⚠️ ደስ የሚያሰኙ ነገሮች ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ናቸው ማለት አይደለም!! 👇 🔘 ደስ የሚያሰኙትን እነዚያን ነገሮች ፈትኖ ማወቅ ግድ ነው ለዚያውም በአእምሮ በመታደስና በመለወጥ። አእምሮ #ካልታደሰ ፣ ለእግዚአብሔር #ካልተገዛ ፣ መነሻው የላዩ አለም ካልሆነ፣ #በፀሎት #በቅዱሱ ቃል ካልተሞላ፣ ዘመኑን #ካልመረመረና እግዚአብሔርን #ለማወቅ ካልወደደ 👉 ስጋው #ስለሚገዛው ለራሱ ደስ የሚያሰኘውን ከማድረግ አይቦዝንም። 🔘 መጀመሪያ እግዚአብሔርን #ለማወቅ መውደድ፤ ቀጥሎ በእኔ ሕይወት ላይ #አላማው ምንድን⁉️ ብሎ ማሰብ ግድ ነው። 🔘 እኛን ደስ ብሎን ይህማ የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ነው🙋 ብለን የምናደርገው ያ ነገር #የእግዚአብሔር ደስታ መሆኑን ማወቅ አለብን‼️ ፈቃድን ለጌታ ያስገዛ፣ ከእርሱ ጋር ጠንካራ #ሕብረት ያለው፣ ለራሱ ደስታ እየሮጠ #በከንቱ ዘመኑን አይጨርስም❌ ጌታን ደስ የሚያሰኘውን ነገር እየደረገ በአእምሮው እየታደሰ #በጎ የሆነውን ያ የእግዚአብሔርን #መንገድ እየተከተለ በማስተዋል ይመላለሳል። 🙏 "የእግዚአብሔር ፈቃድ ባለማወቅ የሚገኘው ሞት ብቻ ነው‼️" ⚠️ አደራ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳታውቁ ምንም ውሳኔ አትወስኑ‼️ #እናንተን ደስ የሚያሰኝ ነገር እንኳ ቢሆን ምንም እርምጃ ለዛ #አትራመዱ። ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁን ሕብረት #ፈትሹ፣ እርሱን ለማወቅ #ውደዱ በአእምሯችሁ #ታደሱ ጌታን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ለማድረግ አትስነፉ።🙏
Open in Telegram
Daily Meditation
ሂድና በ "ሰሊሆም" መጠመቂያ ታጠብ አለው ትርጓሜውም "የተላከ"ማለት ነው። ስለዚ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ። ዬሀ 9:7 and said to him, "Go,wash in the pool of "SILOAM" (which means "sent"). so he went aweywashed and come back seeing. jon 9:7 ለማንኛዉምሀሳብአስታያየት @yenemrchaeysus 👆👆👆👆
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Oct 31, 2026 | 222 |
| Nov 1, 2026 | 214 |
| Nov 3, 2026 | 202 |
| Nov 8, 2026 | 172 |
| Nov 9, 2026 | 177 |
| Nov 11, 2026 | 155 |
| Nov 17, 2026 | 132 |
| Nov 19, 2026 | 101 |
| Nov 22, 2026 | 74 |
| Nov 23, 2026 | 61 |
Most viewed this month
- 01Views226Forwards—Reactions—Comments—
