Account

Posts of E-LMIS - ብቁ

newest first

#627Photo

🚀 የሥራ እድል ማስታወቂያ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት /E-LMIS/ በኩል ከታች በተዘረዘሩት የሥራ ዘርፎች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። 👷 ክፍት የስራ መደቦች 🔹 Animal Science / Production – 11 ቦታ 🔹 Civics and Ethical Education – 1 ቦታ 🔹 Computer Science – 4 ቦታ 🔹 Agri-Business and Value Chain – 2 ቦታ 🔹 Rural Development / Agricultural Extension – 2 ቦታ 🔹 Agricultural Economics – 1 ቦታ 🔹 Agricultural Machinery and Equipment Operation and Maintenance – 12 ቦታ 🔹 Animal Health – 7 ቦታ 📌 ተጨማሪ መስፈርቶች አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማመልከት ይችላሉ። ለወንድ አመልካቾች ዝቅተኛው CGPA 3.5 እና ለሴት አመልካቾች 2.7 አመልካቾች ኦሪጅናል እና ኮፒ የትምህርት ማስረጃዎችን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። የሥራ ልምድ ያላቸው አመልካቾች የሥራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 🏫 ስለሆነም በዚህ የሥራ እድል መወዳደር ለምትፈልጉ በመጀመሪያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ፣ አቅራቢያችሁ ባለ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል /ወረዳ ወይም ቀበሌ/ በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር /Labor ID/ ከያዛችሁ በኋላ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። https://job-forms.lmis.gov.et/apply/post-hr-2026-10-26 ☎️ አስተያየት እና ጥቆማዎን በ 9138 የሥልክ መስመር ይደውሉ።

Open in Telegram
Views50,6000%vs avg
Forwards—
Reactions683
Comments—
#625Text

በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ አረቢያ የሥራ ስምምነት ዙሪያ የተሰጠ ማብራሪያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ አረቢያ መካከል ስላለው የሥራ ስምምነት እና የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ሂደት ዙሪያ የተለያዩ የተሳሳቱ እና መሠረተ ቢስ መረጃዎች ሲሰራጩ ተመልክቷል። ዜጎችና እና ባለድርሻ አካላት ትክክለኛ መረጃ እንዲኖራቸው፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ “አንድም ሰው ወደ ሳዑዲ አረቢያ መሄድ አልቻለም”፤ “የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ የተዘጋጀው ለጥቂቶች ብቻ ነው” ፤ “የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (E-LMIS) ተዘግቷል”፤ “ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች በበቂ ሁኔታ መረጃ አልተሰጣቸውም ” ወዘተ የሚሉ ብዥታ ሊፈጥሩ የሚችሉ፣ መሠረተ-ቢስ አሉባልታዎችን ለማጥራት ይሻል። የኢትዮጵያ የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ሥርዓት የቅጥር ሂደትን ለመቆጣጠር፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ኤጀንሲዎች ሕጋዊ የሥራ ስምሪት እንዲያከናውኑ ለማረጋገጥ እና ለመቆጣጠር ብሎም ሕጋዊ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ክብር ያለው የሥራ ስምሪት ተጠቃሚነትን ለኢትዮጵያውያን ለማረጋገጥ የተመሠረተ ነው። በዚህም ሳዑዲ አረቢያ ለኢትዮጵያውያን የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ዋና መዳረሻ ከሆኑ አገራት አንዷ ስትሆን፣ በኢትዮጵያ ቁጥጥር የሚደረግበት የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ማዕቀፍ ውስጥ ቁልፍ አጋር ሆና ትቀጥላለች። በሳዑዲ አረቢያ የሥራ ስምሪት ውስጥ የሚሠሩትን ጨምሮ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ምኅዳር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው የቅጥር ኤጀንሲዎች የዚህ ሂደት የማይነጠል አካል ሆነው ቀጥለዋል። ይሁንና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በሥራ ስምሪት ሂደት ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ተግዳሮቶችንና ክፍተቶችን ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በማጣራት የማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። ነገር ግን፣ "የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ተዘግቷል" ፣ "ዜጎች እየተሰማሩ አይደለም" ወዘተ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ሙሉ በሙሉ መሠረት የለሽ መሆናቸውን እያስገነዘብን ይልቁንም ሕጋዊ የሥራ ስምሪት ሂደቱ በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ እየተቀላጠፈ የቀጠለ መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን፡፡ በመሆኑም ዜጎች እነዚህን በመሰሉ ከእውነት የራቁ መረጃዎች እንዳይደናገሩ እያሳሰብን፤ መሠረት የለሽና አሳሳች መረጃዎችን በሚያሰራጩ አካላት ላይ ማጣራት በማድረግ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆናችንን እናስገነዝባለን። ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ጋር በተገናኘ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ይፋዊ ድረ-ገጾች ብቻ እንድትከታተሉም እናሳውቃለን፡፡ Clarifications Regarding the Ethiopia-Saudi Arabia Labor Agreement The FDRE Ministry of Labor and Skills (MoLS) has noted with concern several unsubstantiated claims circulating about the Ethiopia–Saudi Arabia employment agreement and the overseas employment process. To ensure the public and all stakeholders have accurate information, the Ministry wishes to address the following allegations directly: “Not one person has gone to Saudi Arabia through the agreement.” “The system was made exclusively for a few.” “The Ethiopian Labor Market Information System (E-LMIS) is closed.” “Overseas Employment Agencies have not been informed.” Here are the verified facts: Saudi Arabia is one of Ethiopia’s main countries of destination for overseas employment and remains a key partner in Ethiopia’s regulated overseas employment framework. Ethiopia’s overseas employment system is designed to regulate recruitment, verify complaint agencies, and facilitate the legal, safe and dignified deployment of Ethiopian workers. Authorized recruitment agencies continue to be an integral part of this process, including those operating within the Saudi Arabia corridor. While the Ministry acknowledges that operational challenges, delays, and individual cases require attention,and are being continuously addressed, they should not be misrepresented as evidence that the entire system is closed or that “nobody” has been able to proceed. Citizens and stakeholders deserve accurate information—not baseless rumours or blanket statements. The Ministry welcomes constructive feedback and remains committed to open communication. But above all, our priority is to ensure that Ethiopian workers receive clear and reliable information about their opportunities.

