Account

Posts of ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

newest first

#8018Text

🚫 ቢዳዓ ያደነቁራል ያሳውራል ! ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይላል የሀገሬ ሰው ! የነሲሐዎች ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ በጣም የሚያስቅና ቢዳዓ ምን ያክል ባለቤቱን የሚያደነቁርና የሚያውር መሆኑን የሚያሳይ ንግግር ሲናገር ሰማሁ ። ንግግሩ በአንድነት ዙሪያ ሲሆን ከአሕባሽ ከሱፍይና ኢኽዋን ጋር አንድ ለመሆን መረጃ ብሎ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ ያመጣል : – { إِنَّ هَٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاعْبُدُونِ } الأنبياء (92) " ይህች (ሕግጋት) አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት ፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና ተገዙኝ "፡፡ ይህን አንቀፅ ከማምጣቱ በፊት ጥቂት ሰዎች አንድነት የሚለው አይጥማቸውም ። ካለ በኋላ እነዚህ ሰዎች (ይህን ላለመቀበል) ያመጡት ምንም አይነት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ምላሽ የላቸውም ይላል ። ቀጥሎ ከምንም በፊት ቁርኣንና ሐዲስ ላይ ለመጣ እውነታ ነው ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው ይልና የሰለፎች ግንዛቤ ሶስተኛ መረጃ ሳይሆን ራሱ ቁርኣንና ሐዲስ ነው ይላል ። አኛም በጣም ልክ ነው ነገር ግን አንተ ከምትለው የሰለፎች ግንዛቤ የት ነው ያለኸው እንልሀለን ። ለማንኛውም ንግግሩን ስሙትና እንመለሳለን : – 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://drive.google.com/file/d/1Y09mITel4547-k1tjt4cZOI9rUBBWpDw/view?usp=drivesdk ለአቶ ኢልያስ አሕመድ የምንለው ለመሆኑ የዚህ የቁርኣን አንቀፅ " አንድ ህዝብ ነው" የሚለው ተፍሲር የየትኛው ሰለፍ ተፍሲር ነው ። እስኪ ይህን የቁርኣን አንቀፅ ከሰለፎች ውስጥ አንተ በምትለው መልኩ ያለ ልዩነት ሁሉም አንድ ነው ለማለት የፈሰረ የሰለፍ ዓሊም አምጣልን ! ነገር ግን ላንተ ይህ ከየት ሊመጣልህ ! መረጃ ሳይል የሚከተልህን የምስኪን ስብስብ የእውቀት ማማ ጫፍ ላይ የተቀመጥክ አድርጎ እንዲከተልህ ያልጣማቸው ሰዎች መረጃ የላቸውም ብለህ የቢዳዓ ፍልስፍናህን ትግታቸዋለህ ። አላህ ሆይ ሐቅን ካሳወቅኸን በኋላ ከመጥመም ጠብቀን ! ይህ አንተ ያመጣኸው የቁርኣን አንቀፅ ከሰለፍ ጀምሮ ያሉ ሊቃውንቶች በአንድ ድምፅ በሚባል መልኩ ኺጣቡ ከዛ በፊት ለተዘረዘሩት ነብያት ሲሆን ትርጉሙም ይህ ዲናችሁ አንድ ዲን ነው ። እሱም አላህን በብቸኝነት ማምለክ ነው የሚል ነው ። ውድ አንባቢያን በአቅራቢያችሁ ያለ ኪታብ መሸጫ ገብታችሁ ቁርኣንን የፈሰሩ ሙፈሲሮችን ተፍሲር አንብቡ ! ለምሳሌ እንአ ጠበሪ ፣ ኢብኑ ከሲር ፣ ቁርጡብይ ፣ ጀላለይን ፣ በሕሩል ሙሒጥ ፣ ፈትሑል ቀዲርና የመሳሰሉትን ። አላህ ነብያቶች ይዘውት የመጡት ዲን አንድ አይነት እንደሆነና እሱም አላህን በብቸኝነት መገዛት እንደሆነ ለነብዩ ኡማህ የነገረበት አንቀፅ ነው ። በግድ ጠምዝዞ ለኡመተል ኢጃባ ነው የሚል አካል ካለም ማለት ያለበት በተውሒድ አላህን በብቸኝነት በማምለክ አንድ የሆናችሁ ህዝቦች ናችሁ ነው ለማመት መሞከር ያለበት ። ነገር ግን እንደ ኢልያስ አሕመድ ያለ ከአሕባሽና ሱፍይ እንዲሁም ኢኽዋን መሪዮች ኋላ ኋላ ድክ ድክ ለሚል በምንም መልኩ ይህ አንቀፅ ለባጢል አንድነት መረጃ ሊሆን አይችልም ። ለማንኛውም እሱ መረጃ የላቸውም ስላለ እኛ ጥይት አናባክንም ። ከዚህ በላይ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ምላሽ የለምና ። ሌላው የአሁኑን የአሕመዲን ጀበልና የአቡበከር አሕመድ ጓደኛ ድሮ በእነርሱ (በኢኽዋኖች ላይ) ምን አይነት አቋም እንደነበረውና በምን መልኩ በእነርሱ ላይ ረድ ያደርግ እንደነበር በሚቀጥለው ድምፁ ስሙት : – ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ https://drive.google.com/file/d/1Wh1vG7YkqRvD0aIrG44F2irbjg3G4yF5/view?usp=drivesdk ይህ ነበር ኢልያስ ከ20 አመት በፊት ! ኮምፕሊትሊ ከመለወጣቸው በፊት ‼ እነአሕመዲን ጀበል ላይ ረድ ያደርጉ በነበረ ጊዜ ! ልክ እንደዚሁ ዛሬ እሱ እየሰራው ባለው መልኩ የቁርኣንና ሐዲስ መልእክትን እየጠመዘዙ ለስሜታቸው በሚስማማ መልኩ መረጃ ብለው ሲያቀርቡ ለነበሩት የሱፍይና ኢኽዋን መሪዮች ለመስላሐ ነው ባሉት የአንድነት ስምምነት ላይ የሰጠውን ረድ በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ አዳምጡት : – 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://drive.google.com/file/d/1iA1QyHSTRkf8YPj9mcobdY9BxEwqcRC3/view?usp=drivesdk አቶ ኢልያስ አሕመድ ምናለ ዝቅጠትህን በልኩ ብታደርገው ! በዚህ ልክ በቢዳዓ መታወርህንና መደንቆርህን አደባባይ ሳታወጣ እየተጃጃልክ መኖርም እኮ ይቻል ነበር ። ከእንደዚህ አይነት ዝቅጠት አላህ ይጠብቀን ። https://t.me/bahruteka