- 02Views219Forwards—Reactions—Comments—
- 03Views214Forwards—Reactions4Comments—
- 04Views202Forwards—Reactions3Comments—
Latest posts
እየፈራን......✍️ • ፈሪ ክርስትያን መሆን ድፍረት ይጠይቃል! • ትልቅ ሚባል ሃጥያት የለም የጥቃቅን ፈቀቅታ ድምር እንጂ! • ከምኔው ተፈጠፈጡ ብለን እንደነግጣለን ከመድረክ ሳይወርዱ ግን እየወደቁ ነበር! • ሰባት አገልጋይ ስለሳቀበት ቀልድ እውነት አይሆንም! • ትኩስ መሆን ትፈልጋለህ ከቻልክ አዲስ ክርስትያን ሰፈር ዋል! • አገልጋይ ሰፈር የሰማኸውን ቀልድ አዲስ ክርስትያን ሰፈር እንዳትደግመው! • ጥንቃቄ ሚፈልገው የሚበላው ዘር ነው እንጂ አረም ባይዘራም ያድጋል! • ቅድስና የአካባጆች ሳይሆን ከኢየሱስ አመል የተጋባባቸው ሰወች ህይወት ነው! • ለእግዚአብሄር ያለህ ክብር ለቃሉ ያለህን ክብር ያክላል! • በልቤ አግኝተውኝ ነው? ያልኳቸው ሰወች አግኝቻቸው ነው? ምልበት ግዜ ይመጣ ይሆናል! • በልቤ ምንም ብል እሰማለው እንዳልኩኝ ሁሉ ምንም ብል ማልሰማበት ግዜ ይመጣ ይሆናል! • ከእግዚአብሄር በቀር እንደበረታ ሚሰነብት የለም! • ከነብር የሚፈጥነው አበኔር እንደ ሚዳቋ ሞቷል! • ከአንበሳ የበረታው ሳዖል እንደ ምናምን አልፏል! • ኮከብም ነዶ ነዶ ይጠፋል! • ሺህ ዘመናት የበራች ጸሃይም ሃይሏን አጥታ እንደደም ትቀላለች! • ለጌታ እንዳልተገቡ እያሰቡ በፍርሃት ማገልገል እንዴት ያለ ብልሀት ነው። • ተጋባዥ ማንም ይሁን ምን አገልጋይ ሆኖ ሙሽራው ያከበረውን ህዝብ መናቅ ሙሽራውን መናቅ ነው። • ኢየሱስ ያከበረውን ህዝብ ማክበር ኢየሱስን ማክበር ነው። • ለኢየሱስ ያለን ፍቅር ለወንድማችን ያለንን ፍቅር ያህል ነው። • እግዚአብሄርን የመውደዳችን ትልቅነት እስከ ወንድም ይለካል • ተለምነን ምናገለግል ሆይ ለምነን ማገልገል እንከለከል ይሆናል። • ሰው ሲያጡ ነው እንዴ ሚጠሩኝ ያልን ሆይ አንድ ቀን መተንፈሻ መድረክ ፍለጋ እንማጠን ይሆናል። • ላለማገልገል ለሰው የሰጠነው ምክንያት በጌታ ፊት ይመጥን ይሆን? • በትዕቢት የጸናው ማግስት ጸጋውን እላዬ ላይ ትቶብኝ ከሚሄድ የሰጠኝን ጸጋ ከላዬ ቢወስድ ራርቶልናል ማለት ነው። • መሰማት ሁሉ ክብር አይደለም መሰማትን ሰጥቶ አምላክ ከአፋችን ቃል ቢሸሸ የየእለት ግማት ነን! እየፈራንህ እናገለግለዋለን።
Open in Telegram🩸አንቺ ሴት!! 🤔 👇👇 አንቺ ልባምና ብርቱ ሴት ስለ ምን ስለ ነገሽ ትጨነቂያለሽ⁉️ ስለምንስ ነገዬ ምን ይሆን ወይ ብለሽ ትካዜ ውስጥ ትገቢያለች🤔⁉️ ስለምንስ ትላንት የነበረሽን ያን በእግዚያብሄር ላይ የመተማመኑን ነገር ዘነጋሽ🤷♂⁉️ እኮ ለምን በራስሽና በእግዚያብሄር ላይ ተጠራጠርሽ😳⁉️ እግዚያብሄር ትላንት በአንቺ ላይ ያለው አላማና ፈቃድ መች ተቀየረ☹️⁉️ መቼስ ዘነጋሽ? እግዚያብሄር የሚጥል አምላክ ቢሆን ኖሮ እስቲ እውነት አንቺ ዛሬን ማየት ትቺይ ነበር🤔⁉️ አየሽ በጭራሽ እግዚያብሄር ከአንቺ ጋር የመሆኑ ለታማኝነቱም ማረጋገጫ ከራስሽ በላይ ሌላ ምስክር የለም🤷♂❌ የእግዚያብሄር ላይ የታመኑ ነገር ግን የወደቁ፤ በአባታቸው ክንድ ላይ የተደገፉ ደግሞ ያፈሩ ከቶውኑ ሰምተሻልን🤷♂‼️ ታዲያ ለምን ዛሬ መታገስ አቅቶሽ ሆድ ባሰሽ😔? ለምንስ ነፍስሽ እንድታስጨንቅሽ እድል ትሰጪያታለሽ!