እግዚአብሔር ኀያል፣ ስሙም ቅዱስ ነው። የቀረቡት ይህንን ይረዳሉ፤ ይቀኙለታልም። ማርያም በውዳሴዋ ይህንኑ አቀረበች፤ "ኀያል የሆነው እርሱ ታላቅ ነገር አድርጎልኛልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው፤ ምሕረቱም ለሚፈሩት ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል" (ሉቃ 1፥49-50)። አምላኳን ይዛ (በማሕፀኗ)፣ አምላኳን ባረከች። እግዚአብሔርን ከሚፈራ ትውልድ ወጥታ የጽድቅ ትውልድ አስቀጠለች። የምሕረቱን ስፋት አስቀጠለች። Luke 1:49-50 for the Mighty One has done great things for me— holy is his name. His mercy extends to those who fear him,from generation to generation. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in TelegramPosts of Daily Injera
በእግዚአብሔር የታሰቡ፣ እግዚአብሔርን ያስባሉ። መክበር ለማክበር፣ መጎብኘትም ለውዳሴ ያበቃል። ኤልዛቤል ማርያምን ለመገናኘት በቀረበች ጊዜና ድምፅዋን ስትሰማ በሆዷ የነበረው ጽንስ ዘለለ፤ በመንፈስም ተሞላች። ማርያምም ቀጥላ እንዲህ አለች፤ "ነፍሴ ጌታን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች፤ መንፈሴም በመድኀኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ትሠኛለች" (ሉቃ 1፥46-47)። ከነፍስ የሆነ ምስጋና፣ ከመንፈስም የሆነ አምልኮ አቀረበች። በመድኀኒቷ ደስ ስለ ተሰች ምስጋና አቀረበች። በውዳሴዋ ደስታዋን አበዛች። Luke 1:46-47 And Mary said: 'My soul glorifies the Lord and my spirit rejoices in God my Savior' @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramየሐና ልብ በእግዚአብሔር ጸና። ለርሱ መሸነፉን ግን ቀጠለ፤ የምስጋናን መዝሙር አመነጨ፤ “እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለም፤ ከአንተም በቀር ሌላ የለም፤ እንደ አምላካችን ያለ ዐለት የለም" (1ሳሙ 2፥2)። እግዚአብሔር ሰጪ ነው፤ የሰጠውንም ይቆጣጠራል። ሰጥቶ የሚወስድ፣ የሚሰስት አምላክ አይደለም። በማንነቱ ሰጪ ነው፤ ካሻውም ይነሣል፤ ሁሉ ለርሱ ነውና። ሁሉን ግን እንደ ቅድስናው ያደርጋል። ከርሱ ለሚቀበሉና ለሚጸኑም ዐለት ነው። በዘመናቸውም መታመኛና ዝማሬ ይሆናቸዋል። 1 Samuel 2:2 there is no one holy like the Lord; there is no one besides you; there is no Rock like our God. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramያመለጠ ሕዝብ ላስመለጠው አምላክ ይቀኛል። የድል መዝሙር ይዘምራል። ሙሴ፣ ማርያምና ሕዝቡ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው" ብለው ዘመሩ (ዘፀ 15፥3)። "ማርያምም ቀጥላ 'ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣ በባሕር ውስጥ ጥሏል፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ እጅግ ከፍ ከፍ ብሏልና' እያለች ዘመረችላቸው" (ቁ. 21)። እግዚአብሔር ለጦር አይዘጋጅም፤ ግን ድንገት ያጠቃል። ሕዝቡን ከወጥመድ ያድናል፤ ከቅርቃር ያወጣል። እየረታ ከፍ ከፍ ይላል። የምስጋና ምርኮንም ይወስዳል። Exodus 15:3 The Lord is a warrior; the Lord is his name. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramየእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚያከብሩ እርሱን ያወቁ ናቸው። ይህ ዕውቀት ደግሞ መቅረብን ያቀርባል፣ በፊቱም ንጹሕ ድፍረትም ይሆናል። እነርሱም ከዮሐንስ ጋራ እንዲህ ማለት ይችላሉ፤ "ትእዛዞቹንም ስለምንጠብቅና በፊቱም ደስ የሚያሠኘውን ስለምናደርግ የምንለምነውን ሁሉ ከርሱ እንቀበላለን" (1ዮሐ 3፥22)። መታዘዛቸው ልመናቸውን ያስውባል፤ ጥያቄያቸውም አቅርቦቱን ይገናኛል። 