Account

Posts of EBC SPORT

newest first

#6422Photo

በገጠመኝ ጉዳት ያየሁት የህዝብ ፍቅር የዓለም ክብረ ወሰንን አሻሽዬ ከማገኘዉ ክብር የበለጠ ነዉ፦‎ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ **** ‎የ2026 የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በዉድድሩ ላይ በገጠማት ጉዳት ምክንያት ስታደርገዉ የነበረዉን ህክምና አጠናቃ በመልካም ጤንነት ወደ ሀገሯ ተመልሳለች። ‎አትሌቷ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት የጀግና አቀባበል ተደርጎላታል። ‎ጀግናዋ አትሌት ትዕግሥት ከደማቁ አቀባበል በኋላ ባስተላለፈችዉ መልዕክት የተደረገላት አቀባበል በቀጣይ የተሻለ ዉጤት እንድታስመዘግብ ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሚሆናት ገልፃለች። ‎አትሌቷ በርሊን ላይ የገጠማት ጉዳት ያልጠበቀችዉን የህዝብ ፍቅርን እንዳሳያት ገልፃ፣ “የተሰጠኝ ፍቅር ክብረ ወሰኑን አሻሽዬ ከማገኘዉ አድናቆት እና ዝና የበለጠ ሆኖ በማግኘቴ እጅግ ተደስቻለሁ” ብላለች። ‎አትሌቷ በፍጥነት ወደ ጤንነቷ እንድትመለስ ላገዟት ሁሉ ምስጋናዋን አቅርባ፣ ከደረሰባት ጉዳት ሙሉ በሙሉ አገግማ ወድቆ የመነሳት ተምሳሌት ለመሆን እንደምትጥር ገልፃለች። ‎ በመሰረት ተስፋዬ #EBC #athletics #TigistAssefa #athlete

Open in Telegram
Views308−47%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#6417Photo

ማንቸስተር ዩናይትድ በብሬንትፎርድ 4 ለ 0 ተሸነፈ ***** በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት በኦልድ ትራፎርድ ብሬንትፎርድን ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ 4 ለ 0 ተሸንፏል። ዩናይትድ በውድድር ዓመቱ ከሊጉ አስራ ሁለቱ ሳምንታት ለስድስተኛ ጊዜ በተረታበት ጨዋታ፣ ብሬንትፎርድ የማሸነፊያዎቹን ግቦች በመጀመሪያው አጋማሽ በ19 እና 32ኛው ደቂቃ ላይ በካሉም ዊልሰን እንዲሁም በሁለተኛው አጋማሽ 82ኛው ደቂቃ ላይ በክርስቶፈር አየር እና በ90+1ኛው ደቂቃ ላይ በኬቪን ሻዴ አማካኝነት አስቆጥሯል። በሁሉም ውድደሮች 40 ግቦች የተቆጠሩበትና በ8 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ነገ ክሪስታል ፓላስ ሃል ሲቲን የሚረታ ከሆነ 20ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ከ40 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘውን የወራጅ ቀጣና ጉዞ ለአራተኛ ሳምንት የሚቀጥል ይሆናል። በማውሪሲዮ ፖቸቲኖ አሰልጣኝነት ስር ሶስተኛ ጨዋታውን አድርጎ ያለ ድል የወጣው ዩናይትድ፣ ብቸኛ የፕሪሚየር ሊግ ድሉን ካሳካ 90 ቀናት ተቆጥረዋል። በውድድር ዓመቱ በስድስት ጨዋታዎች የተሸነፈውና 27 ግቦች የተቆጠሩበት ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ጋር እኩል ከፍተኛ ግቦች የተቆጠሩበት ቡድንም ሆኗል።ባለድሉ ብሬንትፎርድ የውድድር ዓመቱን አምስተኛ ድል ማሳካቱን ተከትሎ በ20 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። #EBC #EPL #PremierLeague #ManchesterUnited #Brentford #MatchDay #football #sports

Open in Telegram
Views708+23%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#6413Photo
Views633+10%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#6408Photo
Views596+3%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6406Photo
Views552−4%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#6403Photo

“ጨዋታዎችን በአምስት እና ስድስት ግቦች ልዩነት ማሸነፍ እፈልጋለሁ” - ሚኬል አርቴታ ***** በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት የፊታችን እሁድ አርሰናል ከ ማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በሰጡት መግለጫ፣ ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ልምምድ እንደሰራ የገለጹ ሲሆን በቀጣይ ሰዓታት ለሲቲ ጨዋታ ስለመድረስ አለመድረሱ እንደሚወሰን ተናግረዋል። ከዴቪድ ራያ በተጨማሪ የመሃል ተከላካዩ ዊሊያም ሳሊባ በቅርብ ቀናት ወደ ጨዋታ እንደሚመለስ ተናግረዋል። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ካሳኩ በኋላ በአስተሳሰብም ሆነ በአጨዋወት ቡድኑ ውስጥ ለውጥ እንዳለ ያነሱ ሲሆን፣ “ተጨማሪ የማሸነፍ ረሃብ በውስጣችን አለ” በማለት ለተጨማሪ ክብሮች እየተጫወቱ እንደሆነ ገልፀዋል። አርሰናል በርከት ያሉ ጨዋታዎችን በአንድ ግብ ልዩነት ማሸነፉ ብዙም አሳሳቢ እንዳልሆነባቸው የተናገሩት አሰልጣኙ፣ “ጨዋታዎችን በአምስት እና ስድስት ግቦች ልዩነት ማሸነፍ እፈልጋለሁ፤ በስታዲየሙ ደጋፊዎች ሆነ ተጫዋቾቹ ላይ የሚፈጥረው ስሜት ልዩ ነው” ሲሉም በሰፊ የግብ ልዩነት የማሸነፍ ውጥናቸውን አብራርተዋል። ፕሪሚየር ሊጉን ማሸነፍ የሚፈልጉት በማንቸስተር ሲቲ ላይ በሚኖር የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ሳይሆን ሜዳ ላይ ድል በማድረግ መሆኑን ተናግረዋል። “ኤንዞ ማሬስካን በግል አውቀዋለሁ፤ ድንቅ አሰልጣኝ ነው። ነገሮችን የሚመለከትበት መንገድም ድንቅ ነው” በማለት ለማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። የደረጃ ሰንጠረዡን በስድስት ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ እሁድ ምሽት 1:30 በኢሚሬትስ ስታዲየም ይደረጋል። በእዮብ ተሰማ #PremierLeague #Arsenal #football #EBC

Open in Telegram
Views661+15%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—