👉 ተይ በያት ነገር ሁሉ ለበጎ ነው፣ ዛሬም ስለዛሬዬ ስለነገዬም አምነዋለው🙏፣ አይጥለኝም አይረሳኝም እደገፈዋለው፣ ተስፋዬ እርሱ ነው ይዋሽ ዘንድም ሰው አይደለም በመጠበቂያዬ ሆኜ እጠብቀዋለው እታገሰዋለሁም❤️🙏 በያት እንጂ 1⃣ ይተው 2⃣ ይረሳ ዘንድ ሰው ባልሆነው አምላክ ነውና የተደገፋችሁት የታመናችሁትም አትፍሩ❌ ታገሱ አሁንም ታገሱ ድልና ፍሬ ያለው ለታገሱት ነውና💪 እስከመቼ እያላችሁ አታጉረምርም ልመናችሁን በፀሎት አስታውቁ በምስጋናም ጠብቁ በጊዜው እራሱ ይመጣልና❤️🙏
Open in Telegram👋 ይህን እውነት አውቀሽ በዚህ እውቀት ልትመላለሺ ልትታዘዢ ልትፈፅሚውም ካልቻልሽ የወንድ ጓደኛ መያዝ አልፎም ትዳር ውስጥ መግባትን አታስቢው!! 👇 1⃣ ባልሽ የቤቱ ራስ ይህን 👉 የእግዚአብሔርን መልካም ፈቃድ እወቂ፤ ልትታዘዢው ልትሰሚው ልታከብሪው የተገባሽ መሆን አለብሽ። ያለበለዚያ እንደ ዘመኑ ክፉ ሃሳብ የገባባቸው አንዳንድ ሴቶች አይ/#no ራስ የሚባል ነገር የለም ብለሽ ከአንቺ የሚጠበቀውን ልታደርጊ ትተሽ ስለ #እኩልነት ልትሰብኪ ከተነሳሽ መጨረሻሽ #ውድቀት ነው። ልባም ሴት ባህሪዋ ይገርማል አውቃበታለች ሴትነትን የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የሆነውን፤ የባሏ ኩራት ናት ቤቷን በመታዘዝ በእጇ የምትሰራ💪 2⃣ ተሸናፊ ሁኚ 👉 በመሸነፍ ማሸነፍን ልትለማመጂ ካልቻልሽ ትዳርን አታስቢው። ፈጥኖ ከመናገር ከንዴትም ከኩርፊያም ቶሎ አምልጪ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝባት አይነት ሚስት መሆን ከፈለግሽ። ትዕግሥት ይኑርሽ ባታጠፊው ተሸነፊና የትዳር ጠላት የሆነውን ሰይጣን አሸንፊ። በቁጣሽ መሃል ፀሃይ አይግባ አንደበትሽን በጥበብ ክፈቺ። 3⃣ በእግዚአብሔር ቃል እውቀት በመንፈሳዊም ሕይወት ካልተሞላሽ ትዳርን አታስቢ‼️ 👉 እንዴት መመላለስ፥ ምን አይነትስ ሚስት መሆን እንዳለብሽ ቤትሽን እንዴት መስራት ማስዋብ የሚያስተምርሽ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በዚህ እውቀት ብቻ ልብሽን ሙይ፤ እንደ ዘመኑ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ኑሪ። የምታተርፊው የምታፈሪውም በዚህ መንገድ ብቻ ነው። 