ባህሪያችንንና ማንነታችንን ይቀርጻሉ። ትልቅም ይሁን ትንሽ፣ እያንዳንዱ ውሳኔ የራሱ የሆነ ውጤት አለው። አንድ ነጠላ ውሳኔ እምብዛም አስፈላጊ እንዳልሆነ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን የበርከቶች ዕለታዊ ምርጫዎች ድምር ውጤት የሕይወታችንን አቅጣጫ እና ጥራት ይወስናል። መልካም ውሳኔዎች አወንታዊ ውጤቶችን የማስገኘት ዝንባሌ ያላቸው ሲሆን፣ ደካማ ውሳኔዎች ደግሞ ብዙውን ጊዜ ወደማይፈለጉ መዘዞች ይመራሉ ። ሕይወት በአንድ አስገራሚ ውሳኔ ብቻ የመቀየር አጋጣሚዋ ጠባብ ነው። ይልቁንም፣ ቀስ በቀስ ወደ ልማድ በሚቀየሩ ወጥ የሆኑ ዕለታዊ ምርጫዎች የምትቀረጽ ናት። እነዚህ ልማዶች ባህሪያችንን ይገነባሉ፣ ባህሪያችን ደግሞ ዕጣ ፈንታችንን ይወስናል። ይህንን አንዘንጋ . . . የወደፊት ሕይወታችን በአብዛኛው ዛሬ የምናደርጋቸው ውሳኔዎች ውጤት ነው። የሕይወታችንን ጥራት ማሻሻል ከፈለግን፣ መጀመሪያ የውሳኔዎቻችንን ጥራት በማሻሻል እንጀምር። ዛሬ እነዚህን ጥያቄዎች ለመጠየቅና ለመመለስ እንሞክር * እስካሁን በሕይወቴ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ያሳደሩት አስፈላጊ ውሳኔዎች የትኞቹ ናቸው? * ዕለታዊ ምርጫዎቼን ወደ ግቦቼ እያስጠጉኝ ነው ወይስ ከግቦቼ እያራቁኝ? * ለወደፊት ሕይወቴ አወንታዊ ተጽዕኖ ሊያበረክት የሚችል፣ ዛሬ ልወስነው የምትችለው አንድ ውሳኔ ምንድን ነው? * የበለጠ ጥበባዊ ውሳኔዎችን የማድረግ ልማድን እንዴት ማዳበር እችላለሁ? እያንዳንዱ ምርጫችን፣ ወደፊት ለምንሆነው ማንነትና ለምንኖረው ኑሮ እጅግ ወሳን መሆኑን አንዘንጋ፡፡ ✍️ ዶ/ር እዮብ ማሞ @enlighten_ethiopia
Open in Telegram#የቆራጥነት_ኃይል_በውሳኔ_ማዕበል_ውስጥ_የማይናወጠው_ማንነት! "የተሳሳተ ውሳኔ መወሰን፣ ምንም አለመወሰን ከሚመጣው ውድመት ይሻላል!" በህይወታችን ውስጥ ብዙ ጊዜ እድሎችን የምናጣው፣ ህልሞቻችን የሚቀበሩትና ወደኋላ የምንቀረው በአቅም ማነስ ሳይሆን "ነገ እወስናለሁ" በሚል ማቅማማት ነው። ቆራጥነት (Decisiveness) ማለት ፍጹም የሆነ ጊዜ ወይም መቶ በመቶ አስተማማኝ ሁኔታን መጠበቅ ሳይሆን፣ ያሉትን አማራጮች አመዛዝኖ ውሳኔዎችን በድፍረትና በወቅቱ መወሰን መቻል ነው። ማቅማማትና መፍራት የጊዜ ሌቦች ናቸው! 📌 ቆራጥ ሰዎችን ከሌላው የሚለዩ 3 ወሳኝ ባህሪያት፦ 1-መወሰን ያለበትን ነገር በጊዜው ይወስናሉ። ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ትልቁ ጥንካሬያቸው ነው። 2-ቆራጥ መሪዎች ወይም ግለሰቦች ውሳኔያቸው ስህተት ቢሆን እንኳ ሰበብ አይፈልጉም፤ ከስህተታቸው ተምረው በፍጥነት ይስተካከላሉ እንጂ ሌላውን አይወቅሱም። 3-ባለፈው ነገር ላይ ከማዘን ይልቅ፣ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ላይ ተመስርተው ቀጣዩን እርምጃ በድፍረት ይራመዳሉ። ወዳጆቼ ሕይወት ምርጫ ነች። በቆራጥነት የማትመራው ሕይወት በሌሎች ሰዎች ውሳኔና በሁኔታዎች እንድትመራ ያደርግሃል። እውነተኛ ቆራጥነት የሚጀምረው ፍርሃትን አሸንፎ የመጀመሪያውን እርምጃ ለመውሰድ ከመደፈር ነው። ውሳኔህ ያንቀሳቅስሃል፣ እንቅስቃሴህ ደግሞ ወደ ስኬት ያደርስሃል። ለማቅማማት ጊዜ የለህም፤ አሁኑኑ በድፍረት ወስን! @enlighten_ethiopia