1 John 3:22 and receive from him anything we ask, because we keep his commands and do what pleases him. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegram#ArtSaturdays ባርነት መገዛትን ብቻ ይጠይቃል። ነጻነት ደግሞ መታዘዝን። በክርስቶስ ለሆኑ ደግሞ የተሰጠው ሕግ (ትእዛዝ) አርነትን የሚያጎናጽፍ ነው፤ "ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ ተመልክቶ የሚጸና፣ የሰማውን የሚያደርግና የማይረሳ ሰው በሥራው ብሩክ ይሆናል" (ያዕ 1፥25)። ቃሉ ከሸክም ወደ ዕረፍት ያመጣል። ይህ ዕረፍት ደግሞ ጠቃሚና ውጤታማ የሚያደርግ እንጂ ለሌላ ባርነት የሚዳርግ አይደለም፤ አንዳንዶች ዕፎይታቸውን ወደ ባሰ እስራት እንደሚለውጡበት። በሰሙት የሚጸኑ ግን ብሩካን ይሆናሉ። ነጻነታቸውም የብዙ ፍሬ ምክንያት ይሆናቸዋል። James 1:25 But whoever looks intently into the perfect law that gives freedom, and continues in it—not forgetting what they have heard, but doing it—they will be blessed in what they do. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramያዕቆብ በማሕፀን ሳለ ታላቁ (ዔሳው) እንደሚገዛለት ተነገረ። ከትንቢቱ በላይ ግን ጥረቱ አየለ፤ በረከትንም አታልሎ ወሰደ። ይህም ከወላጆቹ እንዲሰደድ አደረገው። በመንገድ ሳለ ግን እግዚአብሔር ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የሰጠሁህን ተስፋ እስከምፈጽምልህ ድረስ አልተውህም” (ዘፍ 28፥15)። ከሥጋት ወደ አጎቱ ቤት ባርነት ተሻገር፤ ብዙ መከራ አሳለፈ። ጌታ አምላክ ግን ቃሉን ጠብቆ አብሮት ዘለቀ። የሕይወት ምዕራፉ ከባድ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር እስከ ስህተቱ ታገሠው፤ ተስፋውንም ፈጸመለት። Genesis 28:15 I am with you and will watch over you wherever you go, and I will bring you back to this land. I will not leave you until I have done what I have promised you. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramበምድር ላይ የሚወድቅ ዘር ያበቃቀል ሥርዓት እንዳለው ሁሉ፣ የሰዎችም ዕድገት እንዲሁ ነው። ጌታችን በወይን ተክል በተመሰለበት የዮሐንስ 15ቱ ምሳሌ እንዲህ አለ፤ "በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ፤ ይሰጣችኋልም" (ቁ. 7)። ቅርንጫፍ የራሱ ሕይወት የለውም። አቅርቦቱን ሁሉ ከተክሉ ያገኛል። ከላይ የሚወርደው ዝናብ ቢያረጥበውም እንኳን ሕይወት አይሆነውም። ለልምላሜ የሚሆነውን የሚያገኘው በግንዱ በኩል ነው። እኛም የሚያስፈልገንንና የምንፈልገውን የምናገኘው በርሱ በመኖር ነው። ቃሎቹንም ስንኖር በፈቃዱ ክልል ያቆዩናል። የሚሰጠንን ሁሉ እንድንለምንም ያበቁናል። John 15:7 If you remain in me and my words remain in you, ask whatever you wish, and it will be done for you. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramየሚያምኑትንና የሚወድዱትን መታዘዝ ቀላል ነው። ከእግዚአብሔር በላይ ለዚህ ብቁ የሚሆንስ የት ይገኛል?የሚጠበቀውም መስማማት ብቻ ነው፤ አቅም ከርሱ ዘንድ ይመጣልና። ቃሉ እንዲህ ይላል፤ "ዕሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ" (ኢሳ 1፥19)። የዚህ ግልባጩ ደግሞ ለአጥፊው አልፎ መሰጠት ነው። እግዚአብሔርን ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ 'ዕሺ' አይሉትም፤ ሁልጊዜ እንጂ! እርሱ ለተወሰኑ ጉዳዮችና ለተለዩ ሁኔታዎች ብቻ የሚፈለግ አይደለም፤ ለሁለመናና ለሁልጊዜ እንጂ። Isaiah 1:19 If you are willing and obedient, you will eat the good things of the land; @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramጽድቅና ዓመፅ በሚነጻጸሩበት ብቻ ሳይሆን አንዱ ሌላውን በሚቃረንበት ጊዜ፣ ሕያው አምላክንና የርሱን ብቻ ይዞ መጽናት የባሕርይ ልቀት ነው። እርሱ ዘመኑን ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ሰዎችንም እንዲሁ ይለያል፤ "እግዚአብሔር የንጹሓንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤ ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል" (መዝ 37፥18)። ዕውቀቱ በአቅርቦቱ ይታጀባል፤ በሚሰጠው ተስፋም ያብባል።እርሱን በመስማትና በመታዘዝ ልዩነትን ለሚያሳዩም መዝገቡ ሙሉ ነው። Psalms 37:18 The blameless spend their days under the Lord’s care, and their inheritance will endure forever. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramመታዘዝ አቅርቦትን ይቀድማል። ኤልያስ የእግዘብሔርን ቃል ሰማ፤ አምኖም ታዘዘ። የመጣለት ቃልም መራው፤ "ስለዚህ እግዚአብሔር ያዘዘውን ፈጸመ፤ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ኮራት ወንዝ ሄዶ በዚያ ተቀመጠ። ቍራዎችም ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ውሃም ከወንዙ ይጠጣ ነበር" (1ነገ 17፥5-6)። ቍራ ብልኀ ወፍ ቢሆንም በቀላሉ የሚገራ ግን አይደለም--የኖህን ገጠመኝ ልብ ይሏል። እግዚአብሔር ሲያዝዘው ግን መልእክቱንም ሆነ ጊዜውን አላዛነፈም። ጌታ ቃሉን ለሚታዘዙ ሁሉ ሌላውንም ያስገዛላቸዋል። 1 Kings 17:5 So he did what the Lord had told him. He went to the Kerith Ravine, east of the Jordan, and stayed there. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramአብ የመረጣቸውን ወልድ አነጻቸው፤ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ቀደሳቸው፤ “እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ካወቃቸው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመታዘዝ በደሙ ለተረጩትና በመንፈስ አማካይነት ለተቀደሱት፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ” (1ጴጥ 1፥2)። እነርሱንም ከሰማይ ብቻ የሚገኝ ጸጋ ያገኛቸዋል፤ ሰላማቸውም የማይነጥፍ ነው። በሥላሴ ታውቀዋል፤ በሥላሴ ተዋጅተዋል፤ በሥላሴ ተቀድሰዋል፤ የሥላሴንም በረከት እየተቀበሉ ይኖራሉ። 1 Peter 1:2 who have been chosen according to the foreknowledge of God the Father, through the sanctifying work of the Spirit, to be obedient to Jesus Christ and sprinkled with his blood: Grace and peace be yours in abundance. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegram#ArtSaturdays ሐዋርያዊው ባርኮት ሦስቱንም የሥላሴ አካላት (አምካላት--አምላካዊ አካል) የያዘ ነው፤ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋራ ይሁን” (2ቆሮ 13፥14)። ጸጋ፣ ሰላምና ኀብረት መገኛቸው መለኮት ነው። በርሱ ዘንድ ፍጹም ሰላም፣ ግሩም ኀብረት፣ እንዲሁም ምሉዕ ጸጋ አለ። ቡራኬው የሚያገኛቸው ደግሞ ሀልዎቱን ከትሩፋቱ ጋራ ይካፈላሉ። 