4⃣ ራስሽን የማትገዢ ከሆነ አሁንም ትዳርን አታስቢው‼️ 👉 ገላሽን አክብሪ አትገላለጪ ሸፈን በይ ከትዳር በፊትም ይሁን ካገባሽ ቡሃላ። እንደፈለኩ በራሴ ሰውነት ልትይ ስልጣን የለሽም አንድ #የጌታ ነሽ #የባለቤትሽም ነሽ ስለዚህ ራስሽን ግዢ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኘው በዚህ ነው። ራስሽን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቂ አስተዋይ ጥበበኛ ንቁ ሴት ሁኚ። 🙏 እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበትን የትዳር ሕይወት ለመኖር ከበዙ በጥቂቱ ይህ ከአንቺ እንደ ሴትም ሚስትም የሚጠበቅ ነውና በዚህ እውነት መኖር ይሁንልሽ።🙏
Open in Telegram๏ የኮንስትራክሽን ተቆጣጣሪው ከ 6ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ የሚስራውን ሰራተኛ ይጠራዋል፣ ስራተኛው ሊስማው አልቻለም፡፡ • ስራተኛው የአሰሪውን ጥሪ ሊስማው ስላልቻለ ተቆጣጣሪው መላ ዘየደ፡፡ እናም የሰራትኛውን ሃሳብ ልማግገኘት ሲል ተቆጣጣሪው ከላይ ብር ጣለለት ብሩም ከሰራተኛው እግር ስር አረፈ፣ ሰራተኛው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አሰገብቶ ስራውን ቀጠለ…… • በድጋሜ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት ተቆጣጣሪው መጀመሪያ ከጣለው ብር በላይ ሌላ ብር ጨምሮ ጣለለት፣ የቀን ሰራተኛውም ልከ እንደ መጀመሪያው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አስገብቶ ስራውን ቀጠለ፡፡ • በመጨረሻ ሌላ መላ ዘየደ ብር በመጣል የሰራተኛውን ሀሳብ ማግኘት ስላልቻለ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት አነስ ያለ ድንጋይ አነሳና ወደ ሰራተኛው ወረወረው፣ ድንጋዩም የሰራተኛውን ጭንቅላት አገኝው በዚህ ሰዓት ነበር ሰራተኛው ወደ ላይ የተመለከተው እና ከተቆጣጣሪው ጋር መነጋግር የጀመረው፡፡ --------------------------- : : ይሄ ታሪክ ከእኛ ህይወት ጋር ይመሳሰላል ፈጣሪ ከኛ ጋር መገናኘት ይፈልጋል ነገር ግን እኛ በጣም በ አለማዊ ስራ ራሳችንን ጠምደናል ከዛ ፈጣሪ ትንሽ ስጦታ ይሰጠናል እኛም ስራችንን እንቀጥላለን ከየት እንዳገኘነው ቀጥ ብለን ለማየት ጊዜ የለንም፡፡ በድጋሜ እግዚአብሄር ከመጀመሪያው የተሸለ ስጦታን ይሰጠናል አሁንም ልክ እንደ መጀመሪያው ስጦታውን ወስደን ምስጋናም ለፈጣሪ ሳናቀርብ እድልኞች ነን ብቻ ብለን ስራችንን እንቀጥላልን ከየት እና ከማን እንዳገኘነው ቀና ብለን ለማየት አንሞክርም፡፡ እናም በትንሽ ድንጋይ ስንመታ፣ ማለት ትንሽ ችግር ቢጤ ስታገኘን ወደ ላይ ማየት እና መጮህ ከዚያም ከፈጣሪ ጋር መነጋገር እንጀምራለን፡፡ ስለዚህ ምንግዜም በህይወታችን ስጦታን ስናገኝ በፍጥነት እግዚአብሄርን ማመስገን አለብን በጭራሽ በትንሽ ድንጋይ እስክንመታ መጠበቅ የለብንም ሁሌም ቢሆን ከእግዚአብሄር ጋር በጸሎት እንነጋገር ...