Open in Telegram
Views5,080−22%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
14 h3,560
29 h5,080
  1. After 24 hours5,080
  2. Total to date5,080
#8016Photo
Views5,940−8%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
47 h5,320
67 h5,940
  1. Total to date5,940
#8015Audio
Views4,600−29%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
48 h4,120
68 h4,600
  1. Total to date4,600
#8014Text
Views4,590−29%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
56 h4,330
70 h4,590
  1. Total to date4,590
#8013Link preview

👉    ፍትህ በጋምቤላ ዲማ ወረዳ ኮይ ቀበሌ ለታሰሩ ሰለፍዮች !      ሀገራችን የዜጎችን ሁለንተናዊ መብት ያከብራል የእምነት የአመለካከትና የአስተሳሰብ ነፃነት ይጠብቃል ተብሎ በረቀቀው ህገ መንግስት ነው የምትደዳደረው ። በሌላ በኩል አሁን ሀገራችንን እየመራ ያለው ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አሕመድ የሚመሩት የብልፅግና ፓርቲ መርህ የአንድ ዜጋ ድምፅም ቢሆን እንሰማለን የሚል ነው ። ለዚህም በኢትዮዽያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገራዊ የምክምር ኮሚሽን አቋቁሞ በመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የህዝቡን ብሶትና ሮሮ የያዙ ዜጎች ተሰብስበው ከየአቅጣጫው የመጡ የህዝብ ብሶትና እንግልቶች በመድረኩ ላይ ተነስተዋል ። ከእነዚህ ውስጥ የመጅሊስ አመራሮች ከአንዳንድ ሀላፊነት ከጎደላቸው የብልፅግና የሰላምና ፀጥታ አመራሮች ጋር በጥቅም በሞሞዳሞድ በሰለፍዮች ላይ እያደረሱት ያለውን በደልና ግፍ የመጅሊሱ ተወካዮች ባሉበት ተነስቷል ።     ይህ ማለት በተለያየ ቦታ በኢትዮዽያዊያን ሰለፍዮች ላይ እየደረሰ ያለው እንግልትና በደል ለትላልቅ የብልፅግና አመራሮች ደርሷል ማለት ነው ። ከዚህ በኋላ በሰለፍዮች ላይ የነበረው በደል ቀጠለ ማለት በጣም የሚያሳዝን ነው ።    ከላይ ርእሱ ላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ኮይ ቀበሌ ላይ ሰለፍዮች መጅሊስ አይወክለንም ልዩነታችን መሰረታዊ ነው ። እኛ እስልምናችንን ቁርኣንና ሐዲስ የነብዩ ባልደረቦች በተረዱበት መልኩ መተግበር ነው የምንፈልገው በማለታችው ምክንያት የወረዳው መጅሊስ መድረሳቸውን ዘግቶ ኡስታዞችንና መሻኢኾችን አሳስሮ በማንገላታት ላይ ይገኛል ። በእስር ላይ የሚገኙት የሚከተሉት መሻኢኾች ናቸው : – 1—  ሸይኽ አሕመድ 2 — ሸይኽ ኢብራሂም ዩሱፍ 3 —  ሸይኽ ኑሩ ሙሐመድ 4 — ሸይኽ ሙሐመድ ጀውሀር በጣም የሚያሳዝነው የመጅሊስ አመራሮች ተግባር አይደለም የሁሉንም ዜጋ መብት ለማስጠበቅና ሰላም ለማስከበርና የመንግስትን ሀላፊነት ለመወጣት የተቀመጡ የፀጥታ ሀይሎች እነዚህን ዜጎች ወንጀለኛ ብሎ ማሰሩ ነው ።   ለመሆኑ በየትኛው ህገመንግስትና አዋጅ ነው እምነቴን በነፃነት ማራመድ እፈልጋለሁ ማንም ከኔ ስር ካልሆንክ ብሎ የጭቆና ቀንበር ሊጭንብኝ አይገባም ያለ ወንጀለኛ የሚሆነው ? በየትኛውስ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ ነው የሚቀጣው ? ነው ወይስ የፀጥታ አካሎቹ ተጠሪነታቸው ለመንግስት ሆኖ በህገ መንግስቱ ሳይሆን የሚሰሩት ለመጅሊስ ሆኖ እሱ ያዘዛቸውን ነው የሚያስፈፅሙት ? የሚመለከተው አካል ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጥ ይገባል ።    እኛ ሰለፍዮች ለመጅሊስ አመራሮችም ይሁን ከእነርሱ ጋር በጥቅም ለሚሞዳሞዱ የፀጥታ አካላት መንገር የምንፈልገው ሀገራችን በመጅሊስ አመራሮች ሳይሆን የምትመራው በጠቅላይ ሚ/ር  ዶ/ር አብይ አሕመድ መሪነት በብልፅግና ፓርቲ መሆኑን ነው ። የሀገሪቱ መተዳደሪያ ደንብ ደግሞ የመጅሊስ ደብዳቤ ሳይሆን ህገ መንግስቱ ነው ። በመሆኑም በየቦታው ያላችሁ የፀጥታ አካላት ሀላፊነታችሁ የአንድን ተቋም አላማና ፍላጎት ማስፈፀም ሳይሆን ዜጎች በህገ መንግስቱ ያገኙትን መብት በፆታ በሀይማኖት በጎሳና ብሄር ሳትገደቡ በእኩልነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግና ህግና ስርኣትን በማስጠበቅ ወንጀል መከላከል ነው ። ይህን ትልቅ የህዝብ ሀላፊነት ወደ ጎን በመተው በጥቅም በመተሳሰር ዜጎች እንግልትና በደል ሲደርስባቸው ለበደለኛው አባሪ ሆኖ ስልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም በደል ማድረስ ተጠያቅነትን የሚያስከትል መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን ።    በየትኛውም ቦታ ያላችሁ ሰለፍዮች የናንተ የሰለፍያ ዐቂዳ መከተልና ወደ ሰለፍያ የመጣራት መብት በመጅሊስ አረመራሮች መልካም ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የዜግነትና ህገመንግስታዊ መብታችሁ ነው ። ይህን በተመለከተ ህገመንግስቱ ምን እንደሚልና ለዜጎች ያስቀመጠውን መብት በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ ተመልከቱ : – https://t.me/bahruteka/7614    በጋንቤላ ዲማ ወረዳ ያላችሁ ሰለፍዮች ሆይ መብታችሁን አውቃችሁ አንገታችሁን ቀና አድርጉ ። የታሰሩ መሻኢኾችና ኡስታዞችን ጉዳይ ለሚመለከተው አካል በማድረስና በማስረዳት ላይ ትግል አድርጉ አብሽሩ ይህ እንግልትና በደል ለነስር ሰበብ ሊሆን ይችላል ።    ሌላው የጥምሩ መጅሊስ አመራሮችና ቲፎዞዎቻቸው ሊያውቁት የሚገባው አቡ ጣሊብ ከለላ ሲሰጠው የነበረውን የተውሒድ ዳዕዋን እየተዋጋችሁ መሆኑን ነው ።     ሰለፍዮች መልእክቱ ተደራሽ እንዲሆን ሼር በማድ ሀላፊነታችንን እንወጣ ! https://t.me/bahruteka