2 Corinthians 13:14 May the grace of the Lord Jesus Christ, and the love of God, and the fellowship of the Holy Spirit be with you all. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramመንፈስ ቅዱስ ግሩምና ታላቅ አብራሪ ነው (ከሜንተተር) ነው፤ የቃሉ ባለቤት ቃሉን ይገልጣል። ከአብ የተቀበለውን ተልዕኮ ከኀይሉ ጋራ ይዞ ወርዷል። በቤተ ክርስቲያን ላይ ብቻ ሳይሆን በክርስቲያኖች ሁሉ ላይም አድሯል። ስለ እርሱም ጌታ ያለው ተፈጽሟል፤ “አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል” (ዮሐ 14፥26)። አብ በልጁ የዋጃቸውን እንዲያስተምርና እንዲመራ ላከው። እርሱም እያጽናና ወልድን ተረከ፤ የሚሰሙትንም በወልድ ላይ እያነጸ ወደ አብ አቀረበ። የማያዩት እረኛ ቢሆንም፣ ይሰማል፤ ይመራልም። John 14:26 But the Advocate, the Holy Spirit, whom the Father will send in my name, will teach you all things and will remind you of everything I have said to you. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramታላቁ ተልዕኮ ታላቁን ትእዛዝ ብቻ ሳይሆን ታላቁን አብሮነትንም የያዘ ነው። ክርስቶስ ጌታ እየተለያቸው፣ አብሯቸው እንደሚሆን ነገራቸው፤ “ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ” (ማቴ 28፥19-20)። ተልዕኮው ክቡር ነው፤ በአብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ጀምሮ (ጥምቀት) በሦስቱም አካላት--ሥላሴ-- ደቀ መዝሙር በማድረግ የሚጠናቀቅ። በዚህ ሰማያዊ ሥራ መካከልም መንፈስ የሆነው ጌታ ሁልጊዜ አብሮ ይሆናል። በሥጋ ሲለይ፣ በመንፈስ ተገኝቷል። በርሱም ሥራና አብሮነት የአብና መንፈስ መንፈስ ቅዱስ ሀልዎት እውን ሆኗል። Matthew 28:20 And surely I am with you always, to the very end of the age. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramቃል ሥጋ ከሆነ በኋላ አገልግሎት ለመጀመር ሠላሳ ዓመታትን ጠበቀ። የተልዕኮውንም ዋና ክፍል በዮሐንስ በመጠመቅ ጀመረ፤ “ኢየሱስም እንደ ተጠመቀ ከውሃው ወጣ፤ ወዲያውኑም ሰማይ ተከፍቶ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድበት አየ። እነሆ፤ 'በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው' የሚል ድምፅ ከሰማይ ተሰማ” (ማቴ 3፥16-17)። መጠመቅ ሳይገባው 'ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም' በትሕትና ሲጠመቅ፣ ከሰማይ ተመሰከረለት፤ ከአባትና መንፈስ ቅዱስ ሞገስን ተቀበለ። ሥላሴ በአንድ ኹነት በሦስት ተገለጠ፤ ወልድ በሥጋ፣ መንፈስ በርግብ፣ አብ ደግሞ በድምፅ! Matthew 3:17 And a voice from heaven said, 'This is my Son, whom I love; with him I am well pleased.' @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramብሉይ ኪዳን ስለ ወልድ አምላክ ተናግሯል፤ እርሱንም እንደ ተናጋሪ አቅርቧል፤ ኢሳይያስ ላይም እንዲህ ይላል፤ "ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህን ስሙ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ በስውር አልተናገርሁም፤ ሲፈጸምም እኔ እዚያው ነበርሁ። አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል" (ኢሳ 48፥16)። ጌታ ፊተኛና ሁዋለኛ ነው፤ ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ መኖር አልጀመረም። ጅማሬውን እንደ ጀመረ ፍጻሜውንም ይፈጽማል። እርሱ እንደ ተላከውም ("ልከውኛል") አድርጓል። በአብና በመንፈስ ቅዱስ ተልኳል፤ የሥላሴ ተልዕኮን ፈጽሟል። ቃል—ሎጎስ— የሆነው አምላክ በቃሉ እንደ ተናገረ፣ በሰውነቱ—መሥዋዕቱ—ተናግሯል። Isaiah 48:16 Come near me and listen to this: 'From the first announcement I have not spoken in secret; at the time it happens, I am there.' And now the Sovereign Lord has sent me, endowed with his Spirit. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramሥሉስ ባርኮት--አሮን እና ካህናት የእግዘብሔርን ሕዝብ እንዲህ በማለት እንዲባርኩ ታዘዙ፤ “እግዚአብሔር ይባርክህ፤ ይጠብቅህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፤ ይራራልህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ይመልስልህ፤ ሰላሙንም ይስጥህ” (ዘኍ 6፥24-26)። አብ ይባርካል፤ ወልድ ብርሃን ይሆናል፤ መንፈስ ቅዱስም በእግዚአብሔር ሰላም ውስጥ ያሳድራል። ርኀራኄና ጥበቃ ያሉባቸው እነዚህ ሰማያዊ ትሩፋቶች (ባርኮት፣ ብርሃንና ሰላም) የእግዚአብሔር ታላቅነትና ዘላለማዊነት ያህል ወሰንና ገደብ የላቸውም። Numbers 6:24-26 The Lord bless you and keep you; the Lord make his face shine on you and be gracious to you; the Lord turn his face toward you and give you peace. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegramየራስ ቁር መከላከያ፣ ሰይፍ ደግሞ ማጥቂያ ነው። መዳናቸውን እንደ ራስ ቁር የሚያጠልቁ በሐሳባቸው የጌታ ለመሆናቸው ርግጠኛ ናቸው፤ ከሚያደናግሩ የሐሳብ ፍላጻዎችም አእምሮአቸው ይጠበቃል። በቃሉ እውነት ርግጠኛ የሆኑትን ያህል እጃቸውም የቃሉን ሰይፍ ያነሣል፤ “የመዳንን ራስ ቍር አድርጉ፤ የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው” (ኤፌ 6፥17)። ብዙ ባዶ እጆች ባሉበት፣ መንፈሳዊ ሥራ ፈትነትም በበዛበት ዘመን ቃሉን ያነሡ ያልተፈለገውን ይቆርጣሉ። በቃሉ ሰይፍ እየተበጁም ሌላውን ያበጃሉ። Ephesians 6:17 Take the helmet of salvation and the sword of the Spirit, which is the word of God. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegram#ArtSaturdays የተራራው ስብከት (ማቴ 5-7) ጌታ ከደቀ መዛሙርቱ ጀምሮ ብዙ ሕዝብን ያስተማረበት ክፍል ነው። ያ ሁሉ ትምህርት ግን ተሰምቶ ብቻ አድናቆት የሚቀርብለት ወይም የሚዘከር ብቻ አይደለም፤ “እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል። ዶፍ ወረደ፤ ጎርፍም በዐለትም ላይ ስለ ተመሠረተ አልወደቀም" (ማቴ 7፥24-25)። ቃሉ ከተሰማበት ጊዜ፣ ጉባኤ፣ ሁኔታ በላይ የሚተገበርበት ዝግጅትና ውሳኔ ይፈልጋል። ተቀብለን የምናሰላስለውና የሕይወት ርሀችን የምናደርገው ነው። ከሰሙም በላይ ያደረጉ ብፁዓን ናቸው፤ ብፅዕና ጽናት ነውና። Matthew 7:24 Therefore everyone who hears these words of mine and puts them into practice is like a wise man who built his house on the rock. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest
Open in Telegram