Open in Telegram
Views102,000+102%vs avg
Forwards—
Reactions1,360
Comments—
#624Photo
Views151,000+198%vs avg
Forwards—
Reactions1,223
Comments—
#623Photo

🎓🌍የስልጠና እድል 🚀Yokogawa Electric Corporation ከInternational Organization for Migration (IOM) እና የኢትዮጵያ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች በነጻ የሚሰጥ ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና አዘጋጅቷል። 📚የስልጠና ዘርፎች 🔹Business Ethics & Professional Conduct 🔹Logistics & Supply Chain Management 🔹Import/Export Regulations 🔹የAfCFTA ንግድ እድሎች 🔹የGCC አገራት የስራ ገበያ እና የቅጥር እድሎች 🔹Entrepreneurship 🔹 Workplace Readiness 🔹የጥራት ማረጋገጫና የጥራት ቁጥጥር 🔹የጤና፣ ደህንነት እና አካባቢ ጥበቃ 👥መስፈርቶች 🔹ዕድሜ፦ ከ30 በታች 🔹ትምህርት፦ በ2018 ዓ.ም. የሚመረቁ የባችለር ወይም የማስተርስ ምሩቃን፣ ወይም ባለፉት 2 ዓመታት ውስጥ የተመረቁ። 🔹የትምህርት መስኮች፦ • Supply Chain Management • Procurement • Logistics • Business Administration • Trade Studies • Sustainability • ወይም ሌሎች ተዛማጅ የትምህርት መስኮች። 📍 ቦታ Kaizen Excellence Centre (KEC)፣ አዲስ አበባ 📅የስልጠና ቀን- ከሐምሌ 6–8 ቀን 2018 🎁ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል 1 ተሳታፊ ተመርጦ በYokogawa Internship Program ከ2019 የልምምድ ፕሮግራም ይሳተፋል። ✅ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚኖሩ የተመረጡ ተሳታፊዎች፦ 🔹የትራንስፖርት ወጪ 🔹በስልጠናው ቆይታ የማረፊያ ወጪ ይሸፈናል። 📝አመልካቾች በዚህ https://forms.lmis.gov.et/yokogawa_electric/ በመግባት ትክክለኛ መረጃዎችን ሞልተው ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

Open in Telegram
Views137,000+171%vs avg
Forwards—
Reactions495
Comments—
#622Photo

