Account

Posts of አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE

newest first

#5423Photo

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - ኅዳር 17 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች አንዱ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ በመልካም አስተዳደግና በትምህርት ያደገ ሲሆን፣ በወጣትነቱ ዓለማዊ ሀብትና ክብርን ንቆ ወደ ምንኩስና ገባ። ከወላጆቹ የወረሰውንም ሀብት ለድሆችና ለምስኪኖች አከፋፈለ። በጸሎት፣ በትሩፋትና በመንፈሳዊ ትጋት የጠነከረው ቅዱስ ዮሐንስ በብዙ መንፈሳዊ መጻሕፍትና ተግሣጻት የታወቀ ሆነ። በኋላም የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ ሆኖ በታላቅ ትጋት ምእመናንን አስተማረ። አገለገለ። ቅዱሱ በሹመትና በሀብት የተመኩ ሰዎችንም ሆነ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ከኃጢአትና ከዓመፅ ሥራቸው እንዲታቀቡ ይገሥጽ ነበር። በተለይም ንግሥት አውዶክስያ የአንዲትን ድሃ መበለት መሬት በግፍ በወሰደች ጊዜ እንድትመልስ በመጠየቁና ክፉ ሥራዋን እንድታቆም በመገሠጹ በእርሷ ምክንያት ለሁለት ጊዜ ወደ ስደት ተላከ። በመጀመሪያው ስደት ወደ ቀናች ሃይማኖት ያልገቡ ሰዎችን በማስተማር ወደ እምነት መለሰ። በሁለተኛው ስደት ግን ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው አረፈ። የመጨረሻ ቃሉም፦ «ለሁሉ ነገር ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን» የሚል ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ በስብከቱ ጥልቀት፣ በትምህርቱ ጥበብና በንግግሩ ጣፋጭነት «አፈ ወርቅ» ተብሎ ታወቀ። በርካታ ድርሳናትንና ትርጓሜዎችን ያበረከተ ሲሆን፣ ትምህርቶቹም እስከ ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ ሀብት ሆነው ይገኛሉ። ከዕረፍቱ ከሠላሳ አምስት ዓመታት በኋላ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ትእዛዝ ኅዳር 17 አፅሙ በታላቅ ክብር ወደ ቍስጥንጥንያ ተመልሶ ተቀበረ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፤ ፊትን ዓይቶ የማያዳላ እውነተኜ ሰባኪ፣ የድሆች ጠበቃ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት አስተማሪ እና የሃይማኖት ዓምድ ነው። እግዚአብሔር በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጸሎት ይማረን፤ በረከቱም ትደርብን🙏

Open in Telegram
Views1,660−58%vs avg
Forwards—
Reactions31
Comments—
#5422Photo
Views1,670−57%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#5419Photo
Views2,990−23%vs avg
Forwards—
Reactions28
Comments—
#5414Photo
Views5,020+28%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#5413Text
Views4,880+25%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#5412Text

