የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን የማቅናት ሥራ በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የነበሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን ለማቅናት የተጀመረው የሪፎርም ሥራ በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው
Open in TelegramPosts of EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
መከላከያ እንደ ቤት ነው። መከላከያን ብቻውን ብንገነባ አይዘልቅም። ኢኮኖሚው እሱን የሚሸከም መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል። መከላከያ በአንድ ምሶሶ መቆም አይችልም። ሁሉም ምሶሶዎች መገንባት አለባቸው። እነዛ ምሶሶዎች ደግሞ የአየሩም፣ የምድሩም የቴክኖሎጂውም ነው። በዚህም በመከላከያ ስትራቴጂ አማካኝነት በሁሉም ምሶሶዎች ሸብረክ የማይል ጠንካራ ሠራዊት እየተገነባ ነው። መከላከያ ቴክኖሎጂን በሚገባ የሚጠቀም ተቋም አድርገነዋል። ይህም በውጤቱ እየታየ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Open in Telegram"ዜጎች ከባንክ ጋር ተሳስረው ልክ እንደ ሌላው ዓለም ቤት ገዝተው እየሰሩ የሚከፍሉበት የሞርጌጅ ስርዓት በቅርቡ ይጠናቀቃል" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Open in Telegramኢትዮጵያ የፀናቸው በፈተናዎች ውስጥ አልፋ ነው! ኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቀችው በፈተናዎች ወስጥ አልፋ ነው:: ኢትዮጵያ በተደራጁ ሰራዊቶቿ፤ የተባበረ ልብ ባላቸው ህዝቦቿ እንዲሁም ዋጋ ለመክፈል በማይሰሰቱ ልጆቿ አማካኝነት ፈተናዎችን ተሻግራ ስሟን አጽንታ ይዛለች
Open in Telegramእንደ ቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ያለ በተቀናጀ መንገድ የሚመራ ውስብስብ ፕሮጀክት የትም የለም፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የመሬት ጠረጋ ዝግጅት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፣ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ቀጣይ ምዕራፍ የሆነውን የአውሮፕላን መንደርደሪያ ለመገንባት በአሁኑ ወቅት በጨረታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል
Open in Telegramየ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ለማሳካት ወደ ተግባር ተገብቷል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጉባ ብሥራት የሆነውን የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት እውን ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ የሕግ፣ የፋይናንስ እና የመሬት ዝግጅቶች ተጠናቅቀው ወደ ተግባር መገባቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ነው
Open in Telegram"ከለውጡ በፊት ከተሞች ቅድሚያ የሚሰጣቸው አልነበሩም፤ ዛሬ የኮሪደር መሰረተ ልማትን በመገንባትና የስራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው።"
Open in Telegramየኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በተደረገው የሪፎርም ሥራ ዛሬ ላይ 43 ቢሊየን ብር ትርፍ እያስገኘ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፣ የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከጥቂት ዓመታት በፊት 3.4 ቢሊየን ገደማ ትርፍ ያመጣ እንደነበረ አስታውሰው፣ በተደረገው የሪፎርም ሥራ ዛሬ 43 ቢሊየን ብር ትርፍ ያስገኛል ብለዋል
Open in Telegramየነዳጅ ዋጋ በሊትር ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አንጻር ኬኒያ ----1 ነጥብ 7 ዶላር ጂቡቲ ----1 ነጥብ 77 ዶላር ኡጋንዳ ----- 1 ነጥብ 57ዶላር ታንዛኒያ ----- 1 ነጥብ 53 ዶላር ሩዋንዳ ------1 ነጥብ 99 ዶላር ኢትዮጵያ -----1ነጥብ 04 ዶላር
Open in Telegramበአንድ ቀን ሁለት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ለማካሄድ የሚያስችል ብቃት ተገንብቷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፣ በኢንዱስትሪ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በኢነርጂ እና በቱሪዝም ዘርፎች ተጨባጭ እመርታ መመዝገቡን አስታውቀዋል:: የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ዕድገት ማሳየት መጀመሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህንን ዕድገት በበቂ ደረጃ የሚለካ ሥርዓት እንዳልነበረ አመልክተዋል
