Account

Posts of ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

newest first

#8494Photo

ይህ ወንድማችን በርካታ ማስታወቂያዎችን እየሰራ ነው፣ አንድ ሰው በቅርብ እንዳጫወተኝ ከታች ተነስቶ በቅርቡ ሰርግ ላይ በተለቀቀ አንድ ቪድዮ ምክንያት ተወዳጅ ሆኗል፣ መልካም ነው። ከተሰሩት ማስታዊቂያዎች መሀል ግን ይህ የካናዳ እና የውጭ ጉዞ ማማከር... ወዘተ የሚል እንዲሁም ማስታወቂያው ላይ "በኢትዮጵያ ብቸኛው ከካናዳው IRCC ፈቃድ ያለው" የሚል ይገኝበታል። ይህ አሳሳች የሆነ እንዲሁም ብዙ ህዝብ እንዲጭበረበር ምክንያት ሊሆን የሚችል ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ ቼክ በኩል የካናዳ ኤምባሲን ደጋግመን ስንጠይቅ እንደነገረን እንዲህ አይነት የማጭበርበርያ ስልቶች እንጂ የካናዳ መንግስትም ሆነ ኤምባሲው ከማንም የሀገር ውስጥ ኤጀንት ጋር ስራ አይሰራም፣ ፈቃድም አይሰጥም። ካናዳ የሰው ሀይል ሲያስፈልጋት በመንግስት ተቋሞቿ እና አብራቸው በምትሰራቸው አለም አቀፍ ኤጀንሲዎች በኩል እንጂ በደላሎች ወይም በቲክቶክ እና ቴሌግራም በሚያስተዋውቁ ግለሰቦች እንዳልሆነ የካናዳ ኤምባሲ በአንድ ወቅት ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቆ ነበር። የካናዳ ፍቃድ ያላቸውን ወኪሎች በተመለከተ የበለጠ ለመረዳት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይከተሉ እና ራስዎን ከአላስፈላጊ ወጪ ይጠብቁ: https://www.canada.ca/en/immigration-refugees-citizenship/services/immigration-citizenship-representative/learn-about-representatives.html ማስታወቂያውን የሰራው ወንድማችንን የምታውቁም ቪድዮው የለፍቶ አዳሪ ህዝብን ገንዘብ አስበልቶ እንደ ፊንቴክ አስተዋዋቂ አርቲስቶች ችግር ውስጥ እንዳይገባ ጠቁሙት። @EliasMeseret

Open in Telegram
Views64,800+10%vs avg
Forwards—
Reactions1,217
Comments—
#8493Photo
Views59,800+2%vs avg
Forwards—
Reactions1,393
Comments—
#8491Photo

ልክ የዛሬ አንድ ወር ገደማ ይህን መረጃ አጋርቼ ነበር። ታድያ በወቅቱ አንድ የመንግስት ሹም "ፍፁም ውሸት ነው፣ አንድም የካቢኔ አባል በአምባሳደርነት አይሾምም፣ እንደውም ምርመራ እየተደረገ ነው" ብለው በውስጥ መልዕክት ልከው ነበር። ዛሬ ግን ይፋ የተደረገው እውነታውን አረጋግጧል ⤵️ "ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሙስና፣ በሌብነት እና የህዝብን ሀብት በመበዝበዝ የተደረሰባቸው የካቢኔ አባላት አሉ ብለዋል... ይሁንና እነዚህኑ ግለሰቦች መልሶ አምባሳደር እና ዲፕሎማት አድርጎ መሾም ምን ማለት ይሆን? አንድ ወይም ሁለት ሳይሆን በርካታ ከስልጣን ተነሺዎች በዲፕሎማትነት ወደ ውጪ እንደሚላኩ መረጃዎች ደርሰውኛል፣ አንደኛውማ 'ቻይና ልመደብ ስለሆነ እዛው እንቀጥለዋለን' በማለት ለሀገር ውስጥ እና ለቻይና ባለሀብቶች መናገር ጀምረዋል። ሌባ ቢሆኑም ዲፕሎማት ተደርገው ቢላኩ ብዙም ብር ስለሌለው አይሰርቁም በሚል ስሌት ይሆን? ሌባ ለአመሉ እንዲሉ መስረቅ የለመደ የኤምባሲዎችን ጣርያ ነቅሎ ሊሸጥ ይችላል። ከሁሉም በላይ ግን ዲፕሎማትነትን እና ዲፕሎማሲያችንን የሰረቀ የሚላክበት፣ የሚቀጣበት ተደርጎ የሚወሰድበት አግባብ ልክ አይደለም፣ ሀገራቸውን በቅንነት ለሚያገለግሉ ዲፕሎማቶችም fair አይደለም። የሰረቀን ክስ መስርቶ መፋረድ እንጂ በየኤምባሲው ማጨቅ መፍትሄ አይሆንም።" @EliasMeseret

Open in Telegram
Views50,700−14%vs avg
Forwards—
Reactions648
Comments—
#8490Text