Open in Telegram🩸አ…ራ…ዳ ሴት!!🤔 👇👇 አራዳ የሚለውን ቃል🤔 ለዘመናት ብዙ ሰዎች የየራሳቸውን ፍቺና ትርጉም እየሰጡበት ኖራል አሁንም እየተሰጠ ይቀጥላል👉 ብዙሃኑ አራድነትን ከቁሳቁስ ጋር ሲያገናኘው💴 ሌላው ደግሞ ከአታላይ ብልጥ ከሆነ ሰው ጋርም ያገናኘዋል የተቀረውም ወገን ደግሞ በመልካም መንገድ ላይ ከሚሄድ ሰው ጋር ያዛምደዋል👍 እኔም ከሶስተኛ ወገን አስተሳሰብ ጋር በብዙ የምስማማ ብሆንም አራድነት ግን ከዚህም ያለፈ ነው ብዬ አምናለው ምክንያቱም ያለፈ ስለሆነ🤷♂ አራዳ ሴት ስለሚለው ሃሳብ ሳስብ🤔 እግዚያብሄር ወደ ልቤ ያመጣው አንድ አስገራሚ ነገር ልበላችሁ🤷♂ የአራዳ ትርጉሙ 👇 🔹 አ 👉 አስተዋይ የሆነች🤔 🔹 ራ 👉 ራዕይ ያላት 👀 🔹 ዳ 👉 ዳርቻዋ ሰፊ 🍇 የአራዳ ሴት ትርጉም ይህ ነው በቃ🤷♂ በዚህ ዘመን አራዳ ሴት ማለት👉 ዝም ብላ ወዲህ ወዲያ ጡል ጡል የምታል፣ ገላዋን የምታሳይ፣ ነገዋ ያማያሳስባት☹️፣ በመጠጥና ሱስ የተደበቀች፣ መደነስ መጨፈር መዝፈን አለም የመሰላት🥂፣ መሳሳም ዝሙት ማድረግ እንደ ደስታ የቆጠረች😏፣ በትምህርቷ በስራዋ ላይ ያሾፈች፣ ፌዝ የበዛበት ስፍራ የዋለች ብሎም ከእግዚያብሄር መንገድ ስታ በራሷ አለም የምትራመድ🤦♀፣ ለነገሮች ደንታ ቢስ የሆነች የነገ ስራዋ፣ትምህርቷ አልፎም ትዳርና ልጆቿ የማታስብ፣ መዝለል ብቻ እውቀት የመሰላት ናት ይላሉ🤔 ግን አይደለችም አራዳዋ ሴት👉 አስተዋይ፣ባለ ራዕይ ዳርቻዋም ሰፊ ሴት ናት😲 1⃣ አስተዋይ ስንል👉 በእግዚያብሄር መንገድ መራመድ ነው😲 በእግዚያብሄር መንገድ ስትራመዱ ደግሞ ምን ማድረግና ምን አለማድረግ እንዳለባችሁ🤔፣ በየቱስ ጎዳና ማቅናት እንዳለባችሁ፣ ስለ ነገያችሁስ ምን ማሰብ እንዳለባችሁ አልፎም መልኳሚቷን ነገያችሁ ታውቃላችሁ🍇 2⃣ ባለ ራዕይ ስንል👉 አላማ ያላት፣ነገዋ ግድ የሚላት፣ ነገዋን ስታይ ትልቅ ህልም ያላት ከዛሬዋ ያለፈች ብልህ ማለት ነው💪 3⃣ ዳርቻ ሰፊ👉 ተቆራሽ፣ ረጂ(ለጋሽ)ግን ለታይታ ያልሆነ❌፣ ለብዙዎች የምትደርስ የምትመክር እግዚያብሄር በእርሷ ላይ ያለውን አላማ ተመልክታ🤔 በሰፈር የማትቀር ይልቁኑ ከተማ ሃገርንም የምትወርስ ልበ ሰፊ ማለት ነው💪 አስተዋይ ነኝ🙋 ፣ ራዕም አለኝ አልፎም ዳርቻዬ ሰፊ ነው ትልቅ ህልምም አለኝ💪 የምትይ አንቺ ሴት አራዳ ነሽ እኮ በቃ በአለም ያሉትን ሰነፍ ሴቶችን አትመልከቺ❌ እነርሱ ጊዜያዊ ናቸውና የተባረከ ትዳር ገንዘብም ስራም የምታገኚው እኚህ ውስጥ ነው💪🙏
