ከመጠን በላይ መጾም ወይም ከባድ ተጋድሎ ማድረግ ብቻ ሰይጣንን አያሸንፈውም፤ ሰይጣንን ድል የሚነሱት እውነተኛ ትሕትና፣ ሰውን መውደድ እና ራስን ዝቅ ማድረግም ጭምር ናቸው። #ቅዱስ_አባ_ጶሜን
Open in TelegramPosts of Deacon Chernet
በሕይወትህ እውነተኛ ሰላምን ማግኘት ከፈለግህ ሦስት ነገሮችን አድርግ፦ የራስህን ፈቃድ ተው፣ ራስህን ከማንም በላይ አታድርግ (እድገትህን አትለካ)፣ እናም ራስህን ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ፊት ጣል። #ቅዱስ_አባ_ጶሜን
Open in Telegramእንኳን ለነብያት ጾም በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! ስለጾመ ነቢያት እዚህ ያንብቡ ⬇️ https://t.me/deaconchernetc/351
Open in Telegram#ኅዳር_ዐሥራ_ሁለት_የቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላዕክት_መታሰቢያ_በዓል ኅዳር ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በሰማያት ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ሆኖ የተሾመበት፣ ጻድቁ ኢያሱ ወልደ ነዌን የተራዳበት እና ለቅዱስ ዱራታኦስ እና ለቅድስት ቴዎብስታ ተዓምር ላደረገበት መታሰቢያው ነው፣ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን፡፡
Open in Telegramአንድ ሰው በኃጢአት ወድቆ ብታየው፣ በልብህ አትፍረድበት፤ ይልቁንም 'እርሱ ዛሬ ወደቀ፣ እኔ ደግሞ ነገ እወድቃለሁ' ብለህ አስብ። #ቅዱስ_አባ_ጶሜን
Open in Telegramአንድ ሰው ወንድሙ ኃጢአት ሲሠራ ቢያየውና በዚያው ሰዓት ቢጸልይለት፣ ያ ኃጢአት በእርሱ ላይ ኃይል አይኖረውም፤ ነገር ግን በወንድሙ ላይ ቢፈርድበት፣ ያው ኃጢአት ወደ እርሱ ይሸጋገራል። #ቅዱስ_አባ_ጶሜን
Open in Telegramሰላም ወንድሞች እና እህቶች እንደምን ከረማችሁ !? ነፃ የonline ትምህርት ለመውሰድ ተመዝግባቹ እስካሁን Contact ያልተደረጋቹና በተከፈተው ግሩፕ ውስጥ ያልገባቹ በዚህ ቦት አናግሩን 👉 @Cher2112bot በቅርቡ ስለ ትምህርቱ ሙሉ ገለፃ እንሰጣቸዋለን !
Open in Telegram