Open in Telegram
Views9,310+43%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8011Photo
Views4,190−35%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8010Link preview

🚫 ሰርቆ እንዳይታወቅበት ንፁሑን ሰው ያዙት ሌባ ነው እያሉ መሮጥ ! ማን ያግባሽ ብትባል ምላስ ያለው አለች አሉ ! የምነወር ልጅ ሐቁን ባጢል ባጢሉን ሐቅ ፣ እውነቱን ውሸት ውሸቱን እውነት ፣ ሱናውን ቢዳዓ ቢዳዓዉን ሱና የማስመሰል ብቃቱን ለማሳየት " ባጢልን ለመዋጋት መፍራትም መቀዝቀዝም አያስፈልግም… " እያለ ይቀጥልና " የቢዳዓ ሰዎችንም ታገሉ ። ለእነርሱ ጩኸትና ስም ማጥፋት አትፍረክረኩ ።…" እያለ ይነዳል ። እዚህ ጋር ማንሳት የምፈልገው የሙነወር ልጅ የትኞቹን በእነርሱ ላይ የሚጮኹትን ይሆን ሙብተዲዖች ብሎ ለእነርሱ ጩኸት አትፍረክረኩ የሚለው ! ልብ በሉ ከዚህ በፊት ለተሚዮች በሚል" የሚጮኹትን የማይኖሩ ጉዶች" እያለ ከአ/አ እስከ ደቡብ ወሎ ቢስቲማ ድረስ ሲፅፍ ነበር ። በሌላ ጊዜ ደግሞ መድኸልዮች አትሁንም እያለ ሲያቀረሽ አይተነዋል ። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ እንኳን ነሲሓዎችና ኢኽዋኖች አሕባሾችም ስለነርሱ አያወሩም በስለዋል ብለው እያሞገሱዋቸው ነው ። ስለዚህ የሙነወር ልጅ ተከታዮቹን የሚያጃጅለው በእነርሱ ልቅምቃሚ ቀመር ላይ ቤንዚን ረጭተው የሱና እሳት ለኩሰው አመድ የሚያደርጉትን ለተምይ የሚላቸውን ሰለፍዮችን ነው ሙብተዲዖች ናቸውና ታገሏቸው የሚለውና ለእነርሱ ረድ ቦታ አትስጡ እያለ ባዶ ቀረርቶና ሸለላ እያሰማ ያለው ። ይህ ፋሽኑ ያለፈበት ስሙን ለሰው አወረሰው የሚሉት አይነት ድራማ ምሳሌው ሌባ ሰርቆ የተሰሩቁት ሲያሯሩጡት ሮጦ በሰው መሀል ገብቶ ንፁሁን ሰው ሌባ ነው ያዙት ! ያዙት እንደሚለው ነው ። ሰዎች ንፁሁን ሰው ይዘው ሌባ ነህ ብለው ሲያዋክቡት በግርግር ተሽሎክልኮ እግሬ አውጭኝ ለማለት ስለሚያመቸው ። ለምነወር ልጅ የምንለው ሰዎችን ከማነሳሳትህ በፊት አንተ ራስህ አትፍራ ስማቸውን ጠርተህ እነእገሌ ሙብተዲዖች ናቸው ታገሏቸው በል ። አንተ የፈራኸውን ሞት ለማን ነው የምትነግረው ! ነሲሓዎችንና ኢኽዋኖችን አይደለም ሱፍይና አሕባሾችን ጠርተህ ሙብተዲዕ ለማለት እየከበደህ ባለህበት ደካማ ሞራልህ ሰለፍዮችን በስም ጠርተህ እነእገሌ ሙብተዲዖች ናቸው ብትል ኖሮ እውነትም ጎበዝ እንልህ ነበር ። ለማንኛውም እያጃጃልክ ያለኸው መረጃህ ምንድነው ሳይሉ ጩኸት ብቻ ሰምተው የሚከተሉትን ሙሪዶችህን ስለሆነ አይገርመንም ። ያንተና የተከታዮችህን ምሳሌ ነግሬህ ላብቃ ። ሀገራችን ላይ የሆነ ጎሳ ውስጥ ሬሳ የሚሸጥ ሰው ነበር ። በዚህ ሬሳ በሚሸጠው ሌባ የተማረረው ማህበረሰብ ክተት አውጆ በሱ ጉዳይ ይሰባሰባል ። ሬሳ ሻጩ ጋር ወሬው