🚀 ሜድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግል ማህበር በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS በኩል ከታች በተዘረዘሩት የሥራ ዘርፎች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። 👷 ክፍት የስራ መደቦች 🔹 HR/Admin Officer – 2 ቦታ ትምህርት፡ BA Degree በManagement፣ Accounting ወይም ተዛማጅ ዘርፍ የስራ ልምድ፡ 3–4 ዓመት የቅጥር አይነት፡ ኮንትራት 🔹 Store Keeper – 2 ቦታ ትምህርት፡ Degree በSupply Chain Management፣ Accounting፣ Management ወይም ተዛማጅ ዘርፍ የስራ ልምድ፡ 3 ዓመት የቅጥር አይነት፡ ኮንትራት 🔹 Excavator Operator III – 15 ቦታ ትምህርት፡ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ የስራ ልምድ፡ በExcavator Operator 8 ዓመት የቅጥር አይነት፡ ቋሚ 🏫 ስለሆነም በዚህ የሥራ እድል መወዳደር ለምትፈልጉ በመጀመሪያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር /Labor ID/ ከያዛችሁ በዚህ https://forms.lmis.gov.et/midroc-construction-ethiopia/ በመግባት ትክክለኛ መረጃዎትን ሞልተው ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። 📆 አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 29/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ማመልከት ይችላሉ። ☎️አስተያየት እና ጥቆማዎን በ9138 የሥልክ መስመር ይደውሉ።

Open in Telegram
Views107,000+111%vs avg
Forwards—
Reactions353
Comments—
#619Photo
Views99,600+97%vs avg
Forwards—
Reactions224
Comments—
#610Photo

🎓🏦 በባንክ ዘርፍ መሰማራት ለምትፈልጉ አዲስ ተመራቂዎች 🏦🎓 🌍🌎 በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት /E-LMIS/ ሥራ ፈላጊ ለሆኑ ዜጎች በባንክ ዘርፍ እያደገ በመጣው የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሙያ እድገት ለማድረግ ለሚፈልጉ ወጣት ምሩቃን ዘምዘም ባንክ (ZamZam Bank) 300 ለሚሆኑ Graduate Trainee የስራ እድሎችን አዘጋጅቷል። ✅ የሚፈለጉ መስፈርቶች 🎓 በማንኛውም የማህበራዊ ( Business Filed) 🏦 Graduate Trainee 📅 በመጨረሻዎቹ 3 ዓመታት (2015-2018ዓ.ም ) ውስጥ የተመረቁ፣ 📝 የNational Exit Examination ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁ፣ 💼 የስራ ልምድ አያስፈልግም፣ 🕌 በBanking የባንክ አገልግሎት ላይ ፍላጎት ያላቸው፣ 💻 መሠረታዊ የኮምፒውተር እውቀት (MS Office, Email, Internet) ያላቸው፣ 🗣 ጥሩ የእንግሊዝኛ የመግባቢያ ክህሎት ያላቸው፣ 🤝 የቡድን ስራ፣ የተሻለ ግንኙነት እና የደንበኛ አገልግሎት ክህሎት ያላቸው፣ 📈 ለመማር፣ ለመለወጥ እና ለመላመድ ዝግጁ የሆኑ፣ 🧠 መሠረታዊ የትንታኔና የችግር መፍታት ችሎታ ያላቸው፣ 📍 በተለያዩ ክልልሎች እና ከተማ አስተዳደር ላይ ለመመደብ ፈቃደኛ የሆኑ። 🏫 ስለሆነም ይህንን እድል ለመጠቀም የምትፈልጉ በመጀመሪያ lmis.gov.et በመግባት በመመዝገብ፣ በአቅራቢያችሁ የሚገኘውን የአገልግሎት መስጫ ማዕከል (ወረዳ/ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) በመያዝ በዚህ ሊንክ በመጠቀም https://forms.lmis.gov.et/zemzem_new/ ማመልከት ትችላላችሁ። 📞 ለተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ መስመር 9138 ይደውሉ።

Open in Telegram
Views126,000+149%vs avg
Forwards—
Reactions758
Comments—
#609Photo