Open in Telegram⭕ለምን መጀመር አቃተን? (የስኬት ትልቁ ጠላት መዘግየት ነው) ለምን እንዘገያለን 1.#የውድቀት_ፍርሃት (Fear of Failure) ባልሳካስ? ሰው ምን ይለኛል? የሚለው ስጋት እግራችንን ያስረናል። ያስርሃል። ካልጀመርን ቀድሞውኑ ወድቀናል። ውድቀት መማሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም። ይህ እውነታ መቀበል አለብን። 2. #ራስን_ዝቅ_አድርጎ ማየት (Self-Image) እኔ ይህን ለማድረግ ብቁ አይደለሁም ወይም ይህ ለኔ አይሆንም የሚሉ የውስጥ ድምጾች አቅማችንን ያፍኑታል። ማንም ተወልዶ አልተማረም። ብቃት የሚመጣው በሂደት እንጂ ከመነሻው አይደለም። ይህን ለሾፌሮች ጠይቋቸው ስንቴ እንደተላተሙ ግን አሁን ጀግኖች ሆነው ሌትና ቀን በረሀና ከተማ እንደፈለጉ እንደሚነዱ!! 3. #ፍጹምነትን_መፈለግ (Perfectionism) ሁሉ ነገር እስኪሟላ፣ በቂ ገንዘብ እስኪኖር ወይም "ትክክለኛው ጊዜ" እስኪመጣ መጠበቅ ትልቁ ወጥመድ ነው። #Perfect የሆነ ጊዜ የለም። ባለህ ነገር ጀምር፤ መንገዱ ራሱ ጎደሎውን ይሞላዋል።እምትጠብቀውን perfect እዛ ታገኘዋለህ። 4. በስሜት መመራት (Waiting for the "Mood") "ዛሬ ስሜቱ የለኝም" እያልን ተነሳሽነትን (Motivation) መጠበቅ። #ስሜት_ስራን_አይወልድም፤ #ስራ_ግን_ስሜትን_ይወልዳል። ዝም ብለህ ግባበት፣ ስሜቱ ይከተልሃል። ተማሪ ሆኜ ዛሬ የማንበብ ስሜቴ ሞተዋል ብየ ከፈተናው ውጤት አብሬው ስሞቴ አስታውሳለው።ስራውን ጀምረው ስሜት እራሡ ይመጣል። 5. #በሃሳብ_መጥገብ (Overthinking) ቀንና ሌሊት ስለ ጉዳዩ በማሰብ ብቻ አእምሮህን ማድከም። የገኝሀው እስክትመስል ሁሌ Coming Soon" እያልክ ስራው ሳትጀምረው ግዜህና እድሜህ ይሮጣሉ።ብዙ ባሰብክ ቁጥር የሚያስፈሩ እንቅፋቶች በብዛት ይታዩሃል። እቅድ ማውጣት ጥሩ ነው፣ ግን ተግባር የሌለው እቅድ ቅዠት ነው። #የሚገርም_ሃሳብ_ኖሮህ_ከመሞት፣ #ተራ_ሃሳብ_ኖሮህ_ሞክረህ_መውደቅ_ይሻላል። ዛሬውኑ የመጀመሪያውን እርምጃ ውሰድ! "መጀመር የስኬት ግማሽ መንገድ ነው!" @enlighten_ethiopia
Open in Telegram"ለመጀመር ከብዶሃል? የሮኬቱንም ምስጢር እወቅ!" አንድ ሮኬት ወደ ህዋ ለመመንጠቅ የሚጠቀመው የነዳጅ መጠን እጅግ አስገራሚ ነው። ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ አንድ ሮኬት ካለው አጠቃላይ ነዳጅ ውስጥ 80 በመቶውን (80%) የሚጨርሰው ገና ከመሬት ተነስቶ የመጀመሪያዎቹን ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ለመጓዝ ብቻ ነው! 1. "The Struggle of Starting" (የመጀመሪያው ትግል)፦ ሮኬቱ ከመሬት ስበት (Gravity) ለማምለጥ እጅግ ከፍተኛ ኃይል ያስፈልገዋል። አንዴ ያንን የስበት ክልል አልፎ ህዋ ውስጥ ከገባ በኋላ ግን ያለ ምንም ነዳጅ በከፍተኛ ፍጥነት መንሳፈፍ ይችላል። • የሕይወት ትምህርቱ፦ ማንኛውም አዲስ ስራ፣ ለውጥ ወይም ልምድ ሲጀመር እጅግ ከባድ የሚሆነው ለዚህ ነው። አቅምህ በሙሉ የሚጨርሰው "ለመጀመር" ነው። አንዴ የስንፍና እና የልማድ ስበትን ከሰበርክ በኋላ ግን ጉዞው ቀላል ይሆንልሃል። 