ድርሳን ሃያ ስድስት ማንም የሚሰናከልበትን ነገር አለማድረግን በተመለከተ “በራሱ ርኵስ የኾነ ነገር እንደ ሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄአለሁ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ምንም ርኵስ እንዲሆን ለሚቆጥር ለእርሱ ርኵስ ነው።” (ቁ. ፲፬) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በወንድሙ ላይ የሚፈርደውን ሰው ከገሠጸውና ይህንን ነቀፋ እንዲተው ካደረገ በኋላ፣ መሠረታዊ ወደ ኾነው የክርስትና አስተምህሮ በማለፍ በዚህ ጉዳይ ላይ በእምነት ለደከሙት በተረጋጋና በየዋሃት መንፈስ ኾኖ ትምህርቱን ወደማብራራት ገባ። ሐዋርያው “ይቀጣ ዘንድ ይገባዋል” አላለም። ይህን የመሰለ ነገርንም አልተናገረም። ይልቁንም የሚናገረውን በቀላሉ እንዲቀበሉት ሲል የፍርሀት ሸክማቸውን አቀለለላቸው። ቅዱስ ጳውሎስ፡- “አውቄአለሁ ተረድቼአለሁም፤” ይላል። ነገር ግን እርሱ ያስተማረውን ያላመኑትን ለመቃወምና “ያንተ መረዳት ለእኛ ምናችን ነው? ያን የመሰለ ታላቅ የሙሴ ሕግና ከሰማይ የወረደውን የእግዚአብሔርን ቃል ለመቃወም ያንተ የግል ምስክርነት ምን ዋጋ አለው?” እንዳይሉ ሲል ወዲያውኑ “በጌታ በኢየሱስ ሆኜ” የሚለውን ሐረግ ጨመረ። ትርጉሙም “ይህን የተማርኩት ከራሱ ከክርስቶስ ነው፤ መተማመኛዬም እርሱ ነው” ማለቱ ነው። ስለዚህ ይህ የሰው አስተሳሰብ ሳይሆን የእግዚአብሔርም ሐሳብ ነው ሲላቸውም እንዲህ ብሎአል። ለመሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ በእርግጠኝነት ያወቀውና የተረዳው ምንድን ነው? እርሱ እንተናገረው ያለው በራሱ ርኩስ የኾነ ነገር እንደሌለ ነው። በተፈጥሮው ርኩስ የኾነ መብል የለም፤ ነገር ግን አንድ ሰው እንደመረዳቱ መጠን ርኩስ ሊሆንበት ይችላል። ስለዚህ ርኩስ የሚኾነው ያንን ነገር ርኩስ ነው ብሎ ለሚያስበው ለዚያ ሰው ብቻ እንጂ ለሌላው አይደለም። “ማንኛውንም ነገር ርኩስ እንደ ኾነ ለሚቆጥር፥ ለእርሱ  ርኩስ ነውና።” ቅዱስ ጳውሎስን አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ሊጠይቀው ይችላል፡- “መብል ኹሉ ንጹሕ  አይደለም ብሎ የሚያስበው ወንድምን ይህንን ይረዳ ዘንድ ስለምን አታስተምረውም? ስለምንስ በተሰጠህ ሙሉ ሥልጣንህ ተጠቅመህ ይህ ትክክል ነው ብሎ እንዳይቀበል እንዲህ ብሎ ከማሰብ ልማድና ነገሮችን እንዲህ ከመረዳት እንዲወጣ ስለምን አታደርገውም?” ሊለው ይችላል፤ እርሱም “እንዲህ የማድረጌ ምክንያት አስቀድሜ እርሱን በፍቅር ማቅረብ አለብኝ” ብሎ ይመልስልሃል። እንዲህም ስለኾነ እንደሚከተለው  አለ፤ ከመጽሐፉገጽ421 - 422 የተወሰደ #አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ማኅበረ_ቅዱሳን_ሕንፃ_ግራውዱ_አጠገብ_0988888589_0954838117_ይደውሉ! https://t.me/BetMetsahfte

Open in Telegram
Views4,860+24%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—
#5410Text

#ኢየሱስ_ክርስቶስ_ለምን_ሰው_ሆነ? ጌታ በሲና ተራራ ላይ በእሳት አምሳል ወረደ፤ ሕዝቡ ግን ይኼን እሳት ሊቋቋመው አልቻለም፤ ሙሴንም “አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን፤ እንዳንሞት ግን እግዚአብሔር አይናገረን አሉት።” (ዘፀ. 20፥19) እንደገናም “ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሕያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በሕይወቱ የኖረ ማን ነው?” (ዘዳ. 5፥26) አሉ። የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት ሞት የሚያመጣ ከሆነ ራሱን የእነርሱ እንዲህ ማለት እግዚአብሔርን ዐይቶ ማን በሕይወት ይኖራል? ያስገርማችኋል? ሙሴ ራሱ “እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጣለሁ” ብሏል (ዕብ 12፥21)። 12.14. ታዲያ ምን ይሁን? ለእኛ ድኅነት ሲል የመጣው የሰው ተፈጥሮ ሊይዘው አይችልምና ያጥፋንን? ወይስ ጸጋውን ከእኛ ጋራ አስማምቶ ወደእኛ ልክ ያድርገው? ዳንኤል አንድን መልአክ ማየት አልቻለም፤ እናንተስ የመላእክትን ጌታ ማየት ትችላላችሁን? ዳንኤል ቅዱስ ገብርኤል ቢገለጥለት ወደቀ። መልአኩ ግን በምን ዐይነት መልክ ነው የተገለጠለት? የተገለጠው “በመብረቅ መልክ” ነው (ዳን. 10፥6 እንደ ፀሓይ አይደለም። መልአኩ ዐይኖቹ እንደሚንበለበል ፋና ነው፤ እንደእሳ ምድጃ አይደለም። ድምፁ እንደ ብዙ ሕዝብ ነበር እንጂ የዐሥራ ኹለት ጭፍሮ–መላእክት ድምፅ አይደለም። ነገር ግን ነቢዩ ወደቀ፤ መልአኩም ወደ እርሱ ቀር “አትፍራ፤ ልብህ ያስተውል ዘንድ፥ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህር ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቶአል፤ እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ።” (ዳን. 10፥12 አለው። ዳንኤል እየተንቀጠቀጠ ተነሣ፤ የሰውን ልጅ የምትመስል መጥታ እስክትነካው መልስ መመለስ እንኳን አልቻለም። የታየው መልአክ ወደ ሰው መልክ ሲቀየርለት ዳንኤል መናገር ጀመረ። ምን እንዳለ ስሙ “ከራእዩ የተነሣ ሕመሜ መጣብኝ፤ ኀይልም አጣሁ፤ እስትንፋስም አልቀረልኝም” (ዳን. 10፥17) አንድን መልአክ ማየት የነቢዩን አንደበትና ኀይል የወሰደበት ከሆነ እግዚአብሔርን ቢያይ ሊተነፍስ ይችላል? “ሰው መስሎ እስኪዳስሰኝ ድረስ” በማለት ድፍረቱን እንዳጣ የትንቢት መጽሐፉ ይናገራል። ጌታ የእኛን ድካም ካየ በኋላ የሰው ልጅ እንደሚፈልገው ሁኖ መጣ፤ የሰው ልጅ መስማት የሚፈልገው በቀላሉ እርሱን ከሚመስለው ጋራ በመሆኑ፤ መድኅንም [አዳኙ፣ ኢየሱስ] የሰው ልጆች ይበልጥ እንዲያውቁት የሰውን ባሕርይ ይዞ መጣ። #የቅዱስ_ቄርሎስ_ዘኢየሩሳሌም_ትምህርቶች ከ ገጽ 167 የተወሰደ። https://t.me/BetMetsahfte