ይደርሳል ። ማህበረሰቡ ተሰብስቦ በመፍትሄ ዙሪያ ሀሳብ እየተለዋወጠ ሳለ ሬሳ ሳጩ ቀጥ ብሎ በላያቸው ላይ ሲመጣ ከተሰብሳቢዮቹ ውስጥ ያየው ሰው ያውና መጣ ! መጣ ! ይላል ። ህዝቡም ፀጥ ይልና የሚሆነውን መጠበቅ ይጀምራል ። ሬሳ ሻጩ እንደ ደረሰ ህዝቤ ሆይ ተነስ ተብለሀል ተነስ ይላል ። ህዝቡም ግርርር ብሎ ይነሳል ። ማንም ሳይቀር ሁሉም መነሳቱን ሲያይ ህዝቤ ሆይ ቁጭ በል ተብለሀል ቁጭ በል ይላል ። ህዝቡም ወዲያው ቁጭ ይላል ። የዚህን ጊዜ ሬሳ ሻጩ ለተሰበሰበው ህዝብ አያችሁ እኔ የዚህን ህዝብ ሬሳ መሸጤ ነው ያስቆጣችሁ ! መቆጣት የነበረባችሁ ሬሳውን በመሸጤ ሳይሆን ከነ ህይወቱ ለምን አልሸጥከውም ብላችሁ ነበር ብሎ ጥሏቸው ሄደ ይባላል ። አበቃሁ !!! https://t.me/bahruteka

Open in Telegram
Views8,400+29%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8009Text
Views11,100+71%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8008Text

የሙነወር ልጅ እንዲህ ይላል 👇 ወደፊት ብቻ! ~ ተውሒድ እና ሱናን ለማሰራጨት፣ ከሐቅ ለመከላከል፣ ሺርክንና ቢድዐን፣ ባጢልን ለመዋጋት መፍራትም፣ መቀዝቀዝም አያስፈልግም። ከሐቅ ጎን ለመቆም በየትኛውም ጊዜና ቦታ ይሉኝታ አይያዘን። ወደ ሐቅ ለመጣራት መፍዘዝ፣ መቀዝቀዝ ፈፅሞ አይገባም። ቢድዐንም፣ የቢድዐ ሰዎችንም ታገሉ። ለነሱ ጩኸትና ስም ማጥፋት አትፍረክረኩ። እነሱ ባጢልን ይዘው ያላፈሩትን አትፈሩ። አላህን ይዛችሁ ወደፊት ብቻ!! ቀላል የሚመስሉን ጥረቶች በትብብር ፍሬ ያፈራሉ፣ ኢንሻአላህ። = የሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ ምላሽ 👇 من هؤلاء الذين زعمت محاربتهم ؟ فهلا سميتهم وجليتهم لمتابعيك المخدوعين بك؟ ومن الذين دعوت إلى فضحهم وبيان مخالفتهم للمنهج السلفي وصرحت بعدم التمييع معهم؟  هل يدخل في ذلك دعاة مركز ابن مسعود الذين قد سبق تحذيرك منهم وبيان مخالفتهم للمنهج السلفي قبل أن تنتكس وتتناقض ؟؟؟ وما رأيك في انضمام مركز ابن مسعود إلى الإخوان المسلمين ظاهرا وباطنا  شبرا بشبر وذراعا بذراع ؟ وما رأيك بلقاء أكابر مركز ابن مسعود مع كبار الإخوان  أمس القريب وقبله ؟ هل ذلك من المصالح الراجحة أو من المنكر الذي تظاهرت في إنكاره ودعوت إليه؟ ومن جعل الغراب له دليلا ...يمر به على جيف الكلاب. ولا يلدغ المؤمن في جحر واحد مرتين.

