Account

Posts of Adama Science and Technology University

newest first

#1391Photo

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ ============= የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ የተመራ ልዑክ ቡድን ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ጉብኝት አደረገ ። ልዑኩን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታና ምክትል ፕሬዝዳንቶች በፕሬዝዳንት ቢሮ ተቀብለዋል። በቆይታቸውም የዩኒቨርሲቲውን የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ከጎበኙ በኃላ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ከተማሪዎች ጋር በዓለም አቀፋዊ፣ ቀጣናዊና ሀገራዊ የደህንነት ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። በተጨማሪም ሌተናል ጀኔራሉ ሀገራችን አትዮጵያ አየር ሃይሉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በማስታጠቅ ሉአላዊነቷን ለመስጠበቅ ያናትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ወቅት ዩኒቨርሲቲው ወጣቶችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ብቁ በማድረግ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅዖ አድንቀው፤ተማሪዎች በፍላጎታቸው ወደ ኢትዮጵያ አየር ኃይል በመቀላቀል ሀገራቸውን እና ህዝባቸዉን እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታ በበኩላቸው ወጣቶች በሀገራዊ ጥቅም ላይ ሳይደራደሩ በእውቀታቸውና በክህሎታቸው በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ በመሳተፍ ሀገራቸውን በዘርፉ የበኩላቸዉን አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል። በተጨማሪም ሌተናል ጀኔራሉ ሀገራችን አትዮጵያ አየር ሃይሉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በማስታጠቅ ሉአላዊነቷን ለመስጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ወቅት ተማሪዎች በፍላጎታቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በመቀላቀል ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Open in Telegram
Views6,130+18%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#1390Photo
Views4,770−8%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—
#1389Photo
Views5,450+5%vs avg
Forwards—
Reactions36
Comments—
#1387Photo
Views4,690−10%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#1384Text

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሜንተር ሺፕ እና የጡት ካንሰር ቅድመ መከላከል ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሠጠ =================================== የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨረሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ለዩኒቨርሲቲው በጎ ፍቃደኛ ነባር ሴት ተማሪዎች የሜንተር ሺፕ እና የጡት ካንሰር ቅድመ መከላከል ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አካሄዷል ፡፡ በቦራቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ዝግጀቱ ቁጥራቸው ከ አንድ መቶ በላይ የሆኑ ነባር ሴት ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተቋሙ ቆይታ ወቅት ከሁኔታዎች ጋር በቀላሉና በቶሎ እንዲላመዱ ድጋፍ ለመስጠት እንዲሁም ሴት ተማሪዎች የጡት ካንሰር ቅድመ መከላከል ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያለመ ነው፡፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ተወካይ ወ/ሮ ሰናይት ቡልቴ የሜንተር ሺፕ ምንነት፣ አለማ እና ግብ ለተማሪዎች ያብራሩ ሲሆን ነባር ተማሪዎች አዲስ ገቢዎችን በመደገፍ ከዩኒቨርሲቲው ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በቀላሉ እንዲላመዱ እንዲሁም ከታላላቆቻቸው ጋር የመወያየት እና የመደጋገፍ ልምድን በማዳበር የህይወት ክህሎት ላይ በቂ ልምድ እንዲያገኙ እንደሚያስችል ገልፀዋል ፡፡ በዝግጅቱ ላይ ከአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ከመጡ ተጋባዝ ባለሙያዎች መካከል ዶክተር እስቂያስ ማእረጉ የጡት ካንሰርን በሽታን የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ዶክተር እስቂያስ በገለፃቸውም የጡት ካንሠርን ምንነት፣ አለምአቀፍ የስርጭት ሁኔታና የመከላከያና የጥንቃቄ መንገዶች ላይ ገለፃ አድርገዋል ፡፡ በማስከተልም ከአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የመጡ ባለሙያ ሲስተር ረሂማ ሁሴን dear you የተሰኘ የጡት ካነስር በሽታን ለመለየትና ለመከታተል የሚያስችል መተግበሪያ አስተዋውቀዋል፡፡ በዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይ የጡት ካንሰር በሽታ ታማሚ የነበሩና በህክምና ክትትል ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ የዳኑ ተጋባዥ እንግዳ ተሞክሮዋቸውን ያከፈሉ ሲሆን በአጠቀላይ የእለቱ የስልጠና አጀንዳዎች ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው ዝግጅቱ ተጠናቋል ፡፡

Open in Telegram
Views7,400+42%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—
#1378Photo
Views6,270+20%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#1365Photo
Views7,610+46%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#1363Link preview

ASTU Provides Life Skills Training and Career Counseling for First-Year Students ========================= The Women and Social Affairs Executive Office, in collaboration with the Students’ and Skill Development Coordinator Office at Adama Science and Technology University (ASTU), organized a life skills and career counseling training program for newly admitted first-year students. The two-day training, held at the ASTU Multipurpose Hall from October 10–11, 2026, aimed to help students adapt to university life, develop essential personal and social skills, and make informed decisions about their academic and professional futures. During the opening ceremony, Prof. Yadessa Melaku, Vice President for Academic Affairs, welcomed the participants and noted that joining a university marks an important new chapter in their lives. He emphasized the importance of life skills training in helping students navigate university life effectively and achieve their academic and personal goals. Prof. Yadessa also encouraged students to participate in extracurricular activities alongside their academic studies, highlighting the role of such activities in developing essential life skills and competencies. The training focused on strengthening students’ communication, teamwork, leadership, time management, problem-solving, decision-making, and emotional resilience skills. It also covered reproductive health awareness and drug abuse prevention. In addition, the program provided career guidance to help students identify their interests, recognize their strengths, set clear goals, and explore future career opportunities. Participants expressed their appreciation for the program, describing it as timely, relevant, and impactful. They also expressed a strong interest in seeing similar training programs organized in the future to further support their personal development, academic success, and career readiness. This initiative reflects ASTU’s commitment to promoting students’ holistic development and equipping them with the essential skills and knowledge needed to succeed both within and beyond the university environment. ASTU, the very University for you! We are dedicated to innovative knowledge! For more information: Face book: https://ASTU_Official Website: https://www.astu.edu.et Tele: +251 (0)222113961 Email: [email protected]

Open in Telegram
Views6,300+21%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—