2. "Escape Velocity" (የማምለጫ ፍጥነት)፦ አንድ ሮኬት ከመሬት ስበት ወጥቶ ህዋ ለመድረስ በሰዓት 40,000 ኪሎ ሜትር ፍጥነት መጓዝ አለበት። ይህ ካልሆነ ግን መሬት መልሳ ትጎትተዋለች። • ለአንተ፦** ለውጥ ስትጀምር በግማሽ ልብ አትጀምር። ግማሽ ጉልበት ከተጠቀምክ የድሮ ልማድህ መልሶ ይጎትተሃል። መላ አቅምህንና ትኩረትህን ተጠቅመህ ያንን "የማምለጫ ፍጥነት" መፍጠር አለብህ። ** 3. "Once You Are Out" (አንዴ ከወጣህ በኋላ)፦ ሮኬቱ ህዋ ውስጥ ሲገባ የቀረችውን 20% ነዳጅ ተጠቅሞ ጨረቃ ወይም ማርስ ድረስ መጓዝ ይችላል። • ሳይንሳዊ ሀቅ፦ ትልቁ ስራህ ዛሬ የምታደርገው "መጀመር" ነው። ዛሬ የምታሳየው ጽናትና የምታባክነው ጉልበት ከንቱ አይደለም፤ ወደ ነፃነትህ ክልል የሚያወጣህ ብቸኛው መንገድ ነው! ፦ ለመጀመር መክበዱ የውድቀት ምልክት ሳይሆን፣ የስበትን ህግ እየጣስክ መሆኑን ማሳያ ነው። ዛሬ 80% ጉልበትህን ተጠቅመህ ጀምር፤ ነገ በነፃነት ትጓዛለህ! @enlighten_ethiopia
Open in Telegram የራስን ስሜት የመግዛት 8 ጥበቦች (Mastering Self-Control) 1. የ10 ደቂቃው ህግ (The 10-Minute Rule) አንድን መጥፎ ፍላጎት "አላደርገውም" ብለህ አትታገለው፤ ይልቁንም "ከ10 ደቂቃ በኋላ አየዋለሁ" በለው። ያ የግርግር ስሜት በ10 ደቂቃ ውስጥ ይበርዳል። ጭንቅላትህም ውሳኔ የመስጠት አቅሙን ይመልሳል። 2. ራስህን ይቅር በል (Forgive Your Slips) ራስን መቆጣጠር ማለት ስህተት አልባ መሆን አይደለም። ስህተት በሰራህ ቁጥር ራስህን ከወቀስክ ይበልጥ ወደ ስህተቱ ትገፋለህ። ይልቁንም "ሰው ነኝ ተሳስቻለሁ፣ አሁን ግን እመለሳለሁ" በል። ይቅርታ ለለውጥ መንገድ ይከፍታል። 3. ከባዱን ቀድመህ ጨርስ (Eat the Frog!) የመወሰን አቅምህ (Willpower) እንደ ስልክ ባትሪ ጠዋት ሙሉ ነው፤ ማታ ላይ ግን ያልቃል። ስለዚህ ከባዱንና የሚጨንቅህን ስራ ጠዋት ገና ሳይረፍድ ጨርሰው። ከራስህ ጋር አትከራከር፣ ዝም ብለህ ጀምረው! 4. አካባቢህን አስተካክል (Design Your Environment) "ላለመብላት" ከመታገል ይልቅ "ምግቡን ከፊትህ ማራቅ" ይቀልሃል። ስራ ስትሰራ ስልክህን ሌላ ክፍል አስቀምጥ። ትክክለኛውን ምርጫ ቀላል፣ ስህተቱን ደግሞ ከባድ አድርገው። 5. "አልችልም" ሳይሆን "አላደርግም" (Identity Shift) "ኬክ መብላት አልችልም" ስትል ተገዳጅ ነህ። "እኔ ኬክ አልበላም" ስትል ግን ይሄ ማንነትህ ነው። ቃላትህን ቀይር፤ ማንነትህንም አብረህ ትቀይራለህ። 6. "ለምን?" የሚለውን አጥብቀህ ያዝ (Master Your "Why") የምትታገለው ለምንድነው? ዝም ብሎ "መስራት" አሰልቺ ነው። ነገር ግን "የቤተሰቤን ህይወት ለመቀየር" ወይም "ነጻነቴን ለማግኘት" ስትል ትጋቱ ጣፋጭ ይሆናል። ሰበብህ ከስሜትህ በላይ ይሁን። 7. የእንቅልፍ ሚስጥር (The Sleep Hack) አንጎልህ ሲደክም ስሜትህን የመቆጣጠር አቅሙ ዜሮ ይሆናል። በቂ እንቅልፍ ካልተኛህ ለሱሶችና ለስንፍና ትሸነፋለህ። ጥሩ እንቅልፍ የዲሲፕሊን መሰረት ነው። 8. ራስህን በፈቃድህ ፈትን (Voluntary Hardship) ሁልጊዜ ምቾት አትፈልግ። አልፎ አልፎ ቀዝቃዛ ውሃ ተታጠብ፣ ራቅ ያለ መንገድ በእግርህ ሂድ። ትንንሽ ምቾቶችን መተው ትልልቅ ፈተናዎችን የምትጋፈጥበትን የአዕምሮ ጡንቻ ይገነባል። via -bigonlinetips
Open in Telegramለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!! መልካም በአል!!
Open in Telegram