Open in Telegram✅ ሰዎች ነን በብዙ ውጣ ውረድ በብዙም መከራ የምናልፍ፤ #የሚያደክም #ልብን የሚያርድ #ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ጥቂት አይደለምና በሕይወት ጉዞ #በድካም ልናልፍ #ልንወድቅ #ልንስት እንችላለን። 🤷♂ ✅ ያለንበትን ሁኔታ አይተን በራሳችን አካሄድ የምንወስናቸው ጉዳዮች ዋጋ ሲያስከፍሉን ስንደክምም እንመለከታለን🤦♂። ሰው ነን ስጋ ለባሽ ስህተቶች አይጠፉንም ነገር ግን ለነዚያ ስህተቶች እጅ ከሰጠን ነው እኛም እጅ የምንሰጠው። 🔘 በየትኛውም ልክ ያልሆነ የሕይወት መንገድ ሂጂ በየትኛውም የኃጢአት ሰንሰለት ተያዢ 👉 ተስፋ ግን አለሽ‼️ 🔘 ድቅቅ በይ፣ ተስፋም ቁረጪ መኖርሽንም ጥይው 👉 ተስፋ ግን አለሽ‼️ 🔘 ብቻሽን ቅሪ፤ ሁሉንም አጣሁትም በይ 👉 ተስፋ ግን አለሽ‼️ ✅ ባለቤት አለሽ በመልኩና በምሳሌው የሰራሽ በአንቺ ሁሌም ተስፋ የማይቆረሸጥ❌ #የማይታከም ሕመም #የማይድን በሽታ #የማይጠገን ልብ #ቢወድቅ የማይነሳ #የማይነጻ እድፍ እርሱ ዘንድ የለም፤ እርሱ ሰው አይደለምና ሁሉ ይቻለዋል።🙏 🔘 አንቺ ሴት ዛሬም ተስፋ አለ የተቀማ ነገ የለሽም ነገሽ በሚወድሽ በእግዚአብሔር እጅ ነውና። ቀና በይ አላበቃልሽም የምትኖሪው ብዙ ነገ አለ፤ አዎን ተስፋ አለሽ🙏 " በእኛ ተስፋ የማይቆርጥ ጌታ አለ!! " 🐅
Open in TelegramConnections
Similar channels
OFFICIAL DBUECSF CHANNEL@officaldbuecsfReligion1.08K
ብርሃን ይኹን💡@lettherebelightofficialReligion1.09K
ኡመተ ረሱል@smithhkReligion1.07K
አል-ፈታዋ ሸይኽ ሙሐመድዘይን ዘህረዲን@fetawa_mohammedzainzhReligion1.09K
𓆩 ѕαуяαη 𓆪@al_khuld2Religion1.1K
S H E K A Y I N A H@shekayinahReligion1.1K
ፈለገ~ሰላም~ሰንበት~ት/ቤት ፳፯@felegeselam27Religion1.04K
💡𝐁𝐚𝐫𝐮𝐦𝐬𝐚 𝐉𝐚𝐦'𝐚𝐭𝐮𝐥 𝐤𝐡𝐞𝐲𝐫𝐢𝐢💡@hamzahassen1Religion1.04K