እንኳን ለነቢያት ፆም በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ። #ጾመ_ነቢያትን_#ለምን_እንጾማለን? ✍️ጾመ ነብያት ወይም የገና ጾም #ማክሰኞ ኅዳር 15 ይጀምራል፡፡ ታኅሣሥ 29 በዕለተ #ሐሙስ ይፈታል። ይህ ማለት የዘንድሮ የገና ጾም ከማክሰኞ ኅዳር 15 ጀምሮ የፍስክ ምግቦች አይበሉም። ይህ ጾም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ጾሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነጽር እየተመለከቱ የጾሙት ታላቅ ጾም ነው። ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በጾምና በጸሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ ዓለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው። => ይህ ጾም፣ ጾመ ድህነት፣ ጾመ ማርያም ፣ ጾመ አዳም፣ ጾመ ፊሊጶስ፣ ጾመ ስብከት፣ ጾመ ልደት በመባል ይጠራል። ⛪️1)#ጾመ_ድህነት፡ የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድኅነት ስለተገኘበት ነው። ⛪️2)#ጾመ_ማርያም፡ የተባለበት ምክንያት ንጽይተ ንጹሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህጸኔ ተሸክሞ ልጾም ልጸልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የጾመችው ጾም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል። ⛪️3)#ጾመ_አዳም፡ የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡ ⛪️4)#ጾመ_ፊልጶስ፡ የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ⛪️5)#ጾመ_ስብከት፡ የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡ ⛪️6)#ጾመ_ልደት: የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡ ☞ጾምን ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የበረከት ምንጭ በመሆኑ ጭምር ደስ እያለን ብንጾመው የቅዱሳኑ በረከት ያድርብናል፡፡ ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም ማክሰኞ ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 29 ይፈታል። ጾሙን ጾመን የኃጢአታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
Open in TelegramPosts of የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®
#ማለፊያ_እንጀራም_አልበላሁም "ብዙዎች ቢጾሙም ለእነርሱ መጾም ማለት የጾም ምግብ መብላት ማለት ነው። እነርሱ በጾም ወቅት ለራሳቸው የሚበሏቸውን በጣም ጣፋጭና ገንቢ ምግቦችን ያዘጋጃሉ አልፎ ተርፎም ውድና የማይገኙ ቅመማ ቅመም ይጨምሩባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የጾም ቅቤ፤ የጾም አይብ፤ የጾም ቸኮላታ እንዲያገኙ ይጠይቃሉ። በአጠቃላይ የጾም ምግቦቻችን ብዛትና ዓይነት ከልክ እጅግ ያለፈ ነው። በዚህም ነብዩ ዳንኤል ስለ ጾም የተናገረውን ይዘነጉታል። "በዚያ ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። ማለፊያ እንጀራ አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱንም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።" (ዳን 10፥2-3) በዚህ አባባሉ ውስጥ "ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም" የሚለው ላይ ማተኮር እፈልጋለሁ። አንድ ሰው በጾም ወራት በየዕለቱ ጥሩ ጥሩ ምግቦች እየበላና የሚናፍቀውን ምግብ ለሰውነቱ እየሰጠ የሥጋውን ፈቃድ እንዴት ሊቆጣጠር ይችላል? አይችልም። መንፈሳዊው ሰው የጾም ትክክለኛ ፍቺ ሥጋን በማዋረድ የምግብን ፋላጎት ድል ለማድረግ ካበቃ በኋላ ከቁሳዊው ዓለም በላይ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ያውቃል ። በመሆኑም የጾም ምግቦችን መብላት ብቻ መሆን የለበትም እርሱ በሚጾምበት ጊዜ ግድ የሚለው መታቀብ ነው ። ይህም ማለት የሚመገበው ሙሉ ለሙሉ የጾም ምግብ ቢሆንም ሥጋው ሊያገኛቸው የሚናፍቃቸውን ነገሮች በሙሉ መከልከል ማለት ነው ። ብዙ ሰዎች የሚጾሙት በልምድ ወይም በፊደል ስለሆነ ምንም የሚጠቀሙት ነገር የለም ። እነዚህ ሰዎች ጾምን መለኮታዊ ዓላማውን በመገንዘብ ስለማይጀምሩት ወደ ጾም መንፈሳዊነት ወይም ስለ ትእዛዙ መንፈሳዊነት ሊገቡ አይችሉም። በመሆኑም ሰውነታቸው ይጹም እንጂ መንፈሳቸው አይጾምም። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