Open in Telegramወደብ ሳይኖረን፣ የነዳጅ ዴፖ ሳይኖረን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠመውን የነዳጅ ቀውስ ለመቋቋም በከፍተኛ ድጎማና ነዳጅ ቁጠባ ያከናወነው ስራ ምስጋና የሚቸረው ነው። በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ነዳጅ በድጎማ ማምጣት ብቻ ሳይሆን ያስተዳደርንበት መንገድ ከፍተኛ ምስጋና የሚቸረው ተግባር ነው:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Open in Telegramበኢትዮጵያ የተመዘገቡ አዳዲስ የልማት ሥራዎችን ታሳቢ ያደረገ የ'ጂዲፒ' አለካክ ሥርዓት መተግበር አስፈልጓል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፣ በኢትዮጵያ የተመዘገቡ አዳዲስ የልማት ሥራዎችን ታሳቢ ያደረገ የ'ጂዲፒ' አለካክ ሥርዓት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል:: ለዚህም የዲጂታል ኢኮኖሚን ለአብነት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከለውጡ በፊት የሞባይል ገንዘብ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደማይታወቅና ዛሬ ላይ በትሪሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ እንደሚንቀሳቀስ አብራርተዋል
Open in Telegramከወጪ ንግድ አንጻር ባለፉት ሶስት ወራት 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ማግኘት ተችሏል። ይህ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ25 በመቶ እድገት አለው:: ከሀገራዊ ሪፎርሙ በፊት ካሉ ዓመታት ጋር ካነጻጻርነው ደግሞ የአንድ ዓመት የወጪ ንግድ ገቢ ጋር የሚስተካከል ነው
Open in Telegramበኢትዮጵያ የባንኮች ተቀማጭ 5 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር ደርሷል። አጠቃላይ የማባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥርም 70 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን በኢትዮጵያ 11 ትሪሊን ብር በዲጂታል ፋይናንስ ይዘዋወራል:: ይህም በተለይ የብድር አቅርቦትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አቅም ፈጥሯል
Open in Telegram"የኢትዮጵያ ጂዲፒ 210 ቢሊየን ዶላር በመሆን ከሰሃራ በታች ከደቡብ አፍሪካ እና ከናይጄሪያ ቀጥሎ ሦስተኛው ትልቁ ኢኮኖሚ መሆን ችሏል።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Open in Telegram"የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረበት 2 ነጥብ 6 ትሪሊዮን ሃብት ዛሬ 9 ትሪሊዮን ደርሷል። ትልቅ ይወድም የነበረ ሃብተን በማሰባሰብ አጠቃላይ ሃብቱን በሶስት እጥፍ ማሳደግ ችሏል:: ከገቢ አንጻርም አሁን ላይ 3 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ብር ያስገባል
Open in Telegramየግብር መሰረት ማስፋትን በተመለከተ ኢትዮጵያ ውስጥ የግብር መሰረትን የማስፋት ስራን በደንብ ማየት ይገባል:: በርግጥ ግብር መክፈል ክብር ነው
Open in Telegramኢንዱስትሪ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግብርና የተሻለ ድርሻ መያዝ ችሏል! ግብርና ከጥቅል ዓመታዊ እድገታችን 31 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ አለው። ኢንዱስትሪ ደግሞ 31 ነጥብ 8 በመቶ ድርሻ በመያዝ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጥቅል ዓመታዊ እድገታችን ከግብርና የተሻለ ድርሻ መያዝ ችሏል:: ይህ እንግዲህ ኢንዱስትሪው በፍጥነት እያደገ መሆኑን የሚያመላክት ነው
Open in Telegramየኢትዮጵያን ጥቅል ዓመታዊ ምርት በሚመለከት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢኮኖሚ ክለሳው መሰረት የኢትዮጵያ ጥቅል ዓመታዊ ምርት 210 ቢሊዮን ዶላር በመሆን ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት 3ኛው ትልቁ ኢኮኖሚ መሆን ችሏል:: ይህ ሂደት በጥብቅ ዲሲፕሊን የተመራ ነው
Open in Telegramኢትዮጵያ ያከናወነቻቸው ሪፎርሞች ኢኮኖሚዋ ጫናዎችን ተቋቁሞ እንድጸና አድርጓል:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል:: በማብራሪያቸው በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ያለው ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት፣ ግጭት፣ ንትርክ እና ውድድር በርካታ ችግሮችን ያስከተለ ሲሆን፣ በዋናነትም የንግድ ሥርዓትን ማዛባቱን ጠቁመዋል
Open in Telegramየባቡር መሰረተ ልማትን በተመለከተ የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ኮርፖሬሽንን ለማሻሻል በተከናወኑ ስራዎች ከዚህ በፊት ይገኝ የነበረውን ትርፍ ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወደ 43 ቢሊዮን ብር ማሳደግ ተችሏል:: የነበሩትን ሎኮሞቲቮችን ከ11 ወደ 36 ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፤ አሁን ላይ ከአንድ ሺህ በላይ ጋሪዎችንም ማስተዳደር ችሏል
Open in Telegramየኢኮኖሚ መልሶ ክለሳን በተመለከተ ባለፉት አስራ አንድ ዓመታት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ክለሳ ተካሄዶ አያውቅም:: በመሆኑም አዳዲስ የተጨመሩ ኢኮኖሚዎችን ለማካተትና ሚና የሌላቸውን የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለማስወጣት ባለፉት አንድ ዓመታት ከፍተኛ የሰው ኃይል በማሰማራት የኢኮኖሚ ክለሳ ሲካሄድ ቆይቷል
Open in Telegramሀገራዊ ሪፎርምና ጠንካራ የኢኮኖሚ ስርዓት ግንባታን በተመለከተ በዓለም ላይ እየተፈጠረ ባለው የንግድ ስርዓት መዛባት፤ እንዲሁም በዋና ዋና ምርቶች ላይ ባጋጠመው የምርት እጥረትና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪና የእድገት መገራገጭ አጋጥሟል:: ነገር ግን በኢትዮጵያ ሲከናወን በቆየው የኢኮኖሚ ሪፎርም ስራ ምክንያት ፈተናዎችን የሚቋቋም አቻዮ የኢኮኖሚ ስርዓት መገንባት ችለናል
