Account

Posts of ASTU Network Ⓝ

newest first

#5992Video
Views486−50%vs avg
Forwards—
Reactions16
Comments—
#5982Photo

Forwarded from ASTU Peace Forum

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ ======================== ​የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅዳር 29 ቀን የሚከበረውን 21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን (የአንድነት፣ የመከባበርና የመቻቻል መገለጫ ቀን) ምክንያት በማድረግ ኅዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥና ውጪ የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ፡፡ ​መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ተወካይ የሆኑት ፕሮፌሰር ያደሳ መላኩ ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች ላይ በመሰማራት ለማኅበረሰቡ ተምሳሌታዊ ሥራዎችን ማከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ​በተጨማሪም የፕሬዚዳንት ጽ/ት ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ወርቁ ጅፋራ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው "በብዝሃነት የደመቀች፣ በምክክር የጸናች ሥልጡን ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በተለያዩ መርሐ ግብሮች ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የጽዳት ዘመቻውም ከዝግጅቱ አንዱ መሆኑንም ጠቁመዋል:: ​በመጨረሻም ፕሮፌሰር ያደሳ መላኩ መርሐ ግብሩን ላስተባበሩትና ለተሳተፉት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን በማቅረብ ወደፊትም ተማሪዎች መርሃ ግብሮችን በማውጣት በአዳማ ከተማ የጽዳት ሥራ ላይ እንደሚሳተፉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ ASTU, the very University for you! We are dedicated to innovative knowledge! @peaceforum_astu

Open in Telegram
Views870−10%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#5971Photo
Views1,500+56%vs avg
Forwards—
Reactions22
Comments—