Open in Telegram
Views5,000−23%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8007Text

🚫 የነሲሓ ሙሪዶች የማያልቅ መከራ ! በተደጋጋሚ ለመግለፅ እንደሞከርነው ነሲሐዎች ኢኽዋንይነታቸው በአደባባይ ካወጁ ሰንብተዋል ። የነሲሓ መሪዮች በሰለፍያ ስም ሲነግዱ የነበረው ወጣቱን ለኢኽዋኖች ለማስረከብ አማራጭ የሌለው አካሄድ ነው ብለው ያሰቡ ቢሆን እንጂ የእነርሱ ኢኽዋንይነት ዶክተራቸው እንዳለው ከ10 አመት ወዲህ የመጣ አይመስልም ። ሰለፍዩን ማህበረሰብ ለማለዘብ የተጠቀሙበት መንገድ ለተረዳ ሰው ይህ በጣም ግልፅ ነው ። ሞያ በልብ ነው ብለው በሰለፍያ ስም ሰለፍዩ ወጣቱ ከኢኽዋን ጋር አንገት ላንገት በሚተናነቅበትና አብዛኛው ዳዒና ኡስታዝ እንዲሁም ዑለሞችም ጭምር ስለሰይድ ቁጥብና ሐሰኑል በና በየመድረኩ ያስጠነቅቁ በነበረ ጊዜ ከሀገሪቱ የተለያየ ክፍል በደውራና ኮንፈረንስ ስም እየሰበሰቡ ሰፊነቱ ነጃን ኮርስ እየሰጡ የጥርስ ወርቅ በፍቅህ ኪታብ በየትኛው ባብ ነው የተጠቀሰው ብለው አቅጣጫ ሲያስቀይሩ ነገሩ ግልፅ ነበር ። የነሲሓ መሪዮች ከመጀመሪያ ጀምሮ ኢኽዋንይ ነበሩ የሚለው ግምት በጣም የሚከብደው በጃሊያ አዳራሽ በሱፍዮችና በኢኽዋን መካከል ስለተደረገው አንድነት ያደረጉት ረድ ሲታወስ ነው !። ያ ረድ ወደፊት ወጣቱ አምኖባቸው ይዘውት ወደ ፈለጉት ለመንዳት እንዲያመቻቸው አስበውበት ነበር ማለት በጣም የራቀ የሚራደርገው ዶ/ራቸው ስለነኢብኑ ሙነወር ሲናገር ተውዋቸው ወጣቶች ናቸው ይመለሳሉ ኢብኑ መስዑዶች ከ10 አመት በፊት እንደዚህ አልነበሩም ተለሳልሰዋል ማለቱ ነው ። ምክንያቱም የዶ/ራቸው ንግግር የሚያመለክተው መጀመሪያ ላይ በትክክለኛ ሰለፍይነት ላይ እንደነበሩና በኢኽዋኖች በኩል በተሰራ ስራ ኢብኑ መስዑዶች ከአቋማቸው እንደተመለሱና እነ ኢብኑ ሙነወርም ላይ እየተሰራ እንደሆነና ውጤቱን በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን ያሳያል ። በዙም ሳይቆይ ያሉት ሆኖ እነሳዳቶቹ ዶ/ራቸውና የአሕባሹ መሪ መጅሊሱን ሲቆናጠጡ እድሜ ጠገብ ለኡማ አሳቢ ብሎ የትንቢቱ መፈፀም አበሰሯቸው ። ከዚህ በመነሳት የደረስኩበት ድምዳሜ ነሲሓዎቹ በኢኽዋን በተዘጋቸላቸው ወጥመድ ውስጥ ከገቡ በኋላ ስኳር ሲያቀምሷቸው ብቻችንን መውጣቱ አመርቂ ውጤት አያመጣም ወጣቱን በሂደት እያለዘብን የእንቅልፍ መርፌ ወግተን ካስተኛነው በኋላ በኢኽዋን ባቡር እናሳፍረዋለን ብለው ላያቸውን በሰለፍያ ቀሚስ ሸፍነው ውስጡን ከኢኽዋን የሚሰጣቸውን ተልእኮ ያስፈፅሙ የነበር መሆኑን ነው ። ተልእኳቸውን ሲጀምሩ ከላይ እንዳልኩት ከሀገሪቱ የተለያየ ክፍል በዳዕዋና ማስተማር ላይ የነበረውን የሰለፍይ አርበኛ ሰፊነቱ ነጃ የሚለውን የኢኽዋን ቫዝሊን እየቀቡ በማለዘብ ቀብር ውስጥ ስለወርቅ ጥርስ የሚጠየቅ ይመስል የወርቅ ጥርስ በየትኛው የፍቅህ ባብ ነው የሚገኘው በሚል የጥያቄ ማደንዘዣ በመስጠት ጃሂል ነኝ ብሎ በኢኽዋን ላይ ረድ እንዳያደርግ አንገቱን እንዲደፋ በማድረግ ነበር ። ይህ አካሄድ ውጤታማ እያደረጋቸው መሆኑን ሲያዩ 30 ምክሮች ለወሰን አላፊዮች በሚል ለሰለፍዮች 30 የእንቅልፍ ክኒኖችን በመስጠት አስተኝተው አላህ ካዘነለት ውጪ ለኢኽዋን አስረከቡት ። ከዚህ በኋላ ሙሉ በሙሉ ከኢኽዋን ጋር መደመራቸውን በተለያየ ጊዜ በመረጃ ባሰየነው መልኩ በአደባባይ አውጀዋል ። እነርሱ መጅሊሱ በአዋጅ እንዲፀድቅላችሁ ተደምራችሁ ኑ የሚል ሰበብ ሲያገኙ በአደባባይ መደመራቸውን ሲያውጁ ሙሪዶቻቸው ዑዝር ፍለጋ ይኳትኑ ጀመር ። ለአንዱ ዑዝር አገኘን ሲሉ በሌላ ሜዳ ላይ ፋውል እየሰሩ ሙሪዶቻቸውን ማስጨነቁን ቀጠሉ ! ነገሩ ካፈርኩ አይመልሰኝ ነውና የሙሪዶቹ ጭንቅና መከራ መስማትና ማየት ጊዜ ማባከን ነው በሚል መልኩ እወጃቸውን አጠናክረው ቀጠሉ ። ይህ ሁሉ ሲሆን አብዛኛውን ድርሻ የሚወሰደው ሸይኻቸው ኢልያስ አሕመድ ከኢኽዋን መሪዮች ጋር አብሮ ሪቫን በመቁረጥ ፣ የክብር እንግዳ ሆነው ሲመጡ አቀባበል በማድረግና የተለያዩ ጉዞዎችን አብሮ በማድረግ ነበር ። ይህ ሲባል እነ አዩብ ደርባቸውና ኢልያስ አወል የመዝናኛ ፕሮግራሙን ተመልካች ነበሩ ማለት አይደለም ። እነርሱም እኔንም ጀመረኝ በሚል አይነት ሞራል ከኢኽዋን መሪዮች ጋር በተለያየ መድረክ መደመራቸውን በማያሻማ መልኩ በሚያሳይ ሁኔታ ያውጁ ነበር ። ይህ ሁሉ ሲሆን ሙሪዶቻቸው ብፁኣኖቹ መሪዮቻቸው የሚሰሩት ነገር ሁሉ ለመስለሀና እነርሱ ከኛ በላይ ያውቃሉ በሚል የቅዠት ድርቶ ውስጥ ሆኖ እየተፈራገጡ ማቃዠት ነበር ስራቸው ። የሶሞኑ ግን ለሙሪዶቻቸው ስርኣት ያዙ ማን ተከላከሉ አላችሁ እኛ ኢኽዋንዮች ነን የፈለገ አምኖ ይከተል ያልፈለገ መንገዱ ጨርቅ ያርግለት በሚል የተዘጋጀ መግረፊያ አርጩሜ ይመስላል ። ይኸውም የነሲሓ ዋና ዋና መሪዮች ከአማራ ፣ ከኦሮሞ ፣ ከትግሬ ፣ ከስልጤና ጉራጌ እንዲሁም ሌሎችም የተውጣጡ ተወካዮቻቸው ጋር የኢኽዋን መሪዮችን የክብር እንግዳ አድርገው ጠርተው አልገባው ላለው ሙሪድ እርምህን አውጣ ብለው መደመራቸውን በአደባባይ ሲያውጁ በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ ተመልከቱ : – https://drive.google.com/file/d/1udsCrb4rEfsCSvO7Qve_ei0EmLdhbJLS/view?usp=drivesdk ከዚህ በኋላ ነሲሓዎች ኢኽዋንዮች አይደሉም ብሎ የሚቃዥ ካጋጠመህ ኡቡበከር አሕመድና አሕመዲን ጀበል ኢኽዋንዮች ናቸው ወይስ አይደሉም ብለህ ጠይቀው ! አይደሉም ካለህ ዐቅሉ ጤነኛ አይደለም ወይም አውቆ የጠመመ መሆኑን እወቅ ! እነርሱ ኢኽዋንዮች ናቸው እነኢልያስና አዩብ ደርባቸው ግን አይደሉም ብሎ መቃዠት ከጀመረ የተቃጠለ ኢኽዋንይ መሆኑን አውቀህ ራቀው ከሱ ጋር ጊዜህን አታቃጥል ። https://t.me/bahruteka