Open in Telegramጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማብራሪያ መስጠት ጀምረዋል #Ethiopia #AbiyAhmed #EthiopianParliament #PMAbiyAhmed https://www.youtube.com/watch?v=UFVuzSYNCVg
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 304 |
| 3 h | 2,170 |
- Total to date2,170
በ7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች፡- 1. የታክስ ገቢ አሰባሰብ አሁንም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ መሆኑ ይነገራል:: መንግሥት የታክስ ገቢውን ከሀገር ውስጥ ምርት አንጻር ከፍ ለማድረግ ግብ አስቀምጦ እየሠራ ቢሆንም፣ በንግዱ ማኅበረሰብ በኩል ግን የሚጠየቀው ታክስ ከአቅም በላይ እና የተጋነነ ነው የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 816 |
| 3 h | 2,380 |
- After 1 hour816
- Total to date2,380
ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡ ጥያቄዎች፡- 👉 በሀገራዊ ምክክር የተገኙ የጋራ ምክረ ሐሳቦችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር እና በሕግ፣ በፖሊሲ እንዲሁም በተቋማዊ ማሻሻያዎች ለመተግበር መንግሥት ምን ዝግጅት እና የድርጊት መርሐ ግብር አዘጋጅቷል? በትግበራው ሂደትስ ከመላው ኢትዮጵያውያን እና ከኢትዮጵያ ወዳጆች ምን ይጠበቃል? 👉 ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ እና የነገ ዕጣ ፈንታዋን በጸና መሠረት ላይ ለመገንባት፣ የሀገራችን ረጅም ጊዜ ራዕይ የሆነውን «የመደመር ሥልጣኔ» ታላቅ ስትራቴጂ እየቀረጸች ትገኛለች:: ይህንን ሀገራዊ ሥልጣኔ ለመገንባት በመንግሥት በኩል ምን ዝግጅት እንደተደረገ ቢገለጽ? 👉 የኤርትራ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ሲከተለው የነበረው ተግባር አፍራሽ እና አሉታዊ መሆኑ ይታወቃል
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 1,490 |
| 4 h | 2,680 |
- After 1 hour1,490
- Total to date2,680
የ7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ በይፋ ተጀምሯል:: የጉባኤውን ሙሉ ሂደት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራሪያዎችና ምላሾች በኢቢሲ ዶትስትሪም (EBC DOTSTREAM) እንዲሁም በሁሉም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የመገናኛ አማራጮች በቀጥታ ይከታተሉ!
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 1,890 |
| 4 h | 2,860 |
- After 1 hour1,890
- After 6 hours2,860
- Total to date2,860
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ https://www.youtube.com/watch?v=UFVuzSYNCVg
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 1,900 |
| 4 h | 2,830 |
- After 1 hour1,900
- After 6 hours2,830
- Total to date2,830
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባኤ ተገኝተው ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ የ7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 2 h | 2,140 |
| 5 h | 2,970 |
- After 6 hours2,970
- Total to date2,970
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ይካሄዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 7ኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ይካሄዳል፡፡ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 በጀት ዓመት የመንግሥት ዕቅድ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በወቅቱ ፕሬዚዳንት ታዬ ያቀረቡትን የመንግሥት ዕቅድ መነሻ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግሥት በቀጣይ ትኩረት የሚያደርግባቸውን አቅጣጫዎች በግልጽ እንደሚያስቀምጡም ይጠበቃል፡፡ በአዲሱ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ሥራዎችን እና የተገኙ ውጤቶችንም ያብራራሉ፡፡ ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም ካዳመጠ በኋላ ፕሬዚዳንት ታዬ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ በጉባኤው በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በክብር እንግድነት ይታደማሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሁሉም የዶትስሪም እና መደበኛ የሥርጭት አማራጮች የጉባኤውን ሂደት በቀጥታ ሥርጭት እንደሚያስተላልፍ እየገለጽን እ…
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 2,710 |
| 5 h | 3,550 |
- After 6 hours3,550
- Total to date3,550