🌏✈️ የውጪ ሀገር የስራ ማስታወቂያ 🚀 በህጋዊ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም በተለያዩ ዘርፎች የሰው ኃይል ይፈለጋል። የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም በማስጠበቅ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር ለመስራት የሚፈልጉ አመልካቾች እንዲያመለክቱ እናሳውቃለን። 🚧 የሞያ ዘርፎች፦ 🔹የጥበቃ ሰራተኛ 🔹ፅዳት ሰራተኛ 🔹አጠቃላይ ረዳት 🔹የሲቪል ግንባታ ረዳት 🔹የኮንስትራክሽን ዕለታዊ ሰራተኛ / ረዳት 🔹ኤሌክትሪሻን / የኤሌክትሪክ ባለሙያ 🔹ቧንቧ ሰራተኛ / የቧንቧ ባለሙያ 🔹የኤር ኮንዲሽነር ባለሙያ 🔹ብየዳ ሰራተኛ / የብየዳ ባለሙያ 🔹የእሳት አደጋ መከላከያ ባለሙያ 🔹ግንብ ሰራተኛ / የድንጋይና ጡብ ግንባታ ባለሙያ 🔹ቀለም ቀቢ 🔹ምርጋትና ልስን ሰራተኛ 🔹የጂፕሰም ባለሙያ 🔹የፎርምወርክ አናጺ / የማገር አናጺ 🔹የአሉሚኒየም ስራ ባለሙያ 🔹ላሚኔተር / የላሜራ ስራ ባለሙያ 🔹ማጠናቀቂያ ስራ ባለሙያ 🔹የብረት መዋቅር ሰራተኛ 🔹ስካፎልዲንግ ሰራተኛ 🔹ሪገር እና ምልክት ሰጪ 🔹የመጋዘን እቃ ማሸግ 🔹የፋብሪካ ሰራተኛ 🔹የጭነት አውራጅና ጫኝ ሰራተኛ 🔹የሞተር/ሳይክል አሽከርካሪ 🔹የሲቪል ፎርማን / የሳይት ተቆጣጣሪ 🔹የሲቪል ረዳት ፎርማን / የቡድን መሪ ✅ ለመመዝገብ Labor ID ካሎት ይህን https://forms.lmis.gov.et/uae-new-2/ ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው መመዝገብ። Labor ID ከሌሎት የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ፦ 1. በ lmis.gov.et ይመዝገቡ። 2. በአቅራቢያዎ ባለ የአንድ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ ይስጡ እና የሰራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) ይያዙ። 3. Labor ID ካገኙ በኋላ በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ ገብተው መረጃዎትን በትክክል ሞልተው ያመልክቱ።

Open in Telegram
Views146,000+189%vs avg
Forwards—
Reactions1,843
Comments—
#608Photo

👷🏾‍♂️ወደ ውጭ አገር የምሥራት ህልም አሎት?👷🏾‍♂️ ✈️✈️🌏🌎 በተለያዩ ተፈላጊ በሆኑ የሙያ መስኮች ላይ እየተጠየቀ ባለው የሥራ እደሎች ላይ E-LMIS በኩል ተጠቃሚ ይሁን። ከታች በተዘረዘሩት በርካታ የስራ መስኮች ላይ በማመልከት ዛሬዎኑ የስራውን ዓለም በመቀላቀል ዕውቅዎቶንና እና ልምዶን ወደ ገንዘብ ይቀይሩት:- 🔹 የግንባታ ሰራተኛ/Carpenter / Construction Worker 🔹 የብረታ ብረት ባለሙያ/ Steel Fixer 🔹 ቴክኒሻን / Technician 🔹 ሲቪል ሱፐርቫይዘር / Civil Supervisor 🔹 ምግብ አብሳይ / Chef 🔹 የግንባታ ረዳት ሰራተኛ / Construction Helper 🔹 አጠቃላይ ግንበኛ / General Mason 🔹 የጽዳት ሰራተኛ / Cleaner 🔹 የኤሌክትሪክ ባለሙያ /Electrician 🔹 የቧንቧ ሰራተኛ /Plumber 🏫 ስለሆነም ይሆንን እድል ለትጠቀሙ የምትፈልጉ በመጀመሪያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር /Labor ID/ ከያዛችሁ በዚህ https://forms.lmis.gov.et/uae-new-2/ በመግባት ትክክለኛ መረጃዎችን ሞልተው ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። 📞 ለተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ መስመር 9138 ይደውሉ ። የስራ ባለቤት እርስዎ ነዎት !

Open in Telegram
Views151,000+198%vs avg
Forwards—
Reactions1,630
Comments—
#607Photo
Views148,000+192%vs avg
Forwards—
Reactions1,302
Comments—