የቡጢ፣ የቲክቶክ፣ የቁንጅና ወዘተ. ውድድሮችና ደመቅ ያሉ የገንዘብ ወይም የዓይነት ሽልማቶች እየገነኑ ሲመጡ በአንድ ወቅት እንደ አገር ጎላ ያለ ፋይዳ የነበራቸው፣ ቢቀጥሉ ኖሮ ለብዙ ታዳጊዎች አርአያዎች መሆን የሚችሉ ሰዎች የሚደምቁበት እንዲሁም የሙያተኞችን ተስፋ ሊያለመልሙ ይችሉ የነበሩ የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራሞች ትዝ አሉኝ። አንዱ የሚከተለው ነው። በአገር አቀፍ ደረጃ ለአገር ባበረከቱት አስተዋጽዖ 5 ሰዎች ከፍተኛ እውቅናና ሽልማት እንዲያገኙ የተደረገበት ጊዜ ነበር። ይህን ከሰማን ከአስር ዓመት በላይ ስላስቆጠረ ሁለቱን ተሸላሚዎች ዘንግቻቸዋለሁ። ከሶስቱ፦ የመጀመሪያው እና ትልቅ እውቅና ያገኙት ዶ/ር አብርሐም የሚባሉ በራስ ደስታ ሆስፒታል ስፔሻሊስት ሐኪም የነበሩ ናቸው። የሽልማቱ ምክንያት ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ጨምሮ በቁጥር በጣም በርካታ ህሙማንን ከስራ ሰዓት ውጪ ያለማንም አስገዳጅነት በግል ፈቃደኝነት ለረዥም ጊዜ በነፃ የሕክምና አገልግሎት መስጠታቸው፤ ሁለተኛዋ ስሟን የዘነጋኋት በሙያዋ ነርስ የነበረች ናት። ይህቺ ነርስ ተሸላሚ የነበረችው በራሷ ፈቃደኝነት በራሷ ወጪ በአገሪቱ በሚገኙ በርካታ የጸበል ሥፍራዎች 'ደከመኝ ሰለቸኝ' ሳትል እየተዘዋወረች የጸረ-ኤች አይ ቪ መድኃኒት ያቋረጡ ሰዎችን ጸበልም እየተጠመቁ መድኃኒታቸውንም እንዲወስዱ ለረዥም ጊዜ ስታስተምር (ስትወተውት) የቆየች በመሆኗ፤ ሦስተኛው የመቄዶንያው ቢንያም በለጠ ነው። በተለይ በተለይ የአዕምሮ ሕሙማንን ከወደቁበት እያነሳ ሕክምና እንዲያገኙ በማድረጉ፤ ነበር። እንደዚህ ያሉ የእውቅና እና የሽልማት (ትርጉም ያለው እና ሕይወትን የሚለውጥ) ፕሮግራሞች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች (ለምሳሌ ጤና፣ ትምህርት፣ በጎ አድራጎት...) በአገር አቀፍ ደረጃ በመንግሥት ታግዘው መከናወን አለባቸው። ተጽዕኖአቸውን በበጎ መስመር በብዙ አቅጣጫ መመንዘር የሚቻል በመሆኑ ብናስብበት መልካም ነው። ልጆቻችንን አርአያ አናሳጣቸው! Via Hawlet Ahmed @EliasMeseret

Open in Telegram
Views72,000+23%vs avg
Forwards—
Reactions1,352
Comments—
#8486Photo
Views62,800+7%vs avg
Forwards—
Reactions1,524
Comments—
#8483Photo
Views59,000+1%vs avg
Forwards—
Reactions357
Comments—
#8482Text

ጠ/ሚር አብይ እንደ ፕሬዝደንት ትራምፕ!? የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፉት ሁለት አመታት አብዛኛው ህዝብ በኑሮ ውድነት በተጨነቀበት ወቅት ትኩረታቸውን ዋይት ሀውስን በወርቅ ማንቆጥቆጥ፣ በግብዣ አዳራሽ እና በሚያንፀባርቅ ፑል ግንባታ እና ተመሳሳይ ይዘት ባላቸው "የካቢኔ ፕሮጀክቶች" ላይ አድርገው ነበር። በዚህ ምክንያት በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ አሜሪካውያን በድምፃቸው የሪፐብሊካን ፓርቲን በከፍተኛ ሁኔታ ቀጥተዋል። በኢትዮጵያም በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የሚካሄዱት ደም አፋሳሽ ግጭቶች በየሳምንቱ የብዙ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት እያጠፉ ባሉበት እና የኑሮ ውድነቱ ህዝቡን ክፉኛ ጎዳበት በአሁኑ ወቅት የመንግስት ዋና ትኩረት የኮሪደር ልማት፣ የከተማ ማስዋብ፣ የቤተ-መንግስት ፕሮጀክቶች እና የከባድ መሳሪያዎች ግዢ ላይ ሆኗል። በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ዋና ልዩነት የመፍትሔ መንገዱ ላይ ነው። አሜሪካ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ስላላት ህዝቡ በምርጫ የፖሊሲ ስህተቶችን መቅጣት እና ለውጥ ማምጣት ችሏል። በኢትዮጵያ ግን ዜጎች መሰረታዊ ችግሮቻቸው ተረስተው በመንግስት ፕሮጀክቶች ጥላ ስር እንዲኖሩ ቢገደዱም ይህን አሰራር የሚቀይሩበት ወይም ድምፃቸውን በዲሞክራሲያዊ መልኩ ሰጥተው ነገሮችን መቀየር ባለመቻላቸው ችግራቸውን ተሸክመው ይኖራሉ።  ዜጎች የሀገር ውበት እና ልማት አይጠሉም። ነገር ግን የህይወት ዋስትና፣ ሰላም እና የዕለት ተዕለት የኑሮ እድገት ከምንም በላይ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አገራዊ ጉዳዮች ናቸው። ህዝብ ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሰረታዊ እና አስቸኳይ የህይወት ጥያቄዎች እንዲመለሱ ይፈልጋል። @EliasMeseret

Open in Telegram
Views65,500+12%vs avg
Forwards—
Reactions1,010
Comments—
#8481Text
Views53,300−9%vs avg
Forwards—
Reactions942
Comments—
#8480Photo
Views49,100−16%vs avg
Forwards—
Reactions1,064
Comments—
#8476Photo
Views70,700+21%vs avg
Forwards—
Reactions635
Comments—