Open in Telegram
Views11,100+71%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8006Link preview

👉 የዓሊምነት መለኪያ ሚዛን መዛባት ! يقول الشيخ عبدالسلام بن برجس – رحمه الله–: "في هذا الزمان اخْتلَّ معيارُ كثير من العامّة في تقييم العلماء، فجعلوا كل من وعظ موعظة بليغة، أو ألقى محاضرات هادفة، أو خطب الجمعة مرتجلاً عالماً يُرجع إليه في الإفتاء، ويؤخذ العلم عنه. وهذه رزيَّةٌ مؤلمةٌ، وظاهرةٌ مُزريةٌ، تطاير شررها، وعم ضررها؛ إذ هي من إسناد العلم إلى غير أهله، وإذا وُسد الأمر إلى غير أهله فانتظر السَّاعة ".   عوائق الطلب ص(٣٣).   ሸይኽ ዐብዱሰላም ኢብኑ በርጀስ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ : – " በዚህ ዘመን የብዙ ሰዎች የዑለማእ መለኪያ ሚዛን ተዛብቷል ። ጥሩ ምክር የመከረን ወይም ጀማዓ ላይ ጥሩ ሙሓደራ ያደረገ ፣ ወይም የጁሙዓ ኹጥባ በሽምደዳው ያደረገን ዒልም የሚወሰድበትና ፈትዋ ለመጠየቅ ወደርሱ የሚመለሱበት ዓሊም አድርገው ያያሉ ። ይህ ፊትናው የተስፋፋ ጉዳቱ ሁሉንም ያዳረሰ ትልቅ ሙሲባና በጣም መጥፎ አካሄድ ነው ። ምክንያቱም የዒልምን ሰነድ ባለቤቱ ወዳልሆነ ማስጠጋት ነውና ። አንድ ነገር ባለቤቱ ወዳልሆነ (አካል) ከተጠጋ ቂያማን ጠብቅ " https://t.me/bahruteka

Open in Telegram
Views7,310+13%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8005Link preview
Views5,910−9%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8004Link preview
Views6,820+5%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8003Link preview
Views5,840−10%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8001Link preview

👉 ሰለፍዮችን ከነድክመታቸው መውደድ ! يقول الإمام أحمد – رضي الله عنه – رحمه الله –: " أحبوا أهل السنة على ما كان منهم . أماتنا الله وإياكم على السنة والجماعة، ورزقنا الله وإياكم اتباع العلم . ووفقنا وإياكم لما يحبه ويرضاه ". طبقات الحنابلة (1/345). ኢማሙ አህሊ ሱና በመባል የሚታወቀው የሱናው አንበሳ ኢማሙ አሕመድ የሱና ሰዎችን ሲመክር እንዲህ ይላል : – " የሱና ባልተቤቶችን ካለባቸው ነገር ጋር ውደዱዋቸው ! አላህ በሱናና በጀማዓ ይግደለን, (ቁርኣንና ሐዲስን የምንረዳበት) ዒልም አላህ ይረዝቀን, አላህ ለሚወደውና ለሚፈቅደው ይወፍቀን" ። ኢማሙ አሕመድ የሱና ሰዎች አንዳቸው በሌላው ላይ በሚያየው ድክመት ምክንያት መለያየትና መጠላላት እንደሌለባቸው ከሰው ልጅ ድክመት አይጠፋምና ከነደካማ ጎናቸው መዋደድ ያለባቸው መሆኑን እያስታወሰን ነው ። ሁላችንም ማወቅ ያለብን ማንም ከደካማ ጎን ያገለለ አለመሆኑ ነው ። የሱና ሰዎች ደግሞ ክፍተታቸውን እየዘጉ ድክመታቸው አንዱ በሌላው እያጠነከሩ መሄድ ይኖርባቸዋል ። ይህ ካልሆነ መኖር ያለብን ከመላኢካ ጋር ነው ማለት ነው ! ምክንያቱም ድክመትም ይሁን ስህተት የሌለባቸው መላኢካዎች ስለሆኑ ነው ። ታዲያ እኛ እንዴት አድርገን ነው ከነድክመታችንና ስህተታችን ከመላኢካ ጋር የምንኖረው ? ይህ መሆን ስለማይችል እርስ በርሳችን እየተደጋገፍን እየተራረምን እየተቻቻልን ከግባችን ለመድረስ አንድ ላይ ሆነን መሄድ ይኖርብናል ። ይህንኑ ነው ኢማሙ አሕመድ እየነገረን ያለው ። አንድ በጣም የምትገርመኝና የዛሬ 30 አመት አካባቢ አንድ ቁርስ ቤት ላይ ሻይ እየጠጣሁ ሳለ ቀና ስል ግድግዳ ላይ ተፅፋ የተሰቀለች የስልጥኛ አባባል ላስታውሳችሁ ። አባባልዋ እንዲህ ትላለች : – " አትክሽብነ በከሸህብነ ኢትቀብጥብነ " ሐሳቡ አላህን መለመን ሲሆን ትርጉሟ እንዲህ ነው : – " አላህ ሆይ (ወንጀላችንን) አትፈልግብን, ከፈለግህብን (ወንጀል) አታጣብንም " ይህ አባባል በኋላ እናታችን ዓኢሻ ካወራችውና ቡኻሪና ሙስሊም ከዘገቡት እንዲህ ከሚለው የነብዩ ሐዲስ ጋር ተቀራረበብኝ : – " من نوقش الحساب هلك " وفي رواية " عذب " የአላህ መልእክተኛ በዚህ ሐዲስ እንዲህ ይላሉ : – " በየአንዳንዱ ነገር ምርመራ የተደረገበት ስው ጠፋ " ወይም " ይቀጣል "። በመሆኑም ከስህተት ያገለለ ስለሌለ እየተላለፍን በትልቁ በሱና ገመድ ተሳስረን አላማችንን ለማሳካት በመዋደድና በወንድማማችንት ስሜት ወደፊት ማለት አለብን እላለሁ ካልተመቻችሁ አውፍ በሉኝ ። መልእክቱ በየትኛውም ቦታ ላሉ ሰለፍዮች እንጂ ለተወሰነ ጀማዓ ወይም አካባቢ አይደለም ። http://t.me/bahruteka