Open in Telegramእንኳን "ለነቢያት ፆም በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን። #ጾመ_ነቢያት! ✍🏽=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት:: "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው:: የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ መባልዕት መከልከልን ይመለከታል:: ✝️"7ቱ" አጽዋማት 1. ዓቢይ ጾም 2. ጾመ ፍልሠታ 3. ጾመ ሐዋርያት 4. ጾመ ነቢያት 5. ጾመ ድኅነት 6. ጾመ ነነዌ እና 7. ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ:: 💠በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት ድረስ መጾም ይገባል:: ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት አለውና ይቆየን:: ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ አስፈላጊነቱ ነው:: "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ መጠየቁ ይቀላል:: ☞ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው። ☞ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው። 💠ጾመ ነቢያት ማለት ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: ☞በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስና ቅዱስ ዳንኤል በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: (ዘዳ.9:19, ነገ.19:8, ዳን.9:3) ☞ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል! Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Open in TelegramForwarded from የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®
⛪️ አንተኑ ሚካኤል ⛪️ አንተኑ ሚካኤል መና ዘአውረድከ (፪) ወአንተኑ ለእስራኤል መና(፪) ዘአውረድከ(፪) ዘአውረድከ መና (፫) ሚካኤል(፫) ዘአውረድከ መና #ትርጉም ለእስራኤል መናን ያወረድክ ሚካኤል አንተ ነህ
Open in Telegramእንኳን #ለሊቀ መላእክት "ቅዱስ ሚካኤል" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✍🏽=>ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል:: +ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና:: +በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል:: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7) +ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ:: አምላከ ቅዱሳን በክንፈ ሚካኤል ከክፉው ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም አይለየን:: የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
Open in TelegramForwarded from የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®
እንኳን #ለሊቀ መላእክት "ቅዱስ ሚካኤል" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። 🔥#ህዳር_ሲታጠን🔥 በዚህች ቀን የሰማይ ሰራዊት ሁሉ አለቃቸው መልአከ ምክሩ የምክሩ አበጋዝ ይለዋል የቅድስት ሥላሴ መንጦላእትን የሚከፍትና የሚዘጋ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ቀን ነው። በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ክፍለ ነገድ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡ ተያይዞም በዕለቱ የህዳር ሲታጠን ታሪክ ይነሳል! የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
Open in Telegram#ደብረ_ቁስቋም ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡ ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡ እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡ ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
Open in Telegramየበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!!! Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Open in Telegram#አልአዛር የሚጎበኝበት ጊዜ ይመጣል የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!!! Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
Open in Telegram#ሞኝ_ሰው_ሞት_የሌለ_ይመስለዋል "ከሐሜተኛና ከቀናተኛ ባልንጀራ ፈጥነህ ሽሽ፤ ይህን ከምታደርግ ብቸኝነትን የምትፈጽምበት ብቸኝነት ይሻልሃልና፡፡ ልቡናው የጨለመ ምሥጢር የማይጠብቅ ዝርወ ልብ የሆነን ሰው አትምከር፡፡ ብዙ ባልንጀሮችን አታብዛ ይልቁንም ደግሞ ከሴቶች ጋር። በቤቴ ውስጥ ነኝ ብለህ ባለጸጎችን አትማ፤ ነገርህን ወፍ አውጥቶት በአፍኣ ይገኛልና፡፡ ስትበላ ከሰው ጋር ብላ፤ ስትጠጣ ግን ብቻህን ጠጣ፤ ከመጠጥ በኋላ አብዝተህ በመናገር በባልንጀሮችህ የተናቅህ የተነቀፍህ ትሆናለህና፤ ሰነፍን ብቻውን ብትነግረው በሰገነት ይሰብከዋል፡፡ ሰነፍ ሲዘሙት ጽድቅ የሚሠራ ይመስለዋል፤ ሐሜተኛም ሲያማ የሚጸልይ ይመስለዋል፡፡ ንዝኅላልም ለጸሎት የሚተጋ ይመስለዋል፡፡ ንፉግም ለነዳያን የሚሰጥ ይመስለዋል፤ ለሰነፎችም ጥበብ የላቸውም፤ ጥበባቸውም ከንቱ ነው፤ ከአላዋቂ ባለጸጋ ቁራሽ የሚለምን ድኻ ይሻላል፡፡ ሞኝ ለንጉሥ ባለሟል ወታደር ሆኖ በተመረጠ ጊዜ ሞት የሌለ ይመስለዋል፡፡ ሞኝ ሲሾም ቤቱን ከጎረቤት ከፍ አድርጎ ይሠራል፤ ሞኝ ባለጸጋ በሆነ ጊዜ ደግሞ በባልንጀሮቹ ይመካ ዘንድ በሚስቱ ላይ ሚስት ያገባል፡፡ ለአላዋቂ ድኽነት ይሻለዋል፤ ሀብት ባገኘ ቁጥር ስሕተትና ክፋትን ይጨምራል፡፡ ገንዘቡንም በኋላ መኳንንት ይቀራመቱታል።" የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!!! Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
Open in Telegramየበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 Telegram: ☞https://t.me/joinchat/S3QVyScP7Saom-Lv
Open in Telegramእንኳን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን። =>ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ¤ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል:: ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ¤ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ¤ራሱንም በዘንግ መቱት:: ¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: ¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ¤ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: ¤6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: 7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ¤ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ¤ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: ¤11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው:: ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም:: በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል:: አምላከ ቅዱሳን በአማኑኤል ስሙ: በማርያም እሙ: በፈሰሰ ደሙ: በተወጋ ጐኑ: በንጹሐን ቅዱሳኑ ይማረን:: ''በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ:: ሕማማችንንም ተሸክሟል:: እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው:: እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ:: ስለ በደላችንም ደቀቀ:: የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ:: በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን::'' (ኢሳ. 53:4) የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 Telegram: ☞https://t.me/joinchat/S3QVyScP7Saom-Lv
Open in Telegramእንኳን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ''በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ:: ሕማማችንንም ተሸክሟል:: እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው:: እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ:: ስለ በደላችንም ደቀቀ:: የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ:: በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን::'' (ኢሳ. 53:4) Telegram: ☞https://t.me/joinchat/S3QVyScP7Saom-Lv
Open in Telegram#ምነው_አባታችን! #አንተም_ፍርድን_ትፈራለህን? የአንድ ቀን ንጉሥ ሆኖ የሞተ አንድ ንጉሥ ነበር። ይህ የሆነው በከባድ ነገር አይደለም። ይልቁንም በተሾመ ዕለት ከበው እጅ ከሚነሱት ሕዝብ ብዛት የተነሣ እስትንፋስ አጥሮት ነው። በእውነቱ ኀዘናችን ከሚጎዳን እኛው ደስታ የምንለው ያመጣብን እዳ ብዙ ነው። ረጋሚዎቻችን ካጠፉን ይልቅ አድናቂዎቻችን የገደሉን ይበዛል። ሰዎችን በተቀመጡበት ቦታ እንዳይገኙ፥ ቃላቸውን እንዳይጠብቁ፤ ለሕዝብና ለእግዚአብሔር ለራሳቸውም እንዳይታመኑ የሚያደርጋቸው ጭፍን አድናቂ ነው። እንደ ሰዎች ልክ ብንሆን እንደ እግዚአብሔር አናውቅሞ። አባ አጋቶን ሊያርፍ በተቃረበ ጊዜ ሦስት ቀን ያለ መንቀሳቀስ በአቱ ውስጥ ተኛ። ሦስተኛው ቀን ላይ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አንጻር በአንቃዕድዎ ሰቅሎ ዋለ። ደቀመዛሙርቱም አባታችን ምን ታያለህ? አሉት። እርሱም ወደ ክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እመለከታለሁ ሲል መለሰላቸው። እነርሱም ምነው አባታችን አንተም ፍርድን ትፈራለህን ቢሉት፤ አይ ልጆቼ! እንደ እኔ ሠራሁ ብያለሁ እርሱ ገና ነህ አልሠራህም ቢለኝ የት እገባለሁ ብሎ አስተማራቸው። እንደ እኛ የበሰለው በእግዚአብሔር በፊት ጥሬ ይሆናል። እንደ እኛ ያጸደቅነው በቅድመ እግዚአብሔር ኩኑን ይሆናል። እንደ እኛ ያከበርነው በፍትሐ እግዚአብሔር ኅሡር ይሆናል። ለወደፊት የሚረቡትን ሁሉ እንዲጠፉ ያደረግናቸው ያለመጠን እያደነቅን ስሕተታቸውን የሚያዩበት እድል ነስተናቸው ነው። እንደዚህም ስላደረግን ለሃይማኖትና ለሕዝብ ሳይሆን ለስማቸው የሚሞቱ ድልድሎችን አፍርተናል። እናም ዝምታ የክርስቲያኖች ግርማ ነውና በሥራ እየተናገርን ማንንም ከማድነቅ ከመተቸት ብናርፍ እንዴት ማለፊያ ነው! በዚህ ወቅት አብዝቶ ቢያደንቁት እውነት እየመሰለው ኩራት ጥፋት፤አብዝቶ ቢተቹት ሽንፈት እየመሰለው ክፋት ነው የሚያበዛውና ሰውን በሥራ መዝለፍ። ጌታ ዝም ብሎ ሥራውን ሠርቶ ራሱን እንደገለጠ በሥራ እንገለጥ፤ በሥራ እናመስግን፤ በሥራ እንዝለፍ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምሮ ሲጨርስ አብዝተው ላጨበጨቡለት ሕዝብ ለኔ ማጨብጨባችሁ ምን ያደርገልኛል። ይልቁንስ ያዘዝኳችሁንም ስትፈጽሙ ያን ጊዜ ነው ያጨበጨባችሁልኝ ነበር ያላቸው። ሞኝ ሕዝብ የሚባለው ፈጥኖ የሚያምን ፈጥኖ የሚክድ፥ ፈጥኖ የሚወድ ፈጥኖ የሚጠላ፤ ቸኩሎ የሚያደንቅ ቸኩሎ የሚተች፤ ቸኩሎ የሚመርቅ ቸኩሎ የሚረግም ነው። ይህም ይህ ነው። የነገሩትን ሁሉ ሳይመረመር የሚቀበል ነው። እንደ እባብ ሊገድል የሚያመሰግን አለ። እንደ ዮሐንስ መጥምቅ እናንተ የእፉኝት ልጆች እያለ ለድኅነት የሚዘልፍም አለ። የምንወድውን ያደነቀ ሁሉ ወዳጅ ላይሆን ይችላል። የማይወዱንን ሁሉ የሚነቅፍም አሳቢ አይደለም። አንጥያኮስ የሚባል የፅርዕ ንጉሥ ወደ እስራኤል ግዛት ለማስፋፋት ሲገባ እንዲህ ነበር ያደረገው። ይህ ሰው ጣኦት አምላኪ ሲሆን ወደ እስራኤል ሲመጣ ግን መልኩን ደብቆ፦ በኦሪት አምናለሁ፣ መሥዋዕተ በግዕ እሠዋለሁ፣ ለሥዕለ ኪሩብ እሰግዳለሁ፣ አነጥፋለሁ እጋርዳለሁ አላቸው። በዚህ ሕዝቡን መክፈል ቻለ። ግማሹ ሕዝብ አንጥያኮስን ያህል ንጉሥ ይህን ሁሉ ሊፈጽም ቃል ሲገባ ለምን ወደ መቅደስ እናስገባውም አሉ። ነገሩም አልቀረ ሌሎቹም አመኑና ሰውየው መቅደስ ገባ። በደንብ ሥልጣኑን ካረጋገጠ በኋላ ግን ነገሩን አመጣ። መሥዋዕተ በግዕ በሚሠዋበት ቦታ እርያም ሠዋበት። የሊቀ ካህናቱንም ሚስት በጡቶቿ መቅደስ ውስጥ ሰቅሎ ገደላት። ሊቀ ካህናቱንም በሰም አቅልጦ በብረት ምጣድ ተኩሶ፣ ሌሎችንም በሰይፍ ፈጃቸው። የሚወዱትን ሃይማኖታቸውን ከነሥርዓቱ ከማድነቅ በላይ ለሥርዓቱ ሊታዘዝ ቃል ገብቶ የመጣው በሐሰት ሰዎችን በሞት ሥርዓቱን በክህደት በመጣስ ፈጸመ። በዚህ ዘመንም ወይ አንጥያኮሶች ሆነው የሚያደንቁን፥ ወይ እባብ ለብሰው የሚያወያዩን፥ ወይ የሚጠሉንን በመተቸት የእኛን ድክመት ተጠቅመው ክብር የሚሰበስቡ ፥ሌሎችን በመተቸት ብቻ ለራሳቸው ዝና ከማጠራቀም በቀር ለእኛ ቀዳዳዎች አንድ እንጨት የማይቆርጡ የገቢያ ግርግር ሽፍታዎች ናቸው የበዙት። በሃይማኖትም ሰው ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በረት ወጥቶ የሚኮበልለው ሌላው እውነት ስለሆነ ሳይሆን ሌላው ውስጥ መወደስ እንጅ መገሠጽ ስለሌለ ነው። መብላት እንጅ መጾም፥ መቀማጠል እንጅ ትሕርምት የለም። ሰው እንደሚወደው እንጅ እግዚአብሔር እንደሚወደው ስለማይኖር ነው። ዓለም ደግሞ የራሱን ይወዳል ብሎናል መድኀኒታችን። እንደ ጌታ ፈቃድ ጽሙና ሳይሆን ዝላይ ወዳለበት፥ ሥርዓት ሳይሆን መረን መልቀቅ ወዳለበት የሚጎርፈውም ስለዚህ ነው። እንደ ዮሐንስ መጥምቅ የሚገሥጹን ግን ለሕይውት መንገድ ለክርስቶስ ያደርሳሉ። ለዚህ ነው እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ ልጆቿን ከማመስገን ይልቅ የምትገሥጸው! አሁንም ንስሐ ለመግባት እግዚአብሔር ልባችንን ይስበርልን:: Telegram: ☞https://t.me/joinchat/S3QVyScP7Saom-Lv
Open in Telegram#ማር_ሊቀ_ሰማዕት ማር ሊቀ ሰማዕት ገባሬ መንክር ጊዮርጊስ ኃያል(፪) የዱድያኖስ አምላክ - - ጊዮርጊስ ኃያል ያንን ደራጎን - - ጊዮርጊስ ኃያል አምላክ እንዳልሆነ - - ጊዮርጊስ ኃያል ገድለህ አሳየኸን - - ጊዮርጊስ ኃያል የቤሩት ኮከብ ነህ - - ጊዮርጊስ ኃያል የልዳ ፀሐይ - - ጊዮርጊስ ኃያል ለባሴ ሞገስ ነህ መክብበ ሰማዕት(፪) አዝ= = = = = መከራና ስቃይ - - ጊዮርጊስ ኃያል እያጸኑብህ - - ጊዮርጊስ ኃያል ትናገር ነበረ - - ጊዮርጊስ ኃያል ስለ አምላክህ - - ጊዮርጊስ ኃያል ሥጋህን ፈጭተው - - ጊዮርጊስ ኃያል ይድራስ ሲበትኑት - - ጊዮርጊስ ኃያል ዳግመኛ አስነሳህ አምላከ ምሕረት(፪) አዝ= = = = = አንገትህ ሲታረድ - - ጊዮርጊስ ኃያል ምድር ተናወጠች - - ጊዮርጊስ ኃያል ወተትና ውሃ - - ጊዮርጊስ ኃያል ደምም አፈለቀ - - ጊዮርጊስ ኃያል ሰብዐ ነገሥታት - - ጊዮርጊስ ኃያል እስኪደነቁብህ - - ጊዮርጊስ ኃያል ሰባት አክሊላትን ጌታ አቀዳጀህ(፪) አዝ= = = = = የዚህን ዓለም ጣዕም - - ጊዮርጊስ ኃያል ንቀኸው ጥቅሙን - - ጊዮርጊስ ኃያል በፍቅር ተቀበልክ - - ጊዮርጊስ ኃያል መራራ ሞትን - - ጊዮርጊስ ኃያል ሰማይና ምድር - - ጊዮርጊስ ኃያል ሳርና ቅጠሉ - - ጊዮርጊስ ኃያል ሰማዕተ ክርስቶስ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሉ(፪) Telegram: ☞https://t.me/joinchat/S3QVyScP7Saom-Lv
Open in Telegram