Open in Telegram
Views3,830−2%vs avg
Forwards—
Reactions23
Comments—
#5409Photo

አኰቴተ ቍርባን - በቀሲስ መብራቱ ኪሮስ ገብሩ (ዶ/ር) || 8ኛ ዕትም ◄◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆► ማዕጠንት ዘወርቅ ሠራዒው ካህን “አንቲ ውእቱ” (አንቺ ነሽ) እያለ ሲያዜም ምእመናን “ማዕጠንት ዘወርቅ እንተ ፆርኪ ፍሕመ እሳት . . .” (የእሳትን ፍሕም የተሸከምሽ የወርቅ ጥና [ጽንሐሕ] . . .” በማለት የሚጀምረውን ዝማሬ እያዜሙ መልስ ይሰጣሉ፡፡7 ይሀ ዝማሬ የተወሰደው ከኮፕቲከ ቅዳሴ ሲሆን የመዝሙሩ የእንግሊዝኛ ትርጕም መዝሙረ ማዕጠ ማዕጠንት ዘወርቅ¹8 የተሰኘ ርእስ ሰጥቶታል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ቅዳሴ ከዚህ ዝማሬ በፊት ካህኑና ምእመናኑ እየተቀባበሉ የሚያዜሟቸው (ንስግድ፡- ለአብ ወወልድ ወመ ዐመንፈስ ቅዱስ እንዘ ሠለስቱ አሐዱ፤ ሰላም ለኪ፡- ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማኅደረ መለኮት፤ ሰአሊ ለነ፡- ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላከ)⁹ በኮፕቲክ ቲከ ቅዳሴ ውስጥ አይገኙም፡፡ _ ስለሆነም ሊቃውንቱ ኢትዮጵያውያን አባቶቻ ቶቻችን ከተለያዩ ምንጮች ወስደው የጨመሯቸው ናቸው፡፡ -“ማዕጠንት ዘወርቅ” የሚለው ዝማሬ ምሥጢረ ሥጋዌን (የአምላክ ሰው መሆንን ምሥጢር ዮሐ. 1፥14፤ 1 ጢሞ. 3፥16) ድንቅ በሆነ ምሳሌ የሚያስተምር መዝሙር ነው፡፡ በመለኮታዊ ባሕርዩ የሚያቃጥል እሳት የሆነው ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ከርስቶስ፥ ለማደሪያነት በመረጣት በቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ድንግል ማርያም ማኅፀን አድሯልና የዝማሬው ደራሲ፥ ጌታን በእሳቱ ፍሕም፥ እመቤታችንን ደግሞ ፍሕሙን በሚሸከመው ጥና (ጽንሐሕ)8° መስሎ ያስተምረናል፡፡ ከመጽሐፉ ገጽ 266 የተወሰደ ◄◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆► ዛሬ @orthokiha ለሚያዙ ልዩ ቅናሽ አድርገናል። https://t.me/BetMetsahfte

Open in Telegram
Views4,060+4%vs avg
Forwards—
Reactions19
Comments—
#5407Photo
Views5,780+48%vs avg
Forwards—
Reactions26
Comments—
#5405Photo
Views5,660+45%vs avg
Forwards—
Reactions20
Comments—
#5403Photo
Views5,750+47%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—