Open in Telegram
Views8,620+33%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#8000Link preview
Views5,900−9%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#7999Link preview
Views5,480−16%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#7998Link preview

🔷  የሚቅዳድና ጓደኞቹ - ረዲየላሁ ዐንሁም - ገጠመኝ ! ሚቅዳድ ከጓደኞቹ ጋር ሰለገጠመው ጉዳይ ሲነግረን እንዲህ ሲል ይጀምራል :‑ " እኔና ሁለት ጓደኞቼ በድካም አይናችን ተጋርዶ ጆሯችን መስማት ተስኖት መዲና ደረስን ። ከድካማችን እንላቀቅ ዘንድ ራሳችንን ለሶሐቦች አቀረብን ። ነገር ግን ካገኘናቸው ውስጥ ማንም ድካማችንን የሚያስወግድበት ነገር አላገኘም ! ወደ አላህ መልእክተኛ ሄድን , ወደ ቤተሰባቸው ይዘውን ሄዱ, እቤት ሶስት ሴት ፍየሎች አሉ ። የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - እነዚህ በመካከላችን እለቡ አሉን ። እናልብና እየአንዳንዳችን ድርሻውን ይጠጣል ። ለሳቸውም ድርሻቸውን እናስቀምጥላቸዋለን ማታ ይመጣሉ ። የተኛን የማይቀሰቅስ የተቀመጠ በሚሰማው ድምፅ ሠላምታ ያቀርባሉ ። ከዛ መስጂድ ይገቡና ከሰገዱ በኋላ ድርሻቸውን ይጠጣሉ ። አንድ ለሊት ሸይጣን ወሰወሰኝ ! ድርሻዬን ጠጥቼ ነበር ። እሳቸው አንሷሮች ጋር ሄደው ስለሚጋብዙዋቸው ከዚህ አንድ ጉንጭ ጉዳይ የላቸውም አለኝ ! የሳቸውን ድርሻ ጠጣሁት ። ጠጥቼው ከሰውነቴ ከተቀላቀለና መመለስ የማልችልበት ሁኔታ ላይ መሆኔን ሲያውቅ ተመልሶ ፀፀት ውስጥ ከቶኝ መወስወስ ጀመረ ። ወይ ጥፋትህ ድርሻውን ጠጥተህበታል መጥቶ ሲያጣው ዱዓእ ያደርግብሃል ዱንያህም አኼራህም ትከስራለህ አለኝ ። የለበስኳት ፎጣ ነበረች እግሬን ስሸፍንበት ጭንቅላቴ ባዶ ይሆናል ጭንቅላቴን ስሸፍን እግሬ ባዶ ይሆናል እንቅልፍ እንቢ አለኝ ። ጓደኞቼ ተኝተዋል ። እኔ ያደረኩትን አላደረጉም ። የአላህ መልእክተኛ መጡ ። ሌላ ጊዜ ያደርጉት እንደነበረው አደረጉ ። ወደ መስጂድ ሄደው ሰግደው ተመልሰው ወደ ወተታቸው ሄደው እቃውን ሲከፍቱት ባዶ ነው ! ራሳቸውን ወደ ሰማይ አደረጉ ። በቃ አሁን ዱዓእ ሊያደርጉብኝ ነው  መጥፋቴ ነው አልኩ ። እሳቸውም አላህ ሆይ ያጠጣኝን አጠጣው ያበላኝን አብላው ብለው ዱዓእ አደረጉ ። ከተኛሁበት ተነሳሁና ሻርፔን አስሬ ቢላዋ ፈልጌ ከፍየሎቹ ጮማ የሆነውን ላርድላቸው ሄድኩ ። የመረጥኳት ሳያት ግቷ ሞልቷል ዞር ስል የሁሉም ግት ሞልቷል ። ከቤተሰባቸው እቃ ፈልጌ ሊያልቡበት በማያስቡት አረፋው እስኪሞላ ድረስ አለብኩኝ ። ወደሳቸው ሄድኩ የምትጠጡት አገኛቹሁን ? አሉኝ ። የአላህ መልእክተኛ ሆይ እንካ ጠጣ አልኳቸው ተቀብለውኝ ጠጡ ። ከዛ እንካ ጠጣ አሉኝ አሁንም ጠጡ አልኳቸው ጠጡ ። ከዛም እንካ ጠጣ አሉኝ መርካታቸውንና ዱዓቸውን ማግኘቴን ሳውቅ ተቀብዬ ጠጣሁ ። ከዛም መሬት እስከምደርስ ሳቄን ለቀቅሁት ። ምንድ ነው አንተ ሚቅዳድ ሆይ ? አሉኝ ።ፐየሆነውን ሁሉ ነገርኳቸው ። እሳቸውም ይህ የአላህ እዝነት እንጂ ሌላ አይደለም አሉኝ ። ለምን አነገርከኝምና ጓደኞቻችንን ቀስቅሰናቸው ከኛ ጋር አልጠጡም ? አሉኝ ። እርሶን በእውነት በላከው ጌታ ይሁንብኝ ! እርሶ ጠጥተው ከረኩና እኔ ከርሶ ከጠጣሁ ሌላ ሰው መጠጣቱና አለመጠጣቱ አያሳስበኝም አልኳቸው !*ይለናል :: ኢማሙል ቡኻሪ በሐዲስ ቁጥር (2055) ከዘገቡት ሐዲስ የተወሰደ ። http://t.me/bahruteka

Open in Telegram
Views6,650+2%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—